+ All Categories
Home > Documents > Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Date post: 17-Oct-2014
Category:
Upload: desta-abraha
View: 457 times
Download: 4 times
Share this document with a friend
Description:
ተቋማዊው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሙስና በፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሲጋለጥ አፍቅሮተ ንዋይ እንደበሰበሰ ቅጠል ጭንቅላቱን ያገማው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አመራርና የፈጠ ረው የሙስና መረብ የአገሪቱ ህግና ስርአት የማይገዛው ለብቻው የታጠረ የማፍያ ቡድን ከሆነ በርካታ አመታት አልፏል :: ይህ ቡድን ፦Ø በፈለገው ጊዜ ህግ ያፈርሳል ፣የፈለገው አይነት ህግ ያወጣል Ø የመንግስትና የህዝብ ሃብትን ይዘርፋል፣ ያዘርፋልØ የፈለገውን አላግባብ ይቀጥራል፣ ያልተገባ የትምህርት እድል(Scholarship) ይሰጣል፣ የራሱ የደመወዝ ስኬል በዘፈቀደ(ከሲቪል ሰርቪስ ህግ ውጭ) ያወጣል፣ የአይንህ ቀለም አላማረኝም ያለውንም ያባርራልØ ደካማውን ይሾማል ፣ጠንካራውን በሃሰት ይወነጅላል ይህ ቡድን ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህግ ልእልናን ያለምህረት በመናድ ሙስናን የህይወት መርህና ፍልስፍና ያደረገ ቡድን ነው ። ከአስር አመት በላይ ያስቆጠረው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሙስና ዛሬ መረን ለቆ ወደ ተቋማዊ ሙስና ተሸጋግሯል። በዘመናት የስልጣኔ ጉዞ የተገነቡት መልካም ማህበረሰባዊና ባህላዊ እሴቶቻችንም በዚህ አደገኛ መርዝ ክፉኛ በመሸርሸር ላይ ናቸው።ቡድኑና የሙስና መረቡ በትምህርትና ምርምር ጥራት እና በሀገራችን እድገት አፍራሽ ሚና ከመጫወቱም ባሻገር ማጭበርበር፣ ስርቆት፣ በህገወጥ መንገድ ሳይሰሩ በአቋራጭ ሃብት ማካበት ባህል ሆነው እንዲነግሱና ተቀባይነት ያላቸው የኑሮ መንገድ ሆነው እንዲወሰዱ ዋና ተዋናይ ሆኖ እየሰራ ነው። ይህ ተግባር ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አልፎ መላውን የክልሉ ነዋሪ ያነጋገረ ቢሆንም ሰሚ ያጣ ጩኸት ሆኗል። የዛሬ ሰባት አመት(ህዳር 1997 ዓ ም)የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቸ ባደረጉት የፀረ ሙስና አድማ ምክንያት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁሞ በማጣራት በወቅቱ በቁጥር p165/06 በቀን March 27/2006 በተፃፈ ደብዳቤ ለዩኒቨርሲቲው ማሀበረሰብ በበተነው ሰነድ ተቋማዊ ለውጥ እንደሚያመጣና ተገቢውን አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ መወሰኑን አሳውቆ ነበር። ሆኖም ምንም አይነት ተቋማዊ ለውጥ ሳይመጣ ምንም አይነት ህጋዊ እርምጃ ሳይወሰድ ቡድኑና የሙስና መረቡ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ምክንያት ሆነ።በ 2002ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በፈጠረው አስደናቂ የፀረ ሙስና ንቅናቄ በርካታ ጥቆማዎች፣ሰነዶችና ማስረጃዎች በመቅረባቸው ቦርዱ በተለያየ ጊዜ ሁለት የተለያዩ ኮሚቴዎች አዋቅሮ ነበር። የመጀመሪያው ኮሚቴ ትርጉም ያለው የማጣራት ስራ ሳይሰራ የፈረሰ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የተቋቋመው ኮሚቴም ለሁለት ወራት የማጣራት ስራ ሰርቷል ቢባልም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስለማጣራቱ ሂደት ውጤት የሚያውቀው ነገር የለም። በዩኒቨርሲቲወ የተደረገ መሰረታዊና ተቋማዊ ለውጥም የለም።በመሆኑም ቡድኑና የሙስና መረቡ ብልሹ አሰራሩና ሙስናን ከበፊቱ በተጠናከረ መልኩ እየቀጠለበት ይገኛል። ማፍያው ቡድንና የሙስና መረቡ ዝርፍያውንና ህገወጥነቱን አጠናክሮ የቀጠለበት መሆኑን የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2003 የመውጫ ውይይት አጀንዳ ብሎ ያወጣውን ማየት በቂ ነው። ዋና ዋናዎችን ጠቅለል አድርገን ለንባብ እንዲመች እንደሚከተለው በማቅረብ ዝርዝሩና ሙሉዉን ሰነድ በአባሪ (Attachment) አያይዘናል። 1. ሃገራዊ ሽፋን ባለው ጋዜጣ ወይም ሬድዮ ግልፅ ጨረታ ሳይወጣና ውድድር ሳይደረግ በቀጥታ ግዥ ተፈፅሞ የተገኘባቸው (ሁለት መቶ ሀያ አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ሰባት መቶ ሰባሰባት ብር ከ ሰባ ስድስት ሳንቲም) 225,368,777̣.762. የቁጥጥር ስራና የማማከር ፍቃድ ሳይኖረው የኮንስትራክሸን ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲው የፋሲሊቲ አስተዳደር ፅ/ቤት ዳይሬከተር የኮንስትራክሸን ፕሮጀክቶችን የቁጥጥር (supervision) ስራ የሰራበት (ሰባ ሶስት ሚሊዮን ስልሳ ሶስት ሺ ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ብር) 73,063,911.00 3. የጉምሩክ ዲከላራሲዮንና ተያያዥ ማስረጃዎች ሳይኖራቸው ወጪ የተደረጉ (ሀያ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ አምሳ ስምንት ሺ ስድስት መቶ አስራ ስምንት ብር ከ አምሳ ስምንት ሳንቲም) 25,458,618 .58 4. በማተሚያ ቤት ያልታተሙና ተከታታይ ቁጥር የሌላቸው ለሂሳብ ማወራረጃነት በቀረቡ የክፍያ ደረሰኞች ወጪ የተደረገ (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስድሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከ ሀምሳ ሶስት ሳንቲም) 3,361,999.53 እና ሌሎች በርካታ ዝርዝሮች በአባሪ (Attachment) ከተያያዘው ሰነድ ያንብቡ።በመጨረሻም የቀረን የብርሃን እንጥፍጣፊ ተሟጦ ልንገፈው በማንችል ድቅድቅ ጨለማ ከመዋጣችን በፊት፣ሙስና ህጋዊና ባህላዊ ከመሆኑ በፊት፣ሙሰኞች የማይደፈሩ ንጉሶች ከመሆናቸው በፊት………..ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ የመሩ አብዮታውያን በዚህ ቡድን ይንበረከካሉ የሚል እምነት የለምና ፈጥነው ትውልድ የማዳን ስራ እነዲሰሩ እንማፀናለን።
Popular Tags:
12
Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)
Transcript
Page 1: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 2: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 3: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 4: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 5: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 6: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 7: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 8: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 9: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 10: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 11: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)

Page 12: Federal Audit Investigation on Mekelle University MU Corruption

Created with novaPDF Printer (www.novaPDF.com)


Recommended