+ All Categories
Home > Documents > የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

Date post: 16-Apr-2022
Category:
Upload: others
View: 5 times
Download: 1 times
Share this document with a friend
64
የካቲት 09 ቀን 2009 .
Transcript
Page 1: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የካቲት 09 ቀን 2009 ዓ.ም

Page 2: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት፡ 1. ንግድ ሚኒስቴርን በማነጋገር ለምስረታ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ተሰብስበዋል፤ 2. የአክስዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ናሙና ከንግድ

ሚኒስቴር ካመጣን በኋላ በዝርዝር ተነጋግረንበት ከምናቋቁመው አክስዮን ማኅበር የሥራ ባህርይ አንጻር ማሻሻያ ተደርጎበት የመጨረሻው ረቂቅ ተዘጋጅቷል፤

3. አክስዮን ማኅበሩ የሚኖረው ካፒታል፣ ጠቅላላ አክስዮን፣ ለሽያጭ የሚቀርበው አክስዮን ብዛት፣ የአንድ አክስዮን ዋጋ፣ ለሽያጭ የሚቀርበው ዝቅተኛው አክስዮን ብዛት፣ ለአስተዳደራዊ ወጪዎች የሚከፈል ክፍያ ምጣኔና የመሳሰሉት ተወስነዋል፤

የኩባንያው ካፒታል 10 ሚሊየን ብር እንዲሆን የአንድ አክስዮን ዋጋ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) እንዲሆን ባለአክስዮኖች ከገዙት አክስዮን ዋጋ ስድስት በመቶ ለአስተዳደር ወጪ እንዲከፍሉ፤ ለሽያጭ የሚቀርበው ዝቅተኛው አክስዮን ብዛት 25 እንዲሆን፤ አክስዮን የሚገዙ ሰዎች የመጀመሪያውን ክፍያ ከአክስዮን ማኅበሩ ምስረታ በፊት ከፍለው ቀሪውን

በአራት ዓመታት ውስጥ እንዲከፍሉ፤

Page 3: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት፡

4. አክስዮን መግዛት ለሚፈልጉ ግለሰቦች ዝርዝር ማብራሪያ የያዘ የማስተዋወቂያ ሰነድ ተዘጋጅቶ በዋናው መሥሪያ ቤት፣ በ40/60ና በሌሎችም ፕሮጀክቶች ለሚሠሩ ሠራተኞች መስራች አባል እንዲሆኑ ገለጻ ተደርጎላቸው ሰነዱን ተሰጥቷቸዋል፤ ለድሬዳዋ፤ ለመቀሌና ለአዳሜ ቱሉ ፕሮጀክቶች ሰነዶች በኢሜይል ተልከዋል፤

5. የአክስዮን ማኅበሩን ስያሜ ለማጸደቅ መሟላት ያለባቸውን ህጋዊ ግዴታዎች ለማወቅ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድ ቢሮን በማነጋገርና የአክስዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ በማቅረብ "ኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክስዮን ማኅበር" የተሰኘው ስያሜና የዋና ሥራ አስኪያጁ ስም ተመዝግቦ ለውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ደብዳቤ ተጽፎልናል፤

Page 4: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት፡ 7. የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድ ቢሮ በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት

የመስራች ባለአክስዮኖችን ዝርዝር የያዘ የአክስዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ አቅርበን፤የአክስዮን ማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ለማጸደቅ ቀጥሎ የተገለጹትን ተግባራት እንድናሟላ ተነግሮናል፤

የተከፈለና ያልተከፈለ የአክስዮን መጠንና በንብረት የተመዘገበ የአክስዮን መዋጮ በባለ አክስዮኖች ስም አኳያ እንዲገለጽ፤ የንብረቱ ዝርዝር ከመመስረቻ ጽሑፉ ጋር በአባሪነት እንዲያያዝ፤ የንብረቱ ባለቤት የትዳር አጋር ስምምነታቸው መኖሩ እንዲረጋገጥ፤

በሁለቱም ሰነዶች ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎች እንዲሞሉ፤

የአክስዮን ማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ በማኅበሩ የምስረታ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንዲጸድቅ፤

የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድና ኦዲተሮች ምርጫ እንዲካሄድና የሥራ ክፍፍል እንዲደረግ፤

ባለአክስዮኖች የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት፤ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ዜጎች የተሰጣቸውን ቢጫ ካርድ፣ በውክልና የሚፈርሙ የህጋዊ ውክልና ሰነዳቸውን ይዘው በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሠራተኞች ፊት ቀርበው እንዲፈርሙ፤

የባለአክስዮኖች ብዛት ከሃምሳ በላይ ስለሆነ የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሠራተኞች በእረፍት ቀናት (ከመደበኛ የሥራ ሰዓታቸው ውጪ ቅዳሜ ከሰዓት ወይም እሁድ) ወደ ጽ/ቤታችን መጥተው ባለአክስዮኖችን ያስፈርማሉ፤

ከዚያም የአክስዮን ማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ይጸድቃል፤

Page 5: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት፡

8. በአክስዮን ማኅበሩ አዲስ ድርጅታዊ መዋቅር መሰረት ቀድሞ ኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች ኃ/የተ/ የግል ማኅበር ሲጠቀምባቸው የነበሩ መመሪያዎች ማለትም፤

የሥራ አመራር መመሪያ የድርጅታዊ መዋቅር መመሪያ የስትራቴጂክ እቅድ የመጀመሪያ ረቂቅ የደመወዝ ጥናት የፋይናንስ መመሪያ የሠራተኛ አስተዳደር መመሪያና የግዢ መመሪያ እንደገና ለመከለስ ያላቸው ክፍተት በአደራጅ ኮሚቴው

አባላትና በኩባንያው ባልደረቦች እንዲሁም በውጭ ባለሙያዎች እንዲጠናና በሚሰጠው አስተያየት መሰረት እንዲስተካከሉ እንዲደረግ፤ አዲስ ለሚቋቋሙ የሥራ ክፍሎች ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ሰነድ በአደራጅ ኮሚቴው አባላት እንዲዘጋጅ ተወስኖ እየተሰራ ነው፡፡

Page 6: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

1. ተጨማሪ መስራች አባላት የሚኖሩ ከሆነ ማስፈረሙን አካሂዶ ማጠናቀቅና የአክስዮን ኩባንያው ካፒታል በሙሉ መፈረሙን ማረጋገጥ፤

በውጭ ባለሙያዎች በንግድ ህግ አንቀጽ 6፤ ቁጥር 312/1/ለ እና አንቀጽ 6፤ ቁጥር 316/2 መሰረት በገንዘብ ከሚሸጡ አክስዮኖች ውስጥ ቢያንስ ሩቡን ከምስረታ ጉባዔ በፊት ከባለአክስዮኖች ለመሰብሰብ ዝግ የባንክ አካውንት መክፈት፤

በውጭ ባለሙያዎች በውጭ ባለሙያዎች ለአደራጅ ኮሚቴው ከባለ አክስዮኖች የሚሰበሰበውን ስድስት በመቶ የሥራ ማስኬጃ በጀት ለማንቀሳቀስ የባንክ አካውንት መክፈትና ፈራሚዎቹን ወስኖ ውክልና መስጠት፤

ባለአክስዮኖች በተከፈተው ዝግ የባንክ አካውንት የአክስዮን ድርሻቸውን አንድ አራተኛ እንዲያስገቡ ማድረግ፤ ከምስረታው ጉባኤ በፊት የጠቅላላው ካፒታል አንድ አራተኛ በዝግ የባንክ አካውንት ገቢ መሆኑን ማረጋገጥ፤

ከዚህ በኋላ መከናወን የሚገባቸው ተግባራት

Page 7: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ከዚህ በኋላ መከናወን የሚገባቸው ተግባራት

5. የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ የአክስዮን ማኅበሩን መሥራች ስብሰባ ማካሄድ፤

የአክስዮን ማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ለውይይት አቅርቦ ማጸደቅ፤

የዳይሬክተሮች ቦርድና የኦዲተሮች ምርጫ ማካሄድ፤ 6. ለአክስዮን ኩባንያው ሥራ ማካሄጃ ቢሮ መከራየት፤ 7. የአክስዮን ማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ በውልና ማስረጃ

ጽ/ቤት ማጸደቅ፤ 8. የአክስዮን ባለድርሻዎች በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት አማካይነት የአክስዮን ማኅበሩ

መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ላይ እንዲፈርሙ ማድረግ፤ 9. ለአክስዮን ማህበሩ አዲስ መዋቅር የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን አዘጋጅቶ

ማጠናቀቅ፤ 10. አደራጅ ኮሚቴው ሥራውን አጠናቆ ሂሳቡንም ኦዲት አስደርጎ ለተመረጠው

የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክስዮን ማኅበሩን ሰነዶች ማስረከብ፡፡

Page 8: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች ሕጋዊ ፈቃድ ለማስገኘት የሚያስፈልጉ ቀሪ ስራዎች ዝርዝር

Page 9: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

1. ለአዲስ ንግድ ፈቃድ መሟላት ያለባቸው የአክስዮን ማህበሩ የፀደቀ መመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ ዋና

ቅጂዎችና አዲስ የንግድ ምዝገባ፤ ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ በሁሉም መስራች አባላት የተሰጠ

የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ዋናና የተረጋገጠ ቅጂ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የሥራ አስኪያጁ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፤ ከተፈረሙ አክሲዮኖች ሽያጭ ቢያንስ አንድ አራተኛው ገንዘብ ተከፍሎ በዝግ

ሂሳብ መቀመጡን የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ፤ የሥራ አስኪያጁ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ፓስፖርት መጠን ያለው

ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፤ በማህበሩ ውስጥ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በአባልነት ካሉ እንደ

ሀገር ውስጥ ባለሀበት የተቆጠሩበት ሰነድ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድና የእያንዳንዳቸው የፀና ፓስፖርት ገጽታ ፎቶ ኮፒ፤

ለንግድ ሥራ የሚጠቀምበት ቤት የራሱ ከሆነ የባለይዞታነት ካርታ፣ የኪራይ ከሆነ በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ሰነድ፤

Page 10: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

2. የብቃት ለአዲስ ንግድ ፈቃድ መሟላት ያለባቸው የአክስዮን ማህበሩ የፀደቀ መመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጂዎችና

አዲስ የንግድ ምዝገባ፤ ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ በሁሉም መስራች አባላት የተሰጠ የውክልና

ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ዋናና የተረጋገጠ ቅጂ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የሥራ አስኪያጁ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፤ ከተፈረሙ አክሲዮኖች ሽያጭ ቢያንስ አንድ አራተኛው ገንዘብ ተከፍሎ በዝግ ሂሳብ

መቀመጡን የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ፤ የሥራ አስኪያጁ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ፓስፖርት መጠን ያለው ሁለት

ጉርድ ፎቶግራፍ፤ በማህበሩ ውስጥ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በአባልነት ካሉ እንደ ሀገር

ውስጥ ባለሀበት የተቆጠሩበት ሰነድ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድና የእያንዳንዳቸው የፀና ፓስፖርት ገጽታ ፎቶ ኮፒ፤

ለንግድ ሥራ የሚጠቀምበት ቤት የራሱ ከሆነ የባለይዞታነት ካርታ፣ የኪራይ ከሆነ በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ሰነድ፤

የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው ሴክተር መሥሪያ ቤት፤ ማረጋገጫ ከሚመለከተው ሴክተር መሥሪያ ቤት፤

Page 11: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

3. ለአዲስ ንግድ ፈቃድ መሟላት ያለባቸው የአክስዮን ማህበሩ የፀደቀ መመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ ዋና

ቅጂዎችና አዲስ የንግድ ምዝገባ፤ ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ በሁሉም መስራች አባላት የተሰጠ

የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ዋናና የተረጋገጠ ቅጂ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የሥራ አስኪያጁ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፤ ከተፈረሙ አክሲዮኖች ሽያጭ ቢያንስ አንድ አራተኛው ገንዘብ ተከፍሎ በዝግ

ሂሳብ መቀመጡን የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ፤ የሥራ አስኪያጁ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ፓስፖርት መጠን ያለው

ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፤ በማህበሩ ውስጥ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በአባልነት ካሉ እንደ

ሀገር ውስጥ ባለሀበት የተቆጠሩበት ሰነድ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድና የእያንዳንዳቸው የፀና ፓስፖርት ገጽታ ፎቶ ኮፒ፤

ለንግድ ሥራ የሚጠቀምበት ቤት የራሱ ከሆነ የባለይዞታነት ካርታ፣ የኪራይ ከሆነ በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ሰነድ፤

የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው ሴክተር መሥሪያ ቤት፤

Page 12: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የአንድ አክስዮን ድርሻ፡

• የአንድ አክስዮን መሸጫ ዋጋ - ብር 500.00 • ዝቅተኛው የአክስዮን መጠን - 25 • ዝቅተኛው የአክስዮን ክፍያ መጠን ብር 12.500.00 • ክፍያው የሚጠናቀቅበት ጊዜ - 4 ዓመት • የዓመታዊ ክፍያ መጠን ብር 3.125.00

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክስዮን ማኅበር የአክስዮን ሽያጭን በተመለከተ የተደረገ ማሻሻያ

Page 13: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የአክስዮን ግዢ ዋጋ

25% በየዓመቱ መከፈል ያለበት

ብር

25 500 12,500.00 3,125.00

50 500 25,000.00 6,250.00

100 500 50,000.00 12,500.00

150 500 75,000.00 18,750.00

200 500 100,000.00 25,000.00

250 500 125,000.00 31,250.00

300 500 150,000.00 37,500.00

350 500 175,000.00 43,750.00

400 500 200,000.00 50,000.00

450 500 225,000.00 56,250.00

500 500 250,000.00 62,500.00

Page 14: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

እስካሁን የተከናወነ የአክሲዮን ድርሻ መግለጫ

• ጠቅላላ የተመዘገበ አክሲዮን ብዛት 20,650 • የዶ/ር እሸቱ እና የወ/ሮ ሳራ ድርሻ ብዛት 10,600 = 51% • ጠቅላላ አባላት ብዛት 73 • የተፈረመ የአክሲዮን ክፍያ መጠን ብር 10,325,000 • 25 % የቅድሚያ ክፍያ ብር 2,581,250 • 6 % የሥራ ማስኬጃ ክፍያ ብር 619,500 • በጥሬ ገንዘብ ገቢ የሆነ የአክሲዮን ድርሻ ብር 301,500 • በጥሬ ገንዘብ ገቢ የሆነ ሥራ ማስኬጃ ብር 229,480

Page 15: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን /የአክሲየን 1 ሼር = 500/

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

1 ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ገላን 8600 500 4,300,000.00 1,075,000.00

258,000.00

2 ሳራ ስዩም ቡርሂ 2000 500 1,000,000.00 250,000.00

60,000.00

3 ሜላት እሸቱ ተመስገን 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

4 ማዳን እሸቱ ተመስገን 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

5 ጃላኔ ሙሉነህ መርጊያ 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

6 ናሆም ሙሉነህ መርጊያ 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

7 ኬርማይ እሸቱ ተመስገን 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

8 ናታኒም እሸቱ ተመስገን 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

9 ሀሞና እሸቱ ተመስገን 100 500 50,000.00 12,500.00

3,000.00

10 አለማየሁ ተክሌ ጌታሁን 250 500 125,000.00 31,250.00

7,500.00

Page 16: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

11 ጥላሁን ሚደቅሳ ሄይ 500 500 250,000.00

62,500.00

15,000.00

12 ተወልደብርሃን ወልደገሪማ ገዛኸኝ 400 500

200,000.00

50,000.00

12,000.00

13 መንገሻ ኃይለመለኮት መልካሙ 50 500

25,000.00 6,250.00

1,500.00

14 በቀለ ጎርባ ጅሩ 200 500 100,000.00

25,000.00

6,000.00

15 አየለች ታደሰ ወልደሰንበት 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

16 ኪያን ጥላሁን ሚደቅሳ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

17 ባምላክ አለማየሁ ተክሌ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

18 አጀቡሽ ፍቃዱ ገላን 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

19 የኔነሽ ነጋሽ በላይ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

20 ማጆር ተከስተ ተወልደመድኅን 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን

Page 17: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

21 ቦጋለች ካሳሁን ደምሴ 200 500 100,000.00

25,000.00

6,000.00

22 አሰለፈች በላይ ገሰሰ 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

23 ከበደ ጸጋዬ ተሊላ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

24 ደረሰ ቢርቢርሳ በዳዳ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

25 ዐዲስዓለም ተሸመ ማሞ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

26 አወቀ ጌታቸው ሺፈራው 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

27 አዳሙ ላቀው እንዳለ 250 500 125,000.00

31,250.00

7,500.00

28 ዘካርያስ በቀለ ሻይ 1000 500 500,000.00 125,000.00

30,000.00

29 ማርዬ መርሻሎ በላቸው 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

30 ሽመልስ ጉዳ ሆሴ 200 500 100,000.00

25,000.00

6,000.00

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን

Page 18: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

31 ኅሊና ሰለሞን ተሰማ 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

32 እንዳለ ደምስስ ገብረሚካኤል 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

33 ከሊፋ የሱፍ አህመድ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

34 ትዕግስት ዘመንፈስቅዱስ ገብረአምላክ 100 500

50,000.00

12,500.00

3,000.00

35 ሙሉዬ ዘካርያስ አለሙ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

36 አለሙ በላይ መኮንን 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

37 ፌቨን ገብረየስ ተመስገን 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

38 ሴማን ገብረየስ ተመስገን 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

39 ሙሉጌታ ቸሩ ኃይሌ 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

40 ትዝታ ማሩ ኢላላ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን

Page 19: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

41 ራሔል ጎሹ አንተነህ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

42 ትዕግስት ተመስገን ገላን 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

43 መግደላዊት ዮሐንስ ዮሴፍ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

44 ኖላዊት ጌታቸው 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

45 ተስፉ ተክሌ ወልደሚካዔል 200 500 100,000.00

25,000.00

6,000.00

46 ተክሌ ጥላሁን ይነሱልህ 400 500 200,000.00

50,000.00

12,000.00

47 በረከት ታደሰ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

48 ግርማ አበበ ወልደማርያም 1000 500 500,000.00 125,000.00

30,000.00

49 ቃልኪዳን ተዘራ ሀዋዝ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

50 ሰላም አሰፋ ተድላ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን

Page 20: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

51 ሰለሞን አየለ ዱቤ 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

52 ይበቃል አተፋ 100 500 50,000.00

12,500.00

3,000.00

53 ኤርምያስ አካሉ 800 500 400,000.00 100,000.00

24,000.00

54 ማህደር ሳሙኤል ሚደቅሳ 25 500 12,500.00 3,125.00

750.00

55 ዶ/ር ፍሬው መንግስቱ ጥሩነህ

200 500 100,000.00

25,000.00

6,000.00

56 አዘዘ በትሩ 100 500

50,000.00

12,500.00

3,000.00

57 ሀረገዌይን አድማሱ ዘውዴ 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

58 ሰለሞን ብርሃኑ ተካ 400 500 200,000.00

50,000.00

12,000.00

59 ፍፁም አክሊሉ 400 500 200,000.00

50,000.00

12,000.00

60 በእምነት ድንቁ ኬረሞ 50 500 25,000.00 6,250.00

1,500.00

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን

Page 21: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ተ.ቁ የማኅበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

የተፈረመ አክስዮን ድርሻ

ብዛት

25% በመቶ የአክስዮን ድርሻ

6% ሥራ ማስኬጃ

61 ተመስገን ኦላኒ ሞሲሳ 50 500 25,000.00 6,250.00 1,500.00

62 ዳዊት ወልዴ መስፍን 200 500 100,000.00 25,000.00 6,000.00

63 አብይ ተገኝ ሀብተሚካኤል 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

64 ሄኖክ ክንፈ ቀነኒ 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

65 ኃይሉ ገላን ኤግላት 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

66 ሜሮን አድማሱ ኢታና 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

67 ሮቤል ለገሰ አለማየሁ 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

68 ሮቤል አትክልት በላይ 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

69 ሳህሉ አሳ ታደሰ 25 500 12,500.00 3,125.00 750.00

70 ባጫ ገላ ድንቁ 100 500 50,000.00 12,500.00 3,000.00

71 መሰለ አዲሱ አበበ 100 500 50,000.00 12,500.00 3,000.00

72 ሹሻየ 100 500 50,000.00 12,500.00 3,000.00

73 ዶ/ር ግርማ 100 500 50,000.00 12,500.00 3,000.00

የኢ. ቲ. ጂ አክሲዮን ማህበር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የአክሲዮን ድርሻ መጠን

Page 22: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን

ማህበር አመራር መዋቅር

Page 23: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers
Page 24: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ከአባላት የሚጠበቁ ጉዳዮች • የብድር ፎርም መሙላት /የትዳር ጓደኛን ጭምር ማስፈረም • የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ላይ የመጨረሻ አስተያየት መስጠት • የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ሰነዶችን ማፅደቅ፣ የቦርድ ሥራ አመራር መምረጥ • በተሻሻለው የአክሲዮን ድርሻ መሰረት የምዝገባ ፎርም በድጋሚ መሙላት

Page 25: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

እኛ ከዚህ በታች ስማችን፣ ዜግነታችንና አድራሻችን የተገለፀው መሥራቾች በኢትዮጵያ ሕግ፣በተለይም በ1952 ዓ.ም በወጣው የንግድ ሕግ መሠረት የአክሲዮን ማኅበር ለማቋቋም በመወሰን ይህን የመመሥረቻ ጽሑፍና ከዚህ ጋር የተያያዘውን የመተዳደሪያ ደንብ አውጥተን የማኅበሩን ካፒታል በስማችን አንጻር የተመለከተውን አክስዮን ለመግዛት ተስማማተናል፡፡

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት

ቁጥር

1 ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ገላን ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 2/130

2 ወ/ሮ ሳራ ስዩም ቡርሂ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 2/130

3 ሜላት እሸቱ ተመስገን ስዊድናዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 2/130

4 ማዳን እሸቱ ተመስገን ስዊድናዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 2/130

5 ጃለኔ ሙሉነህ መርጊያ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 2/130

6 ናሆም ሙሉነህ መርጊያ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 2/130

7 ኬርማይ እሸቱ ተመስገን ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቦሌ 03 2/130

8 ናታኒም እሸቱ ተመስገን ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03 2/130

9 ሀሞና እሸቱ ተመስገን ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቦሌ 03 2/130

አንቀጽ አንድ የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ

Page 26: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ

ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

10 አለማየሁ ተክሌ ጌታሁን ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03 4/302

11 ጥላሁን ሚደቅሳ ሄይ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ የካ 09 1294 12 ተወልደብርሃን ወልደገሪማ

ገዛኸኝ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ የካ 08 201

13 መንገሻ ኃይለመለኮት መልካሙ

ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03/05 261/1

14 በቀለ ጎርባ ጅሩ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 07 2199

15 አየለች ታደሰ ወልደሰንበት ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ አራዳ 02 1824

16 ኪያን ጥላሁን ሚደቅሳ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ የካ 09 1294

17 ባምላክ አለማየሁ ተክሌ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቦሌ 03 4/302

18 አጀቡሽ ፍቃዱ ገላን ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቂርቆስ 01 734

19 የኔነሽ ነጋሽ በላይ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቂርቆስ 18 322/05/26 20 ማጆር ተከስተ ተወልደመድኅን ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 12 920

21 ቦጋለች ካሳሁን ደምሴ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ አራዳ 06 520

22 አሰለፈች በላይ ገሰሰ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቂርቆስ 09 649/17

23 ከበደ ጸጋዬ ተሊላ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ልደታ 05 176/ለ

Page 27: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ

ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

24 ደረሰ ቢርቢርሳ በዳዳ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ 02 ፋ151

25 ዐዲስዓለም ተሸመ ማሞ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቃሊቲ አቃቂ 06 315/26

26 አወቀ ጌታቸው ሺፈራው ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ አዲስ ከተማ 07 603

27 አዳሙ ላቀው እንዳለ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ አዲስ ከተማ 02 390

28 ዘካርያስ በቀለ ሻይ ኢትዮጵያዊ አለምገና - አለምገና 378

29 ማርዬ መርሻሎ በላቸው ኢትዮጵያዊት አዋሳ አዲስ ከተማ ፊላዴልፊያ አዲስ

30 ሽመልስ ጉዳ ሆሴ ኢትዮጵያዊ ቢሾፍቱ - አድአ/02 654

31 ኅሊና ሰለሞን ተሰማ ኢትዮጵያዊት ሰበታ - ሰበታዋስ/01 1618 32 እንዳለ ደምስስ ገብረሚካኤል ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 12 821

33 ከሊፋ የሱፍ አህመድ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 03 2620

34 ትዕግስት ዘመንፈስቅዱስ ገብረአምላክ

ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ 11 1521

35 ሙሉዬ ዘካርያስ አለሙ ኢትዮጵያዊ አማራ ክልል

አዊ ጓጉሳ ሽኩዳድ

-

36 አለሙ በላይ መኮንን ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ጉለሌ 07 526/2

37 ፌቨን ገብረየስ ተመስገን ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ የካ 08 397

Page 28: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ

ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

38 ሴማን ገብረየስ ተመስገን ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ የካ 08 397

39 ሙሉጌታ ቸሩ ኃይሌ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ 16 2577

40 ትዝታ ማሩ ኢላላ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ አዲስ ከተማ 06 737

41 ራሔል ጎሹ አንተነህ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ የካ 11 2191

42 ትዕግስት ተመስገን ገላን ኢትዮጵያዊት ሰበታ ሰበታ ሀዋስ 01 287

43 መግደላዊት ዮሐንስ ዮሴፍ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቂርቆስ 02 524

44 ኖላዊት ጌታቸው ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ አራዳ 07 147

45 ተስፉ ተክሌ ወልደሚካዔል ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 07 2148

46 ተክሌ ጥላሁን ይነሱልህ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ጉለሌ 10 636 47 በረከት ተስፋዬ ታደሰ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ 06 -

48 ግርማ አበበ ወልደማርያም ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 01 2747

49 ቃልኪዳን ተዘራ ሀዋዝ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ 06 322

50 ሰላም አሰፋ ተድላ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 09 214/2870

51 ሰለሞን አየለ ዱቤ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ጉለሌ 08 553

Page 29: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ

ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

52 ይበቃል ኢተፋ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ የካ 07 609/ለ/

53 ኤርምያስ አካሉ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ 13 171

54 ማህደር ሳሙኤል ሚደቅሳ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 02 ብ5/04

55 ዶ/ር ፍሬው መንግስቱ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቦሌ 03 4-299

56 አዘዘ በትሩ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 02 2774

57 ሀረገወይን አድማሱ ዘውዴ ኢትዮጵያዊት

58 ሰለሞን ብርሃኑ ተካ ኢትዮጵያዊ

59 ፍፁም አክሊሉ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ የካ 02 R/124

60 በእምነት ድንቁ ኬሬሞ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ አዲስ

61 ተመስገን ኦላኒ ሞሲሳ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ አዲስ ከተማ 14 ብ9/06

62 ዳዊት ወልዴ መስፍን ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ የካ 03 417

63 አብይ ተገኝ ሀብተሚካኤል ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ የካ 03 230/04

64 ሄኖክ ክንፈ ቀነኒ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ልደታ 04 155

65 ኃይሉ ገላን ኤግላት ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ አዲስ ከተማ 17 344

Page 30: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነትና አድራሻ

ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት

ቁጥር

66 ሜሮን አድማሱ ኢታና ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ የካ 19 1194

67 ሮቤል ለገሰ አለማየሁ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ አዲስ ከተማ 03 079

68 ሮቤል አትክልት በላይ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ን/ስ/ ላፍቶ 12 4867

69 ሳህሉ አሳ ታደሰ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ቂርቆስ 08 522

70 ባጫ ገላ ድንቁ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ 08 242

71 መሰለ አዲሱ አበበ ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ቂርቆስ 05 551/44

72 ሹሻይ ታደሰ አረጋይ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ 73 ዶ/ር ግርማ ታደሰ ስዩም ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ

Page 31: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ ሁለት የማኅበሩ መጠሪያ

የማኅበሩ መጠሪያ ስም ኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡

አንቀጽ ሦስት የማኅበሩ ዋና መ/ቤትና ቅርንጫፎች

•የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08፣ የቤት ቁጥር 602/43 ነው፡፡ •ማኅበሩ ቅርንጫፍ ድርጅቶችን በኢትዮጵያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ውጭ ሊያቋቁም ይችላል፡፡

Page 32: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ አራት

የማኅበሩ አላማዎች

ማኅበሩ የተቋቋመበት ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. አርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል፣ ኤሌክትሪካል፣ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ዲዛይን - የጤና፣ የትምህርት ተቋም፣ የኢንዱስትሪ፣

የእርሻ፣ የስፖርትና የመዝናኛ የማዕከሎች፣ የሆቴልና ሪዞርት፣ የላንድ ስኬፕ አርክቴክቸር እና የሪል እስቴት ዴቨሎፕመንት ዲዛይኖችን መስራት፣

2. መንገዶችን፣ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ ተረሚናሎችን፣ ድልድዮችን፣ የባቡር ሀዲዶችን፣ ግድቦችን፣ የተነሎችን አጠቃላይ የዲዛይን ስራዎችን መስራት፣

3. የውሃ ዲዛይን፣ የውሃ ስራዎችን ማጎልበት፣ የከተማና የገጠር ውሃ ልማትና ሳኒቴሽን፣ የአካባቢ ጥናት፣ የዝናብ ውሃና ፍሳሽ፣ ሃይድሮሎክ ስትራክቸር የውሃ ስራ ቁፋሮዎችን እና ወዘተ የዲዛይን ስራዎችን መስራት፣

4. የከተማ ፕላን መሥራት፣ 5. የፕሮጀክት ማኔጅመንትና ጥራት ቁጥጥር ማካሄድ፣ 6. የጂኦ ቴክኒካል ላብራቶሪ ሥራዎችና የማቴሪያል ምርመራዎች ማካሄድ፣ 7. የኮንትራት አስተዳደርና ቁጥጥር እንዲሁም የዋጋ ግምቶችን መሥራት፣ 8. አጠቃላይ የማማከር ሥራዎችን መሥራት፣

8.1 የማኔጅመንት የማማከር አገልግሎት፣ 8.2 አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎች የማማከር አገልግሎት፣

9. በዘርፉ የማሰልጠኛ ተቋማትን በመክፈት የሰው ኃይል ስልጠና መስጠት፣ 10. በአገር ውስጥና በውጭ አገር በንግድ ኢንተርፕራይዞች፣ ማኅበሮችና ከግለሰቦች ጋር በሽርክና መስራት፣ 11. ኮሚሽን ኤጀንት በመሆን ይሰራል፣ በተጨማሪም ከማኅበሩ ሥራና ተግባር ጋር የሚካሄዱ ነገሮችን በሙሉ ይሰራል፣ 12. የኮንስትራክሽን ዕቃዎችና ማሽነሪዎችን መኪናዎችን መሸጥ፣ ማከራየት፡፡

Page 33: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አምስት የማኅበሩ ዋና ገንዘብ

1. የማኅበሩ የተፈረመ ካፒታል ብር ––––––––– /––––––––––––––––––/ ነው፡፡ 2. ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ብር ––––––/–––––––––––/ በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ተከፍሏል፡፡ 3. የማኅበሩ የተፈረመ ካፒታል እያንዳንዳቸው ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ዋጋ ባላቸው በጠቅላላው

/ ––––––––––––––/ ተራ አክስዮን ተደልድሏል፡፡ 4. የማኅበርተኞች የአክስዮን ድርሻ የመዋጮ መጠን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

ተ. ቁ

የማኅበሩ አባላት የአክስዮን ድርሻ

የአንድ አክስዮን ዋጋ

ጠቅላላ መዋጮ የተከፈለ/የተፈረመ

የተከፈለ ያልተከፈለ

በጥሬ ገንዘብ በዓይነት በጥሬ ገንዘብ መዋጮ

በዓይነት በጥሬ ገንዘብ

በዓይነት

1 2 3 4 5

ጠቅላላ ድምር

5. በዓይነት የተደረገው መዋጮ ዝርዝር ግምቱን የሚያሳይ መግለጫ ከዚህ መመሥረቻ ጽሑፍ ጋር ተያይዟል፡፡

Page 34: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ ስድስት

አክሲዮኖች

1.የማኅበሩ አክሲዮኖች ከ1 እስከ –––––––––– ቁጥር ተሰጥቷቸዋል፡፡ 2.አክሲዮን የማስተላለፍ ተግባር

2.1 ማናቸውም አባል በማኅበሩ ውስጥ ያለውን ድርሻ አክስዮን በማናቸውም መልክ ለማስተላለፍ በቅድሚያ ለአባላቱ ወይም ለማኅበሩ ማስተላለፍ ይኖርበታል፣ 2.2 አባላቱ ወይም ማኅበሩ አክስዮኖቹን በማናቸውም ምክንያት ለመግዛት ወይም ለመውሰድ ፍላጎት የሌላቸው እንደሆነ አክስዮኖቹ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሊተላለፉ ይችላሉ፣ 2.3 አክሲዮኖቹን ለማስተላለፍ ጥያቄ ለማኅበሩ በጽሑፍ መቅረብ አለበት፡፡ ማኅበሩም ወይም አባላቱም አክሲዮኖቹን የማይገዙበት ወይም በማናቸውም መልክ የማይቀበሉት ከሆነ ይህንኑ በቃለ ጉባኤ ማስፈር ወይም መያዝ አለባቸው፣ 2.4 የሟች አክሲዮኖች ለሕጋዊ ወራሽ ይተላለፋሉ፡፡ ሆኖም አባሉ ከፈለገ ከሕጋዊ ወራሾቹ መካከል የአክሲዮኑን ወራሽ በቅድሚያ በመሰየም ለማኅበሩ በጽሑፍ ሊያስታውቅና ሊያስመዘገብ ይችላል፣ 2.5 አክሲዮን አይከፋፈልም፡፡ ስለሆነም ማኅበሩ በአንድ አክሲዮን ከአንድ ሰው በላይ በባለቤትነት አይቀበልም፡፡

Page 35: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ ሰባት የባለ አክሲዮኖች ኃላፊነት

ባለ አክሲዮኖች ኃላፊነታቸው በማኀበሩ ውስጥ ባላቸው የአክሲዮን ድርሻ ልክ ነው፡፡

አንቀጽ ስምንት የሂሳብ ዓመት

የሂሣብ ዓመቱ የሚጀመረው ከሐምሌ 1 ሲሆን የሚያልቀው ሰኔ 30 በየዓመቱ ነው፡፡

Page 36: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ ዘጠኝ

የትርፍ አከፋፈል

1.በየሂሣብ ዓመቱ መጨረሻ የማኅበሩን ንብረትና ዕዳ የሚያሳይ የሂሳብ ሚዛን /ባላንስ ሺቲ/ ተዘጋጅቶ ለዳሬክተሮች ቦርድ ይቀርባል፡፡ 2.የማኀበሩን ዓመታዊ የሂሳብ ሁኔታ የሚያሳዩ ሰነዶች፣ ማለትም የሂሳብ ሚዛን /ባላንስ ሺት/፣ የትርፍና ኪሣራ መግለጫ፣ የንብረት ቆጠራ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት፣ የኦዲተሮች ሪፖርት በማኅበሩ መዝገብ ላይ ለተመዘገቡ ባለአክሲዮኖች ቢያንስ ከመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ቀን 15 ቀን አስቀድሞ በሬኮማንዴ ይላካል፡፡ 3.ከዚህ በታች ከንዑስ አንቀጽ 4/ሀ እና ለ/ሥር የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በየዓመቱ ሂሣብ መግለጫ ውስጥ እንደተመለከተው የማኅበሩ የዓመቱ የተጣራ ትርፍ፣ ጠቅላላ ወጪ ዋጋ፣ አላቂ ለሚሆኑ ነገሮች መተኪያ ገንዘብ /አሞርታይዜሽን/፣ አላዋንስ እና ለሌሎች መዋጮዎች ታክስ ያለፈው ዓመት ግዴታዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚታየው የተጣራ ገቢ ነው፡፡ 4.ከተጣራው ዓመታዊ ትርፍ ላይ ሀ. የጠቅላላ ካፒታሉን 2ዐ% እስከሚያክል ድረስ በየዓመቱ 5% ለሕጋዊ መጠባበቂያ ይያዛል፡፡ ለ. ትርፍ መገኘት ከጀመረበት የመጀመሪያ ዓመት አንስቶ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ከተጣራው ትርፍ 15 በመቶ (አስራ አምስት በመቶ) ተቀንሶ ባላቸው አክስዮን መሰረት ለመስራች አባላት ይከፈላል፡፡ ሐ. በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ የፀደቁ ሌሎች ልዩ የመጠባበቂያ ሂሣቦችና የኦሞርታይዜሽን ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ ተራፊው በተከፈለው የአክስዮን ድርሻ ልክ ለባለ አክስዮኖች ይከፋፈላል፡፡

Page 37: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አስር የአስተዳደር አካሎች

የማኅበሩ የአስተዳደር አካሎች፣ ሀ. የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ፣ ለ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሐ. ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡

አንቀጽ አሥራ አንድ ጠቅላላ ስብሰባ

1.የባአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ከፍተኛው የሥልጣን አካል ነው፡፡ ይህም ጉባዔ መደበኛና ድንገተኛ ስብሰባ በደንቡና በንግድ ሕጉ መሠረት ያካሂዳል፤ 2.የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ከመካከሉ ይመርጣል፣ይሾማል፣ይሽራል፤ 3.የውጭ ኦዲተሮችን ይሾማል፣ይሽራል፣አበላቸውንም ይወስናል፡፡

Page 38: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ አሥራ ሁለት የዳይሬክተሮች ቦርድ

1. ማኅበሩ የሚተዳደረው በባለአክሲዮን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመረጡ ቢያንስ 3 ቢበዛ 12 አባሎች ባሉት የዳይሬክተሮች ቦርድ ነው፡፡ የቦርዱም የሥራ ዘመን ሦስት ዓመት ነው፡፡

2. የማኅበሩ የመጀመሪያ የዳይሮክተሮች ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. 2. 3. 4. 5. 3. የዳይሬክተሮች ቦርድ ከአባሎች አንዱን ኘሬዝዳንት አድርጐ ይመርጣል፡፡ 4. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የተመረጠበት ጊዜ ካበቃ እንደገና ሊመረጥ ይችላል፡፡ 5. ዳይሬክተር መለወጥ ቢያስፈልግ የንግድ ሕግ ቁጥር 351 /አስተዳዳሪ ስለ መለወጥ/ ድንጋጌ ተፈፃሚ

ይሆናል፡፡ ዳይሬክተሩ ከሥራው ላይ ቢቀር የንግድ ሕግ ቁጥር 358 ድንጋጌ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም ከሥራው ላይ የቀረ ዳይሬክተር በሌላ ዳይሬክተር ያልተወከለን ዳይሬክተር ለመወከል ይችላል፡፡

6. እያንዳንዱ የተመረጠ ዳይሬክተር የሥራ ጊዜው እስከሚፈፀም ድረስ ቢያንስ በስሙ በማኅበሩ የተመዘገበ አክስዮን ያስይዛል፡፡ የሥራ ዘመኑም ሲያልቅ አክስዮኑ በንግድ ሕግ ቁጥር 349 ሥር በተገለፀው ሁኔታ ይመለስለታል፡፡ በንግድ ሕግ ቁጥር 359 እና 36ዐ ድንጋጌ መሠረት የዳይሬክተሮች ምዝገባ ይኖራል፡፡

7. በሕግ፣ በመመሥረቻ ጽሑፍ፣ በመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በጠቅላላ የባለአክሲዮኖች ጉባዔ ውሳኔ ለሌላ የማኅበሩ አካል ተለይቶ ካልተሰጠ በቀር ለተለየ ሥራ ሁኔታ የሚያስፈልገው የማኀበሩ ሥልጣን ሁሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣን ይሆናል፡፡

Page 39: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አሥራ ሦስት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ተግባር

በንግድ ሕግ ቁጥር 362፣ 364፣ 446 እና 447 ሥር የተገለጹት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የዳይሬክተሮች ቦርድ ከዚህ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡፡

1. የማኀበሩን አስተዳደር መቆጣጠር፣ 2. በጠቅላላው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ከተወሰነው ሳያልፍ የማኀበሩን የንግድ ሥራ ለማካሄድ

አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ፣ 3. የማኅበሩን ሥራ አስኪያጆች ለመሾም እንደአስፈላጊነቱ ጸሐፊዎችን፣ ሠራተኞችን ለመቅጠር፣

ለማሰናበት ለማገድ እንደዚሁም ደመወዝ፣ አበል ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችንና የሥራ ሁኔታዎችን ለመወሰን፣

4. የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ማፍራት መሸጥ፣ 5. በአገር ውስጥ ከሚገኝ ማንኛውም ባንክ፣ የገንዘብ ድርጅት ወይም ተቋም ለማኅበሩ ዓላማዎች

ማከናወኛ የሚውል ብድር በመያዣ ወይም ያለመያዣ ለመበደር፣ ለመደራደር፣ ለመዋዋል ለመፈረም፣

6. በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከኢትዮጵያ ውጪ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማቋቋምን መወሰን፣ 7. ማናቸውንም ተስማሚ ሆኖ ያገኘውን የማኅበሩን ገንዘብ ሥራ ላይ ስለማዋል ሃሣብ ለጠቅላላ

የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ማቅረብ፣ 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ሥልጣኑን ለኘሬዚዳንቱ ለመስጠት ይችላል፡፡

Page 40: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አሥራ ሦስት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ተግባር

9. አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የዳይኘሬዚዳንት፣ ምክትል ኘሬዚዳንት፣ ሥራ አስኪያጅ፣ ዳይሬክተርና ማናቸውም ሌላ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣን የተሰጠው ዳይሬክተር በማኅበሩ ስም ሊፈርም ይችላል፤ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአንድነት ወይም በነጠላ በማኅበሩ ስም ለመፈረም የሚችሉ ተጨማሪ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሥራ አስኪያጆችን ለመሾም ይችላሉ፡፡

10. ሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በኘሬዚዳንቱ ወይም በሥራ አስኪያጁ ሊጠራ ይችላል፡፡ የዳይሬክተሮች ስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሌለ ዳይሬከተር አይሰጥም፡፡ ዳይሬክተሮች የማኅበሩን ሥራ ያካሄዳሉ፣ ውሳኔአቸውም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 358 ድንጋጌ መሠረት ይመዘገባል፡፡

11. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጸሐፊ ይሾማል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔዎች በኘሬዚዳንቱና በጸሐፊው ተፈርመው በቃለጉባዔ መዝገብ ውስጥ ተመዝግበው ይቀመጣሉ፡፡

12. ዳይሬክተሮች በንግድ ሕግ አንቀጽ 365 መሠረት በአንድነትና በነጠላ ለማኅበሩ ለዕዳ ጠያቂዎች ኃላፊነት አለባቸው፡፡

13. ቦርዱ በክፉ ልቦና፣ በተንኮል፣ ወይም ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ ካልሠራ በቀር የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ወይም በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት ባገኘው ሥልጣን ለሠራው ሥራ፣ በሕጋዊ መንገድ ላከናወነው በግሉ ምንም ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

14. የማኅበሩ ዳይሬክተሮች በማንኛውም ሁኔታ ከማኅበሩ ገንዘብ ሊበደሩ ወይም ለግል ዕዳቸው በማኅበሩ ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡

15. የዳይሬክተሮች የአገልግሎት ክፍያ በየዓመቱ በመደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ ይወሰናል፡፡ ይህም ክፍያ ከጠቅላላ ወጪ ውስጥ ይጠቃለላል፡፡

Page 41: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አሥራ አራት ሥራ አመራር

1. የማኅበሩ የአስተዳደር ሥራ በዳይሬክተሮች ቦርድ ተመርጦ የአገልግሎት ክፍያውና አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ የሚወሰንለት የሥራ አስኪያጅ ወይም ዳይሬክተር ወይም ዋናው ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡

2. የሥራ አስኪያጅ ወይም ዳይሬክተር ወይም ዋናው ሥራ አስኪያጅ በመመሥረቻ ጽሑፍ፣ በመተዳደሪያ ደንብና የዳይሬክተሮች ቦርድ በሚሰጣቸው መመሪያዎች መሠረት የማኅበሩን ሥራዎች ይሠራል፣ ማናቸውንም ለማኅበሩ ሥራ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡

3. አቶ አለማየሁ ተክሌ ጌታሁን የአክሲዮን ማኅበሩ የመጀመሪያ የሥራ አስኪያጅ ወይም ዳይሬክተር ወይም ዋናው ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

Page 42: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አሥራ አምስት ተቆጣጣሪዎች /ኦዲተሮች/

1. ማኀበሩ በዓመት ------------ ጊዜ በሚያደርገው ስብሰባ የማኅበሩን ኦዲተር ወይም ኦዲተሮች ይሾማል፡፡ የሚሾመው ኦዲተር ወይም ኦዲተሮች በሂሣብ ምርመራ ሥራ የተፈቀደለት ሰው ወይም ድርጅት ይሆናል፡፡ የነዚህም ኦዲተሮች ተግባር፣ ሥልጣንና ኃላፊነት በሕግ በተለይም በንግድ ሕጉ ቁጥር ከ368 እና 378 መሠረት ይሆናል፡፡

2. የኦዲተሮችም የአገልግሎት ዋጋ በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ይወሰናል፡፡

Page 43: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አሥራ ስድስት የማኅበሩ ቆይታ

ማኅበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ሲሆን በንግድ ሕጉ ቁጥር 495 ሥር በተገለጹት ምክንያቶች የሚፈርስ ነው፡፡

አንቀጽ አስራ ሰባት የማኅበሩ የሥራ ሪፖርት

1. እያንዳንዱ የሂሣብ ማጠቃለያ በሚዘጋበት ጊዜ ዳይሬክተሮች በማኅበሩ ያሉትን ልዩ ልዩ ንብረቶችና ዕዳዎች የሚያመለክት የንብረቱን ዝርዝር የሚይዝ መዝገብ ያደራጃል፡፡

2. ዳይሬክተሮች የዓመቱን የሂሣብ ሚዛን፣ የትርፍና ኪሣራ መግለጫ፣ እንዲሁም ባለፈው የሂሣብ ማጠቃለያ ሥራ ጊዜ ስለማኅበሩ ሁኔታዎችና አሠራር ሪፖርት ያደራጃሉ፡፡

3. ለጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ከመደረጉ 60 ቀን በፊት የንብረት ዝርዝር መዝገብ፣ የሂሣብ ሚዛን፣ የትርፍና ኪሣራ ሂሣብ፣ የዳይሬክተሮች ሪፖርት፣ ለኦዲተር ተዘጋጅተው መሰጠት አለበት፣ በዚሁ ጊዜ እነዚሁ ሰነዶች ለሚመለከተው ንግድ ሚኒስቴር መተላለፍ አለባቸው፡፡

Page 44: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ

አንቀጽ አሥራ ስምንት ጠቅላላ

በዚህ የመመሥረቻ ጽሑፍ ውስጥ ባልተገለጹት የማኅበሩ ጉዳዮች ላይ ሁሉ እንደአስፈላጊነቱ የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ይህ የመመሥረቻ ጽሑፍ ዛሬ ––––– በመሥራች አባሎች ፈራሚዎች –––––– ከተማ ተፈረመ፡፡ መሥራች አባላት ፊርማ

1. ––––––––––––––– –––––––– 2. ––––––––––––––– –––––––– 3. ––––––––––––––– –––––––– 4. ––––––––––––––– –––––––– 5. ––––––––––––––– –––––––– 6. ––––––––––––––– –––––––– 7. ––––––––––––––– ––––––––– 8. ––––––––––––––– ––––––––– 9. ––––––––––––––– –––––––––

Page 45: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን

ማህበር የመተዳደሪያ ደንብ ይህ የመተዳደሪያ ደንብ የመመሥረቻ ሰነዱ አካል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን አግባብ

ባላቸው የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ይመራል፣ ይተዳደራል፡፡

Page 46: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አንድ የባለ አክሲዮኖች/ማኅበርተኞች/ መብቶች

እያንዳንዱ ባለ አክሲዮን፡-

ሀ. በልዩም ሆነ በመደበኛ ጉባዔዎች ላይ በመገኘት ሃሣብ የመስጠት፣ የመቃወም፣ ድምጽ የመስጠት፣ ለ. የማኅበሩን ውሳኔ የመጠየቅ፣ የማግኘት፣ ሐ. የማኅበሩን የተጣራ ትርፍ፣ ማኅበሩም ሲፈርስ በሚደረገው የሂሳብ ማጣራት ድርሻን የመካፈል፣ መ. የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ ሆኖ የመቅረብ፣ ሠ. ካፒታል በመጨመሩ ተጨማሪ አክሲዮኖች የሚታደሉ ቢሆን የቀደምትነት ድርሻ የማግኘት፣ ረ. የማኅበሩ አባላት በሙያ ክህሎታቸው፣ ብቃትና ዝግጁነት ተቀጥረው የመሥራት፣ ሰ. አግባብ ባለው ሕግ፣ በመመሥረቻ ጽሑፍና በዚህ በመተዳደሪያ ደንብ በሚሰጡት መብቶች የመጠቀም፣ መብት ይኖረዋል፡፡

Page 47: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሁለት የአክሲዮን ዋጋ/ፕሪሚየም/

አክሲዮኖች ከተጻፈባቸው ዋጋ በላይ ወጪ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ ሦስት አክሲዮን ስለማስተላለፍ

አክሲዮኖችን ለሌላ ማስተላለፍ የተከለከለ አይደለም፣ ቢሆንም ለመጀመሪያው አምስት ዓመት የግዢ ቅድሚያ የሚሰጠው ላሉት ባለ አክሲዮኖች ይሆናል፡፡

አንቀጽ አራት ስለጋራ ባለቤትነት፤ ስለመያዣ የአላባ መብት

1. አክሲዮኖችን በጋራ የያዙ ባለ አክሲዮኖች ወኪል ይሾማሉ፡፡ የሾሙትን ሰው ስም አድራሻም በባለ አክሲዮኖች መዝገብ ያስመዘግባሉ፡፡ ማኅበሩ መጥሪያዎችን የሚልከው ለዚሁ ለተሾመው ለባለ አክሲዮኖች ተወካይ ይሆናል፡፡

2. በመያዣም ሆነ በአላባ አክሲዮን ያስያዘው ሰው ስም አድራሻ፣ ያስያዘበትን ምክንያት መብቱን ጨምሮ ማስመዝገብ አለበት፡፡ ማኅበሩም ማስጠንቀቂያዎችን /ቲሰስ/ የሚልከው ለባለ አክሲዮኑ ለመያዣ /አላባ/ ተጠቃሚው ነው፡፡

Page 48: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አምስት የባለ አክሲዮኖች ምዝገባ

1. የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ የባለአክሲዮኖችን ዝርዝር የያዘው መዝገብ በማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት እንዲገኝ ያደርጋል፡፡ መዝገቡ በሕግ፣ በመመሥረቻ ጽሑፍና በመተዳደሪያ ደንቡ የሚጠይቁትን ጉዳዮች ሁሉ የያዘ መሆን አለበት፡፡

2. በመዝገቡ ውስጥ ጉድለት /ስሕተት/ መኖሩ እንደታወቀ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ይህን ጉድለት በሰላሣ ቀናት ውስጥ እንዲስተካከል /እንዲታረም/ ያደርጋል፡፡

3. መዝገቡን ለመመርመር ከውስጡም ቅጂዎችን ለመውሰድ መከፈል የሚኖርበትን ሂሳብ የዳይሬክተሮች ቦርድ ይወስናል፡፡ ሆኖም ባለ አክሲዮን የሆነ ሰው ያለክፍያ መዝገቡን ሊመለከተው ይችላል፡፡

አንቀጽ ስድስት

ድርሻቸውን ያልከፈሉ ባለ አክሲዮኖች ግዴታ

1. በየጊዜው መከፈል ያለበትን የአክሲዮን ዋጋ ያልከፈለ ባለ አክሲዮን በወቅቱ ባልከፈለው ገንዘብ ላይ በወቅቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወለድ ምጣኔ መሰረት የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡

2. የመክፈያ ጊዜው ካለፈ በኋላ ድርሻውን በወቅቱ ላልከፈለ ባለአክሲዮን ማኅበሩ ክፍያው እንዲደረግ ይጠይቃል፡፡ ባለአክሲዮኑ ደብዳቤ በደረሰው በሰላሳ ቀን ውስጥ ክፍያውን ባያጠናቅቅ ማኅበሩ ያልተከፈለባቸውን አክሲዮኖች በሀራጅ ለመሸጥ ይችላል፡፡

Page 49: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሰባት የጠፉ አክሲዮኖችን ስለመተካት

ማኅበሩ የሚያድላቸው አክሲዮኖች ጉዳት ቢደርስባቸው፣ ቢበላሹ፣ ቢጠፉ ወይም ቢሰረቁ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ከብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ባልበለጠ ክፍያ እንደገና ይታደላሉ፡፡

አንቀጽ ስምንት ጉባዔዎች

1. የዳይሬክተሮች ቦርድ በሌላ ጊዜና ቦታ እንዲሆን ካልወሰነ በቀር የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ በየበጀት ዓመቱ መጀመሪያ አራት ወር ማለፍ የለበትም፡፡ ድንገተኛ ግን በማንኛውም ጊዜ ሊጠራ ይችላል፡፡

2. መደበኛም ሆነ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሰበሰብ ጥሪ የሚደረገው ከስብሰባው 15 ቀናት በፊት በአገሪቱ ውስጥ በሚታተም ሕጋዊ ጋዜጣ ጥሪ በማድረግ ነው፡፡

3. የመደበኛውም ሆነ ድንገተኛ ጠቅላላ ስብሰባ በምልዓተ ጉባዔ አለመሟላት ምክንያት ሊካሄድ ካልቻለ ሁለተኛ ጥሪ ስብሰባው ከመካሄዱ ስምንት ቀን በፊት ይተላለፋል፡፡ በሁለተኛው ስብሰባ ጥሪ ምልዓተ ጉባዔ ካልሞላ ስብሰባው ቀጥሎ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ይችላል፡፡

4. አግባብ ባለው ሕግ፣ በመመሥረቻ ጽሑፍና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሌላ ጉባዔዎች ይወሰናሉ ከሚባሉ ጉዳዮች በስተቀር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ጉዳዮች ላይ መወያየትና ውሣኔ ማሳለፍ ይችላል፡፡

Page 50: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ዘጠኝ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሰበሰብ የሚደረግ ጥሪ

ሥራ አመራሩ /ሥራ አስኪያጁ/ የተመዘገቡ ባለአክሲዮኖች ወይም ተወካዮቻቸው በጉባዔ እንዲገኙ ተመዝግቦ ባለው አድራሻቸው በተራ የፖስታ መልዕክት አማካኝነት ጥሪ ያደርግላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ሕጋዊ ማስታወቂያ ለማውጣት በተፈቀደለት በማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ በሚከፋፈል ጋዜጣ አማካኝት ጥሪው ሊገለጽ ይችላል፡፡ የጥሪ መልዕክት አግባብ ባለው ሕግ፣ የመመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ የሚጠየቀውን መረጃ /ኢንፎርሜሽን/ ሁሉ ያሟላ መሆን ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ አስር በጉባኤ ላይ ስለመገኘት መቆጣጠሪያና ቃለጉባኤዎች

1. በንግድ ሕጉ አንቀጽ 403 መሠረት በእያንዳንዱ ጉባኤ ላይ የተገኙትን ማህበርተኞች መቆጣጠሪያ ሰነድ መያዝ አለበት፡፡

2. በስብሰባ ላይ የተደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች በንግድ ሕጉ አንቀጽ 411 እና 412 መሠረት በቃለጉባኤ ተመዝግበው እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡

Page 51: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አስራ አንድ የማህበሩን ሰነዶች የመመርመር መብት

ማንኛውም ማህበርተኛ በማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ሰነዶች በማንኛውም ጊዜ ለመመርመር ወይም ኮፒዎችን የመውሰድ መብት አለው፡፡ ሊሰጡት የሚችሉ ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፤ 1. የሂሳብ ሚዛን፣ የትርፍ ኪሳራ መግለጫዎች፤ 2. ያለፉትን ሦስት የሂሳብ ዓመታት በሚመለከት የዳይሬክተሮች፣ የኦዲተሮችና የጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርቶች፤ 3. በእነዚሁ ጠቅላላ ጉባኤዎች የተያዙ ቃለ ጉባኤዎችና የተገኙ አባላት ዝርዝር፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት የእንደራሴነት ስልጣን

1. አንድ ባለ አክሲዮን ማኅበርተኛ ያልሆነ ሌላ ሰው በምትኩ በስብሰባዎች ላይ እንዲገኝ የእንደራሴነት ስልጣን ሊሰጥ ይችላል፡፡

2. ሥልጣኑ በግልጽ በወካዩ ካልተገለጠ በቀር በጉባኤው በእንደራሴነት የተገኘው ሰው መብትና ግዴታ በሚመለከት ከባለ አክሲዮኖች እንደአንዱ ይቆጠራል፡፡

3. በጉባዔ የመተካት ውክልና በጽሑፍ ሆኖ ቀን የተጻፈበት በወካዩ ባለአክሲዮን የተፈረመ መሆን አለበት፡፡ 4. ይህ ዓይነት የእንደራሴነት /ውክልና/ ከሁለት ዓመት በላይ ሊያገለግል አይችልም፡፡

Page 52: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አሥራ ሦስት አጀንዳ

1. የአጀንዳው ግልባጭ ከመጥሪያው ጋር ተያይዞ ለባለ አክሲዮኖች ይላካል፡፡ 2. ጉባዔው በሚካሄድበት ጊዜ የጠቅላላ ጉባዔው አጀንዳ ሊሻሻል ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን እንዲመርጡ

የተፈቀደላቸው ይበልጡን /ማጆሪቲ/ የአክሲዮን ድርሻ የያዙት ሲስማሙበት ብቻ ነው፡፡ 3. የማኅበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ከመደረጉ ሦስት ቀን በፊት ስም የተጻፈባቸው የአክሲዮን ባለሀብቶች በማኅበሩ መዝገብ

መመዝገብ፣ ላምጪው የሚል የተጻፈባቸውን የያዙ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን ማስገባት አለባቸው፡፡ አንቀጽ አስራ አራት

ፀሐፊ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጸሐፊውን ይሾማል፡፡ ጸሐፊው በጉባኤው ላይ የመገኘት ማስረጃ ወረቀት /አቴንዳንስ ሺት/ ያዘጋጃል፡፡ ሕግ የሚጠይቃቸውን ቃለ ጉባዔዎችን ይይዛል፤ ተገቢ ለሆነው የመንግሥት ባለሥልጣን ምስጢር ያለባቸውን ደብዳቤዎች ያደርሳል፡፡ ጸሐፊው ባለአክሲዮን ላይሆን ይችላል፡፡

አንቀጽ አሥራ አምስት የሥራ አመራር

1. የጉባዔዎች ሁሉ ሰብሳቢ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፕሬዘዳንት ነው፡፡ እርሱ የሌለ እንደሆነ ከዳይሬክተሮች በሥራ ቀደምትነት ያለው /ሲኒየር/ ሰብሳቢ ይሆናል፡፡ ሁለቱም የሌሉ ቢሆን ካሉት ዳይሬክተሮች በሥራ ቀደምትነት ያለው ይሰበስባል፡፡

2. የተያዙትን የአክሲዮኖች ወይም የተወከሉትን ቁጥር የሚቆጣጠሩ ከባለአክሲዮኖች ወይም እንደራሴዎች መካከል ሁለት ድምጽ ተቀባዮች ይሾማሉ፡፡

3. ማንኛውም ባለአክሲዮን ወይም እንደራሴ በምስጢር እንዲሆን ካልጠየቀ በቀር ማንኛውም ውሣኔ የሚተላለፈው በድምጽ ቆጠራ ነው፡፡

4. ምልዐተ ጉባዔን /ኮረም/ እና የድምጽ ብልጫን በሚመለከት በ1952 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ቁጥር 421፣425 እና 428 የተደነገገው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

Page 53: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽአስራ ስድስት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ግዴታዎች

1. የዳይሬክተሮች ቦርድ በሕግ፣ በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍና በመተዳደሪያ ደንብ በጉባዔው ውሳኔዎች የተሰጡትን ሥልጣንና ግዴታዎች ይፈጽማል፡፡

2. የዳይሬክተሮች ቦርድ በተለይ የሚከተሉት ሥልጣንና ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡ ሀ. የማህበሩን ሥራ ይመራል፡፡ ለ. ጠቅላላ ጉባዔው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የማኅበሩ ዓላማ ግቡን የሚመታበትንና የሚሰምርበትን እርምጃዎች ሁሉ ያከናውናል፡፡ ሐ. ከጸሐፊዎች /ክለርክስ/ ከሌሎች ሠራተኞች በቀር፣ የሥራ ኃላፊዎችን ይሾማል፡፡ ደመወዛቸውን ይተምናል፡፡ ስጦታን፣ ስንብትንና ጡረታን በሚመለከት ይወስናል፡፡ መ. የማኅበሩን የማይንቀሳቀሱም ሆነ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ይገዛል፣ ይሸጣል፡፡ ሠ. የብድር የመያዣ ውሎችን ይዋዋላል፡፡ ለማኅበሩ ተቀጣሪዎች የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የተለያዩ ዕቅዶችን ያዘጋጃል፡፡ ረ. በኢትዮጵያ ወይም ከኢትዮጵያ ውጪ የማኅበሩ ቅርንጫፎች እንዲከፈቱ ይወስናል፡፡ ሸ. ተገቢ/ጠቃሚ የመሰለውን ሀሳብ፣ የማህበሩን ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግን ጨምሮ፣ ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል፣ 3. ዳይሬክተሮች በማኅበሩ ሥራ አስኪያጅነት ወይም ወኪልነት የጋራ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

Page 54: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አስራ ሰባት ስለ ዳይሬክተሮች መምረጥና መሻር

1. በተደጋጋሚ ለመመረጥ ያላቸው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ የአስተዳዳሪዎች የሥራ ዘመን ሦስት ዓመት ነው፡፡ ሆኖም ተተኪው ተመርጠው እስከሚረከቧቸው ድረስ በሥራ ላይ ይቆያሉ፡፡ የዳይሬክተሮች ምርጫ የሚከናወነው በምስጢር ድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ነው፡፡

2. አንድ ወይም ከዚያ በላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ቢጎድሉ/ቢወጡ፣ ቀሪዎቹ ከግማሽ በላይ ከሆኑ በወጡት ምትክ ከባለአክሲዮኖች መካከል መርጠው ይሾማሉ፡፡ ቀሪዎቹ ዳይሬክተሮች ከግማሽ በታች ከሆኑ የጎደሉትን ለመሙላት ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራሉ፡፡ የተሾሙም ካሉ ለዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ቀርበው ውሳኔ ይሰጥባቸዋል፡፡ ሹመቱ የጸደቀ እንደሆነ የተተካው ሰው ያቋረጠውን የአገልግሎት ዘመን ይሸፍናል፡፡ ሹመቱ ተቀባይነት ካላገኘ ክፍት ቦታው በዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ይተካል፡፡

አንቀጽ አስራ ስምንት ስለ ዳይሬክተሮች የአክሲዮን መዝገብ

የዚህ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ አምስት ድንጋጌዎች እንዳግባቡ የዳይሬክተሮች የአክሲዮኖቻቸውን አመዘጋገብ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

Page 55: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ የዳይሬክተሮች የሥራ ዋጋ አበል

1. ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው በሚቀጥለው የሂሳብ ዓመት ለዳይሬክተሮች ቦርድ ሊከፈል የሚገባውን አበል ይወስናል፡፡

የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ተመራጮች ለመጀመሪያው ሂሳብ ዘመን ብር ----------------- /-------------------/ አበል ያገኛሉ፡፡

2. በተጨማሪም አባላቱ የሚከተለውን ክፍያ ያገኛሉ፡፡ ሀ. የተጣራው ዓመታዊ ትርፍ ከተከፈለው ዋጋ ገንዘብ እስከ ---------------- በመቶ/% / ------------ ---------

----/ የሆነ እንደሆነ፣ ------------------ በመቶ/% ይሆናል፡፡ ለ. የተጣራው ትርፍ ከተከፈለው ዋጋ ገንዘብ እስከ -------------------------- በመቶ /% / ------------ ---------

----/ በላይ ከሆነ -------------%/በመቶ ይሆናል፡፡ ሆኖም ለባለአክሲዮኖች የትርፍ ክፍያ ካልተደረገ በተራ ቁጥር 2ሀ እና ለ የተጠቀሰው ጥቅም ለዳይሬክተሮች አይከፈላቸውም፡፡ ሆኖም የተጣራ ትርፍ ወደ ኩባንያው ካፒታል ወይም ወደ ተቀማጭ ሂሣብ እንዲዛወር ከተወሰነ የዳይሬክተሮች ከተጣራ ትርፍ ጥቅም የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡

አንቀጽ ሃያ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጉባዔ

1. በሌላ ጊዜ ወይም ቦታ እንዲሆን ካልተወሰነ በስተቀር የዳይሬክተሮች ቦርድ ወር በገባ -------------ቀን በማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት ጉባዔ ያደርጋል፡፡ ሆኖም የቦርዱ እጅግ ቢዘገይ ጉባዔ በሁለት ወር ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ መሆን አለበት፡፡

2. ከዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ በሚደረገው የመጀመሪያው የቦርድ ሰብስባ የዳይሬክተሮች ሰብሳቢ /ፕሬዝዳንት/ ይመርጣሉ፡፡ ሰብሳቢው ለአንድ ዓመት ወይም የሚተካው ሰው ቦታውን ተረክቦ ሥራውን እስከሚጀምር ድረስ ያገለግላል፡፡ ቦርዱ የሾመውን ሰብሳቢ ሊሽረው ይችላል፡፡

3. የማኅበሩ ፀሐፊ የጉባዔውን መዛግብት ይይዛል፡፡

Page 56: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ አንድ ስለ ሥራ አመራር

1. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይሾማል፡፡ 2. ሥራ አስኪያጁ የማኅበሩን ዓላማና ተግባር በሚመለከት የሚከተሉትን ሥራዎች ለማከናወን ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ

መሠረት፤ ሀ. ከዳይሬክተሮች ቦርድ የተሠጠውን አጠቃላይ መመሪያ በመመርኮዝ ማኅበሩን ለመምራት በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት ማኅበሩ ለተቋቋመበት ዓላማ ግብ መምታት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ለ. የማኅበሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ሐ. የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ በሚያዘው መሰረት ዓመታዊ በጀት፣ የሥራ ፕሮግራም፣ የሂሳብ ሪፖርት እንዲሁም ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ካዘጋጀና ከመረመረ በኋላ ለቦርዱ ያቀርባል፡፡ መ. ሠራተኛ ይቀጥራል፣ ዕድገት ይሰጣል፣ ያስተዳድራል፣ የደመወዝ ክፍያ የሥራ ሁኔታዎችን ይወስናል፣ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑትን ኃላፊዎች መርጦ እንዲሾሙ ለቦርዱ ያቀርባል፡፡ ሠ. በዳይሬክተሮች ቦርድ በተፈቀደው የሥራ ፕሮግራም መሠረት የማኅበሩ የሂሳብ አያያዝ ደንብ ሥርዓት በሚፈቅደው መሠረት ወጪዎችን ያጸድቃል፡፡ ረ. የማኅበሩን ዓመታዊ ሂሣብ የሚመረምሩ የውጪ ኦዲተሮችን ምርጫ ሹመት በሚመለከት ለቦርዱ ሃሳብ /ምክር/ ያቀርባል፡፡ ሰ. ግዢና ሽያጭን በተመለከተ ከሥሩ ለሚገኙት ሠራተኞች መመሪያ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ሸ. የማህበሩን ዓላማ ለማሳደግ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን ያቋቁማል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ቀ. የሥራ መጓተትን የሚያስቀር፣ ትርፋማነትን የሚጨምር የተቀላጠፈ የቁጥጥር መዋቅርና አሠራር ይዘረጋል፡፡ በ. የሠራተኛ ሕጎችና የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በሚፈቅዱለት መሠረት በሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ ተ. ከላይ ከተጠቀሱት ተግባሮች ጋር የተዛመዱ ሌሎች ሥራዎችንም ያከናውናል፡፡

Page 57: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ አንድ ስለ ሥራ አመራር

3. የዳይሬክተሮች ቦርድ የቅርብ ክትትል በማድረግ የተሰጠውን ሥልጣን በከፊል

ወይም በሙሉ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥን ማስያዝንም ጨምሮ፣ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ ውክልና መስጠት ይችላል፡፡

4. ዋናው ሥራ አስኪያጅ ወይም እርሱ በሚወክለው ተወካይ በማንኛውም

የዳይሬክተሮች ቦርድ ጉባዔ ላይ ይገኛል፡፡ በውይይቱም ተካፋይ ሊሆን ይችላል፡፡ ድምጽ መስጥት ግን አይፈቀድለትም፡፡

Page 58: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ ሁለት ስለ ኦዲተሮች

1. ኦዲተሮችና ረዳት ኦዲተሮች በሕግ፣ በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍና በመተዳደሪያ ደንብ የተጠቀሱት ሥልጣኖችና ግዴታዎች አሏቸው፡፡

2. ማንኛውም ኦዲተር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሥልጣኖችና ግዴታዎች ይኖሩታል፤ ሀ. የማህበሩን መዛግብትና ሰነዶችን መመርመር፣ ለ. የማኅበሩን ንብረት፣ የሂሣብ ማመዛዘኛ፣ ትርፍና ኪሣራውንም የሚያሳዩትን መዛግብት ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣ ሐ. የዳይሬክተሮች ቦርድ የሰጠው ሪፖርት የማህበሩን ትክክለኛ ገጽታ የሚያሳይ መሆኑን ማረጋገጥ፣ መ. ሥራውን ለማከናወን አስፈላጊ ነው ብሎ የሚያምንበትን መዝገብ፣ ሰነድ፣ ቃለ ጉባዔ መረጃዎችን ባለበት ማየት መመርመር፣ ሠ. በዓመታዊና በማናቸውም ጉባዔ መገኘት፣ ረ. ሌሎች ግዴታዎችንም መፈጸም፣

Page 59: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ ሶስት ስለተጨማሪ ኦዲተሮች

የካፒታሉ ሃያ አምስት በመቶ (25%) ያላነሰ ይዞታ ያላቸው ባለአክሲዮኖች በራሳቸው ወጪ ተጨማሪ ኦዲተሮች ሊሾሙ ይችላሉ፡፡ የተጨማሪ ኦዲተሮች ሥልጣንና ግዴታ ቀደም ሲል ከተመረጡት ኦዲተሮች ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡ የተጨማሪ ኦዲተሮችን የሥራ ዋጋ አበል በሚመለከት ማኅበሩ በከፊል ወይም በሙሉ ይከፍል እንደሆነ ጠቅላላ ጉባዔው ይወስናል፡፡

አንቀጽ ሃያ አራት ሕጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ

1. ከተጣራ ትርፍ በየዓመቱ 5% ለሕጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ ይነሳል፡፡ ይህም የሚሆነው ሕጋዊ የሆነው የመጠባበቂያ ገንዘብ የማኅበሩን ዋጋ ገንዘብ 20% እስኪደርስ ነው፡፡

2. ከዳይሬክተሮች ቦርድ ወይም ከማንኛውም ኦዲተር ሃሳብ የቀረበለት እንደሆነ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ተጨማሪ ወይም አማራጭ የመጠባበቂያ ገንዘብ እንዲኖር መወሰን ይችላል፡፡

አንቀጽ ሃያ አምስት የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት

1. ማኅበሩ በሕጉና በንግድ አሠራር መሠረት ተቀባይነት ያለው የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት ይኖረዋል፡፡ 2. ማኅበሩ ሂሳቡን በዓመት አንድ ጊዜ መዝጋት ይኖርበታል፡፡

Page 60: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ ስድስት ስለ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል

1. የማኅበሩ ዕዳዎችና ወጪዎች ከተቀነሱ እንዲሁም የመጠባበቂያ ገንዘብ ከተነሳ በኋላ ከትርፍ ቀሪ የሆነው ገንዘብ ለባለአክሲዮኖች እንዲከፈል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡

2. ትርፍም የሚከፋፈለው ባለአክሲዮኖች በከፈሉት ገንዘብ መጠን በውል በተጠቀሰው የቀደምትነት መብት መሠረት ነው፡፡

3. የትርፍ ድርሻዎች የሚከፈሉበት ቀንና የአከፋፈሉ ሁኔታ በዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ናቸው፡፡

አንቀጽ ሃያ ሰባት ስለ ማኅበሩ መፍረስና ሂሣብ ማጣራት

1. ማኅበሩ በሕግ በተመለከተውና በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ መሠረት ይፈርሳል፡፡ 2. ማኅበሩ እንዲፈርስ ጠቅላላ ጉባዔው በወሰነ ጊዜ ማህበሩ ሦስት ሂሳብ አጣሪዎች ይሾማል፡፡ 3. ማኅበሩ እንዲፈርስ ትዕዛዝ የተሰጠው በፍርድ ቤት ውሳኔ ሲሆን የዳይሬክተሮች ቦርድ ጠቅላላ ጉባዔውን

ጠርቶ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በተሰጠ 15 ቀን ውስጥ ሦስት ሂሣብ አጣሪዎች ይሾማል፡፡ 4. ማንኛውም የማኅበሩ አባልም ሆነ ኦዲተር የሂሳብ አጣሪዎችን ሹመት በመቃወም ያመለከተ እንደሆነ የቀረበው

መቃወሚያ በቂ ምክንያት ያለው ሆኖ ካገኘው ጠቅላላ ጉባዔው ሹመቱን ሊሽረው ወይም ሊያስቀረው ይችላል፡፡

5. ሹመቱ በተካሄደበት ጊዜ በጠቅላላ ጉባዔው ውሣኔ የተሰጠበት ካልሆነ፣ ለሂሣብ አጣሪዎች የሚከፈለው አበል ማኅበሩ በፈረሰበት ጊዜ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ በሚከፈለው አበል ልክ ነው፡፡

Page 61: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ ስምንት የኦዲተሮች ሥልጣንና ግዴታዎች

1. የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ለሂሳብ ዓመቱ የሚያገለግሉ ኦዲተሮችን ይመርጣል፣ 2. ሂሣብ አጣሪዎች ከዳይሬክተሮች እጅ የማኅበሩን ሀብቶችና የሂሣብ ሰነዶች በኃላፊነት ይቀበላሉ፡፡

ዳይሬክተሮችም የመጨረሻው የሂሳብ ማጠቃለያ ጊዜና የሂሣቡ ማጣራት በተጀመረበት ጊዜ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ያደረጉትን የሥራቸውን መግለጫ /ሪፖርት/ ያቀርቡላቸዋል፡፡

3. የኦዲተሮች ሥልጣን፣ ግዴታዎችና መብቶች በንግድ ሕጉ በተወሰነው መሠረት ይሆናል፡፡ 4. ያለው ገንዘብ የማኅበሩን ዕዳዎች ለመክፈል በቂ ሆኖ ያልተገኘ እንደሆነ ሂሣብ አጣሪዎች ባለአክሲዮኖች

በአክሲዮኖቻቸው ላይ ያልከፈሉትን ድርሻ እንዲከፍሉ ይጠይቋቸዋል፡፡ 5. ሂሣብ አጣሪዎች በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ወይም በጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣናቸውን የሚቀንሱ ውሳኔዎች

ካልተደረጉ በቀር የሂሳብ ማጣራቱን ተግባር በመልካም ለማካሄድ ሙሉ የሆነ ሥልጣን አላቸው፡፡ በተለይም የማህበሩን ሀብት በጅምላ ለመሸጥና የተለያዩ ጉዳዮችን በስምምነት ለመጨረስ፣ ለመግባባትና ለመዋዋል ይችላሉ፡፡ በፍርድ ቤትም የማኅበሩ ነገረፈጅ ይሆናሉ፡፡

6. ተጀምሮ ለነበረው ውል አፈጻጸም ወይም የሂሳብ ማጣራቱ ጥቅም ያስገደደ ካልሆነ በቀር አዲስ ሥራዎች ለመጀመር አይችሉም፡፡ በዚህ በመተዳደሪያ ደንብ ከተደነገጉት ውሣኔዎች ውጪ ለሚሰሯቸው ሥራዎች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

7. ጠቅላላ ጉባዔ የመረጣቸውን የሂሣብ አጣሪዎች ሥልጣን ሊወሰን ይችላል፡፡

Page 62: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር የመተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ የማጠቃለያ ድንጋጌ

በመመስረቻ ጽሑፍ ወይም በዚህ መተዳደሪያ ደንብ በግልጽ ያልተካተቱ ጉዳዮች በንግድ ሕጉ መሠረት ይወሰናሉ፡፡

መስራቾች ስም ፊርማ ---------------------------------- ------------- ---------------------------------- ------------- ---------------------------------- ------------- ---------------------------------- ------------- ---------------------------------- --------------

Page 63: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ኢ.ቲ.ጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማህበር ለማቋቋም በግል ከዶ/ር እሸቱ ተመስገን ገላን የተወሰደ ብድር የውለታ ቅፅ

የተበዳሪ ሰራተኛው ስም አቶ/ወ/ሮ/ወ/ት፡ የሚሰራበት ክፍል፡ አድራሻ፡ ክ/ከተማ ወረዳ የቤ/ቁ ስልክ፡ የተፈረመ የአክሲዮን ድርሻ ብር፡ 25% የአክሲዮን ድርሻ ብር 6% የስራ ማስኬጃ ብር ሲሆን በ2009 የበጀት ዓመት የተወሰደ ብድር ብር በፊደል፡ ብድር የተጠየቀበት ምክንያት፡ የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማህበር ለማቋቋም የአክሲዮን ድርሻ ክፍያ ለመግዛት፡፡ ተከፍሎ የሚያልቅበት ጊዜ፡ ከ እስከ ተበዳሪው ጠቅላላ የብድሩን መጠን የአክሲዮን ማህበሩ ከተቋቋመበት ቀን አንስቶ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከአክሲዮን ትርፍ ድርሻ እንዲሁም በተጨማሪ ከራሴ በሟሟላት እስከ አራተኛው የበጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ከፍዬ ለመጨረስ በመስማማት ይህን ውለታ ወድጄ እና ፈቅጄ ፈርሜያለሁ፡፡ የትዳር ጓደኛ ማረጋገጫ እኔ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ት የትዳር ጓደኛዬ የሆነው/ችው የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማህበርን ለማቋቋም የአክሲዮን ግዢ ለመፈፀም የተደረገውን ብድር አውቄና ተስማምቼ በውለታው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለመክፈል በጋራ ተስማምተን ፈርመናል፡፡ ሰራተኛው/ዋ ብድሩን ሳይከፍል/ሳትከፍል ድርጅቱን ለቅቃ/ቆ ቢወጣ/ብትወጣ ያለበትን/ባትን እዳ አበዳሪው ከአክሲዮን ማህበሩ ላይ ከምናገኘው ማናቸውም ጥቅማጥቅም ወይም ጠቅላላ /በከፊል የአክሲዮን ድርሻ በውሉ ዘመን መጨረሻ ላይ መውሰድ እንደሚችሉ ተስማምተናል፡፡ የውለታው ዘመን መጨረሻ 2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ይሆናል፡፡

ተበዳሪ አበዳሪ ስም፡ ስም፡ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ገላን ፊርማ፡ ፊርማ፡ (ባለትዳር ካልሆኑ በፎርሙ ላይ "የለኝም" ብለው ይፃፉ እና በድጋሚ ስምዎን ፅፈው ይፈርሙ፡፡) የትዳር ጓደኛ ስም፡ ፊርማ፡ ምስክሮች፡ 1ኛ. ስም ፊርማ፡ 2ኛ. ስም ፊርማ፡ 3ኛ. ስም ፊርማ፡ ይህ ፎርም በ 3ኮፒ ተሰርቶ 1ኛው ለአበዳሪ፣ 2ተኛው ለተበዳሪ፣ 3ተኛው ለአክሲዮን ማህበሩ አስተዳደር ፋይል መያያዝ አለበት፡፡

Page 64: የካቲት 09 ቀን 2009 ዓም - ETG Designers

ኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክስዮን ማኅበር የባለአክስዮኖች የምዝገባ ቅጽ

ሙሉ ስም ከነአያት ------------------------------------------------------------------ የትውልድ ዘመን ------------------------- ጾታ ---------------- የጋብቻ ሁኔታ ------------------ የመኖሪያ አድራሻ --------------------- ከተማ፤ ----------------------- ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ ---------፤ የቤት ቁጥር ------------፤ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስፖርት ቁጥር --------------------------------- ስልክ ቁጥር --------------------------- ኢሜይል -------------------------------------------------- ባለትዳር ከሆኑ፤ የባለቤትዎ ሙሉስም ከነአያት --------------------------------------------------- አድራሻ ---------------------- ከተማ፤ ----------------------- ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ ------------- የቤት ቁጥር -------------------፤ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስፖርት ቁጥር --------------------------------- ስልክ ቁጥር -------------------------------፤ ኢሜይል -------------------------------------------------- የሙያ መስክ -----------------------------፣ የሙያ ደረጃ --------------------------------------- በሙያዎ በአክስዮን ማኅበሩ ውስጥ መደበኛ ሠራተኛ ሆነው ለመስራት ፈቃደኛ ነዎት? ------------------ ለመግዛት የሚፈልጉት አክስዮን ብዛት --------፤ የአንዱ አክስዮን ዋጋ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)፣ ጠቅላላ ዋጋ ብር ----------------፤ (-------------------------------------------------) ለሥራ ማስኬጃ ወጪ ክፍያ የገዛሁትን የአክስዮን መጠን 6 በመቶ ማለትም ብር --------------- (--------------------------------------------------------) በአንድ ጊዜ በምዝገባ ወቅት ለመክፈል ተስማምቻለሁ፡፡ ከላይ ስሜ/ስማችን የተጠቀሰው በኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክስዮን ማኅበር አክስዮን ለመግዛት የተስማማሁ/ንና እስከ ------------------- ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ የገዛሁትን/ነውን አክስዮን ጠቅላላ ዋጋ አንድ አራተኛ በአክስዮን ማኅበሩ ዝግ የባንክ ሂሳብ አዋሽ ባንክ ካዛንቺሽ ቅርን. 0130496711600/ 01304096772400 ገቢ የማደርግና/የምናደርግና ቀሪውንም በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብና መመሥረቻ ጽሑፍ መሰረት የምከፍል/የምንከፍል መሆኔን/መሆናችንን አረጋግጣለሁ/እናረጋግጣለን፡፡ ሙሉ ስም ---------------------------------- ፊርማ ------------------------ ቀን --------------------- የባለቤትዎ ሙሉ ስም -------------------------------- ፊርማ---------------------- ቀን----------------------


Recommended