+ All Categories
Home > Documents > Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ...

Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ...

Date post: 12-Mar-2020
Category:
Upload: others
View: 36 times
Download: 0 times
Share this document with a friend
24
Ze-Habesha Newspaper June 2014 No. 64 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ሰኔ 2006 / ቅጽ VI ቁጥር. 64 / የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት አካል ይሁኑ ዕውነት ያሸንፋል Tax! ታክስ! Tax! ታክስ! Tax! ታክስ! ከጃንዋሪ 2014 ጀምሮ ታክስዎን የሚሠራልዎ በሙያው አንቱታን ያገኘው አክሎግ ነው ጥርስዎን ለመታጠብ፣ ለመነቀል፣ ለማስተካከልና ለሌሎችም ወደ ዊሎ የጥርስ ህክምና ይምጡ አፕል ጋራዥ Apple Auto Repair - Engine - Brakes - Suspension - Transmission - Electrical - Body - Interior More... የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን $25 ብቻ የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃው እና ጉልበቱ በ20$ ብቻ። 3601 Minnehaha Ave, Mpls, MN55406. የዓለም ዋንጫን ማን ያነሳል? “የእናቶች ምርቃት ሕይወት ሆኖኛል” ገጽ 15 ላይ ገጽ 21 ላይ ገጽ 3 ላይ Universal Realty Group ዮሐንስ፡- 651-3343029 በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለውና በሕዝብ ልብ ውስጥ በምግባት “ሕዝባዊ አርቲስት” የሚል ስያሜ ያለው አርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ (ቴዲ አፍሮ) በሰሜን አሜሪካ ከሚያቀር ባቸው ትላልቅ ኮንሰርቶች መካከል ሚኒሶታን አንዷ በማድረግ ጁላይ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በዳውን ታውን ሚኒያፖሊስ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ። ባለፈው ቅዳሜ በሲያትል በብዙ ሺህ ሕዝብ የሚቆጠር አድናቂዎቹ የታደሙበትን የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት ያቀረበው ቴዲ አፍሮ በሚኒሶታ የሚያቀርበውን ኮንሰርት ብዙዎች ከወዲሁ በጉጉት እየጠበቁት የሚገ ኝ ሲሆን ድምጻዊውም በተለይ በሳንሆዜና በኒውዮርክ ሥራዎቹን ካቀረበ በኋላ ሚኒሶታ መምጣቱን በጉጉት እንደሚጠብቀው የቅርብ ምንጮች አስታውቀዋል። ሙሉ የሙዚቃ አልበም ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀና በቅርቡም ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ የሚነገርለት ከጥላሁን ገሠሠ ቀጥሎ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በመረከቡ “ንጉሥ” የሚል ስያሜን በአድናቂዎቹ ስላገኘው ቴዲ አፍሮ የተሰናዳ ዘገባ በውስጥ ገጽ የቀረበ ሲሆን ቅዳሜ ጁላይ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የዚህ ንጉሥ ድምጻዊ ኮንሰርት የሚደረግበት አድራሻ፦ Mill City Nights - 111 5th St N, Minneapolis, MN 55403 ለአቅጣጫና ስለዋጋ ለመጠየቅ 651-955-6091፣ 612-226-8326 ወይም 612-423-7009 ይደውሉ አበበ ገላው ለኢሳት 4ኛ ዓመት ሚኒሶታ ይመጣል ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር በመሆን “ኢሳት የኔ ነው” በሚል በሚኒሶታ በተዘጋጀው የ4ኛ ዓመት ፈንድራዚይንግ ላይ እንደሚገኙ አስተባባሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። እንደ አስተባባሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ይኸው ለኢሳት ራድዮና ቲቪ ማጠናከሪያ ይውል ዘንድ የተዘጋጀው ይኸው ዝግጅት እሁድ ጁላይ 13 ቀን 2014 በሴንት ፖል ኬሊ ኢን ሆቴል የሚደረግ ሲሆን የአበበ ገላውን እና ሳዲቅ አህመድን ዝግጅት ዝነኛው ድምጻዊ ተሾ መ አሰግድ እንደሚያጅበው ታውቋል። የዝግጅቱ ፍላየር በውስጥ ገጻችን ታትሟል። አህመድ ዋሴ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ የሚኒሶታ ሰው ሆነ በሚኒሶታ የዘ-ሐበሻ ደጋፊዎች እና ተጋባዥ የክብር እንግዳው አርቲስትና አክቲቪ ስት ታማኝ በየነ በተገኙበት የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ 6ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በድምቀት ተከበረ። በዚሁ የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት በዓል ላይ በሚኒሶታ መልካም ነገ ር ለማህበረሰባቸው ካደረጉ ወገኖች መካከል አንዱ የሆነውና በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ራድዮ ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ አህመድ ዋሴ የዓመቱ ምርጥ ሰ ው በሚል በዘ-ሐበሻ ተሸልሟል። (አህመድ... ወደ ገጽ 21 የዞረ) “በዘ-ሐበሻ ላይ በየወሩ መልዕክት የማስተላልፈው ራዕይ ታይቶኝ ነው” ፀሎት የምትፈልጉ ወይም ጥያቄ ያላችሁ፦ ከፓስተር ደስታዬ ክራውፎርድ በ612-225-8269 ይደውሉ። 1901 Portland Ave S, Minneapolis MN 55404 ፓስተር ደስታዬ በዘ-ሐበሻ ላይ በየወሩ ለምን መልዕክት ለማስተላለፍ እንደተገደደች ለማወቅ በገጽ 21 ይመልከቱ በተለያየ ሁኔታ ውስጥ የፈረሰው የሰው ሕይወት በ እግዚአብሔር ቃል የሚገነባበት ዘመን። በየቀኑ ከጠዋቱ 10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት፤ አርብ ከምሽቱ 6 ሰዓት በመምጣት የእግዚአብሔርን በረከት አብራችሁን ተካፈሉ። ስለታላቁ ረመዷን ጾም
Transcript
Page 1: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

Ze-Habesha Newspaper June 2014 No. 64 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ሰኔ 2006 ᴥ / ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 64 / የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት አካል ይሁኑ ዕውነት ያሸንፋል

Tax! ታክስ! Tax! ታክስ! Tax! ታክስ!ከጃንዋሪ 2014 ጀምሮ ታክስዎን የሚሠራልዎ

በሙያው አንቱታን ያገኘው አክሎግ ነው

ጥርስዎን ለመታጠብ፣ ለመነቀል፣ ለማስተካከልና ለሌሎችም ወደ ዊሎ የጥርስ ህክምና ይምጡ

አፕል ጋራዥ Apple Auto Repair

- Engine- Brakes- Suspension- Transmission

- Electrical- Body- InteriorMore...

የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን

$25ብቻ

የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃውእና ጉልበቱ በ20$

ብቻ።

3601 Minnehaha Ave, Mpls, MN55406.

የዓለም ዋንጫን ማን ያነሳል?

“የእናቶች ምርቃት

ሕይወት ሆኖኛል” ገጽ 15 ላይገጽ 21 ላይ ገጽ 3 ላይ

Universal Realty Group

ዮሐንስ፡- 651-3343029

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለውና በሕዝብ ልብ ውስጥ በምግባት “ሕዝባዊ አርቲስት” የሚል ስያሜ ያለው አርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ (ቴዲ አፍሮ) በሰሜን አሜሪካ ከሚያቀርባቸው ትላልቅ ኮንሰርቶች መካከል ሚኒሶታን አንዷ በማድረግ ጁላይ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በዳውን ታውን ሚኒያፖሊስ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ። ባለፈው ቅዳሜ

በሲያትል በብዙ ሺህ ሕዝብ የሚቆጠር አድናቂዎቹ የታደሙበትን የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት ያቀረበው ቴዲ አፍሮ በሚኒሶታ የሚያቀርበውን ኮንሰርት ብዙዎች ከወዲሁ በጉጉት እየጠበቁት የሚገኝ ሲሆን ድምጻዊውም በተለይ በሳንሆዜና በኒውዮርክ ሥራዎቹን ካቀረበ በኋላ ሚኒሶታ መምጣቱን በጉጉት እንደሚጠብቀው የቅርብ ምንጮች አስታውቀዋል። ሙሉ የሙዚቃ አልበም ዝግጅቱን

እንዳጠናቀቀና በቅርቡም ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ የሚነገርለት ከጥላሁን ገሠሠ ቀጥሎ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በመረከቡ “ንጉሥ” የሚል ስያሜን በአድናቂዎቹ ስላገኘው ቴዲ አፍሮ የተሰናዳ ዘገባ በውስጥ ገጽ የቀረበ ሲሆን ቅዳሜ ጁላይ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የዚህ ንጉሥ ድምጻዊ ኮንሰርት የሚደረግበት አድራሻ፦

Mill City Nights - 111 5th St N, Minneapolis, MN 55403 ለአቅጣጫና ስለዋጋ ለመጠየቅ 651-955-6091፣ 612-226-8326 ወይም 612-423-7009 ይደውሉ

አበበ ገላው ለኢሳት 4ኛ ዓመት ሚኒሶታ ይመጣልጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር በመሆን “ኢሳት የኔ ነው” በሚል በሚኒሶታ በተዘጋጀው የ4ኛ ዓመት ፈንድራዚይንግ ላይ እንደሚገኙ አስተባባሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። እንደ አስተባባሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ይኸው ለኢሳት ራድዮና ቲቪ ማጠናከሪያ ይውል ዘንድ የተዘጋጀው ይኸው ዝግጅት እሁድ ጁላይ 13 ቀን 2014 በሴንት ፖል ኬሊ ኢን ሆቴል የሚደረግ ሲሆን የአበበ ገላውን እና ሳዲቅ አህመድን ዝግጅት ዝነኛው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ እንደሚያጅበው ታውቋል። የዝግጅቱ ፍላየር በውስጥ ገጻችን ታትሟል።

አህመድ ዋሴ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ የሚኒሶታ ሰው ሆነበሚኒሶታ የዘ-ሐበሻ ደጋፊዎች እና ተጋባዥ የክብር እንግዳው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በተገኙበት የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ 6ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በድምቀት ተከበረ። በዚሁ የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት በዓል ላይ በሚኒሶታ መልካም ነገር ለማህበረሰባቸው ካደረጉ ወገኖች መካከል አንዱ የሆነውና በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ራድዮ ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ አህመድ ዋሴ የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል በዘ-ሐበሻ ተሸልሟል። (አህመድ... ወደ ገጽ 21 የዞረ)

“በዘ-ሐበሻ ላይ በየወሩ መልዕክት የማስተላልፈው

ራዕይ ታይቶኝ ነው”

ፀሎት የምትፈልጉ ወይም ጥያቄ ያላችሁ፦ከፓስተር ደስታዬ ክራውፎርድ በ612-225-8269 ይደውሉ።በ1901 Portland Ave S,

Minneapolis MN 55404ፓስተር ደስታዬ በዘ-ሐበሻ ላይ በየወሩ

ለምን መልዕክት ለማስተላለፍ እንደተገደደች ለማወቅ በገጽ 21 ይመልከቱ

በተለያየ ሁኔታ ውስጥ የፈረሰው የሰው ሕይወት በ እግዚአብሔር ቃል

የሚገነባበት ዘመን።በየቀኑ ከጠዋቱ 10 ሰዓት እስከ

12 ሰዓት፤ አርብ ከምሽቱ 6 ሰዓት በመምጣት የእግዚአብሔርን

በረከት አብራችሁን ተካፈሉ።

ስለታላቁ ረመዷን ጾም

Page 2: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 2

Page 3: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 3

Ze-Habesha Newspaper is Legally Registered in state of

Minnesota - USA

Founded in December 2008 Publisher :-

ZeHabesha LLC

ዋና አዘጋጅ:-

ሔኖክ ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in Chief:-

Henok A. Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:- ሊሊ ሞገስ፣

[email protected]ሮቤል ሔኖክ፣

[email protected]ቅድስት አባተ

ዘላለም ገብሬ (ቺካጎ)[email protected]

አማካሪ፡- ዶር ዓብይ ዓይናለም

Ze-Habesha newspaper Address:-

6938 Portland Ave, Richfield MN 55423

) 612-226-8326 www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabeshawww.twitter.com/zehabesha

“Journalism can never be silent: that is its greatest virtue and its greatest fault. It

must speak, and speak immediately, while the echoes of wonder, the claims

of triumph and the signs of horror are still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ - አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ መልዕክት

ተመስገን ደሳለኝ

(የፋክት መጽሔትአዘጋጅ እንደጻፈው)

…ዕለቱ የሁለት ሺ ሶስት ዓመተ ምህረት የመስቀል በዓል የተከበረበት ማግስት፤ ሰሜናዊቷ የኤርትራ አዋሳኝ ወልቃይት ገና ከእንቅልፏ ሙሉ ለሙሉ ባለመንቃቷ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ጎፈሪያቸው የተንጨ(ባረረ ፋኖዎች በውስጧ ካሉ ተቋማት ወደ አንዱ እያመሩ ስለመሆኑ የጠረጠረች አትመስልም፤ ከኤርትራ የተነሱት ፋኖዎች መዳረሻ በወረዳዋ ታዋቂ የሆነው አወርቅ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመሆኑ፤ ማንም ልብ ሳይላቸው ልክ እዚያው እንደደረሱ፣ ከፊሎቹ በሰለጠነ ወታደራዊ ስልት ትምህርት ቤቱን ከአጥር ውጪ በመክበብ ድንገተኛ ጥቃት የሚሰነዝር ኃይል ከመጣ ለመከላከል ሲያደፍጡ፤ የተቀሩት ደግሞ ወደ ውስጥ በመግባት በግቢው የሚገኙ መምህራን ሜዳው ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ፤ በጥቂት ደቂቃዎችም ውስጥ ሁሉም በተባለበት ቦታ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በዕቅዱ መሰረት መፈፀሙን በጥንቃቄ ሲከታተል የነበረው የቡድኑ መሪ በቅድሚያ ስለራሱና ጓደኞቹ ማንነት እና ስለወከሉት ድርጅት አጭር ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የትግሉን ዓላማ በስፋት አብራርቶ አስረዳ፤ ሌሎች ጓዶቹም የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ዋና ዋና ርዕሶች የሚገልጹ በአማርኛና ትግርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን የማደል ስራቸውን በማጠናቀቃቸው እንደአመጣጣቸው በሽምቅ ተዋጊ ስልት ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡ ይህ በሆነ በአስራ ሁለተኛው ቀን (መስከረም 30) ደግሞ እዛው ወረዳ ወደሚገኝ ሌላ ትምህርት ቤት ለተመሳሳይ ዓላማ ድንገት ተመልሰው መጥተው ነበር፤ ሆኖም መንገድ ላይ ካደፈጡ ፖሊሶችና ታጣቂዎች ጋር ፊት ለፊት ተገጣጥመው በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ከእነርሱ ወገን አንድ ሲሰዋ፤ ከፖሊስ አባላት አንድ ቆስሏል፤ አንድ መምህርም በገዛ ቤቱ በተቀመጠበት በተባራሪ ጥይት ቆስሏል፤ ፋኖዎቹም የዚያ ቀን ዓላማቸው ከሽፎ ወደመጡበት የኤርትራ በርሃ ተመልሰው ለመሄድ ተገድደዋል…

ፊታችሁን ወደ ሰሜን…ከወዳጆቼ ግርማ ሰይፉና በላይ ፍቃዱ ጋር መቀሌን ለመጎብኘ

ት የነበረን ዕቅድ በተለያዩ ምክንያቶች እየተሰናከለ፤ መልሶ እየተወጠነ ጥቂት ለማይባሉ ወራት ሲጓተት ቆይቶ፣ በግንቦት መጨረሻ ዕለተ-አርብ ምሽት ላይ፣ ህወሓት እነ ለገሰ አስፋውን በኃይል አባርሮ በእጁ ወደአስገባት ሞቃታማዋ የትግራይ ርዕሰ-መስተዳድር መቀመጫ ደረስን፤ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ከባድ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተፈጭተው የሚጋገሩባትን፣ የአጼ ዮሀንስ ከተማ ለአራት ቀናት ተቆጣጠርናት ስናበቃ፤ ‹ከእግር እስከ ራሷ…› ለማለት ባያስደፍርም፣ የቻልነውን ያህል በጉብኝት አካለልናት፤ በተናጠልም መነሻዬን ‹ሮሚናት› አደባባይ (መሀል እምብርቷን) አድርጌ በአራቱም አቅጣጫ ለመቃኘት ሞክሬያለሁ፤ በዋናነት ትኩረቴን የሳበው ከሰማዕታቱ ሐውልት በስተሰሜን ተንጣሎ የሚገኘው መንደር ነው፤ መንደሩ በዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተውቦ ሲታይ፣ የደቡብ አፍሪካዋ ጽዱ ከተማ ኬብ-ታዎን ያሉ ቢመስልዎ ስህተቱ የእርስዎ አይሆንም፤ ስለምን ቢሉ? እየተመለከቱ ያሉት ስነ-ሕንፃ ውበት እጅግ በተራቀቁ ዘመን አመጣሽ የግንባታ ቁሳቁሶች የተንቆጠቆጠ መንደር ነውና፡፡ ወደቦታው ይዞኝ የሄደው ጎልማሳ የባጃጅ አሽከርካሪ ‹‹በትግራይ ክልል ባሉ 46ቱም ወረዳዎች በተለያየ ጊዜ በኃላፊነት ከተመደቡ አስተዳዳሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ እዚህ መኖሪያ ቤት አላቸው›› ሲለኝ ግን ማመን ቢያዳግተኝም አድናቆቴ ወደ ከፍተኛ ድንጋጤ ተቀይሯል፤ ምክንያቱም ቤቶቹ በመንግስት ደሞዝ ሊሰሩ ቀርቶ፣ ሊታሰቡ እንደማይችሉ በግልፅ ያስታውቃሉና ነው፤ ታዲያ! ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ምናልባት የአስተዳዳሪዎቹ ደሞዝ እንደ አክሱማውያን ዘመን በወቂት (በወርቅ ድንጋይ) ይሆን እንዴ?

የሆነው ሆኖ አንጋፋዎቹ ‹የታገለ-ያታገለ፣ በድል አጥቢያ አርበኝነት ያገለገለ፣ በሀገር ሀብት እንዳሻው የመምነሽነሽ መብት አለው› እንዲሉ፣ ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ አገሬውም ይህንን እውነታ አብጠርጥሮ በ

ማወቁ አካባቢውን ‹‹ሙስና ሰፈር›› ብሎ እንደሚጠራው ስሰማ፣ ጎልማሳው የነገረኝን ወደማመኑ ጠርዝ ተገፋሁ፡፡ መደበኛ ባልሆነ መልኩ የተወያየኋቸው በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ በዛ ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎችም ባለንብረቶቹ የህወሓት ካድሬዎች እንደሆኑ መስማታቸውን አረጋግጠውልኛል፡፡ በይበልጥ ደግሞ ሁለት ልጆቻቸውን በትግሉ እንዳጡ ያወጉኝ አንድ አዛውንት ምንም እንኳ እተባለው አካባቢ ሄደው ቤቶቹን በአይናቸው አለማየታቸውን ባይሸሽጉኝም፣ በተሰበረ ስሜትና ምሬት በዋጠው ድምፅ ‹‹እነርሱ በእኛ ልጆች ደም ተረማምደው፣ ለድል ከበቁ በኋላ ዓላማቸውን ትተው የሀገርን ሀብት በመዝረፍ ራሳቸውንና ዘመዶቻቸውን ባለፀጋ ማድረግ እንደቻሉ በሰማሁ ቁጥር፣ ልጆቼ የተሰዉት በደርግ ወታደሮች ጥይት ሳይሆን በገዛ የበረሃ ጓዶቻቸው ክህደት እንደሆነ አድርጌ በማሰብ በቁጭት ስለምብሰክሰክ ሀዘኑ እንደ አዲስ ያንገበግበኛል›› ሲሉ መስማት ምንኛ እንደሚያሸማቅቅ ማንም ለመገመት አይከብደውም፡፡

የዚህ አይን ያወጣ ዘረፋ መነሾም ድርጅቱ በተለይም የ1993ቱን ‹ዳግማዊ ህንፍሽፍሽ› ተከትሎ ያጋጠመውን የታማኝ ሰው እጥረት ለማሟላት መስፈርቱ ‹‹ህወሓትን እንደ ግል አዳኝ›› መቀበል ላይ የሚያተኩር እንጂ፤ የስነ-ምግባር ጉድለት ኖረ አልኖረ አሳሳቢው ባለመሆኑ እንደነበረ ይነገራል፡፡ በዚህ ድምዳሜም የቀድሞ አመራሮቹ ጭምር እንደሚስማሙ አስተውያለሁ፡፡ እውነታውን የሚያውቀው የከተማዋ ነዋሪም ቢሆን፣ ደፍሮ ህወሓትን ‹‹ሌባ!›› ብሎ ባያወግዝም፤ ተቃውሞውን ለመግለፅ መንደሩን ‹‹ሙስና ሰፈር›› በማለት መሰየሙ በራሱ አንድ ማሳያ ነው፡፡ መቼም በመቀሌ እልፍ አእላፍ ሰላዮች ከመሰግሰጋቸውም ባለፈ፣ ከምሁር እስከ ሊስትሮ፣ ከነጋዴ እስከ አርሶ አደር በጠንካራ ጥርነፋዊ መዋቅር የተጠፈሩባት ከመሆኗ አኳያ፣ ግንባታውንም ሆነ ነዋሪው የሰጠውን ስያሜ፤ ትላንት መለስ ዜናዊ፣ ዛሬ ደግሞ እነ አባይ ፀሀዬ ‹አልሰሙ ይሆናል› ብሎ ማሰቡ “ፀሀይ በምዕራብ ትወጣለች” አይነት ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ሌላው የከተማዋ ‹‹ጥቁር ሐውልት›› ተብሎ ሊጠቀስ የሚችለው፣ ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ በ2003 ዓ/ም በወርሃ ነሐሴ በታተመችው ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ (በቅርቡ ባሳተመው ‹‹ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ›› በተሰኘ መጽሐፉም አካቶታል) ‹‹ገረቡቡ-የመቀሌው አፓርታይድ መንደር›› በሚል ርዕስ ካስነበበን ‹‹የግንቦት ሃያ ፍሬ›› ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ዮናስ በጽሑፉ እንደገለፀው መንደሩ የተመሰረተው በድፍን መቀሌ በምቾቱ የተሻለ በሚባለው መልከዓ-ምድር ላይ ነው፤ ባለቤቶቹ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ጥቂት ባለሀብቶች መሆናቸውንም ሆነ፣ የደቡብ አፍሪካውን የጭቆና ስርዓት የሚያስታውሰው መጠሪያ ስሙ ከመንደሩ አጎራባች ያሉ የኤስ.ኦ.ኤስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዳወጡለት ወዳጃችን ዮናስ ጨምሮ ማስነበቡ አይዘነጋም፡፡ …እነሆም መቀሌ እንዲህ ነች፤ በጉራማይሌ ገፅታ የተገነባች፤ ህወሓታውያኑን በምቾት የምትንከባከብ፤ ሰፊውን ሕዝቧን ደግሞ ምድራዊ ፍዳ የምታስቆጥር፡፡

በነገራችን ላይ ከተማዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ መግዘፏን አስተውያለሁ፤ ይህ ግን የፈረደበት ድፍን ትግራዋይን በተለየ መልኩ ተጠቃሚ ሆኗል እንደማለት አይደለም፤ ዳሩ የዚህ አይነቱን የሕንፃ ጋጋታ ከክልሉ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የአድሎአዊነት ማሳያ አድርገው ሊወስዱት እንደሚችሉ አስባለሁ፡፡ ጥያቄው ግን ይህ አይደለም፤ ይ

ልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤተ-መንግስትን የሚያስንቁ መኖሪያ ቤቶቿ ለተርታው ነዋሪ ምን ፈየዱለት? የሚል እንጂ፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለም ይህ ኩነት በዋናነት የሚያመላክተው መቀሌ፣ በህወሓት መካከለኛና ከፍተኛ ካድሬዎች፤ እንዲሁም እነርሱን በተጠጉ ባለሀብቶች ወደ ሀጢአን ቅጥርነት እየተቀየረች መሆኗን ነው፤ ይህን ለማለት ያስደፈረኝ አንድም ብዙዎቹ ግንባታዎች ግለሰባዊ እንጂ መንግስታዊ አለመሆናቸው ሲሆን፤ ሁለትም ሕንፃዎቹ መኖሪያ ቤቶች እና ሆቴሎች በመሆናቸው ነው (እያወራን ያለነው ስለኢንዱስትሪዎች አይደለም)፡፡ እናሳ! ይህ አይነት ግንባታ ለንብረቱ ባለቤቶች ካልሆነ በቀር ለትግራይ ሕዝብ ምኑ ነው? …ርግጥ ነው እነዛ ለ17 ዓመታት ያህል የሰው ልጅ ይቋቋመዋል ተብሎ የማይታሰብ መከራ እየተቀበሉ ተራሮቹን ያንቀጠቀጡ ታጋዮች፤ ከድሉ በኋላ እሳት የላሱ፣ የመርካቶ ነጋዴን በብልጠት የሚያስከነዱ ሆነዋል፡፡

እዚህ ጋ ሳይነሳ የማይታለፈው ሌላው ነጥብ የከተማዋ ነዋሪ በፍፁማዊ ጨዋነት እንግዳ ተቀባይ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ያልኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ ሳይሆን፣ በየሬስቶራንቶች እና መንገዶች ላይ ካጋጠሙኝ በመነሳት በደምሳሳው የታዘብኩትን ተንተርሼ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ፡፡ ጓል መቀሌዎችንም፣ ‹‹የቐንየልና፣ ክብረት ይሃበልና!›› እላለሁ (ይህ ምስጋና ግን የደህንነት ሰራተኞችንም ሆነ፤ ችግር እንዳይፈጠርብን ሊጠብቀን እንደመጣ የገለፀውን የከተማዋ ፖሊስ አዛዥን አይመለከትም፡፡)

የሹክሹክታ ወሬ…መቀሌ በከፍተኛና መካከለኛ ካድሬዎች የቅንጦት መኖሪያ ቤቶ

ች ከመጥለቅለቋ በተጨማሪ፣ ገዥው-ፓርቲን በተራ ወቀሳም ቢሆን ስሙን ማንሳት ላልተጠበቀ የከፋ አደጋ የሚዳረግባት የአፈና መንደር መሆኗን ለመታዘብ ብዙ ድካም የሚጠይቅ አይደለም፤ በጥቂት ቀናት ቆይታዬም የታዘብኩት እውነታ አረናንና አንድነት ፓርቲን ተቀላቅለው ከሚታገሉ የከተማዋ ወጣቶች በስተቀር፣ በነዋሪው ላይ አስፈሪ ፍርሃት ማርበቡን የሚያስረግጥ ነው፡፡ በተለይም አድራሻና ማንነታቸው የማይታወቅ ‹‹ነጭ ለባሽ›› የሚል ተቀፅላ መጠሪያ ያላቸው ታጣቂዎች ‹በተቃዋሚነት የጠረጠሩትን በሙሉ አፍነው በመውሰድ ያሻቸውን ያደርጉታል› የሚል ወሬ በሹክሹክታ መዛመቱ፣ የፍርሃቱ አንድ መነሾ ሳይሆን አይቀርም ብዬ አስባለሁ፡፡ ወሬው በሕዝብ ዘንድ ይህን ያህል ስር የሰደደ ፍርሃት ማሳደር የቻለበት ምክንያት፣ ከበረሃው ዘመን ጀምሮ ‹‹ደርግን ይደግፋሉ›› ወይም ‹‹ይሰልላሉ›› ተብለው የተጠረጠሩ ነዋሪዎችን ድርጅቱ ለእንዲህ አይነት ተልዕኮ ባሰለጠናቸው አባላቱ ከመኖሪያ መንደራቸው በውድቅት ሌሊት እያፈነ ከወሰዳቸው በኋላ የደረሱበት አለመታወቁ ነው፤ ይህ ትውልድ ለፍርሃት እጅ መስጠቱም ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ ይነገራል፡፡ ካድሬዎቹም እንዲህ አይነት የበረሃ ወሬዎችን ሆነ ብለው እያጋነኑና እየቀባቡ በሕዝቡ መሀል ማናፈሱን ዛሬም ስለመቀጠላቸው ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች አረጋግጠውልኛል፡፡ በአጠቃላይ በትግራይ፣ በቀድሞው የህወሓት መስራች አቶ አስገደ ገ/ስላሴ አገላለጽ ‹‹ሕዝቡ ሁሉ እስረኛ ነው››፡፡

ከአፈናዊ ማስፈራሪያዎችና ማሸማቀቂያዎች በተጨማሪ በከተማዋ ሥራ-አጥነት አለቅጥ (ትግራይ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

[ከትግራይ መልስ...]

የትግራይን መስቀል ስለመሸከም

ረመዳን ታላቁ ወር የተሰኘበት የቁርኣን ራዕይ የወረደበት በመሆኑ ብቻ አይደለም፡፡የአላህ ራህመትና ፀጋ የሚወርድበት፣ተትእግስትን የምንማርበት፣ሪዝቅ የሚጨምርበት፣ አንዱ ለሌላው ጥሩ የሚያ

ስብበት የሚተዛዘንበት፣ሙዕሚኖች ከምንግዜውም በላይ ፍቅራቸውና አንድነታቸውየሚጠናከርበት፣ፈላህ የሚወጡበት ወር ነው፡፡ሙዕሚኖች አላህን(ሱ.ወ) በከፍተኛ ደረጃ የሚያልቁበት፣የሚያመሰግኑበት፣ቁርኣን በብዛት የሚቀራበት፣ግዴታ ያልሆኑ ብዙ ኸይር ስራዎች የሚሰሩበት፣ምፅዋት የሚለገስበት ወር ነው፡፡ረመዳን ማንም በዓለም ውስጥ ያለ ሙስሊም በኢማኑና በአላህ ፍራቻው መጠን ድርሻውን የሚያገኝበትና ልቡም በሰላምና በእርጋታ የሚሞላበት የሁሉም ዓይነት ኢባዳዎች አለማቀፋዊ ፀደይ ወቅት ነው፡፡ ይህን ዓለም አቀፋዊ የኢባዳና የፀደይ ወቅት ለማየት አላህ እድሉን ሰጥቶህ ወደ ተከበረውና የተቀደሰው የአላህ ቤት(ሀረም) መሄድ ብትችል የዚህን ቅዱስ ወር የተከበሩ ቀናትንና ሌሊቶችን በራስህ ዓይን ማየት ትችል ነበር...ቀን ቀን አላህን የሚያስታውሱና ስሙን የሚቀድሱ ቁርኣንን የሚያነቡና በአላህ ትዕዛዝ እና መመሪያዎች ላይ የሚመክሩ ቡድኖች የሚስተዋሉበትና ካዕባን ለመዞር (ጠዋፍ ለማድረግ) ጉጉት ያላቸው ምእምናን ደግሞ በካዕባ ዙሪያ ተጨናንቀው የሚስተዋሉበት ቦታ ነው፡፡ሌሊት ሌሊት ደግሞ መንፈስን የሚያነቃቁና የኢማን ቀለብ የሆኑ ተሀጁድ ሰላቶችን በየቦታው ሲሰግዱ ማየት ምንኛ ያስደስታል፡፡በአብዛኛው ወንጀለኛ የነበሩ ሰዎች ልብ ውስጥ የኢባዳ ፍቅር ይቀሰቀሳል፡፡በመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት በተለይ አላህን ለማኝ ሙዕሚኖች ቁጥር በብዙ እጥፍ ይጨምራል፡፡እስኪ ተመልከት በካዕባ ዙሪያ ለጠዋፍ ሲባል ከሚቀረው ትንሽ ቦታ በስተቀር ግቢው (ሀረሙ) በሙሉ በሰጋጆች ይጨናነቃል፡፡ፀጥ ባለውና ሰላም በሰፈነበት የእኩለ ሌሊት ወቅት ከፊት ለፊትህ በጥቁር ሃርማ ቀለም የተሸፈነውን ግዙፉን የአላህ ቤት ግንብ፣የተከፈተው ሰማይና ድንበር የለሹ የጠፈር ስፋት፣የዓለማት ጌታ የሆነውን አላህን በመጀመሪው ሰማይ ለርሱ በሚገባው መልኩ መኖርን ማሰብ፣ይህ ሁሉ ተዳምሮ ልብህ በሀሴት እንድትሞላ ያደርግሃል፡፡

በዚህ ህይወት የሚዘራ የደስታና የብርሃን አየር መካከል የሃረም ኢማም ቁርኣንን ሲቀሩ የሰማ ሰው ቁርኣን በዚያን ወቅት የወረደ ይመስል በጅጉ ይመስጠዋል፣ውስጣዊ ስሜቱ ይነካል የኢማሙ ድምጽ ሲስተጋባ ልክ ድምጽ ጠፈርንና ሰማያትን አቆራርጦ ያላንዳች እገዳ ወደ አላህ ዙፋን ለመድረስ የሚከንፍ ያክል ይሰማዋል፡፡

ደስታውን መቆጣጠር ይሳነዋል፣ምሉዕነት በቁርኣን ይሰማዋል፡፡እዚህ ደግሞ የአላህ አንቀፆች በተነበቡ ቁጥር አንዳች ስሜት ሰውነቱን ውርር ያደርገዋል፣ስለወንጀሉ ስቅስቅ ብሎ ያነባል ስላሳለፋቸው ከንቱ ጊዜያት ያስባል..ዋ ጥፋቴ ይላል..ያረብ እያለ ወደ ጌታው ይማፀናል፣ተስፋ ሳይቆርጥ የራህመቱን በር ይቆረቁራል...፡፡

ከዚያም በዚህ በተቀደሰ ስሜት ሁሉም ሰው ለራሱ፣ለትውለዱ፣ለዓለም ሙስሊሞች በሙሉ፣ለኢስላም ሲሉ በመታገል ላይ ላሉ፣ለሙስሊም መንግስታት መሪዎች፣ለወጣቱ፣ለኢስላም መከበር፣በህይወት ላሉና ለሞቱ ሙስሊሞች በሙሉ ምህረትን ለመጠየቅ ዱዓዎችን ያደርጋሉ፡፡

እነዚህ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውና ለወደፊቱ መልካም ምንዳ ተስፋ ሰጪ የሆኑ ጊዜያት ቢራዘሙ የሁሉም ሰው ልብ ይመኛል፡፡ማን ያውቃል እነዚህ መልካም ስራዎቸ ቢሰሩባቸው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ምንዳ የሚያስገኙባቸው ጊዜያት እድለኛ ለሆነ ሰው ተመልሰው ሊመጡለት ይችሉ ይሆናል፡፡እጅግ አዛኝና ሩህሩህ የሆነው አላህ ረጂ የሌለውን ወደሱ ብቻ ከጃይ የሆነውን ባሪያውን በፍቅርና በውዴታ እንደሚያየው የሁሉም ሰው ልብ በውስጡ በርግጠኝነት ያምናል፡፡በፈጣሪና በፍጡራኑ መካከል የሚጋርድ ምንም ነገር የለም፡፡ፈጣሪ እሱን የሚለምኑ እጆችን ባዶ አይመልሳቸውም ይህ የኢባዳ ጉጉት፣ደስታ እነዚህ የኢማንና የቂን (እርግጠኝነት)

ደረጃዎች በዚህ የረመዳን ወቅት ብቻ የሚገኙ ናቸው::ፆም በትርጉም ደረጃ መታቀብ፣መከልከል፣መተው...ማለት

ሲሆን ከሸሪኣ አንጻር ሲተረጎም ደግሞ፡-ዒባዳነቱን በማሰብ ከፈጅር መውጣት ጀምሮ ጸሀይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ባለው ሰዐት ውሰጥ ከምግብ፣ከመጠጥ፣ከወሲባዊ ተራክቦና ከሌሎ

ችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች ተከልክሎ መቆየት ማለት ነው፡፡ ረመዷን በአመት አንዴ የሚመጣ ለተወሰኑ ቀናትም አብሮን የሚቆይ ታላቅ እንግዳ ነው፡፡ታዲያ ሲመጣ ታላላቅ ችሮታዎችን አቅፎና በርካታ ሽልማቶችን ጭኖ ነውና ጎበዝ ይሄኔ ነው መባነን!! በመሆኑም ለዚህ እንግዳ ነው የዋጋውን ያህል ግምት ልንሰጠውና በጥሩና መልካም መስተንግዶም ልናስተናግደው ይገባል የሚባለው..ከመጥፎ ስነ-ምግባር ርቀን ከውጭም ሆነ ከውስጥ ንጽህናችንን ጠብቀን ጸድተን፡፡ ኒያ የነገሮች ሁሉ ማሰሪያና መንደርደሪያ ነውና ጾማችንን ከመጀመራችን በፊት ጥሩ ኒያ (ቁርጠኛ ሃሳብ)ሊኖረን ይገባል፡፡የአንድ ወር

ብቻ ማለትም የረመዷን ባሮች ብቻ ላለመሆን፣በረመዷን ሆነ ከረመዷን ዉጪ በአላህ መንገድ በፅናት ለመቀጠል፣ከረመዷን ትሩፋቶች ተካፋይ እንድንሆን ጾማችንም ተቀባይነት እንዲኖረው ከቂም በቀል፣ከተንኮል፣ከምቀኝነት፣ከጥላቻና ከመሳሰሉተት እኩይ ምግባሮች ልንፀዳ፣ ልንነይት ግድ ይላል፡፡አፍው መባባልን እናስቀድም፣ላጠፋብን ይቅር እንበል፣ለበደልናቸው ይቅርታን እንጠይቅ፣ ሃቅም ካለብን እንክፈል ሰድበንም ቢሆን ክብሩን ዝቅ ያደረግነው ካለ ዛሬውኑ አፉታ እንጠይቅ፣ ንፁህና አዲስ ሆነን ሰላማዊ በሆነ ልቦና በጠራ ህሊና ረመዷንን እንጹም፡፡ የተጣሉት መታረቅ አለባቸው፤ቂም የያዙም ከሆዳቸው አውጥተው ሊጥሉ ያስፈልጋል፤ግድም ይላቸዋል፡

ረመዷን ቁጥር ስፍር የሌለው አጅር የሚገኝበት ስራዎች በእጥፍ ድርብ ተባዝተው የሚከፈሉበት ወር ነው፡፡ትንሽ ስራ ትልቅ ትርፍን፣ጥቂት ጥረት ብዙ ምንዳን ታስገኛለች፡፡በውስጡ የሚሰሩ ሱናዎች እንደ ግዴታ(ፈርድ) ምንዳ(አጅር) አላቸው፡፡የግዴታዎቹማ...እጥፍ ድርብ ነው ምንዳቸው! ይህ እንግዲህ ከአላህ (ሱ.ወ) የሆነ ችሮታ(ስጦታ) ነውና ትልቅ እድለኝነትና ደስታ ሊሰማን ይገባል፡፡ሙሰሊም አድርጎ ሲያበቃ ረመዳንን ለሰጠን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡አልሃምዱሊላህ!! ስለ ረመዷን ስናስብ በርካታ ነገሮች ከፊታችን ድቅን ይላሉ፣ትዝታዎች ይጫራሉ...

እርግጥ ነው ረመዷን በመካከላችን ያላታሰበ ፍቅር፣መተዛዘን፣መተሳሰብ፣መቀራረብ በሙሰሊሞች መካከል ከምንጊዜውም በላይ ይሰፍንበታል፤አንድነታቸው ይጠናከርበታል፤ድሆች ይታወሱበታል፤ደካሞች፣ ሚስኪኖች የት ናቸው ተብሎ ይጠየቁበታል፡፡

ረመዷን ከማንም በላይ ለሙሳፊሮች፣ለችግረኞችና አስታዋሽ ላጡ ሁሉ የጠበቀ ወዳጅ ነው፡፡የረመዷን ሽታው ድባቡ በረከቱ ለሁሉም ፍጥረታት ይተርፋል፤የራህመት ወር ነውና ሰውም ሆነ እንስሳ ግዑዝ ነገሮች ሁሉ ይናፍቁታል፡፡ረመዷን ዱኣ ተደርጎ ምላሽ የማነፈግበት ወር ነው፡፡ቀደምት ሙሰሊሞች (ሰለፎች)ታላላቅ ድሎችን አግኝተውበታል፡፡በዚህ ወር ነው እውነትና ውሸት የተለየበት ታላቁ የበድር ድል የተገኘው፤በቁረይሾች ከመካ የተባረሩት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እና ባለደረቦቻቸው ከስደት አገግመው ድልን ጨብጠው መካንም የከፈቱት፡፡ሰሃቦች ይህ ወር ሲመጣላቸው በታላቅ ሃሴትና ደስታ ተሞልተው ይቀበሉታል፤ሲለያቸውም የሚሸኙት እጅግ የሚወዱት ወዳጅ የተለያቸው ያህል እንባቸውን አፍስሰውና ሀሃዘናቸውም እጅግ ብርቱ ሆኖ ነው፡፡

ረመዷንን ከሌሎች ወራቶች ለየት ያደረገው... ረመዳን ታላቅ የእዝነት ወር ነው አላህ ከሌላው ወርና ጊዜ

በበለጠ ሁኔታ እዝነት ችሮታውን ለባሮቹ ይገልፅላቸዋል፡፡በውስጡ ተሸቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ ዘንድ የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ፣ሸይጣኖች ይታሰራሉ በሸይጣን መታሰርም የአላህ ባሮች ተጠቃሚ በመሆን ነፍስያቸውን (ረመዷን... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

[የረመዷን ወር]-አንዳንድ ነጥቦች ስለታላቁ ረመዷን ጾም

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያEmbassy Suites Bloomington is looking for a

full-time Housekeeping Room Attendant.

ብሎሚንግተን የሚገኘው ኢምባሲ ስዊት ሆቴላችን ሃውስኪፒንጎችን መቅጠር ስለሚፈልግ ለሥራው ፍላጎትና ፍቅር

ያላችሁ ሆቴላችን ድረስ በመምጣት ማመልከት ትችላላችሁ።

Address: 2800 American Blvd W, Bloomington, MN 55431

Phone:(952) 884-4811

Page 4: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 4

የራስ ሬስቶራንት ሳምንታዊ

የዲጄ ፕሮግራሞችዘወትር ሰኞ፦

የሻማ ምሽት ዲጄ ዋይ ዋይማክሰኞ፡ -

ላይኛው ባር ዲጄ ራሽ ማክሰኞ፦

ታችኛው ባር ዲጄ ጆኒ ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋርረቡዕ፡ -

ዲጄ ሳሚ በሃገርኛ ሙዚቃሐሙስ፡-

ላይኛው ባር “God Bodies Night” ከ150 በላይ ሰዎች የሚገኙበት ምርጥ ምሽት

ሐሙስ፡- በታችኛው ባር ዲጄ ጆኒ ከምርጥ

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋርሁሌ አርብ፦

በላይኛው ራስ ባር ምርጥ የዲጄ ምሽት ከ12 አቀንቃኞች ጋርሁሌ አርብ በታችኛው ራስ ባር ዲጄ ቢኬ

ሁሌ ቅዳሜ፦ በላይኛውም በታችኛውም የራስ መዝናኛ የኢትዮጵያ ምሽት

ሁሌ እሁድ፦ 18+ ሐበሻ ምሽት በላይኛው ባር ዲጄ ኢዋምና ባቢ

ሁሌ እሁድ በታችኛው ባር፦ሬጌ ምሽት

Page 5: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 5

Page 6: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 6

የወሩ ታላቅ ዜና

ቴዲ አፍሮየሕዝብ ፍቅርና ውዝግብ ያልተለየው ዝናተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ወደ ሙዚቃው ዓለም ተቀላቅሎ ወደ ዝና ማማ መውጣት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ መነጋገሪያ ከመሆን ያመለጠ አርቲስት አይደለም፡፡ በ1993

ዓ.ም ማብቂያ ላይ ባወጣው የመጀመሪያ ‹አቦጊዳ› አልበሙ የሙዚቃ አድማጩን ጆሮ ለመቆጣጠር የቻለው ቴዲ አፍሮ በወቅቱ በአለቤ ሾው ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ቀርቦ ‹25 ዓመቴ ቢሆንም ፍቅረኛ ገና አልያዝኩም › ባለ ማግስት የከተማው ወጣት ሴቶች አይን ማረፊያ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚሁ ይፋ ካልወጣ የሴቶች አደን ጋር ተያይዞ የመጀመሪያውን ውዝግብ አስተናገደ፡፡ ‹በሴት ልጅ ጡት ላይ ፊርማ ፈርሟል› በሚል ተሰራጨው ወሬ ከከተማ ወሬነት አልፎ የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ገበያ መጥሪያና ማሻሻጪያ ሆኖ ነበር፡፡‹የተባለውን ነገር አላደረኩም፤ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ኩሩዎች ናቸው፡፡ ይህንን ነገር እንዳደርግ አይጠይቁኝም ፤ እኔም አላደረኩትም› ብሎ በወቅቱ ለታተመችው ቅፅ 1 ቁጥር 1 ቁም ነገር መፅሔት ላይ ቢናገርም አድናቂዎቹን ከማሳመን በቀር የወሬ ማጣፈጫነቱን አላስቀረውም ነበር፡፡

ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ውዝግቡን በዚሁ መልኩ ለመቋመጨት ጥረት ቢያደርግም ከዚሁ አልበሙ በፊት በሰራው የመጀመሪያ ካሴቱ ሳቢያ ለሌላ ውዝግብ የተዳረገው ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱን ሳያወጣ ለዓመታት አስቀምጦት የነበረው ቮይስ ሙዚቃ ቤት የአቦጊዳ አልበሙ የአድማጭን ጆሮ መቆጣጠር ተመልክቶ አዲሱን አልበም ለገበያ ያቀረበው ወዲያውኑ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ‹የአቦጊዳን አልበም ሽያጭ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለበሁበት ደረጃ ፈፅሞ የማይመጥን› ያለውን ከዓመታት በፊት የተሰራውን ካሴት ‹ሳያስፈቅደኝ መልቀቅ የለበትም› በሚል ሌላ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡ ተፈጠረው ውዝግብ መሀል ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ገብቶ በሽምግልና ጉዳዩን እንዲፈታ እስኪያደርግ ድረስ በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ነበር፡፡

በዓለም ዋንጫ ላይ የታዘበኳቸው

የአፍሪካ ቡድኖች- በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

ቴዲ በሙዚቃ ስራው ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ህይወቱና በሚያደርጋቸው ቃለ ምልልሶቹ ዝናውን ከፍ እያለ ቢመጣም ምርጫ 97 ተከትሎ ገበያ ላይ በዋለሁ ሶስተኛ ‹ጃ ያስተሰርያል› አልበሙ ሳቢያ ውዝግቡ ከግለሰብ ወደ መንግ

ስት ዞሮ ነበር፡፡ ይፋዊ በሆነ መንገድ መንግስት ተቃውሞውን ባይገልፅም ዘፈኑ በማንኛውም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እንዳይተላለፍ ከመከልከል ጀምሮ ለጉዳዩ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ በመስጠት የውዝግቡን ጡዘት እንዳከረረው እናስታውሳለን፡፡ ከምርጫው ጋር የተያያዘው ውጥረት ቀስ እያለ ቢረግብም ከመንግስት ጋር ያለው ውዝግበ ከአንድ ዘፈን ወደ ሶስት አድጎ ከ‹ካብ ዳህላክና› እና ‹ሼ መንደፈርን› ጨምሮ ታይቷል፡፡ መንግስት በወቅቱ ከነበረው ፖለቲካዊ ራስ ምታት ተረጋግቶ ሚሊኒየሙን ለመቀበል ሽር ጉድ በሚልበት ወቅት ቴዲ አሁንም የህዝቡን የልብ ትርታ ያዳመጠ ‹አበባ አየሽ ሆይ› የተሰኘውን ተወዳጅ ባህላዊ ዜማ ለእርቅ አውሎት ብቅ አለ፡፡ ከፓለቲካ እስረኞች መፈታት ጋር ተያይዞ የእርቅ መንፈሱ በሁሉም ሙዚቃ አድማጭ ጆሮ ማንቃጨል ቢጀምርም መንግስት ግን ዘፈኑን ዘወትር በየሚዲያው ላይ ሲለቀቅ ሁኔታውን በዝምታ ከመመልከት ውጪ ‹ሆ በል ከበሮ ሆ በል አንተ ማሲንቆ ስታይ ሰው ታርቆ› በሚለው ስንኝ ከህዝቡ ጋር እስክስታ ለመውረድ ሳይችል ቀርቷል፡፡የቴዲ አፍሮ የእርቅ መንፈስ ሚሊኒየሙን ብቻ ሳይሆን ባህር ማዶ ተሻግሮ ለመዝፈንና ለማስጨፈር ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ከሚሊኒየሙ ጋር ታኮ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ቢዮንሴ ኖውልስ በቴዲ አፍሮ ‹አበባ አየሽ ሆይ› ዜማ ወገቧን ይዛ ስትጨርፍር ታይታለች፡፡

ቴዲ በዘፈኑ የሀገሩን ልጆች አልፎ የውጪ ሰዎችን ማማለል ቢችልም ከመንግስት ጋር የገባው ውዝግብ ከዚህ ቀደም ከግለሰቦች ጋር እንዳለው አይነት ተራ የሚባል አልነበረምና ወደ እስር ቤት የሚገባበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በብዙዎቹ አድናቂዎቹ ዘንድ አሁንም ድረስ እንደሚታመነው ‹ቴዲ አፍሮ በመኪና ሰው ገጭቶ አምልጧ› የሚለውን የአቃቤ ህግ ክስ ለመቀበል ዳግም መወለድ የሚያስፈልጋቸው ይመስላል፡፡ ‹ደጉ ይበልጣል› የተባለውን የ18 ዓመት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ስለመግደሉና ስለማምለጡ በወቅቱ መነጋገሪያ የነበረው ክስ ከብዙ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ምልልስ በኋለ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ሲቋጭ ‹ቴዲ እንደ በፊቱ ተወዳጅ ሥራዎቹን ይሰጠን ይሆን ›የሚል ጥርጣሬ መኖሩ አልቀረም፡፡ የፈጠራ ስራ ችግር የሌለበት ቴዲ ከእስር ቤት በወጣ በሶስተኛው ወር ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን በልመና ሥራ ላይ

ለተሰማሩ ወገኖች ማቋቋሚያ አደረገ፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይም ያገኘውን ከአንድ ሚሊየንም ብር በላይ ገንዘብም ለኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር አስረከበ፡፡

ከሚያወጣቸው አልበሞች ጋር ተያይዞ ውዝግብ የማያጣው ቴዲ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋርም ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዘፈኖች መመሳሰል ጋር በተያያዘ በሰይፉ ፕሮግራም ላይ በቀረበ ዘገባ ሳቢያ ጉዳዩ በስምምነት እስኪፈታ ድረስ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ ቴዲ የሌሎቹን ያህል አይሁን እንጂ ከረዥም ጊዜ ማናጀሩ አዲስ ገሠሠ ጋርም ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የተለያዩ ሲሆን በተደጋጋሚ ተሰርቀው በወጡ ነጠላ ዜማዎቹ ሳቢያም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የቴዲ አራተኛ ካሴትም ውዝግብ መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ‹ጥቁር ሰው› በሚል ርዕስ ያወጣው አልበም ከፍተኛ የሙዚቃ ችሎታውን ያሳየበትና አዳዲስ የአዘፋፈን ስልቶችን ያካተተበት ሥራው ቢሆንም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፓለቲካዎ አቋም ጋር ተያይዞ ተቃውሞ የገጠመው ወዲያውኑ ነበር፡፡ ጉዳዩ ከታሪክ አንፃር መታየት ያለበትና የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር በሚል የተሰራ ሙዚቃ እንደሆነ የተለያዩ ሰዎች የየራሳቸውን አስተያየት በማከል በየመገናኛ ብዙሃኑ ላይ ለመከራከር መሞክሩም ፓለቲካዊ መልክ የተሰጠውን ውዝግብ ለማብረድ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ከዚህ ውዝግብ ቀጣይ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ‹ወደ ፍቅር ጉዞ› የሚል ስያሜ የተሰጠው የሙዚቃ ኮንሰርትም በበደሌ ቢራ ስፖንሰር አድራጊነት ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ክልሎች በመጓዝ ለማሳየት ፕሮግራም ቢዘረጋም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ተያይዞ ‹ሰጠ› በተባለ ቃለ ምልልስ ሳቢያ በደሌ ቢራ ኮንሰርቱን ሰርዞታል፡፡ በደሌ ኮንሰርቱን ለመሰረዝ ምክንያት የሆነው ቴዲ ሰጠ በተባለው ቃለ ምልልስ ሳቢያ የተቆጡ ወገኖች ‹በደሌ ቢራን እንዳይጠጡ!› የሚል የቅስቀሳ ዘመቻ በመጀመራቸው እንደሆነና ከንግድ ስራ አንፃር ኮንሰርቱን መሰረዝ አዋጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ቴዲ የተባለውን ቃለ ምልልስ እንዳልሰጠ፤ ይልቁንም በመፅሔቱ የተፈጠረ ተራ ስህተት እንደሆነ ገልጾ ለመከራከር ቢሞክርም ሰሚ ያገኘ አይመስልም፡፡ ጉዳዩ ስር እየሰደደ የመምጣቱ አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወደሰደውም የዘመቻው ቀስቃሾች የቴዲን ኮንሰርት በማሰረዝ ብቻ ሳይገቱ ሌላም የመልስ ምት መሰጠት እንዳለበት የሚያሳስቡ ቅስቀሳዎች ተጠናክረው በመሰጠታቸው የጥቁር ሰው ተነፃፃሪ ተቃራኒ ነጠላ ዘፈን በአንድ አርቲስት ተሰርቶ ተለቋል፡፡

ይህ የውዝግብ አዙሪት ባልተቋጨበት ሁኔታ ኮካ ኮላ ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ በየሀገሩ ከሚያሰራቸው አርቲስቶች መሀከል (ቴዲ አፍሮ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

በዚህ አለም ዋንጫ ላይ የአፍሪካን ቡድኖች ስመለከት ምንም እድገትና ተስፋ አላየሁባቸውም፡፡ በአውሮፓ ስመ ጥር ተጨዋቾች ይዘው በእንቅስቃሴ ለመብልጥና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሸነፍ የሚያስችል ነገር አይታይባቸውም፡፡ጋና ከአሜሪካ ጋር ሲጫወት ተጀምሮ እስኪያልቅ ጋና ክሮስ ሲያደርጉ ነበር፡፡ በቀኝ በኩል ሮጠው ይመጡና ያሻማሉ፡፡እንደገናም ያሻማሉ …አሁም ያሻማሉ፡፡ገና ወደዚያ ሲመጡ እንደሚያሻሙ ያስታውቃል፡፡ ሻሞ መሆኑን የአሜሪካ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳ ያለውም ተመልካችን በቴሌቪዥን መስኮት ስር ያለው ሁሉ ያውቃሉ ፡፡ የአሜሪካ ተጨዋቾች ረጃጅም ናቸው፡፡ ዝላይም ከጋና ይሻላሉ ፡፡ኳሱን አሜሪካኖች እንደሚያገኙ እየታወቀ ክሮስ ሲያደርጉ ለምን ይሄን እንደማይቀይሩ ግልጽ አልነበረም፡፡ያንን ሁሉ ክሮስ አሜሪካኖች በቴስታ መመለሳቸው ብቻ ሳይሆን ጋና እየተጠቃ የነበረው ራሳቸው ክሮስ አድርገው ከሚመለሰው ኳስ መሆኑ ሲታይ ዋጋ ቢስ ክሮስ ነበር፡፡የሚገርመው በቀኝ ያን ሁሉ ክሮስ አድርገው ባከነና አንድ ኳስ በግራ ሄደው ልጁ ስላልተመቸው ለአዩ በተረከዝ አቀበለው፡፡አዩ አገባው፡፡አሜሪካኖቹ እንዲህ አይነቱ አመጣጥ ይቸግራቸዋል፡፡ልጁ ለአዩ በተረከዝ ያቀበለው ስላልተመቸው ነው እንጅ ክሮስ ነበር የሚያደርገው፡፡መቀባበሉ የሚያዋጣ ቢሆንም ጋና የተቃኘው በክሮስ ነው፡፡እርግጥኛ ነኝ አሰልጣኙ በተረከዝ በመስጠቱ‹‹እንዲህ አይነት የቄንጥ አጨዋወት አልፈልግም ››እንደሚሉት ነው፡፡መቀባበሉ ከእዚያ በኋላ ሳይደገም በክሮስ ዘለቀ፤ አለቀ፤ ተጠናቀቀ፡፡ ካሜሩን ክሮስ፤ ናይጀሪያ ክሮስ…..የአፍሪካ ቡድኖች ክሮስ ኤክስፖርት የሚደርጉ ይመስል ስራቸው ይሄ ሆነ፡፡ ናይጀሪያ ከደካማ ኢራን ጋር አየነው፡፡ አንድ ተጨዋች ማለፍ እንኳን ቸግሯቸው ኳሱ ሲበላሽ የኛ ቡድን ቀሽም መሆኑ እንጂ ናይጀሪያ በዚህ አቋሙ ማለፍ አልበነበረበትም፡ናይጀሪያ ነጣቂ ቡድን ነው ፡፡ጉልበተኛና በመደምሰስ አጨዋወት ላይ ያተኮረ ሆኖ እነርሱ ጠንካራ በሆኑበት በጉልበት ጨዋታ ገባንና ተበልጠን ተሸነፍን፡፡ የተሸነፍነው ለመሸነፍ ስለገባን ነው፡፡እኛ ጥሩ በሆንበት ነገር ናይጀሪያን ብነገጥም እንጥለው ነበር፡፡አሁን ያየሁት ናይጀሪያ ደካማ ነው፡፡ ጨዋታወም አይስብም፡፡

…..በ1998 አለም ዋንጫ የነበረው ናይጀሪያ ከመቼውም የተሻለ ነው፡፡ ከፊት የሚመሩት እነካኑ፤ፊኒዲ፤ኦኮቻና ነበሩ፡፡ ካኑና ፊኒዲ መሮጥ አይችሉም፡፡ በረጅሙ ሲጣልላቸው አይታጉሉም ይተውታል፡፡ወደፊት ተቀባብለው ሲሄዱ ጎል እንደሚያገቡ፤ሊያገቡ እንደሚችሉና ተጋጣሚን ስጋት ውስጥ አንደሚከቱት ያስታውቃል፡፡እነርሱ መቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን እዚያ ቡድን ውስጥ ኳስ የማይችሉትን እንደግድግዳ ተጠቅመው እያስገቡ ይጫወቱ ነበር ፡፡ይሄ ቡድን ከሁለት አመት በፊት በአትላንታ ኦሎምፒክ በብራዚል 3ለ0 ተመርቶ 4ለ3 ሲያሸንፍ በክሮስ ሳይሆን እነካኑ የኳስ ሂደቱን ስላሳመሩት ነው፡፡ ቡድኑ ወደ ፊት ሲሄድ እንደሚያገባና እንደሚያስጨንቀ ያስታውቃል፡፡ያሁኑ ቡድን ኳስ ይዞ ለማጥቃት ሲሄድ ያ ኳስ እነርሱ ላይ ተመልሶ ጫና እንደሚፈጥር ያስታውቃል፡፡

……ካሜሩን ነገሮችን ሁሉ በጉልበት ለመጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ በጉልበት ቢበልጡም፤ ደምስሰው ኳስ ቢቀሙም ያገኙትን ኳስ በትክክል ማቀበል አቅቷቸው ለባለጋራ እየሰጡ መጨረስ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ያለው ነገር እንኳን አልታየባቸውም፡፡ያገኙትን ኳስ በማባከን ጨረሱ፡፡ ክሮሽያ 4ለ0 ሲያሸንፋቸው ጨዋታው ይደገም ቢባል እንኳን ካሜሩን በልጦ ላመሸነፍ እንኳን የሚችልበት ነገር አልነበረም፡፡ጉልበት ላይ መመስረታቸው ነገሮችን የሚቃኙበት እውቀት አልነበራቸውም፡፡ በክርን መትቶ በቀይ የወጣውም አፈጻጸሙን ሀይል ላይ ማድረጉ ቡድኑ የተመሰረተበትን ነገር ለማሳየት ይመስላል፡፡ ካሜሩን እንዲህ እንዲጫወት ጋና ክሮስ እንዲያደርግ ናይጀሪያ የግርግር ጨዋታን እንዲመርጥ መደረጉ አፍሪካ ውስጥ በእውቀት የሚጫወት ሰው ያለመኖሩ ሳይሆን አሰልጣኞች የመረጡላቸው አጨዋወት እንደሆነ ያሳያል፡፡ካሜሩን ፍጹም ከኳስ ውጭ ሆኖ ክሮስ ብቻ ሳይሆን ርግጫን ማዕከል ያደረገ ነበር፡፡1990አለም ዋንጫ የነበረው ካሜሩን መራገጥና ኳስ መጠለዝ ብቻ ነበር ፡፡ቡድኑ መልክ የሚይዘው ሮጀር ሚላ ሲገባ ነው፡፡ ሚላ እድሜው 38 ነበር፡፡ መሮጥ አይችልም (ከሌሎቹ ጋር ሲነጻጸር)ጉልበትአይጠቀምም፡፡፡ በተለይ ከእንግሊዝ ጋር ሲፋለጡ ተቀይሮ ገብቶ ጓደኞቹን እንደግድግዳ እየተጠቀመ ኳስ እየሰጠና እየተቀበለ እንግሊዝን ምጥ ውስጥ አስገብቶ ነበር፡፡ እሱ ሲገባ ክሮስ ቀረና ሚላ ላይ ተመሰረተ፡፡እሱ ሱገባ ካሜሩን ያስፈራለል ፡፡እሱ ቤንች ላይ ሆኖ ካሜሩን ይጠልዛል፡፡ ጉልበት ለመንጠቅ እንጅ ኳስ ለመቀባበልና ተቀባብሎ ባለጋራን ለማስጨነቅ አይጠቅም፡፡በካሜሩንና በእንግሊዝ ጨዋታ ላይ ሜዳውን ሚላና (የአፍሪካ... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

SUB-SAHARAN AFRICAN YOUTH and FAMILY SERVICES (SAYFSM)

Lakkoofsa bilbilaa፡ (651)644-3983, (651)644-1470, (612)554-5676የስልክ ቁጥር፤ (651)644-3983, (651)644-1470, (612)554-5676

SAYFSM Dhaaba Hawaasummaa namoota dhalootan Afrikaanota ta’aniifi tajaajila garaagaraa kan laatudha.-Daddarbaa Vayirasii HIV/AIDS to’achuudhaafi dhaabni kun (SAYFSM) barnoota fayyummaa barsiisa, Kondomii raabsa, akkasumas qorannaa dhiigaa tola hojjeata-Qorannaan dhiigaa kun namoota leenjii ga’aa fi ragaa ogummaa qa-baniin raawwatama-Namnni fedha qoratamuu qabu waajjira SAYFSM keessatti yookiin bakka abbaan dhiimmaa itti amanetti qoratamuu danda’a-Namni nubiratti (SAYFSM) qoratamu icitiin odeeffannoosaa sadarkaa cimaatti eegama.**************************************************************************** SAYFSM Dhaabbata MNsure wajjin walii galuudhan namoota In-shuuraansii fayyaa hinqabneefi gargaarsa iyyannoo barreessuu laataHanga ammaatti jiraattota Minnesota tiifi gargaarsa heddu kennee jiraOdeeffannoon abbaan dhimmaa himatu hundi icitiidhaan eegamaMNsure tti iyyannoo galfachuu yoo barbaaddan beellama otuu hin qa-batin yeroo gabaabaa keessatti dhimma keessan xumurattu

* SAYFSM በትዉልድ አፍሪካዊያን ለሆኑ ግለሰቦች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሰብአዊ ድርጅት ነዉ፤* የ HIV/AIDSን ስርጭት ለመግታት ድርጅቱ (SAYFSM) ኮንዶም ያድላል፣ የጤና ትምህርትና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ ነጻ የደም ምርመራ ያከናዉናል፤* የደም ምርመራዉ በቂ ስልጥና ባላቸዉና ችሎታቸዉ በተመሰከረላቸዉ ባለሙያዎች ይከናወናል፤* HIV ለመመርመር ፍላጎት ያለዉ ማንኛዉም ግለሰብ በድርጅቱ በጽህፈት ቤት ወይንም ባለጉዳዪ ባመነበት ቦታ ምርመራዉ ሊከናወን ይችላል* በ SAYFSM ምርመራ የሚደረግለት ግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃዉ በከፍተኛ ደረጃ ይጠበቃል። ***************************************************** SAYFSM ከMNsure ጋር በመተባበር የህክምና እንሹራንስ ለሌላቸዉ ግለሰቦች የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ሁኔታዉ በፈቀደ መሰረት እንሹራንስ እንዲያገኙ እርዳታ ያደርጋል* እስከ አሁን ድረስ ለብዙሃኑ የሚኒሶታ ነዋሪዎች በርካታ አገልግሎት ሰጥቷል* ባለጉዳይ የሚሰጠን መረጃ በሚስጥር ይጠበቃል* በ MNsure ድረግጽ (web site)የማመልከቻ ቅጽ ለመሙላት ከፈለጉ ያለቀጠሮ ጉዳይዎን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይፈጽማሉ

1885 University Ave. W #297 St. Paul, MN 55104 Phone: 651-644-3983

Page 7: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

ፖለቲካ ኢኮኖሚ አሜሪካ ማኅበረሰብ

ከግርማ ሰይፉ(የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል)

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሌጋሲ እናስቀጥላለን ያሉ ሰዎች …. የሰውዬውን ሌጋሲ እየሸረሸሩት እንደሆነ ያወቁ አይመስለኝም፡፡ አውቀውት የራሳቸውን ሌጋሲ ለማኖር ከሆነም እሰዬው የሚያሰኝ ነው፡፡ ሰሞኑ ለጅቡቲ መንግሰት ውሃ አቅርቦት በሚመለከት አንድ አዋጅ ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ ትንሽ ጫጫታ መነሳቱ የሚታወስ ነው፡፡ የዚህ ነገር ደግሞ አንጓ ያለው ደግሞ የመንግሰት ተጠሪ ሚኒሰትሯ ወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ ጥቅሙ ፖለቲካ ነው ያሉት ላይ ነው፡፡ ከምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያ ምን ጥቅም ታገኛለች? በሚል ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ ጥቅሙ ፖለቲካ ነው የሚል ነበር፡፡ ከዓለም የባህር በር/ወደብ ከሌላቸው ሀገሮች በህዝብ ብዛት አንደኛ የሆነችውን ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት የተደረገው ደባ እየዋለ እያደር ብዙ ዕዳ እንደሚያስከፍለን ምልክቱ እየታየ ነው፡፡

በእኔ እምነት ህወሃት/የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ከሻቢያ ጋር በመተባበር በዕቅድ ይዞት ነበር ለሚባለው የትግራይ-ትግረ መንግሰት ምስረታ አንፃር ሲታይ ቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል የባህር በር እንዳይኖረው ማድረግና በሚመሰርቱት የትግራይ-ትግረ መንግሰት ጥገኛ ማድረግ ተገቢ ሊመስል ይችላል፡፡ በ1980 መጀመሪያ ኢህአዴግ የሚባል ግንባር ሲመሰርቱ ግን የአማራው ክንፍ ኢህድን/ብአዴን በመጨረሻም ኦህዴድ እና ደኢህዴን የተቀላቀለው ግንባር ለዚህ እቅድ ገብሮ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ በመጀመሪያ በዚህ ደረጃ ማን ያወያያቸዋል ካልተባለ በስተቀር፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ቢሆን ከኢሳያስ ጋር ያጣላቸው የሚመስለኝ ብዙ ሰው እንደሚለው በኢትዮ-ኤርትራ ቅጥ ያጣ ግንኙነት የትግል ጓዶቻቸው ተበሳጭተው ባደረጉባቸው ግፊት ብቻ ሳይሆን የሚኒሊክ የሚሏት ኢትዮጵያ ቤተመንግሰት ውስጥ ቁጭ ብሎ ከአሰመራ ትዕዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ጭምር ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ በሁሉም መስፈርት ትልቅ ሀገር ነች፡፡ የሚያሳዝነው ግን ይህችን ትልቅ ሀገር ለመምራት እድል አግኝተው ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት እድል ያለመፍጠር፤ እድል ሲገኝም ለመጠቀም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ነው፡፡ አሰበውት የነበረ ነገር ካለም ይዘውት ሄደዋል፡፡

አሁን ባለው አለማዊ ሁኔታ እንዲሁም አሁን በምድር ላይ ባለው ተጨባጭ እውነት ትግራይ- ትግረ ቅዥት ነው፡፡ ሊሳካ የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ ለምን? እያልን ደጋግመን መጠየቁን እናቁምና በዚህ ሃሳብ መነሻ ግን ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ሀገር በ

ለጅቡቲ ውሃ በነፃ ለምን? - የባህር በር ሸቀጥ ነው ወይ?

ከኢሳያስ ከበደእመቤት ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሯ በመመለሷ ደ

ስተኛ ሆናለች፡፡ በ1993 ዓ.ም መስከረም ወር አካባቢ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ስትጓዝ መንገዱ አልጋ በአልጋ ሆኖላት አልነበረም፡፡ ከ10 ክፍል በላይ ልትቀጥለው ያልቻለችውን ትምህርት ትታ አዲስ አበባ ውስጥ መቀመጥ አልታያትም፡፡ የተወለደችውና ያደገችው ጅማ ቢሆንም ወደ አዲስ አበባ ከመጣች ግን ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ እናቷ ወታደር አባቷን ተከትለው ሸገር ሲገቡ እሷ በአያቷ እጅ ነው ያደገችው፡፡ አያቷ ከልጅነቷ ስላሳደጓት እናትና አባት ጅማን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ለመክተም ጓዛቸውን ሲጠቀለልጁ ‹‹እሷን ከእኔ ነጥላችሁ ከወሰዳችሁ እናት አለኝ ብለሽ እንዳትመጪ- እንደሞትኩ ቁጠሪኝ›› ብለው ስለተማረሩ ነው እመቤት እዚያው እንድትቀር የተወሰነው፡፡ የመጀመሪያ ልጅ ብትሆንም ወትሮም ከእናትና አባቷ ይልቅ የምታውቀው የአያቷን ጣእም ነውና ከርሳቸው ተለይታ ወላጆቿን ተከትላ አዲስ አበባ መግባትን አልወደደችም፡፡ አድጋና ነፍስ አውቃ 8ኛ ክፍልን ስትጨርስ ግን አዲስ አበባ መጥታ መማር እንዳለባት የወሰነችው ራሷ ናት፡፡ አንድም ያሳደጓት አያቷ በድንገተኛ ህመም የ7ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች በማረፋቸው ሌላም አዲስ አበባ ገብታ ብትማር የተሻለ መሆኑን ስላሰበች እናትም ስለገፋፏት ነው ሸገር የገባችው፡፡

ዛሬ 10ኛ ክፍልን ብታጠናቅቅም ከዚያ በላይ ለመግፋት የሚያስችል ነጥብ አልመጣላትም፡፡ ስለዚህ ስራ ከመፍታት ብላ በተለያዩ ካፍቴሪያዎች ውስጥ የአስተናጋጅነት ስራ ሞክራለች፡፡ ነገሩ ‹‹ከእጅ አይሻል ዶማ›› ሲሆንባት ነው ወደ ውጪ ሀገር ስለመጓዝ ማለም የጀመረችው፡፡ በወቅቱ በቀላሉ ልትጓዝበት የምትችልበት መንገድ የሃጂና ዑምራ ጉዞ ነው፡፡ አንድ ሰው በደላላ አግኝታ የእርሱ ሚስት እንደሆነች ተደርጎ በሙስሊም ስም ፓስፖርት ካወጣችና ኒካ ካሰረች በኋላ ፕሮሰሱ ብዙ አልቸገራትም፡፡ ከወላጆቿ አስቸግራና ራሷም ያጠራቀመችውን ገንዘብ ጨምራ በ6 ሺ ብር ወጪ ከሃጅና ዑምራ ተጓዦች ጋር ተቀላቅላ ዘይነባ በሚል ስም ሳዑዲ ገባች፡፡ አራት ዓመታትን ያሳለፈችው በተለያዩ ቦታዎች የቤት ሠራተኛ ሆና በማገልገል ነበር፡፡

ዛሬ አዲስ አበባ ስትመለስ የተሰማት ስሜት ልዩ ነበር፡፡ ወላጆቿን

ማግኘቷና ታናናሽ እህትና ወንድሞቿን አድገው ማየቷ- ከዚህም በላይ የናፈቀችውን አገሯን ደግሞ ለመመልከት በመታደሏ ደስ ብሏታል፡፡ አመጣጧ ለእረፍት ሲሆን ከ5 ወር በኋላ በሌላ ወረቀት ወደ መጣችበት አገር ለመመለስ እቅድ ይዛለች፡፡

ጊዜዋን ከወላጆቿና ከምታውቃቸው ጓደኞቿ ጋር እያሳለፈች ነው፡፡ አዲስ አበባ ከገባች ከ15 ቀናት በኋላ ነበር ወደ ጅማ ሄዳ ዘምድ ወዳጆቿን ለመጠየቅ የተነሳችው፡፡ እናቷ አብረዋት ሊሄዱ ከተነሱ በኋላ የግል ጉዳይ ስለገጠማቸው በሌላ ቀን ሊመጡ ተነጋግረው ነው ብቻዋን የተጓዘችው፡፡ ለዘመድ አዝማድ የሚሰጡትን ስጦታዎችና የገዛቻቸውን ነገሮች ይዛ በአውቶብስ ወደ አባ ጅፋር ሀገር ጉዞ ጀመረች፡፡ ይህ ጉዞ ለእመቤት ዘመዶቿንና የናፈቋትን ጓደኞቿን የምታይበት ብቻ ሆኖ አልቀረም፡፡ በመንገዱ ላይ አጠገቧ ተቀምጦ ከነበር አንድ ሰው ጋር ለመተዋወቅ እድል ፈጥሮላታል፡፡

ጋሻው በዚያን ዕለት ወደ ጅማ የሚጓዘው ከአዲስ አበባ በስራ ምክንያት ተቀይሮ የሄደ የልብ ጓደኛ ሀገሩን እንያይ ባቀረበለት ግብዣ መሰረት ነው፡፡ ስለሆነም ጅማ ላይ ተጨማሪ ጓደኛ ልትሆነው የምትችል ልጅ ሲያገኝ ስለሀገሩም ስለራሷም አንዳንድ ነገሮችን እየጠየቃት ተግባብተው ነው መንገዱን የጨረሱት፡፡ በጉዟቸው ላይ እመቤት ለጋሻው ሁሉንም ታሪኳን ነግራዋለች፡፡ ከውጪ መምጣቷንና ቤተሰብ ለመጠየቅ የምትሄድ መሆኑን ጭምር፡፡ ለረጅም ጊዜ የሚተዋወቁ ያህል ብዙ የተጨዋወቱትና ስለራሳቸው መረጃ የተለዋወጡት የጉዞ ጓደኞች አጋጣሚውን ወደውታል፡፡ እመቤት በተለይ ረጅሙን ጉዞ የሚያቀልላት አጫዋች በማግኘቷ ተደስታለች፡፡ እሱም በልጅቷ ውበትና ሳቂታነት ተማርኳል፡፡ ጅማ ሲገቡ ደግሞ መገናኘት የሚችሉበትን ዕድል አመቻችተው ነበር የተለያዩት ስልክ ተለዋውጠዋል፡፡ እመቤትን አውቶብስ ተራ ሲጠብቋት የነበሩት ዘመዶቿ ሲቀበሏት ጋሻውን ጓደኛው መጥቶ ወስዶታል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተገናኙት ሁለቱ ሰዎች ከዚያን ቀን ጀምሮ አንዳቸው ለሌላኛቸው አስፈላጊ ሰዎች መሆናቸው እስኪሰማቸው ድረስ ቅርርባቸው ጠንክሮ ነበር፡፡

ጅማ መንገዱ ላይ የተጀመረው ትውውቅና በዚያች ከተማ ያሳለፏት የጥቂት ቀናት የጓደኝነት ቆይታ የተጠናከረው አዲስ አበባ ከተመለ

ሱ በኋላ ነው፡፡ ጋሻው ለእመቤት በጣም ጥሩ ሰው ሆኖ ነው የቆየው፡፡ እመቤት በጋሻው ጥሩነት፣ አሳቢነትና መካሪነት እንዲሁም የልቧን ልታጫውተው የምትችል ሁነኛና ቁም ነገረኛ ሰው መሆን በጣም ነበር የተደሰተችው፡፡ በየዕለቱ እየተደዋወሉና በየዕለቱ እየተገናኙ ግንኙነታቸውን ከተራ ጓደኝነት ወደ ፍቅር አሳደጉት፡፡ እመቤት ጋሻውን ወዳዋለች፡፡ ለረጅም ጊዜ የምታውቀው ያህል አክብራዋለች፡፡ በተለይ ለርሷ አሳቢነቱና በማንኛውም ሁኔታ በህይወቷ ውስጥ ጠቃሚ ሰው መሆን እንደሚችል በሚሰጣት አክብሮትና ፍቅር ማረጋገጥ መቻሉ የዚህችን ወጣት ልብ በቀላሉ ለመግዛት አስችሎታል፡፡

አንዳቸው ስለሌላቸው የሚያውቁት አንዳች ነገር የሌለ እስኪመስል ድረስ የየግል መረጃዎቻቸውን ሁሉ ተለዋውጠዋል፡፡ እመቤት የምታውቀው ጋሻው ብዙ ጊዜ ትዳር ለመመስረት ሞክሮ ያልተሳካለት በሚያከብራቸውና ሁሉን ነገር በሰጣቸው ሴቶች የተከዳ ከአንዴም ሁለቴ ህልሙን በናዱበት ፍቅረኞቹ የተጎዳ መሆኑን ነው፡፡ እርሱ ጥሩ ሆኖ ሳለ ያጋጠሙት ሴቶች ታማኝና የትዳር ሰው ለመሆን ባለመቻላቸው ውስጡ እጅግ መጎዳቱን በዚህ የተነሳም ከዚህ ወዲያ ፍቅር የሚለውን ነገር ፈጽሞ እንደማይሞክረው ለራሱ ቃል ገብቶ የነበረ ሰው መሆኑን ነው የምታውቀው፡፡ በመሀል ከእርሷ ጋር ሲተዋወቅ ከዚህ ጥርጣሬ ጋር ሆኖ ስለነበር ደጋግሞ በእርግጥም ልቡን እንደማታደማውና ያለፉት ያስቀየሙትን እንደማትደግመው እየመላለሰ ጠይቋት ያረጋገጠ በመሆኑ በነገራት ታሪክ ላይ አንዳች ጥርጣሬ አላደረባትም፡፡ እሷም የምትፈልገው ታማኝና ቃሉን አክባሪ እንዲሁም ለጊዜያዊ ግንኙነት ሳይሆን ለዘላቂ ትዳር ራሱን ያዘጋጀ ሰው ስለሆነ በዚህ በኩል እንደ ተሳካለት አምናለች፡፡ አንዳቸው ለሌላቸው እግዚአብሔር የጣለላቸው ገፀ በረከት መሆናቸውን አምነዋል፡፡ በተለይ እመቤት የወደፊት የትዳር አጣማጇን ባግኘቷ ውስጧ በደስታ ሰክሯል፡፡ ጥሩ ጊዜ አሳለፉ- በፍቅር እንዲህ ልቧ በመጥፋት የመጀመሪያዋ የሆነው እመቤት ጋሻውን ወደደችው ብቻ ሳይሆን አመለከችው ማለት ይቀላል፡፡ የቅርብ ጓደኛዋ አምሳለ እንዳለችው የሁለቱ ፍቅር እመቤት ጋሻው ያላትን ሁሉ ከመፈፀምና እያንዳንዱን እንቅስቃሴዋን ከእርሱ ፍላጎትና ጥያቄ ጋር የማጣጣም ባህሪ ከማዳበር ባለፈ ለጋራ ኑሮ ጎጆ እስከመቀለስ (የልጅቷ... ወደ ገጽ 10 የዞረ)

ተለይ ትግራይን በቅርብ ርቀት የባህር በር እንዳይኖር ተግቶ መስረት ምን ዓይነት ልክፍት እንደሆነ የሚያሰረዳን እንፈልጋለን፡፡ ባህር እንዲኖረን ጥረት እናድርግ ሲባል ጦር ናፋቂዎች እንደሚሉን እምነቴ ነው፡፡ ይህ መልስ ግን ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል፣ጥፋትን መሸፈኛ ነው፡፡ አሁን ያለው ጥፋት ጥፋትን በጥፋት ማረሙ ላይ፡፡

ይህ ግትር አቋም እንደ አፍ ወለምታ ብቻ ሳይሆን ቋሚ የገዢው ፓርቲ መርዕ አድርገው ወደብ ሸቀጥ ነው ያሉን ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በህይወት እያሉ ነው ወደብ ሽቀጥ ብቻ እንዳልሆነ ምልክቱን ያዩት፡፡ በመስከረም 2004 ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ከጅቡቲ ጋር የነፃ (እንዲሁም ከፍለን) ውሃ ለማቅረብ የተስማሙት፡፡ ሁለት ዓመት አስቆጥሮ ደግሞ ይህ ሰምምነት ህግ ይሆን ዘንድ ለምክር ቤት ቀርቦዋል፡፡

ዛሬ ጅቡቲ በምትባል አንዲት ትንሽ ሀገር በፀባይ ለመያዝ ውሃ በነፃ ለዚያውም ከነሙሉ የደህንነት ጥበቃው ጋር መስጠት ጥቅሙ ወደብ ሽቀጥ ነው ብለው ያሰተማሩን ትምህርት ትክክል ያለመሆኑን ከማረጋገጥ በላይ ነው፡፡ ወደ ዘለገ ያለ የፖለቲካ ጥቅም አለው ለሀገር ደህንነትም ወሳኝ ነው፡፡ ዛሬ የዚህ የተሳሳ

ተ ወደብ ሸቀጥ ነው ፍልስፍና ለወደብ ኪራይ ከምንከፍለው ገንዘብ በተጨማሪ በነፃ ውሃ ልናቀርብ መሆኑ ነው፡፡ በእኔ እምነት በቅርባችን ያለችው መሪዋ አማርኛ አቀላጥፈው የሚናገሩት ጅቡቲዎች ውሃ ቢያገኙ ደስ ይለኛል፡፡ የሃረሪ ክልል ከድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ውሃ እንደሚያገኘት ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ችሮታ ደግሞ ሁሌ ቤት ሞልቶ ሲተርፍ ከሆነ ስጦታው ብዙም ላያስገርም ይችላል፡፡ ያለን በማካፈል ስሜት ሲሆን ደስ ይላል፡፡ እነካ በንካም ትክክል አይደለም፡፡

የሚቆጨው እና የሚያንገበግበው ግን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወጪ አድርጋበት የገነባቸውን አሰብ የግመል ውሃ መጠጫ እንዲሆን ፈቅደውና ተስማምተው፤ እንደ ሸቀጥ እንገዛዋለን ብለው ያሰቡትን የጅቡቲ ወደብ ከፈተኛ ዋጋ እያሰከፈለ ቢሆንም አሁንም በዓይነት ደግሞ የምንከፍልበት ፖለቲካው ሁኔታ መፈጠሩ ነው፡፡ ለጅቡቲ ከጫት እስከ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ከመብራት እሰከ መጠጥ ውሃ የማቅረብ ፍቅራችን ጥቅሙ ፖለቲካ መሆኑ መታመኑ ትልቅ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ወደብ ሸቀጥ ነው ብለውን ነበር እኮ፡፡ ለባቡር ግንባታ የሚያስፈልገውን ብድር ዋስትና የሰጠች ሀ

ገር አሁን ደግሞ የመጠጥ ውሃ ቢያገኙ ምን ይላቸዋል በሚል የህግ ረቂቅ ቀርቧል፡፡ በነገራችን ላይ በመሃል ሀገር የጅቡቲ መንግሰት የእርሻ መሬት እንዳለው መዘንጋት የለብንም፡፡

ብዙ ሰው ያልተረዳው ነገር ኢትዮጵያ ነዳጅ ብታመርትና በጅቡቲ በኩል ለመላክ ከወሰነች ነዳጅ በነፃ የምንሰጥበት ግዴታ ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታሰብ ማነኛውም ወደ ወጭ የሚላክ ምርትን ዋጋው እጅግ በጣም ውድ ነው፡፡ ዋጋ ውድ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ የሎጀስቲክ ስርዓቱ ነው እያሉ ሊያታልሉን ይሞክራሉ እንጂ ከሎጀስቲክ ስርዓቱ ውስጥ ዋነኛው የባህር በር የሌለን መሆኑ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር ዋጋ ትልቁ መስፈርት ነው፡፡ የባህር በር ናፍቆታችን መቼም ቢሆን በደረቅ ወደብ ምስረታ እንደማይሳካ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የግመል መጠጫ እንዲሆን የፈረድንበትን የአሰብ በር ኢትዮጵያዊያን በአማራጭነት የምንጠቀምበት ሁኔታ አጀንዳ መሆን አለበት፡፡ እሰከዚያ ድረስ ከጅቡቲ ጋር ያለንን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ከዚህም በላይ አጠናክረን መቀጠል ምርጫ አይደለም ግዴታ ነው፡፡

ወደብ ተራ ሽቀጥ አይደለም! ወደብ ለአንድ ሀገር ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካው እድገት ወሳኝ የሆነ ግብዓት ነው፡፡ ለሀገር ደህንነትም ጭምር፡፡ ኤርትራዊያን ሞልቶ ከተረፈ የባህር በሮቻቸው አንዱን በተለይም በኢትዮጵያ ብብት ውስጥ የሚገኘውን የአሰብ ወደብ በነፃነት ሰሜት መጠቀም መቻል ይኖርብናል፡፡ ይህ ማለት በጅቡቲ ወደብ መጠቀም ይቆማል ማለት አይደለም፡፡ መተንፈሻችን ይሰፋል ማለት ነው፡፡

የነፃነት ዋጋ ስንት ነው? በሚል መፅሃፌ ላይ “ጅቡቲ ያለ ኢትዮጵያ ሀገር ነች ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ …. ኢትዮጵያ አሁን እያቀረበችው ያለውን መሰረታዊ አቅርቦት በማሻሻል የጅቡቲ ዜጎች በኢትዮጵያ የትምህርት ዕድል የሚያገኙበትን እና ድሬዳዋን እና አካባቢዋን ተመራጭ ሀገራቸው እንዲያደርጉት መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ ኢትዮጵያዊያንም በጅቡቲ የኤኮኖሚ ትስስር ፈጣሪ እንዲሆኑ መንግሥት ቀጥተኛ ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡” ብዬ ነበር፡፡ በማስከተልም “በእኔ ዕይታ ኢትዮጵያ ለሁሉም ጎረቤት ሀገሮች ቅድሚያ መስጠት ይኖርባታል፡፡ በተለይ ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና (ጅቡቲ... ወደ ገጽ 23 የዞረ

የልጅቷ እምባ አሳዛኝ የወንጀል ታሪክ

ቦታ፡- Phalen Regional Park (1600 Phalen Dr, Saint Paul, MN)

ሰዓት፡- ከጠዋቱ 8:00 ሰዓት ምዝገባ ሲሆን፤ በ9:00 ሰዓት ውድድሩ ይጀምራል፤ ከዛም ለውድድር አሸናፊ ለሆኑ የሽልማት ፕሮግራም እንዲሁም

በቦታው ለተገኙ ተሳታፊዎች ቀለል ያለ ምሳ ተደርጎ ከቀኑ 12:00 ሰዓት የፐሮግራሙ ፍፃሜ ይሆናል።

የዚህ ዝግጅት ዋናው አላማ የሰውን ልጅ ጤንነትን እና ማህበራዊ ህይወትን የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ ነው:: በዚህ ዝግጅት ማንኛውም

ሰው መጥቶ መሳተፍ ይችላል:: ቲኬት $10 ነው፤ ከ18 አመት እድሜ በታች ለሆኑ እንዲሁም ከ60 አመት በላይ ለሆኑ ያለምንም ክፍያ

ቲ-ሸርት በነፃ ይሰጣል::

አዘጋጅ፡ የደ.ሰ.መ.ቤ.ክ የጤናና ማህበራዊ ክፍልና የደ.ሰ.መ.ቤ.ክ ሰበካ ጉባኤ

Place:- Phalen Regional Park (1600 Phalen Dr, Saint Paul,

MN)Date: - Saturday July 19, 2014 from 8 am. to 12 pm.

The goal of this event is solely to promote the health and social interaction in the community. The 5K Run/Walk event is open to everyone. Ticket is available in DSMA

Church and on the date of the event at Phalen Park. The ticket is $10 to cover the cost of T-shirt. Seniors above age

of 60 and children below 18 are sponsored by DSMA Parish Nursing Program.

Organizers:-DSMA Parish Nursing Program and DSMA Church

Page 8: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 8

እንመካከር

የዶ/ር ዓብይ ምክር፦ ውድ አንባቢያችን በህክምና ስለተሰጠህ ምክንያት ብትገልፅልንም ምን እንደሆነ ዘርዘር አድርገህ አላብራራህልንም፡፡ ሆኖም ችግርህን ስንመለከተው ከፕሮስቴት እጢ ጋር ተመሳሰለብን፡፡ እኛ ስለ ፕሮስቴት እጢና ካንሰር ምንነት እናስረዳሃለን፡፡ ከዛ ባለፈ አንተ በኩላሊትና ተመሳሳይ አካላቶች ህክምና ልዩ እስፔሻሊስቶች ጋር እንድትሄድ በግላችን እንጠቁምሃለን፡፡

የፕሮስቴት እጢ በወንዶች ብቻ የሚገኝ የሰውነት አካል ሲሆን ከወንዶች የስነ ተዋልዶ አካላት ውስጥ አንዱ በመሆን ይጠቅማል፡፡ ይህ እጢ የሚገኘው ከሽንት ፊኛ በታች ሲሆን የሽንት ትቦ የመሀከለኛውን ክፍል ዙሪያ ከቦ ይገኛል፡፡ ይህ የኦቾሎኒ ያክል መጠን ያለው የፕሮስቴት እጢ ከዕድሜ ጋር መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን በተግባሩም ለስፐርም የሚሆነውን ፈሳሽ ከሚያመነጩ የሰውነት አካል ውስጥ አንዱ ሆኖ ይገኛል፡፡

ለዛሬ የምንመለከተው ዋናው ርዕስ የፕሮስቴት እጢ በሚያድግበት ወቅት የሚከተለውን ሁለት አይነት ችግር ነው፤

1. የካንሰር ምልክት/ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት እጢ ማበጥ/ማደግ (Benign prostatic Hypertrophy) እና

2. የፕሮስቴት ካንሰር

የካንሰር ምልክት/ጠባይ የሌለው የፕሮቴስት እጢ ማበጥ/ማደግ Benign prostatic

Hypertrophyይህ ካንሰር የማያስከትል የፕሮስቴት እጢ ማበጥ ሲሆን መሰ

ረታዊ ምክንያት በውል ባይታወቅም በዕድሜ ለውጥ የሚከተሉ የሆርሞኖችን መለዋወጥ ተከትሎ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል፤ በዚህም ሳቢያ በአብዛኛው የዚህ ችግር ተጠቂዎች የሆኑት ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ናቸው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የፕሮስቴት እጢ በሽንት ትቦ ዙሪያ የሚገኝ እንደመ

ሆኑ መጠን መጠኑ በጨመረ ቁጥር ቀስ በቀስ የሽንት ትቦን የመጫንና በዚህም ሳቢያ የማጥበብ ብሎም ጨርሶ የመዝጋት ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሽንት ፊኛ በዚህ ጠባብ ትቦ ሽንትን ለማስወጣት በሚደረገው ጥረት የሽንት ፊኛ ጡንቻ ማደግና መጠንከር ይከተላል፡፡ ይህም የሽንት ፊኛ ውስጥ ያለው የሽንት መጠን ተሟጦ የመውጣት ስሜት ከማስከተሉም በላይ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንና ለሽንት ቧንቧ ጠጠር መፈጠር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ሁኔታዎች እየተባባሱ በመጡ ቁጥርና ጊዜው በረዘመ ቁጥር የኩላሊት መጎዳትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶች/የህመም ስሜቶች

የፕሮስቴት እጢ የማደግ ስሜትን ማስከተል የሚጀምረው የሽንት ትቦ ላይ ጫና በማስከተል ሽንት እንዳይወጣ መከልከል ሲጀምር ነው፡፡

- በመጀመሪያ ደረጃ ሽንት የመሽናት ስሜት ከመጣ በኋላ መሽናት ለመጀመር ጊዜ መፍጀት፣

- ሽንት ጨርሶ ያልወጣ ያልወጣ መስሎ መሰማት፣ - ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና ማጣደፍ፤ - በሌሊት ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ ከእንቅልፍ ለሽንት መ

ነሳት፤ - ሽንት በሚሸኑበት ወቅት መጠኑ መቀነስና መቆራረጥ እንዲ

ሁም ለመሽናት መታገል፤ - ሽንት ሸንተው ከጨረሱ በኋላ የመንጠባጠብ ሁኔታ፤ - በአንድ አንድ ሁኔታ ሽንት ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መል

ኩ መፍሰስ፤ - በሽንት ትቦና ፊኛ አካባቢ ያሉት ትናንሽ የደም ስሮች ሽን

ት ለማስወጣት በሚደረገው ግፊት መበጣጠስና በሽንት ውስጥ ደም የመከሰት ሁኔታ፤

- የሽንት ትቦ ከነአካቴው የተዘጋ እንደሆነ ደግሞ ፊኛ ከመጠን በላይ መወጠርና በታችኛው የሆድ ክፍል ከፍተኛ የህመም ስሜት መሰማት፤

- የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተከሰተም እንደሆነ በመሽናት ወቅት የማቃጠል ስሜት በብልት ላይ መሰማትና እንዲሁም የሰውነት ትኩሳት መከተል ሊታዩ ይችላሉ፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ግዴታ በአንድ ላይ ይከሰታሉ ማለት ባይሆንም በእነዚህ ጥቂት ስሜቶች ብቻ ቢኖሩም የዚህ ችግር ምልክት ለመሆን ይበቃሉ፡፡ እነዚህ ስሜቶች በሚኖሩን ጊዜ በምን ማወቅና ማረጋገጥ ይቻላል የሚለውን ከታች የምንመለከተው ይሆናል፡፡

ፕሮስቴት ካንሰርየፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ በብዛት የሚታይ ሁኔታ

ቢሆንም እንደ አብዛኛው የካንሰር አይነቶች መንስኤው በውል አይታወቅም፡፡ በፕሮስቴት እብጠት ሳቢያ በቀዶ ጥገና ከሚወገዱ የፕሮስቴት እጢዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚገኘው የፕሮስቴት እብጠት ካንሰር መሆኑን ያመለክታል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ የፕሮስቴት ካንሰር ቀስ በቀስ የሚያድግና የሚሰራጭ እንደመሆኑ መጠን አስከፊ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት ስሜት ላያስከትል ይችላል፡፡

ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶች/የህመም ስሜቶች

ከላይ እንደተጠቀሰው የፕሮስቴት ካንሰር አደገኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ በአብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት ባያስከትልም በፕሮስቴት እብጥት ሳቢያ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ነገር ግን የፕሮስቴት ካንሰር መሰራጨት ከጀመረ በኋላ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንደ አጥንት፣ ኩላሊት

ብሎም ወደ አንጎል በመሰራጨት የተለያየ አይነት የህመም ስሜቶችና ሁኔታዎችን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ይህንን ችግር በምን ማረጋገጥ ይቻላል?አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች በሚሰሙበት ወቅት

ወይም የጤና ባለሙያ ይህንን ሁኔታ በሚጠራጠርበት ወቅት ሊደረጉ ከሚገባቸው ምርመራዎች ውስጥ፤

- በፊንጢጣ በኩል ጣትን በማስገባት የፕሮስቴት እጢው ማበጥ አለማበጡንና፣ ከዚያም በተጨማሪ አስፈላጊ የሆኑ የመለያ ነጥቦችን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡

- ከዚህም በተጨማሪ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ችግሩ መኖሩንና ከሆነም ደግሞ ካንሰር የመሆንና ያመሆኑን ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ መገመት ይቻላል፡፡

- የፕሮስቴት ዕጢ ማደጉንና እንዲሁም ካንሰር የመሆን ዕድሉን ሊነግረን የሚችልም የደም ምርመራ እንደመኖሩ ይህንን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እንዲያውም ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ላይ ይህንን የደም ምርመራ በየዓመቱ ማድረግና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

- ከፕሮስቴት ዕጢ ናሙና በመውሰድ የእጢውን ሁኔታ ማረጋገጥም ተመራጭ የሆነውና እርግጠና ሁኔታውን ሊነግረን የሚችል የምርመራ አይነት ነው፡፡

- የፕሮስቴት ካንሰር የተሰራጩ እንደሆነም እንደየአስፈላጊነቱ የተጠቃውን የሰውነት አካል የተለያዩ ምርመራዎች ማድረግ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ስሜቶች የሌላ ህመም መገለጫ ሊሆኑ እንደመቻላቸው አስፈላጊውን ምርመራ እንደየአስፈላጊነቱና በደረጃ ማድረግ መሰረታዊ ነው፡፡ ስለዚህም ትንሽ ነው ብለን ጊዜ የሰጠነው የፕሮስቴት ዕጢ ችግር ለባሰ ሁኔታ ሳያጋልጠን በጊዜ ህክምና ብንወስድበት ስለ ህመሙም አውቀን የቅድመ ጥንቃቄ ወይም የመከላከል እርምጃ ብንወስድ መልካም ነው፡፡

አልፎ አልፎ በብልቴ ላይ የሚወጣው እብጠት ምንድን ነው?ከአንድ ዓመት በፊት ሽንት መሽኛዬ አካባቢ አልፎ አልፎ እየታየኝ የመጣው ምልክት ግራ መጋባትን ጭንቀትን ስላስከተለብኝ ነው፡፡ በቆለጤ ፍሬ ላይ አልፎ አልፎ እየጠፋ የሚመጣ የእብጠት ምልክት ከጀመረኝ ጊዜ ጀምሮ ሽንቴ ቶሎ ቶሎ ይመጣል፡፡ እብጠቱ የራሱ

ን ወቅት ጠብቆ ቢጠፋም ተመልሶ ይመጣል፡፡ አሁን ግን በራሱ ጊዜ ተመልሶ ይጠፋል ብዬ ብጠብቅም በጣም ቆየብኝ፡፡ ከዚህ ባለፈ ሌሊት ሌሊት ሽንትም ጀማምሮኛል፡፡ ሆኖም እየተቆራረጠ ችግር ሆኖብኛልና ከምንም በላይ ግን አለመረጋጋት ፈጥሮብኛል፡፡ ወደ ህክም ብሄድም ኢንፌክሽን ነው ተብዬ መርፌ ብቻ ታዘዘልኝ፡፡ ሆኖም አማራጭ ስላጣሁ ችግሬ ምን እንደሆነ አስረድታችሁኝ ማድረግ የሚገባኝን ጥንቃቄ ካለ እንድትነግሩኝ እለምናችኋለሁ፡፡ አምሳሉ

ራስን በራስ የማጥፋት ፍላጎትን እንዴት መግታት ይቻላል?ከፍቅረኛዬ ጋር የምኖረው በኑሯችን አነስተኝነት የተነሳ የደስ

ተኝነት ስሜት በመሀላችን ብዙም አልሰፈነም፡፡ በአጭሩ ለማስረዳት ጓደኛዬ ራሱን ለማጥፋት ሙከራ አድርጓል፣ ስራ ትቶም እቤት ቁጭ ብሏል፡፡ የስነ ልቦና ባለሞያን እንዳላማክር አቅም የለኝም፡፡ እሱም ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ የኑሮ ውድነቱ እየተባባሰብን ሲመጣም የበለጠ ሓሳብ እየገባኝ እኔም ጭንቀቴ እየጨመረ ነው፡፡ ጓደኛዬ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ዝምታው እየጨመረ ሃሳብ ሆኖብኛል፡፡ እባካችሁን ካልሆነ እኔ እንኳን በምን መልኩ ልረዳት እችላለሁ? ራስ የማጥፋት ፍላጎትንስ እንዴት መግታት ይቻላል? ኬ.ኤም

የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፡ ውድ ኬኤም እኛም አፀፋውን እየመለስን በመጀመሪያ ደረጃ የራስሽን ስሜት ማሸነፍ ስትችዪ ነው እሱንም መርዳት የምትችዪው፡፡ ሆኖም እኛ ራስን ስለማጥፋት በሰፊው የምንለው ይኖረናል፡፡ ከዚህ ባለፈ እነዚህን መርሆዎች በመከተል ለጓደኛሽ እንክብካቤ ልታደርጊ ትችያለሽ እንላለን፡፡

ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም፣ ይሻላል በተስፋ ሲጓዙ መክረም

ራስን የማጥፋት ሁኔታ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ችግር ሲሆን በአብዛኛው ሰዎች ከቁጥጥራቸው ውጪ የሆነ የተስፋ መቁረጥ ጥግና የኑሮ መጨለም በሚጋጥማቸው ጊዜ የሚከተል ችግር ነው፡፡ አንዳንዴም ከሰዎች መገለልንና መበደልን ለማስቆም ብሎም በሌሎች ዘንድ ትኩረት ለማግኘት የሚደረግ ሙከራም ይሆናል፡፡ ከልብ ባይደረግም እንደማስፈራሪያ መንገድም ነው ማለት ነው፡፡ ራስን ማጥፋት የሚለው ሃሳብ ሶስት አይነት ሁኔታዎችን ያቀፈ ሲሆን፡-

1. የራስ ማጥፋት ሃሳብ /ሙከራ /Suicide gesture/ ራስን የማጥፋት ውጥኑና ሙከራው ለጉዳትና ለሞት የማይዳርግ ሆኖ ሲገኝ፤ 2. ራስን የማጥፋት ሙከራ /Suicide attempt/ ራስን የማጥፋት ፍላጎቱም ሆነ ውጥኑ ጠንካራና ለሞት የሚዳርግ ሆኖ ሳለ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ ሲቀር፤ 3. ራስን ማጥፋት /completed

suicide/ ራስን የማጥፋት ሙከራ ሲሳካና ለሞት ሲዳርግ ናቸው፡፡ በመሰረቱ በራስ ማጥፋት ላይ የተሰሩ ጥናቶች በዋነኝነት የተመሰረቱት የሞት የምክስር ወረቀት በማየት እንደመሆኑ መጠን የእውነተኛው ቁጥር ጥናቶች ከሚያመላክቷቸው የበለጠ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በአለማችን ውስጥ ያለውን ሁኔታ ስንመለከተው ራስን ማጥፋት ከመጀመሪያዎቹ አስር ሞት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ውስጥ ሲመደብ በወጣቶችና በጎልማሶች ላይ ደግሞ የሁለተኛን ቦታ ይዟል፡፡ በተጨማሪም 30 በመቶ የሚሆነው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የሚከሰተው ሞት እና 10 በመቶ የሚሆነው ከ25-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ሞት የሚከተለው በዚህ ራስን በማጥፋት ሳቢያ ነው፡፡ 70 በመቶ የሚሆኑ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በተለይ ከ60 ዓመት በላይ ባሉ ወንዶች ላይ ይህ ቁጥር እጅግ እየቸመረ ይሄዳል፡፡ ነገር ግን የራስ ማጥፋት ሙከራ ከ30 ዓመት በታች ባሉ ሰዎች ላይ በዝቶ ይታይ እንጂ የመሳካቱ ሁኔታ አሁንም ቢሆን ከሌላው የእድሜ ክልል ያነሰ ሆኖ ይገኛል፡፡

በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ውስን ያሉ ሁኔታዎችን ስንመለከት - የራስ ማጥፋት ሙከራን ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በ3 እጥፍ በበለጠ ሲሞክሩ የመሳካቱ ሁኔታ ግን በወንዶች ላይ በ4 እጥፍ ከሴቶች በልጦ ይገኛል፡፡

- የራስ ማጥፋት ባላገቡ፣ በተፋቱ እንዲሁም ባለቤታቸው በሞት በተለየባቸው ሰዎች ላይ የበለጠ ሆኖ ይገኛል፡፡

- የከተማ ነዋሪዎች ከገጠር ነዋሪዎች የበለጠ ራሳቸውን የማጥፋት ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡ በቤተሰብ ውስጥ ራስን የማጥፋት ሙከራ ወይም ስኬት የኖረ እንደሆነ ይህ ሁኔታ በሌሎች የቤተሰብ አካል ውስጥ የመደገም ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡

- የጥቁር ዘር ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን የማጥፋት ቁጥር ከነጮች ያነሰ ይሁን እንጂ የጥቁሮችም የራስ ማጥፋት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

- አብዛኛው በእስር ቤት ውስጥ ያሉ በተለይ ጥፋት ያላጠፉ ሰዎች ራሳቸውን የማጥፋት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

- ከአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ በጦር ሠራዊት ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ የህግ ባለሙያዎችና ሐኪሞች/በተለይም ሴቶች ሐኪሞች/ ራሳቸውን የማጥፋት እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት የሚችሉባቸው ምክንያቶችበአብዛኛው ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት የሚወስኑበት ምክንያት አንድና ውሱን ሳይሆን የተደራረበ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት ነው፡፡ ከተለያዩ ምክንያቶች ውስጥም ጥቂቶቹን ስንመለከት፡-

- የስነ አእምሮ ችግር ያለባቸው ሰዎች በተለይም ከፍተኛ ድብርትና ስኪዞፍሬኒያ ያለባቸው ሰዎች ለዚህ ሁኔታ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ የተለያዩ የስነ አዕምሮ ችግሮች በተጓዳኝ ወይም በተጨማሪ ድብርትን ያስከትሉ እንደሆነ ለዚህ ችግር የተጋለጡ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ስኪዞፍሬንያ ያለባቸውን ሰዎች ለምሳሌ ስንመለከት ራስን የማጥፋት አላማቸው ጠንካራ እንደመሆኑ መጠን በአብዛኛው ጊዜ ሲሳካላቸው ይታያል፡፡

- የተለያየ የሱስ ተገዢ የሆኑ ሰዎች ራስን ለማጥፋት የበለጠ የተጋለጡ ናቸው፡፡ አብዛኛው ሱስ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮች በተለይም አልኮልንና አደንዛዥ ዕፆችን ስንመለከት ድብርት የማስከተልና በሌላም በኩል ደግሞ የመደፋፈር እንዲሁም የጀግንነት ስሜት ስለሚያስከትሉ ራስን ለማጥፋት ሙከራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡ - የተለያዩ የማህበረሰብ ችግር ያለባቸው ሰዎች ማለትም ሀዘን ያጋጠማቸው፣ የቅርብ ሰው በሞት የተለያቸው፣ ገንዘብ ማጣት፣ ከቅርብ ሰው ጋር መለየት፣ የብቸኝነት ኑሮ እንዲሁም የመሳሰሉት ሁኔታዎች ለዚህ ችግር ሊዳርጉ ይችላሉ፡፡

- የስነ ፀባይ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ስንመለከት በአብዛኛው ጊዜ በቶሎ የሚናደዱና ትዕግስት የሌላቸው ሰዎች፣ የንዴታቸው መገለጫ የተጋነነ የሆኑ ሰዎች፣ ጭንቀት የመቀበልም ሆነ መፍትሄ የመፈለግ ባህሪያቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች፣ እንዲሁም ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ሰዎች ለዚህ ሁኔታ የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ አይነት ሰዎች በተጨመሪ አልኮል የመጠጣት፣ የአደንዛዥ ዕፅ የመተቀምና ህገወጥ ስራ የመስራት እድላቸው ከፍ ያለ እንደመሆኑ ከዚህ ሁኔታ በተጋነነ መልኩ ይጋለታሉ ማለት ነው፡፡

ራስን የማጥፊያ መንገዶችበአብዛኛው ጊዜ ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት የሚተቀሙባቸ

ው ዘዴዎች እንደ ፀባይ፣ ባህል፣ ለአጋጣሚው የሚዳርጉ መንገዶች መኖር ወይ አለመኖር፣ የመሳሰሉት ሁኔታዎች ይለያያሉ፡፡ በጥቅሉ ግን ስንመለከት ወንዶች በብዛት የሚጠቀሙበት መንገድ ኃይለኛና ቁርጠንነት የተሞላበትን እርምጃዎች የመውሰድ ባህል ሲኖራቸው፣ ሴቶች ደግሞ መለስ ያለ መንገዶችን ይጠቀማሉ፡፡ ይህንን ስንል ለምሳሌ ወንዶች ራሳቸውን በሽጉጥ በመተኮስ፣ በገመድ አንገታቸውን በማነቅ እንዲሁም ከፍተኛ ከሆነ ፎቅ ላይ ራስን በመወርወር የመሳሰሉትን መንገዶች ሲጠቀሙ፣ ሴቶች ደግሞ መድሃኒት መውሰድና ራሳቸውን በጋዝ በማፈን የመሳሰሉ መንገዶችን ይጠቀማሉ፡፡ በአጠቃላይ ሰዎች ራሳቸውን ለማትፋት የእውነት ሲፈልጉና ሰዎችን ብቻ የማስፈራራትና ሰውን ትኩረት ወደ እነሱ ለማድረግ በመሞከር ራስን የማጥፋት ሙከራ ሲያደርጉ የሚጠቀሙባቸው መንገዶች የተለያዩ ናቸው፡፡ በአንዳንድ ሁኔታም ከአንድ በላይ መንገዶችን በመተቀም የነገሩን መፈፀም የበለጠ እርግጠኛ የሚያደርጋቸውን መንገዶች ይጠቀማሉ፡፡ ለምሳሌ ደብዳቤ ጽፎና ምክንያቱን አስረድቶ ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረግ፡፡

ሰዎች ይህ አይነት ሁኔታ በሚያጋጥማቸው ጊዜ ምን ማድረግ ተገቢ ነው? አንድ ሰው ማንኛውም አይነት ከላይ የ

ተጠቀሱት ራስን የማጥፋት ሙከራ ለማድረግ የሚገፋፋ ስሜትና ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሲገኝ ለነገሩ መፍትሄ ለመሻት ከመሞከርም በላይ የስነ አዕምሮ ሐኪም ጋር በመውሰድ /በመሄድ/ አስፈላጊውን የምክር አገልግሎት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ ራስን የማጥፋት ሙከራም ያደረገን ሰው በመጀመሪያ ደረጃ እንደየአስፈላጊነቱ ወደ ህክምና ማዕከል በመውሰድ የድንገተኛም ሆነ ሌላ የህክምና አገልግሎት ካገኘ በኋላ ወደ የስነ አዕምሮ ሐኪም መውሰድ ግድ ይላል፡፡ ማንኛውም ሰው ራስን የማጥፋት ሙከራ አንድ ጊዜ ካደረገና ካልተሳካለት የመደገም ዕድሉ ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ችላ ሳይሉ አስፈላጊውን ክትትልና እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

BISRAT ALEMAYEHU & ASSOCIATES

Meet your Friendly and Experienced professionals@

The Center for Multi-ServicesTax, Insurance, Real Estate, Notary, Application

Forms,Translation and More

ታክስ፣ ኢንሹራንስ፣ ሪል እስቴት፣ ኖታሪ፣ ውክልና፣ትርጉምና በርካታ ተዛማጅ አገልግሎቶች

WISER INSURANCE AGENCY, St. PaulMore Insurance Companies, More Price Choices!

[Auto. Home. Life. Health. Business]

Address: 1821 University Ave. W. Suite S-301 Saint Paul, MN 55104Tel: 651 649 0644 / 651 209 6077 Fax: 651 649 0620

ማሳሰቢያበዘ-ሐበሻ የጤና አምዶች ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ ለማስተማሪያነት እና ግንዛቤ ለመስጠት እንጂ እንድትታከሙበት አይደለም። ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ህመም ሲሰማ ወደ ዶ/ር ጋር በመሄድ በዶ/ር ትዕዛዝ እንድትታከሙ አደራ እንላለን።

፩ * አንድ . 1 ---፪ * ሁለት . 2 ---፫ * ሶስት . 3

በኢትዮዽያዉያን ታሪክ የመጀመርያ የሆነዉ ፣ በአመለካከት ልዩነት ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮዽያዉያንንና ትዉልደ ኢትዮዽያዉያንን ሁሉ እንዲሳተፉበት ሆኖ የተዘጋጀ ፣ በአቀራረቡ ልዩና በርዕሰ ይዘቱ ሀገራዊ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የሆነዉ ፣ የኢትዮዽያዉያንንና የትዉልደ ኢትዮዽያዉያንን ሁለንተናዊ እድገት ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ የሚንቀሳቀሰዉ ታላቁ የምክክር ቀን ከ Friday July 25 እስከ

Tuesday July 29 በ Metropolitan State University St.Paul, Minnesota, USA ይካሔዳል ። ለሙሉ መረጃ www.tesfa-efd.orgን ይጎብኙ !

እርስዎና ልጆችዎም የዚህ ታሪካዊ ዝግጅት አካል እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋልእርስዎ :- ድረ ገፃችንን በደንብ ይጎብኙ : ጥያቄ አስተያየት ወይም ሀሳብ ካለዎት (952) 465-6786 ይደዉሉ :

[email protected] ኢሜል ያድርጉልን ። ለመምጣት ሲወስኑ ድረ ገፃችን www.tesfa-efd.org ዉስጥ “Reservation” ገፅ በስተቀኝ ከላይ በኩል የሚገኘዉን ቅድመ ማሳወቂያ ቅፅ ፎርም Summit 2014 Reservation Form በመሙላት መምጣትዎን በቅድሚያ ያሳዉቁን ። ፎርሙ ድረ ገፃችን ላይ ይገኛል! … ቦታ መኖሩን ካረጋገጥን በሁዋላ የይሁንታ ምላሽ በ ኢ-ሜይል እንሰጣለን ። ከዚያ በሁዋላ ከስራዎ (ትምህርትዎ) ፈቃድ ይዉሰዱ ። በዕለቱም በሙሉ የአገር ባህል ልብስና ባህላዊ የፀጉር አሰራር አምረዉ ደምቀዉ አሸብርቀዉ ከቦታዉ በሰዐቱ ከዋናዉ የስብሰባ አዳራሽ

Conference Hall ይገኙልን!ልጆችዎ :- በአገር ባህል ልብስ ባህላዊ የፀጉር አሰራር አምረዉ ደምቀዉ አሸብርቀዉ ከቦታዉ በሰዐቱ ከ Art Exhibition Hall

ይምጡልን!

** በነገራችን ላይ ዕድሜአቸዉ ከ 18 በታች የሆናቸዉ ትዉልደ ኢትዮዽያዉያን ልጆች የፈጠራ ስራዎቻቸዉን እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል :- ለሙሉ መረጃ ቀጥሎ ያለዉን ይመልከቱ ። ልጆችዎም እን

ዲያነቡት ይጋብዟቸዉ **

KIDS ART Exhibition , Hosted by TESFA-EFD , July 25-29 2014 @ Metropolitan State Univer-sity, 700 East 7th Street, Saint Paul, Minnesota 55106 , USA

About the Exhibition :-Kids of all ages (Under 18) are allowed to bring their art works at the ‘Exhibit Hall’ of the Metropolitan State University on July 24th, 2014. Parents are expected to (must) accompany their kids always and during the entire summit duration. Our team members shall be there at all times to guide parents and kids.The Theme of the kids Art Gallery is MY DREAM, which is an opportunity given to our kids to express and share their dreams and hopes. The vision can be about themselves, their com-munity OR the world. They can use any form of arts like drawings, paintings, photographs, sculptures, metal arts, wood arts, etc.A kid can only display one work and it must be originally his/hers. The kids will be the sole owners of their work. Their work shall be visited by the public and participants of summit 2014 through the entire duration of the summit, they will be rewarded later for their effort and their arts will be displayed on the official website of our organization and also year book of Summit 2014.

For more questions, Please contact us via [email protected] or (952)-465-6786 .Our team is looking forward to meet you all at Summit 2014 !

ለበለጠ መረጃና ማብራሪያ :- (952) 465 -6786 ይደዉሉ ! [email protected] ኢ-ሜይል ያድርጉ ! የዚያ ሰዉ ይበለን!

*--- ኢትዮዽያ ለዘላለም በክብር ትኑር ---*

Page 9: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 9

ሁለት ፈረሶች እንደነበሩ ተነገረ፡፡ አንደኛው እጅግ ለምለም በሆነ ሰፊ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ፣ ሲያሻው ደግሞ በግራ በቀኝ ገብስ ፈስሶለት፣ ሲጠማው የሚጠጣው ውኃ በሜዳው መካከል ኩልል ብሎ እየወረደለት፣ አውሬ እንዳይተናኮለው ዙሪያውን በውሻ እየተጠበቀ ይኖር ነበር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሣር ዘር ለአመል ያህል ብቻ እዚህም እዚያም በበቀለበት፣ ጭው ባለ ደረቅ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ ያገኛትን እየነጨ፣ ከዕለታት በአንድ ቀን ከደጋ የዘነበ ዝናብ በአካባቢው ሲያልፍ የሚያገኘውን ጥፍጣፊ ውኃ እየተጎነጨ፣ ሌትና ቀን ምን ዓይነት አውሬ መጥቶ ይዘነጥለኝ ይሆን? እያለ በሥጋት ይኖር ነበር፡፡

ምንም እንኳን ሁለቱም ፈረሶች በኑሮ በማይቀራረብ ሜዳ ላይ በመከራና በቅንጦት ተለያይተው ቢኖሩም የኑሮ ጥያቄ ግን አገናኝቷቸው ኖሯል፡፡ ያ እንዲያ በለመለመ መስክ ተሠማርቶ እምብርቱ እስኪነፋ ሆዱ እስኪቆዘር እየበላ ሲተኛ ሲነሣ የሚውለው ፈረስ ‹‹ይኼ ሣር ያለቀ ዕለት፣ ይኼም ውኃ የነጠፈ ጊዜ፣ እነዚህም ውሾች እኔን መጠበቅ ትተው የሄዱ ጊዜ፣ ይኼስ ገብስ የጠፋ ቀን ምን ይውጠኝ ይሆን? ያስ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡ ይኼ ጥያቄ ምንጊዜም ይረብሸው ነበር፡፡

ያ በደረቅ ሜዳ ላይ እዚህም እዚያም የበቀለች ሣር እየነጨ ከርሱን ሲደልል የሚውለው ፈረስ ደግሞ ‹‹መቼ ይሆን አልፎልኝ ለምለም መስክ ላይ ውዬ፣ ከፈሰሰ ውኃ እንደ ልቤ ተጎንጭቼ፣ ያለ ሥጋት አድሬ የሚነጋልኝ? ያ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡

እዚህ ሀገር ያለን ሰዎች በሁለቱ ፈረሶች ጥያቄ ውስጥ ወድቀናል፡፡ አንደኛው መስኩ ለምልሞለት፣ ውኃው መንጭቶለት፣ ሥጋቱ ጠፍቶለት፣ ሕይወቱ ቀንቶለት የሚኖረው ሰው ጥያቄ ነው፡፡ እንዴት ሜዳው ላይ እንደደረሰ አያውቀውም፤ ብቻ አንድ ቀን ተቀለጣጥፎም፣ ተጣጥፎም፣ ተለጣጥፎም፣ ራሱን ሜዳ ላይ አግኝቶታል፡፡ ለስንትና ስንት ፈረስ የሚበቃውን መስክ ብቻውን ተሠማርቶበታል፡፡ አገር የሚያጠጣውን ወንዝ ብቻውን ይንቦራችበታል፡፡ ጥጋብን ከልኩ በላይ፣ ምቾትንም ከመጠን አልፎ ቀምሶታል፡፡ ድህነትን ረስቶ የት መጣውን ዘንግቶታል፡፡ ግን ሥጋት አልለቀቀውም፡፡

ይኼ መሥመር የተበጠሰ ዕለት፣ ይኼ ሥርዓት ያለፈ ቀን፣ ከእገሌ ጋር የተጣላሁ ጊዜ፣ ቀን የዞረችበኝ ሰዓት፣ የተነቃ ለታ፣ ዕቁቡ የተበላ ጊዜ፣ ካርታው ያለቀ ቀን፣ መንገዱ የታወቀ እንደሆን፣ ሕግ የተቀየረ ቀን፣ ምን ይውጠኝ ይሆን? ያችስ ቀን መቼ ትሆን? እያለ ይጠይቃል፡፡ እየበላ ይሠጋል፣ እየጠጣም ይጨነቃል፤ አይቷል፣ ሰምቷል፡፡ ድንገት ለምለሙ ሜዳ ላይ ተገኝተው ድንገት ከሜዳው የጠፉ አሉና፡፡

አሁን ሆዱ ተቀይሯል፤ አንገቱ ተቀይሯል፤ እጁ ተቀይሯል፤ መቀመጫው ተቀይሯል፤ ማረፊያና መዋያው ተቀይሯል፡፡ ይህንን ያጣ ዕለት ምን ይውጠዋል?

ያኛውም ፈረስ አለ፡፡ እንደ ዐርባ ቀን ዕድል ሆኖ የደረቀ መስክ ላይ ውሎ እንዲያደር የተፈረደበት፤ ቢሄድ ቢመጣ፣ ቢወርድ ቢወጣ ከዚያ መስክ መላቀቅ ያቃተው፡፡ መቼ ይሆን የእኔስ ሜዳ በሣር ተሞልቶ እንደነዚያ ሣር የምጠግበው እያለ ምኞት የገደለው፡፡ የእኔስ ወንዝ መቼ ይሆን ውኃ ሞልቶት ሳልጨነቅ የምጠጣው? እያለ ሃሳብ ያናወዘው፡፡ የእርሱ ቤት እየፈረሰች ከጎረቤቱ ዘጠኝ ፎቅ ሲበቅል አይቷል፡፡ ስትተከል፣ ውኃ ስትጠጣ፣ አላያትም፡፡ እንዲሁ ብቻ ፎቋ በቀለች፡፡ ስትገዛ ያላያት፣ ፍንጥር ያልጠጣባት መኪና እንዲሁ ሽው እልም ስትል አያት፤ እናም ምን ዓይነት ፈረሶች ይሆኑ ለዚህ የሚበቁት እያለ ይጠይቃል፡፡ ዝርያቸው ምን ቢሆን ነው? መልካቸውስ ምን ቢሆን ነው? የፈረስ ጉልበታቸውስ ምን ያህል ቢሆነ ነው? ፍጥነታቸውና ቅልጥፍናቸውስ እንዴት ያለ ቢሆን ነው? ጌቶቻቸውንስ እንዴት አድርገው ቢያገለግሏቸው ነው? እንዲህ ለምለም መስክ ላይ የለቀቋቸው? እኛም ስናገለግል ኖረናል፤ ጋሪ ስንጎትት፣ እህል ስንሸከም፣ ዕቃ ስናጓጉዝ ኖረናል፤ ጌቶቻችን ሲጋልቡን ኖረናል፤ ግን እነርሱ ምን ያህል ቢያስደስቷቸው ነው ይህንን ዕድል የሰጧቸው? እያለ ይጠይቃል፡፡

ለመሆኑ እነርሱ ናቸው ወደ እኛ የሚመጡት ወይስ እኛ ነን ወደ እነርሱ የምንሄደው? ለመሆኑ የኛን ድህነት ነው ወይስ የእነርሱን ሀብት ነው የምንካፈለው? በርግጥ ከኛም የሄዱ አሉ፤ ከእነርሱም የሚመጡ አሉ? ይላል፡፡ አንዱ ሜዳ ላይ ተሠማርተን እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን መጋጥ ሲገባን ለምን ሁለት ዓይነት ሜዳ ሆነ፡፡ አሁን እኛና እነር

የሁለት ፈረሶች ጥያቄ

ከዳንኤል ክብረትDanielkibert.com

ሱ እኩል ‹‹ፈረስ›› ተብለን እንጠራለን? እኛ ‹‹ሌጣ ፈረስ›› ነን፣ እነርሱ ደግሞ ‹‹ባለ ወግ ፈረስ›› ናቸው፡፡

ግን ይሁን፤ እሺ መቼ ይሆን እኛስ እንደነርሱ የምንሆነው? መቼ ይሆን ያለ ሥጋት ውለን የምናድረው? ለምለሙን መስክ ማን ይነካዋል፤ ላለው ነው ድሮም የሚጨመርለት፤ የኛ የድኾቹን መስክ ነው ለሀብታሞቹ የሚሰጡት፤ የድኾቹን ደረቅ መስክ ሀብታሞቹ የሚቀኑበትን ያህል እኛ በእነርሱ ለምለም መስክ አንቀናም፡፡ ደግሞ አንድ ቀን ይመጣሉ፡፡ ‹‹ይህንን መስክ ለምለም ማድረግ እንፈልጋለን›› ይላሉ፡፡ እኛም ደስ ይለናል፡፡ የዘመናት ምኞታችን አይደል? መንገዱ ጠፍቶን እንጂ እኛም ለምለም ማድረግ እንፈልግ ነበርኮ? መንገዱን ያወቀው ሰው ሲመጣ ለምን እንቃወመዋለን፡፡

ግን ይቀጥሉና ሌላ ነገር ይሉናል፡፡ ‹‹መስኩን ግን ለምለም የምናደርገው ለእኛ እንጂ ለእናንተ አይደለም›› ይሉናል፡፡ ለምን? ለምን? እኛ ለምለም ሣር አይወድልንም? እኛ ለምለም የምናደርግበትን መንገድ ለምን አያሳዩንም? ባያሳዩንስ ለምን አይፈቅዱልንም? ባይፈቅዱልንስ ለምን አይተውንም? እንላለን፡፡ ይህ ግን ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የለውም፡፡ እኛም ጥያቄውን የምናውቀውን ያህል መልሱን አናውቀውም፡፡ ስንጠይቅም ‹‹ምላሽ›› እንጂ ‹‹መልስ›› የሚሰጥ አናገኝም፡፡

እኛም ከዚያ መስክ እንወጣለን፣ ወደሌላ መስክም እንዛወራለን፤ አሁንም ቅንጥብጣቢ ሣር እንፈልጋለን፤ ጥፍጣፊ ውኃ እናስሳለን፡፡ ያ እኛ የነበርንበት መስክ ግን በአንድ ጊዜ ይለመልማል፡፡ ውኅው ጅረት ሆኖ ይፈስበታል፡፡ ይገርመናል፡፡ እኛ እዚያ ሳለን፡፡ ውኃ አልነበረም፡፡ እንደ ወር በዓል ቀን ቆጥረን ነበር የምናገኘው፡፡ አሁን ግን ይንፎለፎላል? ለመሆኑ እኛ ምን ብለን መጠየቅ ነበረብን? ይኼ ራሱ ሌላ ጥያቄ ይሆንብ

ናል፡፡ መቼ ይሆን እኛስ እንዲህ ባለው መስክ ላይ የምንሠማረው? እንላለን፡፡ የማይሳካ ምኞት እንመኛለን፤ የማይመለስ ጥያቄ እንጠይቃለን፡፡

እዚያም ቤት ሌላ ጥያቄ አለ፡፡ ፀሐይዋ እንደወጣች ትቀጥል ይሆን? ወንዙ እንደፈሰሰ ይቀጥል ይሆን? ነፋሱ እንደነፈሰ ይቀጥል ይሆን? ሣሩ እንደለመለመ ይዘልቅ ይሆን? እኔስ እንደተወደድኩና ሞገስ እንዳገኘሁ እኖር ይሆን?

ሰውየው ስለ አውሮፕላን አነዳድ የሚገልጥ ማኑዋል አገኘና አውሮፕላኑን አስነሥቶ አበረረ፡፡ ገጹን ይገልጣል፤ የተጻፈውን ይፈጽማል፤ አውሮፕላኑም ይበራል፡፡ በቀጣዩ ገጽ ላይ ምን እንዳለ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ገጹ ተገንጥሎ ቢገኝ ምን ማድረግ እንዳለበትም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ብቻ ይገልጣል፣ ያነባል፣ ይነካካል፣ ይበራል፡፡ አውሮፕላኑ ተነሥቶ በሃያ አምስት ሺ ጫማ ከፍታ ላይ ሲደርስ የመጨረሻው ገጽ ላይ ደረሰ፡፡

‹‹ክፍል ሁለትን በክፍል ሁለት መጽሐፍ ይመልከቱ›› ይላል፡፡ ክፍል ሁለት መጽሐፍ ግን የለውም፤ የት እንዳለም አያውቅም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበትም አልተዘጋጀም፡፡ ስለዚህም እንደወጣ መውረድ ጀመረ፡፡ ያውም በዝግታ ሳይሆን እየተምዘገዘገ፡፡

እናም እኛ በለምለም መስክ ላይ ያለን ፈረሶች፣ አንድ ክፉ ቀን መጥቶ ‹‹ክፍል ሁለትን በሌላ መጽሐፍ›› ቢለንስ? ምን ይውጠናል? ለመሆኑ ክፍል ሁለት የት ነው ያለው? እስካሁን ያሳየን የለም፡፡ እኛ የምናውቀው የየዕለቱን ምዕራፍ ብቻ ነው፡፡ ያንን እናነባለን፣ በእርሱ እንኖራለን፣ ቀጣዩን ምዕራፍ አናውቀውም? ስለዚህም እኛም እንጠይቃለን? እንዲሁ እንዘልቅ ይሆን? ብለን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

የፍቅረኛህን ስሜቶች

የምትረዳባቸው 4ዱ ዘዴዎች

ቅድስት አባተ ከሚኒያፖሊስ

ፍቅርህን የምትገልፅበትን ወሳኝና አመቺ ጊዜ አሳልፈህ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በፍቅረኞች ቀን የበለጠ ፍቅርህን የምትገልፅበትና የምታጠነክርበት ጊዜ ሆኖ ልታገኘውና ይህንንም ዕድል ተጠቅመህበት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን መቼም ቢሆን ልትዘነጋው የማይገባህ ነገር ከአንተ የፍቅር አሰጣጥ ቀጥሎ የእሷ የፍቅር ስሜትና አገላለፅ ምን ይመስላል የሚለውን ልታረጋግጥ ያስፈልጋል፡፡ ፍቅርህን አንተ ብቻ እየገለፅክላት ከእሷ ምንም አይነት ምላሽ ካላገኘህ ወይ በአንተ የፍቅር አሰጣጥ ላይ ወይም ደግሞ በእሷ የፍቅር አመላለስ ላይ ችግር ሊኖር እንደሚችል መጠርጠር አለብህ፡፡ ወይም ደግ እሷ የፍቅር ሰው ላትሆን ትችላለችና ፍቅርን እንዴት መስጠትና መቀበል እንዳለበት ልታስተምራት ይገባል፡፡ ይህ ትልቅ የቤት ስራ ሊሆንብህም ይችላል፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ሰጥቶ በመቀበል ህግጋት ውስጥ የሚተገበር ነገር ነው፡፡ ስለዚህም የእሷንም የፍቅር ስሜት ምን እንደሚመስል ማረጋገጥ አለብህ፡፡ ይህ ደግሞ ለአንተ ያላትን የፍቅር ስሜት የምታይበትና ምን ያህል እንደምታፈቅርህ ትልቁ ማረጋገጫህ ይሆናል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ ሁኔታዎችንና ቴክኒኮችን ልትተገብራቸው ይገባል፡፡ ከእነዚህ ወሳኝ መንገዶች መካከልም የሚከተሉትን በዋናነት ልናነሳቸው እንችላለን፡፡

1. ለአንተ ድርጊቶች አጋርነቷን ማሳየቷአንተን በተለያዩ አጋጣሚዎች የምትንከባከብና በምትሰራቸው ስራዎች ሁሉ እርዳታዋን የምትሰጥህ ከሆነ በትክክልም በውስጧ የፍቅር ምልክት እንዳለ ትረዳለህ፡፡ ለአንተ በሚኖራት አጋርነት ፍቅርህን አግኝታ ጥሩ የፍቅር መልስ እየሰጠችህ እንደሆነ ስለምትገምት ይህ አካሄዷን ልታውቅላት ይገባል፡፡ 2. በአንተ ላይ የራስ መተማመኗን ማሳየቷበየትኛውም አጋጣሚ ቢሆን አንተን የፍቅር አጋሯ አድርጋ ከቆጠረች ምንም አንተ በምትፈራው ሁኔታ ውስጥ እንኳን ቢሆን በራስ በመተማመኗ የፍቅር አገላለጿን አትቀይረውም አትረበሽምም፡፡ በተለይም ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ከአንተ ጋር ሆኖ ቢያገኟት ያለምንም መርበትበት በፍፁም የራስ መተማመን አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ ልታስረዳቸው ስትሞክር ታያለህ፡፡ ይህ ደግሞ ፍቅሯን መግለጿ ብቻ ሳይሆን ለአንተ ያላትን የጠለቀ ታማኝነትንም እያሳየች የመሆኑን ልታውቅ ይገባሃል፡፡ 3. ወደ አንተ ያላት ቅርብ የሆነ አቀራረብሴት ልጅ አንተ የምትሰጣትን ፍቅር አይታ እሷም ለአንተ ፍቅር ምላሽ ውስጧ የተነሳሳና ፍቅሯንም ልትገልጽልህ ስትፈልግ ወደ አንተ በጣም ትጠጋለች፤ እጆችህን ትደባብስሃለች፣ ትከሻህንና ጉንጭህን ታሻሽሃለች፡፡ ባልጠበቀው አጋጣሚም ደስ በሚል ሁኔታ ልትስምህ ትችላለች፡፡ ይህ ደግሞ መመሪያ አካባቢ የፍርሃት ስሜት ካላት ወይም የውስጧ የፍቅር ስሜት በአንዴ የሚገፋፉት ከሆነ በዚህ መልኩ ለአንተ የፍቅር ስሜት እንዳላት ልታረጋግጥልህ ትፈልጋለች፡፡ 4. ጥልቅ የሆነ እይታዋአብራችሁ ሆናችሁ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በምታሳልፉ ጊዜ እሷ አንተ ፊት ሆና የምትናገረውን ነገር እየሰማች አይኖችህን በጥልቀት አፍጥጣ የምታይህ ከሆነ በእይታዎቿ ውስጥ የአይኗና የፊቷ እንቅስቃሴ ፍፁም ትኩረት ሰጥታህ ከመገኘቷም በላይ ውስጧ ያለውን የፍቅር ስሜት ያሳብቅባታል፡፡ ይህ ደግሞ የውስጧን የፍቅር ስሜት በቀላሉ እንድትረዳ ያደርግሃል፡፡ ተጨማሪ 6ቱን ለማንበብ ድረገጻችን ይግቡ።

Nuru Dedefo, ESQ.Attorney at Law & Counselor

- Car Accidents- Work place Injuries- Immigrations- Family Law- Criminal Law

If you have legal issues, you need a lawyer who fights

for your rights. Nuru Dedefo fights for your rights.

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421

(763)-781-5254 (office), (612-559-0489) Cell(763)-781-5279 Fax

Page 10: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 10

ጎረምሶች በልጃገረዶች ላይ

የሚማረኩባቸው 24 ምክንያቶችከሮቤል ሔኖክ1. ሁልጊዜም እነሱ ማራኪ መዓዛ አላቸው፤ ክሬምና ሻምፖ ተቀብተውም ቢሆን እ

ንኳን፤2. ሁልጊዜም ልጃገረዶች ከትከሻችሁ አጠገብ ጭንቅላቶቻቸውን በተፈላጊው ሰዓት

በትከሻዎቻችሁ ትይዩ ስታገኙት የሚፈጠርባችሁ የርህራሄ ስሜት፡፡ 3. ሁልጊዜም ልታቅፏቸው ስትፈልጉ አንገታቸው ለክንዶቻችሁ ተመጣጣኝነት ስ

ላላቸው፡፡ 4. ሊስሟችሁ በዚያን ሰዓት በዓለም ላይ ድንገተኛና ትክክለኛ የሆነውን የማይረሳ ደ

ስታ ስለሚሰጥ፡፡ 5. በሚመገቡበት ጊዜ የሚያሳዩት እርጋታ፣ የሚታይባቸው ዝምታ፣ ማራኪነት፡፡ 6. ሲለባብሱና ሲዘንጡ ብዙ ሰዓት መፍጀታቸው የሚያበሳጭ ቢሆንም፤ በመጨረሻ

ግን በተሻለ ጥራትና ውበት ልዩ ሆነው ስለሚቀርቡ፡፡ 7. ከቤት ውጪ ያለው የአየር ፀባይ መጠን ወደ ዜሮ ዲግሪ የወረደ ቢሆንም እንኳን

ሁልጊዜም ሞቃታማና ፍልቅልቅ፣ የሙቀት መስህብ ስለሀነ፡፡

8. ምንም አይነት ልብስ ይልብሱ የማያምርባቸው የልብስ አይነት የለም፡፡ በሩሲያ ምሳሌያዊ ንግግር ውስጥ ‹‹የ13 ዓመት ልጃገረድ ያደረገችው የባርኔጣ ዝርያ ሁሉ ያምርባታል›› ወይም በአሁኑ ዘመን እንደምናየው የተሰራችው የፀጉር እስታይል ሁሉ… ያጠለቀችው መነፅር ሁሉ… ያንጠለጠለችው ሎቲ ሁሉ… ያደረገችው አንባር ሁሉ…

9. በዚያኛው በኩል ያለውን ህብር የመፍጠር ፍላጎት ያህል ወይም በተሻለ ሁኔታ ክፍተቱን (ጎዶሎውን) የመሙላት እኔነታቸው፡፡

10. ድርድር ሲያካሂዱ የሚያሳዩት ፅሞና እና እርካታ፡፡11. እጆቻችንን መያዝ በፈለጉ ጊዜ እንዴት በቀላሉ ሊያገኟቸው የሚችሉበት ዘዴ፡፡ 12. ፈገግታቸውና አሳሳቃቸው፡፡ 13. ወንዶች በአንድ ነገር ጎበዝ ሆነው ሲሸለሙ ከማንም እንኳን ደስ አለህ ከሚል በር

ካታ ስሞች መሃል የእነሱን ስናገኝ የሚፈጠርብን ስሜት፡፡ 14. ከተዋወቃችኋቸው አንድ ሰዓት ያልሞላ እንኳን ቢሆንም ‹‹ከዚህ በላይ የሚያቃ

ቅር ነገር ባንነጋገር እና በምንግባባቸው ጉዳዮ ላይ ይበልጥ ብናተኩር›› የሚለው አይነት የአቀራረብ ዘዴያቸው፡፡

15. በጣም ጥሩ ነገር ስታደርጉላቸው ደስታቸውን ለመግለፅ የሚጠቀሙበት የአሳሳም ዘዴ፡፡

16. አፈቅርሻለሁ ባልና ሰዓት አይኖቿ ውስጥ የሚንተከተኩው የስሜት እሳት የሚፈጥረው ማግኔታዊ መስህብ፡፡

17. አስተቃቀፋቸው ደስ ሲላቸውም ይሁን ሲያዝኑ እንዴት አደርገው እንደሚያቅፉ፡፡

18. በተለይም ሲያለቅሱ እንዴት አድርገው ነው እቅፋቸው ውስጥ የሚወድቁት፡፡ 19. ይቅርታ የሚጠይቁበት ብልሃትና መንገድ፡፡ 20. ተቆጥተው እንኳን ሊመቷችሁ ሲቃጡ የሚመቱበት ቦታና ልስላሴው ርህራሄ የ

ታከለበት መሆኑ፡፡ 21. ባንቀበለውም እንኳን ላደረጉት ነገር መፀፀታቸውን የሚያሳዩበት መንገድ፡፡22. አትተወኝ፣ አትራቀኝ እፈልግሃለሁ፣ እመኝሃለሁ፣ ላጣህ አልሻም፣ የሚሉባቸው

ዘዴዎች፡፡ 23. አንተ በተራህ አትተዪኝ፣ እፈልግሻለሁ፣ እመኝሻለሁ፣ ላጣሽ አልሻም በምትላቸ

ው ጊዜ ሃሳባቸው ተቃራ ቢሆንም እንኳን የሚቀበሉበት መንገድ፡፡ 24. ዓለምን አካባቢያቸውን፣ ደህንነታቸውን፣ ፍቅራቸውን ለመጠበቅ ሲሉ በሚያፈ

ሱት እንባና በአለቃቀስ ዘይቤአቸው፡፡ ስትወዳቸው ወይም ስትጠላቸው እነርሱ የሚያስቡበት መንገድ አንተን ካጡህ ሞት

ብቻ የሚታያቸው መሆኑን ወይም በተቃራኒው እነሱን ለብቻቸው ጥለሃቸው ለብቻህ ልትሞት መወሰንህ ሆኖ ነው የሚታያቸው፡፡ ምክንያቱም ከአንተ ጋር ፍቅር ከጀመሩ በኋላ ለአንተ ልባቸውን ከከፈቱ በኋላ በህይወትም በሞትም መነጣጠል የለም ብለው ስለሚያምኑ ነው… ትክ ብለህ ስታያቸው በነፍሳቸው መጠን ወይም በዘብራቃ ድምፅ ቃና ቢስ ንግግር እያደረግህም ቢሆን እንኳን ሞቱን የጠበቀ የፍቅር ህብር እየሰጠ ሸካራውን የሚያለሰልስ ልብ ነው ያላቸው፡፡ ልጃገረዶችን ወደ ሚሊዮን በሚጠጉ የተለያዩ ምክንያቶች እናፈቅራቸዋለን፡፡ በአካል ብቻ ሳይሆን በልባችንም ጥልቀት ጭምር፡፡

The First Ethiopian Health & Social

Affairs Website

ትዝብት ከአሜሪካ

ፒያሣ ገበያ ሲመጡ ምንም እንደማያጡ ይተማመኑ

የልጅቷ እምባ ...ከገጽ 7 የዞረእቅድ አድርሷቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ታዲ እመቤት

ጋሻውን እንጂ አካባቢውን አታውቀውም፡፡ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በአክርቴክትነት እንደ

ሚሰራ፣ ጦር ኃይሎች አካባቢ ከእናቱ ጋር እንደሚኖርና የሚያስተምራቸው ሁለት ታናናሾች እንዳሉት፣ አባቱ መሞታቸውን፣ እናቱ ዘወትር እንዲያገባ እንደሚጨቀጭቁት እሱ ደግሞ የቤተሰቡ ነገር እንደሚያስጨንቀው ነው የነገራት፡፡ አምሳለ በዚህ ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ እመቤት ስለ ጋሻው ያወራችው ነገር ሁሉ እውንት ስለመሆኑ ከእርሷ ውጪ ለሌላ አካል መረጃ ስለሌላት ጓደኛዋ ያለቻትን አምና ከመቀበል ውጪ አማራጭ አልነበራትም፡፡ ጋሻው አንድም ሰው ለመተዋወቅ ስለማይፈልግና ‹‹ጓደኛ ፍቅር ያደፈርሳል እንጂ አይጠቅምም›› የሚል አቋም ስለነበረው እመቤት ጓደኛዋን ልታስተዋውቀው- አምሳለም በዚህ አጋጣሚ ጋሻውን ልታየው አልቻለችም፡፡ ስለዚህ ስለርሱ የምትሰማው እመቤት በምትነግራት ወሬ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ እመቤት ቲኬቷ የሚቃጠልበት ጊዜ ደረሰ፡፡ በ3 ወር ውስጥ ለመመለስ ይዛ የነበረውን እቅድ ለማክበር አልቻለችም፡፡ ጋሻውን ተለይታ መሄድ የማይሆን ሆነባት፡፡ ናፍቆቱን የምትችለውም አልመሰላትም፡፡ በዚህ ሳቢያ መወሰን አቅቷት መዋለል ጀመረች፡፡ በዚህ በኩል ጋሻው ተመልሳ እንዳትሄድ ይወተውታታል፡፡ በተለይ ደግሞ በፍቅር መካከል የሚፈጠር ክፍተት ለችግር እንደሚዳርግ በመንገር መለያየታቸው ክፉ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ያስረዳታል፡፡ በሌላ በኩል ቤተሰቦቿ እዚህ መቀመጥ እንደሌለባት ይወተውቷታል፡፡ በተለይ አዲስ ባመጣችው ባህሪና ሁሌም ውጪ ውጪ በማለቷ ገንዘቧን እያባከነች መሆኑ የተሰማቸው እናቷ ቶሎ ወደመጣችበት እንድትመለስ ይጨቀጭቋት ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ያሸነፈው ሃሳብ የጋሻው ሆነ፡፡ እመቤት ወደ ውጪ ተመልሳ የመሄድ ሃሳቧን ሰረዘች፡፡ አሁን ሙሉ ምርጫዋና የወደፊት እቅዷ በጋሻው እጅ ገብቷል፡፡

አብሮነትሁለቱ ጥንዶች በተዋወቁ በ6ኛው ወር ነው አብረው የ

መኖር ሃሳብ ያመጡት፡፡ ጋሻው እመቤትን ቤት ተከራይተው መኖር እንደሚገባቸው ይወተውታት ያዘ፡፡ አራት ዓመት ሰርታ ያመጣችውን 78 ሺ ብር ህይወታቸውን ለመመስረት ሊጠቀሙበት እንደሚገባም ይጨቀጭቃት ጀምሯል፡፡ እመቤት በዚህ ፍጥነት የጠየቃትን አብሮ የመኖር ጥያቄ ለመመለስ ተቸገረች፡፡ በተለይ የጓደኛዋ ተደጋጋ ማስጠንቀቂያ ከቤተሰቦቿ ጋር የፈጠረችው ግጭት ጥቂት ወደ ራሷ እንድታስብ ቢያደርጋትም ከጋሻው ግን የበለጠባት የለም፡፡ ጋሻው የባንክ ቡኳን እሱ ጋር አስቀምጦ ገንዘብ ማውጣት ስትፈልግ ብቻ እንድታወጣ ለማንም ቤተሰብን ጨምሮ ገንዘብ እንዳትሰጥ አድርጓታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመስሪያ ቤት ማህበር ያለው መሆኑንና ለዚያ ቅድሚያ ክፍያ 30 ሺ ብር እንደሚያስፈልግ ነግሯት አውጥታ ሰጥታዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቢቸገሩ 2 ዓመት ብቻ መሆኑን ገልፆላጽ አሁን ግን ቤት ተከራይተው ቢኖሩና ጋብቻቸውን በሚመቻቸው ጊዜ ቢያደርጉት የተሻለ መሆኑን አሳምኗታል፡፡ እመቤት ይህን ሁሉ ስታደርግ ያማከረችው አንድም ሰው እንደሌለ ስታውቅም ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ተወቻቸው፡፡ ሁለት ክፍል ያላት አነስተኛ ቤት ተክለሃይማኖት አካባቢ ተከራዩ፡፡ ለቤቷ የሚያስፈልገውን ዕቃ በሙሉ ከ15 ሺ ብር በላይ አውጥታ የገዛችው እሷ ናት፡፡ በአንድ ግቢ ውስጥ ያለው ቤት ከርሷ ጋር ሌሎች ሁለት ተከራዮችን የያዘ ነው፡፡ መንደር ውስጥ ለውስጥ የገባ ቢሆንም ቤቱን ግን ሁለቱም ወደውታል፡፡ ጋሻውና እመቤት አብረው መኖር የጀመሩት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ የእመቤት ቤተሰቦች የልጃቸውን ከጉዞ መቅረትና ወንድ ወድዳ ቤት ተከራይታ መውጣት ፈፅሞ ያልደገፉት ነገር በመሆኑ በተለይ አባቷ አይኗን ሊያዩት እንደማይፈቅዱ ተናግረዋል፡፡ እሷም በፍላጎቷ ማንም መግባት የሌለበት መሆኑን በመግለፅ ነው ከቤት የወጣችው፡፡ እናትየው ግን አላስችል ስላላቸው በተደጋጋሚ ጊዜ ደውለውላት አልፎ አልፎ አባቷ በሌሉ ጊዜ እየመጣች ታያቸዋለች፡፡ ጋሻው ቀን ቀን ወደ ስራ ብሎ ይሄድና ምሽት ላይ ይመታለ፡፡ አብሯት ያድራል፡፡ ህይወታቸውን መምራት ጀመሩ፡፡ ሁለት ወር ያህል ከኖሩ በኋላ ለምን እንደማይጋቡ ደጋግማ ትጠይቀው ነበር፡፡ በዚሁ ላይ አንድም ቀን ጓደኞቹንና እናቱን ሊያስተዋውቃት ያለማሰቡ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ መጣር ጀመረች፡፡ ጋሻው እሷን ለሁሉም የሚያስተዋውቃት ድንገት ሁሉንም ሊያስደንቅ በሚችል ሁኔታ እንደሆነ እስከዚያው ግን አንድም ሰው እንዲያውቅበት የማይፈልገው ፍቅራቸው የሰው አፍ ውስጥ እንዳይገባ ፈልጎ መሆኑን በመንገር ይሸነግላት ነበር፡፡

በሌላ በኩል ያስቀመጠችው ገንዘብ በየጊዜው እየተመዘዘ ማለቁም እመቤትን አስጨንቋታል፡፡ ብዙ ገንዘብ

ወጪ አድርጋ ቤቱን ማቋቋሟ ሳያንስ በሰበብ አስባቡ ገንዘብ እንድትሰጠው የሚጠይቃትን ጋሻውን ማስተናገድ በዝቶባታል፡፡ የወሰደው 30 ሺ ብር ሳያንስ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረ ገንዘብ ከባንክ እንድታወጣ ያደርጋት ነበር፡፡ የቤት አስቤዛ የምትገዛው እሷ ናት፡፡ እሱ ለጊዜው እናትና ታናናሾቹን እየረዳ በመሆኑ መስመር እስኪያሲዛቸው እንድትታገሰው ነግሯት ስለነበር ልትጫነው አልፈለገችም፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም ቤቱን እንድትሞላው- ሁሌም ደግሳ እንድትጠብቀው- ሁሉም ቢራና ወይን ከቤት እንዳይጠፋ መፈለጉ የልጅቷን የገንዘብ አቅም አመናመነው፡፡ ሶስት ወር ሲያልፋት ቢያንስ ቀለበት ማሰር እንዳለባቸው ትወተውተው ጀመረ፡፡ ለዚህም ምላሻ አላጣም፡፡ ቀለበት ማድረግ ብቻውን ዋጋ የሌለው መሆኑንና በቅርቡ ጋብቻቸውን መፈፀማቸው ላቀር ሌላ ወጪ መፍጠር የሌለባቸው መሆኑን ይነግራታል፡፡ ሁሌም ለምትጠይቀው ጥያቄ አሳማኝ ምላሽ አያጣምና በተቻለ መጠን እሱን ለማስቀየም ለማትፈልገው እመቤት ነገሩን በትዕግስትና በተስፋ መጠበቅ ብቻ ነበር አማራጯ፡፡

6 ወራት 1998 ጥቅምትእመቤት ጓደኛዋን ፈለገቻት፡፡ በጋሻው የተነሳ የራቀቻ

ትን ጋሻው ፈጽሞ እንዳታገኛት ብሎ ያለያያትን ጓደኛዋን ፈለገቻት፡፡ አሁን ነገሮች በፈለገችው መንገድ እየተጓዙ አይደሉም፡፡ በባንክ አካውንቷ የቀራት ገንዘብ 20 ሺ ብር ብቻ ነው፡፡ በ6 ወር ውስጥ ከ50 ሺ ብር በላይ አውጥታለች፡፡ ይህን ገንዘብ ለማግኘት 4 ዓመት ፈጅቶባታል፡፡ ጋሻው ገንዘብ የሚበቃው ሰው አይደለም፡፡ ተቃውሞ ስታቀርብ ሁሌም ያኮርፋል፡፡ ከእኔ ገንዘብሽን ታስቀድሚያለሽ ይታላል፡፡ በዚህ ትሳቀቃለች፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የገንዘቡ ማለቅ አያሳስበውም፡፡ ህይወታቸው የሚመራው በርሷ ገንዘብ ሳይሆን በርሱ ደመወዝ እንደሆነ ደጋግሞ ቢነግራትም አንድም ቀን ሻሽ እንኳን ገዝቶላት አያውቅም፡፡ ውጪ ከርሷ ጋር ለመታየት ይፈራል፡፡ ጓደኞቹን፣ እናቱን አካባቢውን አያስተዋውቃትም፡፡ አብረው የሚወጡት ምሽት ላይ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ቀን ቀን ስራ እያለ ከእሁድ እስከ እሁድ ቤት አይገኝም፡፡ ምሽት ላይ ነው አብሯት የሚሆነው፡፡ እሷ ጋር ሲመጣ ሞባይሉን ያጠፋዋል፡፡ በየ15 ቀኑ ፊልድ እያለ ለአንድ ሳምንት ቆይቶ ይመለሳል፡፡ በእነዚያ ጊዜያት ሁሉ ስልኩ ይዘጋል፡፡ ከኔትዎርክ ውጪ ስለሆንኩ ነው ይላታል፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ፀባዩ እየተለወጠ መጥቷል፡፡ እንዳትጸንስ ሁሌም ቢሆን ያስጠነቅቃታል፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ልቧ ውስጥ ከፊል ጥርጣሬ እያሳደረባት ሲመጣ ጓደኛዋን ፈልጋ አግኝታ አዋየቻት፡፡

አሁን ከእንቅልፏ መባነን ጀመረች፡፡ ጓደኛዋ ሊሆን ይችላል ያለችውን ነገር ሁሉ ነገረቻት፡፡ ይህ ሰው ምናልባት እያጭበረበራት እንደሆነ ለማወቅ ማድረግ ያለባትን ሁሉ አስረዳቻት፡፡ በተለይ እሰራበታለሁ የሚልበትን መስሪያ ቤት በመጠየቅ እንድትተባበራት አማከረቻት፡፡ በዚህ መልኩ እመቤት በጋሻው ላይ ጥናት ማድረግ ጀመረች፡፡ አድርጋ የማታውቀውን ነገር ማድረግ ጀመረች፡፡ ጋሻው ለሽንት ከቤት ሲወጣ ቦርሳውን መበርበር ጀመረች፡፡ የመስሪያ ቤት መታወቂያ የለም፡፡ ነገር ግን የአንዲት ሴት ፎቶ ግራፍ አለ፡፡ በግምት 2 ዓመት የሚሆነው ወንድ ልጅ ያቀፈች ወጣት ነች፡፡ እመቤት ደነገጠች፡፡ ነገር ግን ምናልባት ዘመዱ ልትሆን ትችላለች ብላም አሰበች፡፡ የቀበሌ መታወቂያውን አየችው፡፡ ነዋሪነቱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 18 ውስጥ መሆኑን ይናገራል፡፡ ከቤተሰቦቼ ጋር ጦር ኃይሎች እኖራለሁ ያለው ሀሰት መሆኑን ጠርጥራለች፡፡ ይህን አድራሻ በወረቀት ላይ መዘገበችና ያዘች፡፡ በማግስቱ ለጓደኛዋ ነገረቻት፡፡ ቀስ በቀስ ጋሻው እውነተኛ ሰው እንዳልሆነ ለመረዳት የቻለችበትን መረጃዎች አገነች፡፡ ስልኩን ሳያይ አውጥታ በውስጡ የተቀዱትን የቪዲዮ ምስሎች ተመለከተች፡፡ በፎቶ ግራፍ ላያ ያየቻትን ሴት አይነት ሴት አለች፡፡ አንድ ህፃን ልጅ በተደጋጋሚ ጊዜ ተቀርጿል፡፡ ደነገጠች፡፡

ጓደኛዋ ይህን ካወቀች በኋላ እመቤት ጋሻውን ማውጣጣት እንዳለባት አሰበችና ተመካከሩ፡፡ አንደ ቀን ጋሻውን ‹‹ለምን ከሰዎች ጋር እንደማታስተዋውቀኝ ገብቶኛል፡፡ ልጅና ትዳር እንዳለህ ደርሼበታለሁ፡፡ ስለዚህ ገንዘቤን መልስልኝ›› እንድትለው ነገረቻት፡፡

ህዳር 17/1998ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ በር ተንኳኳ፡፡ ቀኑን ሙሉ

ቤት ተቀምጣ በሃሳብ ስትብሰከሰክ ለዋለችው ለእመቤት ይህ ምሽት የመጨረሻ ነው፡፡ ውስጧ ተበሳጭቷል፡፡ የተለየ ስሜት ተሰምቷታል፡፡ የመከዳት ስሜት ተሰምቷታል፡፡ በሀሰት የሚሸነግላት፣ የሚያታልላት ልቧን በሰረቀበት የማባበያና የማሳመኛ ቃሉ ሌላ እንዳታስብ አድርጎ አዕምሮዋን የጋረደባት እጅግ ስለምትወደውና ሌላ ለማሰብ ራሷን ስላላዘጋጀች ነበር፡፡ አሁን ግን ቆም ብላ ስታስብ የሆነው ሁሉ ተረት ተረት መስሎ ታያት፡፡ ስለዚህ ዛሬ እውነቱን የምታውቅበት ዕለት ነው፡፡ ጋሻው ወደ ቤት ገባ፡፡ እንደተለመደ

ው እቅፍ አድርጎ ሳማት፡፡ መጠት መጠጥ ሸቷታል፡፡ ለምን እንደመጣ ጠየቀችው፡፡ የሆኑ ከውጭ የመጡ የመስሪያ ቤት እንግዶችን ሲያስተናግድ ቢራ መጠጣቱን ነገራትት፡ ከዚህ በኋላ ነበር ጦርነቱ የተጀመረው፡፡

ስራ የሌለው መሆኑንና እስካሁንም የተጫወተባት እንደሚበቃ ነገር ግን የወሰደባትን ገንዘብ ሁሉ እንዲመልስላት ካልሆነ ግን ለሚስቱ እንደምትደውልላት አስጠነቀቀችው፡፡ ቱግ አለ፡፡ ይህ ወሬ ያወራላት ሀሰተኛ እነርሱን ለመለያየት የፈለገ ሰው መሆኑን ነገራት፡፡ ነገር ግን እራሷ ማወቋንና ከሞባይሉ ውስጥ ያየችውን ቪዲዮ እንዲሁም ቦርሳው ውስጥ ያየችውን ፎቶግራፍ ሁሉ ነገረችው፡፡ ቦርሳውን ከፍቶ እንዲያሳያትና ሞባይሉንም አውጥቶ ቪዲዮውን የማን እንደሆነ እንዲገልፅላት ጠየቀችው፡፡ ተቆጣ፡፡ የእርሱን ሞባይልና ቦርሳ ለመጎርጎር ፈፅሞ መብት የሌላት መሆኑንና ቢያደርገውም የሚያገባት ነገር የሌለ መሆኑን ገለፀላት፡፡ ፀብ ተቀሰቀሰ፡፡ እመቤት ህይወቷን ማበላሸቱንና ከዚህ በኋላ ምንም አይነት ግንኙነት እንዲኖራት የማትፈልግ መሆኑን ነግራ ሌላ ግንኙነት እንዳለው ያንንም የሰራትን ሄዳ በመንገር እንደምትበጠብጥበት ስትነግረው አነቃት፡፡ መታገል ጀመሩ፡፡

እመቤት ራሷን መቆጣጠር ተስኗት መጮኽ ጀመረች፡፡ ልትቧጭረው ፈለገች፡፡ እሱም ይደብድባት ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ ባላሰበችው ሁኔታ አጠገቧ ያገኘችውን የኒኬል ብርጭቆ ወርውራ ስትመታው እጇን ጠምዝዞ ጣላት፡፡ አጠገቡ ያገኘውን የሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ ሲይዝ ልትቀማው ታገለችው፡፡ በጩኸት ሰው መጣራት ጀመረች፡፡ አፏን አፍኖ ወደ ታች የሰነዘረው ቢላዋ ዘወር ስትል ትከሻዋ ላይ ተሰካ፡፡ ጮኸችና ወደቀች፡፤ ግርግሩን የሰሙ ሰዎች ተሯሩጠው ወደበሩ ሲደርሱና እሱ ከፍቶ ሲወጣ አንድ ሆነ፡፡ ድንገት መሬት ላይ ወድቃ በደም ተበክላ ያዩዋት የቤቱ አከራይ ‹‹ገድሏታል›› ብለው ሲጮኹ ጋሻው ከአካባቢው ተፈትልኮ ጠፋ፡፡ ሰዎች በዚህ ምሽት ተሯሩጠው ቢፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ እመቤትን ከወደቀችበት አንስተው በኮንትራት ታክሲ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወሰዷት፡፡ ሐኪሞች በድንገተኛ ክፍል ከእጇ ላይ የሚፈሰው ደም ከቆመላት በኋላ አልጋ አስያዟት፡፡ ህይወቷ ተርፏል፡፡

ከሳምንት በኋላፖሊስ በደረሰው መረጃ መሰረት ባደረገው ማጣራት

ጋሻው የሚኖርበትን አድራሻ ከእመቤት ጓደኛ አግኝቷል፡፡ በስልኩ ሲደወል ስልኩ የተዘጋ መሆኑን ቢገልፅም ፖሊስ ግን የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ይዞ ያለበት በአድራሻ ድረስ ሄዶ ቤቱን አገኘው፡፡ የሚኖርበት ቤት ውስጥ አያቱ አሉ፡፡ ሰሞኑን መጥቶ እንደማያውቅ የሄደበትን እንደማያውቁ ተናገሩ፡፡ ጋሻው ስራ የለውም፡፡ አልፎ አልፎ ደላልነት ይሞክራል፡፡ ከአንዲት ሴት ወልዶ እሷ አሁን አረብ አገር እየሰራች ነው፡፡ ተጋብተው ይኖሩ የነበረ ሲሆን እሷ ወደ ውጭ ስትሄድ ነው ወደ አያቱ ቤት የተመለሰው፡፡ ልጁን እያሳደገ ነው፡፡ ልጅቷ ከዓመት በኋላ ተመልሳ ትመጣለች፡፡ ህጋዊ የጋብቻ ወረቀትም ነበረው፡፡

ከ15 ቀናት ክትትል በኋላ ፖሊስ በጥቆማ ምሽት ላይ ወደ ቤቱ ሲመጣ ጋሻውን በቁጥጥር ስር አዋለው፡፡ በወቅቱም የእመቤትን የባንክ ደብተር ካስቀመጠበት እንዲያመጣ አደረገው፡፡ በመግደል ሙከራ ወንጀል ክስ የቀረበበት ጋሻው ከዚህ በተጨማሪም በማታለልና በማጭበርበር የሰው ገንዘብን ለራስ ጥቅም በማዋል ተከሷል፡፡ በህይወት የተረፈችው እመቤት ጋሻው እስር ቤት ከገባ በኋላ የሆነውን ነገር ሁሉ አረብ አገር ላለችው ሚስቱ ስልኳን ፈላልጋ ደውላ ነግራታለች፡፡ ልጅቷ ባለችበት ሆና ጋሻው የሚባል ባል እንደሌላትና አገሯም እንደማትመጣ ልጇን ግን እንደምትረዳ ለቤተሰቦቿ ነግራቸዋለች፡፡ ቤተሰቦቿም የተፈፀመውን ታሪክ አውቀዋል፡፡ ጋሻው በፈፀመው ወንጀል እስር ቤት ቢገባም እመቤት ከአካል ጉዳት ባሻገር የማይጠገን የህሊናና የሞራል ጉዳት ደርሶባታል፡፡ ከቤተሰቦቿ ጋር አብራ መኖር ብትጀምርም የጥፋተኝነት ስሜቱ ጠንቶበት ነበርና ከጓደኛዋ ጋር መኖር መርጣለች፡፡ በፍርድ ቤት የጋሻው ጉዳይ በመታየት ላይ ሳለ ነበር ወደ ውጭ ሃገር የተመለሰችው፡፡ የቀራትን 20 ሺ ለዚሁ ፕሮሰስ አውላ ሌሎች ብዙ ዓመታትን ጉልበቷን እየገበረች ብር ለማጠራቀም ይህችን ሀገር ጥላ ሄደች፡፡ አምሳለ እመቤት ተመልሳ ወደዚህች አገር ትመለሳለች የሚል ተስፋ የላትም፡፡ ምናልባትም ዛሬም ድረስ ይህችን አገር አላየቻት ይሆናል፡፡ አጭበርባሪው ግለሰብ ግን በወህኒ ቤት ለሰራቸው ተደራራቢ ወንጀሎች ፍርዱን እየተቀበለ ነው፡፡ ምናልባት ሚስቱ ስትመጣ በጋብቻ ላይ በመማገጥ ወንጀል ክስ ልትመሰርትበት ወይም ህሊናው ይቅጣው ብላ ልትተወው ትችል ይሆናል፡፡ ያ ታሪክ ዛሬ ቀላል ቢመስልም በተጎጂዎቹ ሴቶች ላይ የጣለው ጠባሳ ግን ምናልባትም የህይወት ዘመናቸውን ሙሉ ይከተላቸው ይሆናል፡፡

Page 11: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 11

Page 12: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 12

ረመዷን.... ከገጽ 3 የዞረ

የሚያሸንፉበት እድል ያገኛሉ፤በስነ-ምግባርም ጥሩ ይሆናሉ በረመዳን ወደ አላህ ተመላሾች ይበዛሉ፣መስጂዶችም ይሞላሉ፤ ረመዷን የዚክር ማብዛት፣የሰላትና የቂያም ወር ነው፣ሃሳቡን አሳምሮ፣ኒያውን አስተካክሎ ብዙ የቆመ ገደብ የለሽ ምንዳውን ያፍሳል፡፡ረሱላችን(ሰ.ዐ.ወ) ረመዷንን በኢማንና አጅሩን በአላህ ላይ በመተሳሰብ የጾመ(የቆመ)ያለፈው ሀጢያቱ ይማርለታል ብለዋል፡፡ የረመዳን የመጀመሪዎቹ አስሩ ቀናት የራህመት(የእዝነት)፣መሀከለኛው የመግፊራ(የምህረት)፣ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶች ኢትቁን ሚነናር(ከእሳት ነጻ የመውጫ) ቀናቶች ናቸው፡፡ አላህ ከሚጠቀሙት ያድርገን!

መፆም ግዴታ የሚሆንባቸዉ፤ ሙስሊም የሆነ፤ አዕምሮ ሙሉ ጤነኛ የሆነ፤ መንገደኛ ያልሆነ፤ ለአቅመ አዳም(ሃዋ የደረሱ)

መፆም ግዴታ የማይሆንባቸዉ• ሙስሊም ያልሆነ፤ • የአዕምሮ በሽተኛ• መንገደኛ (ሙሳፍር) ፤ • ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች• የመዳን ተስፋ የሌላቸዉ፤ በእድሜ የገፉ ሽማግሌዎችና አ

ሮጊቶች እንዲሁም የአልጋ ቁራኛ በሽተኞች• የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ነፍሰ-ጡር ሴቶች(በራሳቸ

ዉና በጽንሱ ላይ አደጋ የሚያስከትል ከሆነ)-ቀዳ ይኖረዋል• በወር አበበ ላይ ያለች ሴት-ቀዳ ያለባት• ከወሊድ ደም ያልፀዳች እናት-ቀዳ ያለባት ፆም የሚያበላ

ሹ ነገሮች፤ • ምግባዊ ይዘት ባይኖረዉም ሆን ተብሎ ወደ ሆድ ዉስጥ የገባ ነገር ሁሉ

• ሆን ብሎና ፈልጎ ማስታወክ• ፆም ዉሎ ሳለ በቀኑ ማብቅያ ላይ ቢሆንም የወር አበባ

መታየት• በመነካካት፤በማየት፤በመተሸሸትም ሆነ በመሳሳም የብል

ት ዘር ፈሳሽ መፍሰስና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ ስለዚህ ፆማችን ከሚያበላሹ ነገሮችን በተለይ አይናችን ከሀራም መቆጦብና ካላስፈላጊ ቦታዎች ራሳችንን አርቀን መልካም ስራዎችን በመስራት ረመዳንን እናሳልፍ

ከረመዷን ገበያዎች…*ቁርኣን *ዱኣ * ሰደቃ *ተራዊህ *ተውባህ ሌሎችም... ረመዳን ለሙስሊም ኡማ የአመቱ ትልቅ የኸይር ገበያ ፤አላ

ህ ለኡማ የሰጠው ሽልማት ነዉ፡፡በዚህ ወር ዉስጥ የሚሰራ ስራ ሌሎች ወራቶች ዉስጥ ከሚሰሩ ስራዎች ጋር እኩል አይደለም፡ በ70 እጠፍ ብልጫ አለው፡ አንድ የሱና ሰላት ከሌላ ወር የግዴታ ሰላት ጋር እኩል ናት፡፡ አንድ የግዴታ ሰላት ደግሞ ከሌላ ወር 70 ግዴታ ሰላት ጋር እኩል ናት፡፡ እንዲሁም ቁርዓን መቅራት፣ዱዓ፣ሰደቃ፣ ተራዊህና የመሳሰሉት ሁሉም ምንዳቸዉ እጥፍ ድርብ ነዉ፡፡ የረመዳን ገበያ በዐመት አንዴ የሚገኝ ነውና ነገ ከነገ በስቲያ እያልን ረመዳን እንዳያመልጠን!!

ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት

የነዚህን አስር የረመዳን ቀናት በተለይም ለሊቶች ትልቅ ደረጃ የሚሰጣቸው ስለመሆኑ የተለያዩ ነጥቦችን ማንሳት ቢቻልም ዋና ዋናዎቹን ለመጠቆም ያህል፡- የረመዳን ወር ትልቅ ወር መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ስለ ትልቅነቱም ብዙ ሳንሰማ ወይም ሳናነብ አልቀንም፡፡የረመዳን ወር የላቀ ትልቅ ወር እንደመሆኑ ሁላ ከቀናቶቹና ከለሊቶቹ የመጨረሻዎቹ አስሩ ለየት ያለ ቦታ ሊሰጣቸው የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚህን አስርት የረመዳን ቀናት በተለይም ለሊቶች ትልቅ ደረጃ ልንሰጠቸው እንደሚገባ የሚያመለክቱ የተወሰኑ ነጥቦችን በአጭሩም ቢሆን መጥቀስ አስፈላጊ ነው፡፡

አንደኛ፡- የአላህ መልዕክተኛ በነዚህ አስርት ቀናት እና ለሊቶች የነበራቸው የዒባዳ(የአምልኮ)ሁኔታ የምዕመናን እናት ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ትገልጸዋለች፡፡ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ (በዒባዳ) ላይ ይተጉ ነበር›› መልዕክተኛው ከለሊቱ አብዛኛውን ክፍል ከእንቅልፍ በመራቅ ህያው ያደርጉት ነበር፡፡ አሁንም ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ብላለች፡፡‹‹የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ሲገባ ለሊቱን በዒባዳ ላይ በማሳለፍ ህያው ያደርጉ፣ ቤተሰባቸውን ያነቃቁ (ይቀሰቅሱ) ፣ ቀበቷቸውን በማጥበቅ ይተጉ ነበር፡፡›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ በሐዲሱ ውሰጥ ‹‹ቀበቷቸውን ያጠብቁ ነበር›› በሚል የተጠቀሰውን ቃል

በተመለከተ ብዙ የሐዲስ ተንታኞች እንዳሉት“ለማለት የተፈለገው በከፍተኛ ሁኔታ በዒባዳ ከመጠመዳቸ

ው የተነሳከሴቶቻቸው ይርቁ ነበር ለማለት ነው’’ ፡፡

ሁለተኛ፡- የእነዚህን አስር ቀናት እና ለሊቶች ትልቅነት የሚያሳየን በውስጣቸው ‹‹ለይለተል ቀድር›› የተባለችው ለሊት መኖር ነው፡፡ ይህች ለሊት ከሌሎች የምትለይበት ብዙ መለያዎች ያላት ስትሆን ከነርሱም መካከል፡-

1. ቁርአን የወረደባት ለሊት መሆኗ2. ከአንደ ሺህ ወራት የምትበልጥ መሆኗ3. የተባረከች መሆኗ4. መላኢካው ጅብሪል መልዕክትን ከአላህ ይዞ በብዛት የ

ሚወርድባት መሆኗ5. ሰዎች በከፍተኛ አምልኮ ውሰጥ የሚገቡ ከመሆኑ አንፃር

ከእሳት ሰሊም ወይም ነፃ የሚወጡባት ለሊት መሆኗ6. በዚህች ለሊት አላህ ምንዳውን እንደሚከፍለው በእርግ

ጠኝነት በማመን እንዲሁም ከይዩልኝ እና መሰል ዱንያዊ ፍሊጐቶች ርቆ ሰላትን መስገድ

ያበዛ ወንጀሉ የሚታበስ መሆኑ ነው፡፡ሶስተኛው፡- በእነዚህ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ መግባት የመል

ዕክተኛው ሱና ነው፡፡ ኢዕቲካፍ ማለት እራስን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ መዘውተር ነው፡፡

እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ብላለች፡፡ ‹‹ነብዩ እስኪሞቱ ድረስ ከረመዳን የመጨረሻዎቹን አስርት ቀናት እራሳቸውን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ ይዘወትሩ ነበር፡፡›› ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት፡፡

በሰላም ደርሰው ጾማቸውን ከሚቀበላቸው ሰዎች አላህ ያድርገን አሚን!!! zehabesha.com

የአድራሻ ለውጥሚሚ ወደ አዲሱ ሳሎኗ ገብታ

የተለመደውን አገልግሎት እየሰጠች ነው።

አዲሱ አድራሻችን ሚድዌይ (ሴንትፖል) ከሬንቦ ጀርባ ዳንስ

ስቱዲዮ አጠገብ ነው። ይምጡ!

Page 13: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 13

ስታዲየም .... ከገጽ 21 የዞረ

ታላላቅ ክለቦች መሐል የሚጠቀምበት ኮረንቲያስ ፓውሊስታ የተሰኘው ክለብ ነው፡፡ 4 ሚሊዮን የሚጠጋው የሳኦፓ

ውሎ ነዋሪ ስታዲየሙን ከቦታል፡፡ 6,000 ሠራተኞች በግንባታው ላይ የተሰማሩ ሲሆን፤ ከ100 በላይ ሠራተኞች ስታዲየሙ ዘመናዊነት እንዲላበስ አድርገዋል፡፡ በ2014 የተሰራው ስታዲየም 65,807 ተመልካች ያስተናግዳል፡፡ ብራዚል ከክሮሽያ፣ ሆላንድ ከቺሊ፣ ዑራጓይ ከእንግሊዝ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ ከቤልጂየም የ2ኛ ዙርና 1 ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን ያስተናግዳል፡፡

6. አሬና ፎንቴኖቫ፡ - እ.ኤ.አ በ1951 የተገነባ ሲሆን፤ ኦክታቪዮ ማንጋቤይራ ይሰኝ ነበር፡፡ አሁን ግን ለ2014 የአለም ዋንጫ ተስተካክሎ አሬና ፎንቴኖቫ ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ሳልቫዶር በተሰኘው ከተማ ውስጥ የአለም ዋንጫ ጨዋታ ሲካሄድ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ከህዳር 2007-2010 ተዘግቶም ቆይቷል፡፡ 52,048 ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፤ ስፔን ከሆላንድ፣ ጀርመን ከፖርቱጋል፣ ስዊዘርላንድ ከፈረንሳይ፣ ቦስኒያ ከኢራን እንዲሁም የ2ኛው ዙር ጨዋታና 1 ሩብ ፍፃሜ ግጥሚያን ያስተናግዳል፡፡

7. አሬና ፓንታል፡ - 39‚859 ተመልካች የመያዝ አቅም አለው፡፡ ስታዲየሙ ከአለም ዋንጫው ጨዋታው ውጪ ኢግዚቢሽንና የንግድ ባዛር ይካሄድበታል፡፡ ‹ሜክሲቶና ኦፔራሪዮ› የተባሉ ክለቦች በስታዲየሙ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ቺሊ ከአውስትራሊያ፣ ሩሲያ ከኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ናይጄሪያ ከቦስኒያ፣ ጃፓን ከኮሎምቢያ የሚያደርጉት የዓለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታን ያስተናግዳል፡፡ ስታዲየሙ ኦ.ቬራዳኦ ‹‹አረንጓዴው ሜዳ›› ተብሎ በህዝቡ ዘንድ ይጠራል፡፡

8. አሬና ፐርናምቡኮ፦ ኮትድቯር ከጃፓን፣ ጣሊያን ከኮስታሪካ፣ ክሮሺያ ከሜክሲኮ፣ አሜሪካ ከጀርመን እና አንድ የ2ኛ ዙር ጨዋታ ይስተናገድበታል፡፡ ከ64 አመት በፊት በ1950 የተካሄደውን የብራዚል የአለም ዋንጫን አስተናግዷል፡፡ ሬስቶራንት፣ ሲኒማ ቤትና ሱቆች ተካተውበታል፡፡ 42‚583 ተመልካቾችን ይይዛል፡፡ ከጉ

ኢራራፒስ አየር ማረፊያ 19 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ስታዲየሙ ሬኪቭ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡

9. አሬና ባይክሳዳ፦ በ1914 ሲመሰረት ስታዲዮ ጆአኪም አሜሪካ ይባል የነበረ ሲሆን፤ አሁን በድጋሚ በ1999 ሲታደስ ስሙ ወደ ‹‹አሬና ባይክሰዳ›› ተዛውሯል፡፡ በኩርቲባ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ይኸው ስታዲየም 38‚533 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው፡፡ አትሌቲኮ ፓሬኔስ ክለብ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ኢራን ከናይጄሪያ፣ ሆንዱራስ ከኢኳዶር፣ አውስትራሊያ ከስፔን፣ አልጄሪያ ከሩሲያ ይጫወቱበታል፡፡

10. ስታዲዮ ካስቴላኦ፦ ፎርታሌዛ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ የ2010 ፊፋ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የተካሄደበት ሲሆን፤ ኡራጓይ ከኮስታሪካ፣ ብራዚል ከአሜሪካ፣ ጀርመን ከጋና፣ ግሪክ ከኮትዲቯር እንዲሁም ከ2ኛው ዙርና ከሩብ ፍፃሜ አንድ አንድ ጨዋታ ይካሄድበታል፡፡ በፎርታሌዛ ከተማ 2 ክለቦች ይገኛሉ፡፡ ስታዲየሙ በ1973 ሲገነባ ገቨርናዶር ፕላሲዶ ካስቴሎ የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን፤ 1900 መኪና ማቆሚያ ፓርክ አለው፡፡ ሲኒማ ቤት፣ ሆቴልና የኦሎምፒክ ማዕከልም አለው፡፡ 60‚348 ህዝብ ይይዛል፡፡

11. ስታድዮ ዳስ ዱናስ፦ በናታል ከተማ የሚገኘው ይኸው ስታዲየም ሜክሲኮ ከካሜሩን፣ ጋና ከአሜሪካ፣ ጃፓን ከግሪክ፣ ጣሊያን ከፓራጓይ የሚያደርጓቸውን የምድብ ጨዋታዎች ያስተናግዳል፡፡ ሙሉ መጠሪያው ስታዲዮ ክላውዲዮ ዲ. ቫስኮን ሴሎስ በአጠር ባለ ስያሜው ደግሞ ማቻዳኦ ይባላል፡፡ ለከተማው ትልቅ መስህብ የሆነ ሲሆን፤ 38‚958 ተመልካችን ያስተናግዳል፡፡ ስታዲየሙ በ1972 መገንባቱ ይነገራል፡፡ አልከሪም፣ አሜሪካና ኤቢሲ የተሰኙ ክለቦች የኛ መሆን አለበት ብለው ተፋልመውበታል፡፡

12. ስታዲዮ ቤይራ ሪዮ፦ ፖርቶኦሌግሬ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ በግሮሚዮ አጠገብም ይገኛል፡፡ ስታዲየሙ በጣም አስፈሪ የሆኑ የደርቢ ትንቅንቆችን አስተናግዷል፡፡ የኮፓ ሌበርታዶሬስ ፍፃሜና 5 የአለም ዋንጫ ጨዋታን ያስተናግዳል፡፡ 42‚991 ህዝብ የሚይዘው ቤይራ ሪዮ ፈረንሳይ ከሆንዱራንስ፣ አውስትራሊያ ከሆላ

ንድ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ ከአልጄሪያ፣ ናይጄሪያ ከአርጀንቲናና 1 የ2ኛ ዙር ጨዋታ እንዲያስተናግድ ፕሮግራም ተይዞለታል፡፡ በ1969 የተገነባ ሲሆን፤ ይፋዊ ስሙ ‹‹ስታዲዮ ጆሴ ፒንሄሮ ቦርዳ›› ይባል እንደነበር ይነገራል፡፡

የዓለም ዋንጫ .... ከገጽ 21 የዞረበቀጥታ በጐሎቹ ላይ የሚያነጣጥሩ ይሆናል። በቴክኖሎጂው

ኳሷ መስመሩ ላይ ካረፈች ለመሐል ዳኛው ምልክት የምትሰጥ ሲሆን፤ የዳኛው ሰዓት የመንዘርና መብራት ምልክት የሚያሳይ ይሆናል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በ1 ሰከንድ ውስጥ በመሆኑ የጨዋታው ሂደት ካለመቋረጡም በላይ የእግርኳስን ጣዕም እንደማያበላሽ ተነግሮለታል። ከዚህ በተጨማሪ የብራዚል የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ለ12 ስታዲየሞች እደሳና ግንባታ 3.5 ቢሊየን ዶላር ወጪ ያደረገ ሲሆን፤ 600 ሚሊየን ዶላር ብቻ ለማራካኛ ስታዲየም ዕደሳ ወጪ ተደርጓል። 16 ቢሊየን ዶላር አለም ዋንጫውን ለማዘጋጀት የብራዚል መንግስት ያወጣው ወጪ ሲሆን፤ በርካታ ብራዚላውያንን ይህን በይፋ ተቃውመዋል። ለ64ቱ ጨዋታዎች 3.3 ሚሊየን የመግቢያ ቲኬቶች መዘጋጀታቸውን የገለፀው ፊፋ ደግሞ ውድድሩ በሰላም እንደሚጠናቀቅ ያለውን ተስፋ ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ አወዛጋቢው ዦዜ ሞውሪንሆ በበኩላቸው ከየምድቡ የሚያልፉትን ሁለት- ሁለት ሐገሮች ገምተዋል። በዚህ መሰረት ከምድብ 1 ብራዚልና ሜክሲኮ፣ ከምድብ 2 ስፔንና ኔዘርላንድ፣ ከምድብ 3 አይቬሪኮስትና ግሪክ፣ ከምድብ 4 ጣሊያንና እንግሊዝ፣ ከምድብ 5 ፈረንሳይና ስዊዘርላንድ፣ ከምድብ 6 አርጀንቲናና ናይጄሪያ፣ ከምድብ 7 ጀርመንና ፖርቱጋል፣ ከምድብ 8 ሩሲያና ቤልጂየምን ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ ሲሉ ግምታቸውን ሰንዝረዋል።

3.2 ቢሊየን ህዝብ በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከተውና 37 ሚሊዮን ፓውንድ ለአሸናፊው የተመደበበት አለምአቀፋዊው የእግርኳስ ድግስ የአለም ዋንጫ በብራዚል ሲጀመር፤ በመክፈቻው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን ፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና መራሄ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ጨም

ሮ ከ11 በላይ የሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል። ሻምፒዮናው እስከ ሐምሌ 6/2006 በድምቀትና በጉጉት ሲካሄድ ይሰነብታል። በሌላ በኩል ከ32ቱ ሐገራት በጣም ውድ ቡድን የተባሉ 6 ሐገራት ታውቀዋል። በዚህም መሠረት ስፔን 916 ሚሊዮን ዶላር በሚያወጡ ኮከቦቿ ቀዳሚ ሆናለች። ጀርመን በ828 ሚሊየን ዶላር፣ ብራዚል በ689 ሚሊየን ዶላር፣ ፈረንሳይ በ607 ሚሊየን ዶላር፣ አርጀንቲና በ577 ሚሊየን ዶላር፣ ቤልጂየም በ513 ሚሊየን ዶላር በሚያወጡ ስብስባቸው ከ2-6 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የናይኪና አዲዳስ የአለም ዋንጫ ጦርነትበሁለቱ ካምፓኒዎች መሐል የሚደረገው ፉክክር የአሜሪካና ጀ

ርመን ቀዝቃዛ ጦርነት ተብሏል። የጀርመን ትጥቅ አምራች ድርጅት አዲዳስ በዘንድሮው አመት ያገኘው 2.7 ቢሊየን ዶላር ገቢ ከአምናው የአሜሪካን ናይኪ ካምፓኒ 1.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ አንፃር ከፍተኛ ልዩነት የፈጠረ ነው ተብሏል።

ናይኪ ለአለም ዋንጫው 25 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጉ ታውቋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ኔይማር፣ ዌይን ሩኒና ጄራርድ ፒኬ የአዲዳስን ትጥቁን ለብሰው በብራዚሉ የአለም ዋንጫ የሚገኙ ሲሆን፤ ናይኪም ጀርመን፣ ስፔን፣ አርጀንቲናና ኮሎምቢያ ጋር ባለው ስምምነት በአለም ዋንጫው ትጥቁን እያስተዋወቀ ይገኛል።

ሁለቱም ካምፓኒዎች በገበያው ላይ ያላቸውን የበላይነት በማስፋት የየሐገራቸው መኩሪያ ለመሆን ከፍተኛ ሥራ እየሰሩ ነው። በተለይ ናይኪ ካምፓኒ በሊዮኔል ሜሲ ስም ጫማ አሰርቶ ለገበያ በማቅረብ አዲዳስ ላይ ብልጫውን ለመውሰድ እየጣረ ነው። አዲዳስም አርፎ አልተቀመጠም። ከ1970 ጀምሮ ከፊፋ ጋር የነበረውን ውል በማደስ ለቀጣዮቹ 60 ዓመታት የፊፋ ስፖንሰር ለመሆን አድሷል። አዲዳስ ከብራዚሉ የአለም ዋንጫ ጋር በተያያዘ 2.6 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት እንደሚችል እየተነገረለት ይገኛል። ምንጩ ከአሜሪካ የሆነው ናይኪና በጀርመን ውልደቱ የሚጠራው አዲዳስ የሐገራቸውን ስም ከፍ ለማድረግ በዓለም ዋንጫው ላይ እያደረጉ ያለው ትግል 20ኛው የዓለም ዋንጫው ሌላ አጓጊ ክስተት ተደርጐ ተወስዷል።

በችግርዎ ጊዜ አብረንዎት እንቆማለን

Page 14: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 14

ተኩስ በ$25 ብቻ

በቅርቡ ከሃገር ቤት መጥታ በሳሎናችን ሥራ የጀመረችው ስታይሊስት በከተማው በአዳዲስ የሹሩባዋ ዲዛይኗ

ብዙ እየተወራላት ነው፤ መጥተው ይጎብኟት

ካንሰር... ከገጽ 22 የዞረህክምና ያደረጉ ሴቶች በማህፀን ካንሰር የመያዝ ዕድል ሊገ

ጥማቸው ይችላል፡፡ያልተመጣጠነ የሴታሴትነት ጾታዊ ሆርሞን፡- በህክምናው

ቃል ፖሊሳይስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (polycystic ovary syn-drome (PROS)) የሚለው የሆርሞን መዛባት አይነት ሴቶች ያልተመጣጠነ የሴታሴትነት ጾታዊ ሆርሞን (imbalance of female sex hormones) በሚገጥማቸው ጊዜ የሚከሰት ሲሆን ይህም ሁኔታ የወር አበባ ዑደት መዛባትን፣ በዕንቁላል ማፍሪያቸው አካባቢ ውሃ የቋጠረ እብጠትን፣ ለማርገዝ ያለመቻልንና ሌሎችንም የጤና እክሎችን ያስከትላል፡፡ ከሁሉም በላይ ያልተመጣጠነ የሴታሴትነት ፆታዊ ሆርሞን ያለባቸው ሴቶች የማህፀን ካንሰር እንደሚገጥማቸው ተረጋግጧል፡፡

የሆርሞን ተጠቃሚነት፡- አንዳንድ ሴቶች በወር አበባ ጊዜያቸው መዛባት ምክንያት ሆርሞኖችን ለመተካት የሚያስችል የህክምና አይነትን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ የሆርሞን ህክምና ደግሞ የማህፀን ካንሰርን ሊያስከትል እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህም ሆኖ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች በማህፀን ካንሰር የመያዝን አደጋ ይቀንሱታል፡፡

ታሞክሲፊን፡- የጡት ካንሰርን ለመከላከል የሚወሰድ የመድሃኒት አይነት ሲሆን ይህንን የመድሃኒት አይነት ለረዥም ጊዜ የሚጠቀሙ ሴቶች በማህፀን ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

ሌሎች ለማህፀን ካንሰር መከሰት የሚጠቀሱት ምክንያቶችበአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙት ታዋቂ ሳይንቲስቶ

ች ለማህፀን ካንሰር መከሰት በዋነኝነት የሚጠቀሱ መንስኤዎችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥናት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ እስካሁን በተደረጉት ጥናቶች መሰረት ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ያልተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣትና የአ

ካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ያለማድረግ ለማህፀን ካንሰር መከሰት በምክንያትነት የሚጠቀሱ ነጥቦች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የስኳር ህመምተኛ የሆኑ ሴቶች እና በፓፒሎማ ቫይረስ የተጠቁ ሴቶች በማህፀን ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

9. የነጭ የደም ሴል ካንሰርይህ የካንሰር አይነት በነጭ የደም ሴል ውስጥ የሚከሰት ሲሆ

ን የተፈጥሮ የመከላከል አቅምን በማውረድ በቆሽት፣ በጉሮሮ እና በአጥንት መቅኔ ውስጥ ካንሰር እንዲከሰት የሚያደርግ ነው፡፡ ለዚህ የካንሰር አይነት የሚያጋልጡት ምክንያቶች ደግሞ፡-

- የተዳከመ ተፈጥሯዊ የመከላከል አቅም- ዕድሜ፡- በዚህ የካንሰር አይነት ከሚጠቁት ሰዎች መካከል

አብዛኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ነው፡፡- ለፀረ ተክል እና ለፀረ ነፍሳት የሚሆኑ መድሃኒቶችን ለመሳ

ሰሉት ኬሚካሎች መጋለጥ- የተፈጥሮ የመከላከል አቅምን የሚያጠቁ ህመሞችበነጭ የደም ሴል ካንሰርን ለማስወገድ ወይም ለመከላከል የ

ሚያስችል ዘዴ እስካሁን ድረስ አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ኤች.አይ.ቪ የመሳሰሉትን ተፈጥሯዊ የመከላከል አቅምን ከሚያሳጡ በሽታዎች ራስን መጠበቅ ከነጭ የደም ካንሰር ለመታደግ ያስችለናል፡፡ ምክንያቱም ይህንን የካንሰር አይነት ከሚያስከትሉት ህመሞች አንዱ ኤች.አይ.ቪ በመሆኑ ነው፡፡

ማጠቃለያ፡- የአኗኗር ዘይቤን በመቀየርና በማሻሻል፣ የአመጋገብ ለውጥን የመሳሰሉ ቀላል ለውጦችን በመፍጠርና በየጊዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማድረግ ከማንኛውም የካንሰር አይነት ራሳችንን ለመታደግ እንችላለን፡፡ ሴቶችን በማጥቃት ገዳይ ከሆኑት የካንሰር አይነቶች ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ አምስቱን ገዳይ የካንሰር አይነቶች በዚህ መልኩ ካቀረብን ዘንድ ከማህፀን ካንሰር ጋር የሚያያዘውን የማህፀን አፍ

ካንሰር በሚመለከት ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ማህጸን በእንግሊዝኛ (Uterus or womb) ተብሎ የሚጠ

ራ እና በሴቶች ሆድ ውስጥ በፊኛ እና ፊንጢጣ መካከል የሚገኝ ደግሞም ሾጠጥ ያለ ቅርፅ ያለው ኦርጋን ነው፡፡ ይህ አካል ሴቶች በእርግዝና ወቅት ፅንሱ እስኪወለድበት ጊዜ ድረስ የሚያድግበት ነው፡፡

ማህፀን በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም የማህፀን አፍ (Cervix or Mouth of uterus) እና ፅንሱን የሚይዘው አካል (corpus or body) የሚባሉት ናቸው፡፡ ኮርፐስ ማለትም ፅንሱን የሚታቀፈው አካል በማህፀን ገበር እና በጡንቻማ ህብረ ህዋሳት የሚዋቀር ነው። አብዛኛው የማህፀን ካንሰር የሚከሰተው ደግሞ በውስጣቸው ገበር ውስጥ መሆኑን ጥናቶች አረጋግጠውታል፡፡

በአሜሪካ በምትገኘው የኒውዮርክ ግዛት ውስጥ የማህፀን ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ ከሚያጠቁት የካንሰር አይነቶች በ4ኛ ደረጃ የሚገኝ ነው፡፡ በየዓመቱ በዚህ ግዛት ውስጥ ከ3600 ሴቶች በላይ የሚሆኑት በዚህ የካንሰር አይነት እንደሚጠቁና 600 የሚሆኑት ደግሞ እንደሚሞቱ መዘገቡ የማህፀን ካንሰር ምን ያህል አደገኛ መሆኑን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡

10. የማህፀን አፍ ካንሰር የማህፀን አፍ በማህፀን ታችኛው ክፍል የሚገኝ ሲሆን ፈረን

ጆች ይህንን የማህፀን ክፍል አንዳንዴ ዩተረን ሴርቪክስ ብለው ይጠሩታል፡፡ ይህ የማህፀን ክፍል ማህፀንን ከብልት ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡ ለሰውነት አካል ቅርብ የሆነው የማህፀን አፍ ደግሞ ኢንዶሴርቪክስ ተብሎ ይጠራል። ከብልት ቀጥሎ የሚገኘው የማህፀን አፍ አካል ኤክሶ ሰርቪክስ ወይም ኤክቶሰርቪክስ ይባላል፡፡

የማህፀን አፍን ሸፍነው የሚገኙት ሁለቱ ሴል አይነቶች ሶክዋሞሴልስ እና ግላንዱላር ሴልስ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነኚህ ሁለት የሴል አይነቶች የሚገናኙበት ቦታ ደግሞ ትራንስፎርሜ

ሽን ዞግ ተብሎ ይጠራል፡፡ አብዛኛው የማህፀን አፍ ካንሰር የሚከሰተውም በዚሁ ቦታ ላይ ነው፡፡

አብዛኛዎቹ የማህፀን አፍ ካንሰር የሚጀምሩት በማህፀን አፍ ገበር ላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሴሎቹ በድንገት ወደ ካንሰርነት የሚለወጡ አይደሉም፡፡ መደበኛ የሆኑት የካንሰር አይነቶች መጀመሪያ ቀስ በቀስ ወደ ቅድሞ ካንሰርነት መለወጥ ይጀምራሉ፡፡ የህክምና አዋቂዎች ይህንን የሴሎች የቅድመ ካንሰር ለውጥ በተለያየ ስም ይጠሩታል፡፡ ከእነኚህም መገለጫዎች መካከል ሰርቪካል ኢንትራኢፒቴሊያል፣ ስክዋሞስ ኢንትራኢፒቴሊያል ሌዝዩን እና ዳይስፕላዚያ ናቸው፡፡ ይሁንና እነኚህ የቅድመ ካንሰር ለውጦች በምርመራ ማወቅና በህክምና ካንሰር እንዳይዘን መከላከል እንችላለን፡፡

የማህፀን አፍ ካንሰር እና የቅድመ የማህፀን አፍ ካንሰሮች ምን አይነት ገፅታ እንዳላቸው በማይስክሮኮፕ እይታ መረዳት ይቻላል፡፡ የማህፀን አፍ ካንሰር በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የሚከፈል ነው፡፡ እነኚህም ስኩዋሞስ ሴል ካርሲኖማ እና አዴኖካርሲኖማ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከማህፀን አፍ ካንሰሮች ውስጥ ከ80-90 በመቶ የሚሆኑት ስኩዋሞስ ሴል መሆናቸው በጥናት ተረጋግጧል፡፡

ስኩዋሞስ ሴል ካርኪኖማ የተባለው የማህፀን አፍ ካንሰር አይነት ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ኤክሶሰርቪክስ እና ኢንዶሰርቪክስ በሚገናኙበት ቦታ ላይ ነው።

ሌሎቹ የማህፀን አፍ ካንሰሮች ደግሞ ብዙውን ጊዜ አዴኖካርሲኖማ ተብለው የሚታወቁት ናቸው፡፡ የማህፀን አፍ አዴናካርሲኖማስ ላለፉት 20 እና 30 ዓመታት የተለመዱ ሆነዋል፡፡ ይህ የማህፀን አፍ ካንሰር የሚከሰተው ደግሞ ሙከስ ግላንድ ሴልን በሚያመርትበት በአዲኖካርሲሞናስ ውስጥ ነው፡፡

ምንም እንኳን የማህፀን አፍ ካንሰር ብዙውን ጊዜ በቅድመ ካንሰር የለውጥ ሂደት የሚከሰት ቢሆንም የቅድመ ካንሰር ለውጥ ከታየባቸው ሴቶች ውስጥ (ካንሰር... ወደ ገጽ 19 የዞረ)

Page 15: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

ጆሲ ኢን ዘ ሐውስበራሱ የሙዚቃ ስልት በመጫወት ተወዳጅነት ለማትረፍ የ

ቻለ ድምፃዊ ነው፡፡ እስከዛሬም በተለያዩ አገራት እየዞረ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አድናቂዎቹን በማዝናናት ላይ ይገኛል፡፡ ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ጆሲ ኢን ዚ ሃውስ›› (Jossy in the house) የሚል የራሱን ቶክ ሾው የኢቢኤስ የቲቪ ጣቢያ ማቅረብ ከጀመረ በኋላ የፕሮግራሙ ይዘት የብዙ የኢቢኤስ ተመልካቾችን አይን ሊስብ የበቃ ባለሙያ ለመሆን ችሏል፡፡

በተለይ በዚህ ዓመት በትንሣኤ በዓል ላይ አቅርቦት በነበረው ፕሮግራሙ ላይ የቀድሞዋን ተወዳጅ ድምፃዊ ማንአልሞሽ ዲቦ ልጆች ገጥሟቸው በነበረው የህይወት ፈተና ዙሪያ በሰራው ዘጋቢ ፊልም ምክንያት ልቡ ያልተሰበረ የፕሮግራ ተከታታይ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡

ዛሬ መተሳሰብና መረዳዳት እንደሰማይ በራቀበት ዘመን ዮሴፍ (ጆሲ) በፕሮግራሙ ላይ እንዲህ የተረሱና የወገን ድጋፍ የሚያሻቸው ወገኖችን ከህዝቡ ጋር በማገናኘት ህይወታቸው እንዲለወጥ ያደረገው አስተዋፅኦ የተከታተሉ ተመልካቾች እደግ፣ ተመንደግ፣ ተባረክ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ዙሪያ ከድምፃዊና የቶክ ሾው አዘጋ ዮሴፍ ገብሬ ጋር ያደረግነው ቆይታ እነሆ፡-

ጥያቄ፡- አዲሱ አልበምህ ከምን ደረሰ? ዮሴፍ፡- አልበሙ ከሞላ ጎደል አልቋል፡፡ ለፋሲካ ይደርሳል

የሚል ሃሳብ ነበረን፡፡ አንዳንድ የስፖንሰር ሺፕና ሌሎች ጉዳዮች ነበሩን፡፡ እነዚያን ጉዳዮች ፋሲካ ከመድረሱ በፊት ነበር የጨረስነው፤ ከዚያ በኋላ ያሉት ነገሮች ለማስተካከል እየሞከርን ነው ያለነው፡፡ የጆሴ ሾው ምዕራፍ 3 ልጀምር ስለሆነና ትንሽ ለየት ባለ መልክ ይዘን ለመውጣት ስለፈለግን ትንሽን ድካሞች ነበሩበት፡፡ ያንን አስተካክለን አልበሙ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለ1 ወር ከ15 ቀን ውስጥ ለአድማጭ ወደ መልቀቁ እንሄዳለን፡፡

ጥያቄ፡- አልበሙን ዜማ፣ ግጥምና ቅንብር ከእነማን ጋር ነበር የሰራኸው?

ዮሴፍ፡- በርካታ ሰዎች አሉበት፡፡ ይልማ ገ/አብ፣ ጌትሽ ማሞ፣ መለሰ ጌታሁንና ሙያው ላይ ይሰራሉ የሚባሉ የተለያዩ ሰዎች ጋር ነው የሰራሁት፡፡ ዜማውና በቅንብርም ሁሉም ጋር ነው የተሰራው ማለት ይቻላል፡፡

ጥያቄ፡- በዚህ አልበም ላይ የበፊቱን ስታይል ይዘህ ነው የመጣኸው ወይስ የተለየ?

ዮሴፍ፡- የበፊቱ እስታይል 6 ወይም 7 ዓመት በፊት ነው ይዤ የወጣሁት፡፡ ያኔ ደግሞ ወታት ነበርኩ፣ አሁን ወደ መብሰሉ ስለሆንኩ በዚያው ልክ በሰል ያሉ ዜማዎች ናቸው፡፡ ለበፊቱ አድናቂዎችም የሚሆኑና እንዲሁም አገራዊ ፋይዳ ያላቸው መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ፣ ሀገርኛ ባህልን የሚያስተዋውቁ ሆነው የዕድሜዬን ያህል አልበሙም አድጎ ይወጣል፡፡

ጥያቄ፡- የአልበሙ ርዕስ ታውቋል? ዮሴፍ፡- የተመረጡ ርዕሶች አሉት፡፡ ግን ሊወጣ ሲል ነው አ

ንዱ ርዕስ የሚመረጠው፡፡ ጥያቄ፡- አልበሙን የገዛው ወይም የሚያከፋፍለው ማነው? ዮሴፍ፡- ያንን ለጊዜው ምስጢር ላድርገውና ስፖንሰርሽፕ ከ

አንድ ካምፓኒ ጋር ጨርሰናል፡፡ ከዚ ባለፈ ግን የማከፋፈል ስራው እንዴት እንደሚሆን እያሰብንበት ስለሆነ ለጊዜው ይፋ አልሆነም፡፡

ጥያቄ፡- በአንተ እይታ አሁን እንደሚታወቀው የሙዚቃው ኢንዱስትሪ የገጠሙት ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?

ዮሴፍ፡- ምክንያቶቹ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ሁልጊዜ እንደሚባለው የኮፒራይት ያለመከበር ችግር ዋነኛው ነው፡፡ ነገር ግን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀዛቀዘ የሚያመላክቱ እንደ ብዙአየሁ አይነት ስራዎች አሉ፡፡ የብዙአየሁ አልበም በደንብ ተሰምቶ ነበር፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን ተሰርተው መቅረብ የሚችሉ አልበሞች አሉና ከእነኛ አንዱ የመሆን ዕድል አልመህ ያለውን ስራ በደንብ አጠንክረህ ሰርተህ ማቅረብ እንጂ ከሙያው ጨርሶ መራቅ አያስፈልግም፡፡ ምናልባት ከሚሰሙ ስራዎች መካከል አንዱ ትሆናለህ፡፡ አለበለዚያም ሪስኩን ወስደህ የሚመጣውን መቀበል ነው፡፡

ሌላው ግን ሁሉ ነገር ጨምሯል፣ ዛሬ አንድ ማኪያቶ አንዳንድ ቦታ 13 ብር ገብቷል፡፡ ከጓደኛህ ጋር ሆነህ ሁለት ማኪያቶ ከጠጣህ 26 ብር ነው፡፡ የእኛን ሲዲ በ25 ብር ለመግዛት እንደ ከባድ ይቆጠራል፡፡ አብዛኛው ሰው ለሙያው የሚሰጠው ቦታ ከ

ደብል ማኪያቶ በታች ሆኗል፡፡ ለሙያው ክብር ብንሰጥ መልካም ነው፡፡ ድሮ እኛ ልጅ እያለን አዲስ ዘፈን ሲወጣ በየሙዚቃ ቤቱ ደጃፍ እንሰባሰብ ነበር፡፡ ሌላው ችግር ብዙ በመፅሔትና ጋዜጦች ላይ አላግባብ የአርቲስቱ ይሰጥ የነበረው ያልሆኑ ስም ማጥ

ፋቶች ይወጡ ነበር፡፡ ወደ መፍትሄው ስንሄድ ያንን ገፅታ ለመቀየር አርቲስቱ ዝም

ብሎ ከመዝፈን ባለፈ በማህበራዊ ስራዎች ውስጥ ራሱን ማሳተፍ አለበት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እኔም የጀመርኩት ነገር አለ፡፡ እኔ ብ

ቻም ሳልሆን የሙያ ባልደረቦቼም በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፈው ያ ገፅታ ከተቀየረ በኋላ ህዝቡ ውስጥ የእኔነት ስሜት ፈጥሮ ገበያውን የመመለስ ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡

ጥያቄ፡- አንተስ ለአዲሱ አልበም ከአድማጮችህ ምን ትጠ

ብቃለህ? ዮሴፍ፡- መልካም ነገሮችን እጠብቃለሁ፤ ጥሩ ነገሮች ይሆና

ሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ጥሩ ነገር ሰርቻለሁ፡፡ በተለያዩ ባለሙያዎች አሰምቼ በጣም ቀና የሆነ ምላሽ ነው ያገኘሁት፡፡ አድማጩ ሰምቶት ደግሞ የሚሰጠውን ምላሽ አብረን እናየዋለን፡፡

ጥያቄ፡- ‹‹ጆሊ ቶክ ሾው››ን እንዴት ጀመርከው? ዮሴፍ፡- ት/ቤት ውስጥ እያለሁ ሚኒ ሚዲያ ውስጥ እሰራ ነ

በር፡፡ ከ9-12ተኛ ክፍል ስማር በጣም ታታሪ ጋዜጠኛ ስለነበርኩ ይመስለናል የሚኒ ሚዲያው ኃላፊ ጭምር ነበርኩኝ፡፡ 10ኛ ክፍል ላይ የህዝብ ግንኙነትና የተማሪዎች ተወካይ ተብዬ ከ3 መምህራን ጋር የሹመት ደብዳቤ ደርሶኛል፡፡

ጥያቄ፡- የት ነበር የምትማረው? ዮሴፍ፡- ናዝሬት አዳማ አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ነበር የምማረ

ው፡፡ እዚያ ነበር የጋዜጠንነት ህይወት የጀመርኩት፡፡ በየእረፍቱ እየገባሁ አምስቱን ቀናት ሙዚቃ ማሰማት፣ ስነ ፅሑፍ ማቅረብና ፕሮግራም መምራት የመሳሰሉትን እሰራ ነበር፡፡

መርካቶ ከወንድሜ ጋር ቢዝነስ እየሰራሁ ኢትዮ-ኒውስ፣ ዘ ፕሬስ፣ አዲስ አድማስ ላይ ከ60 በላይ አርቲክሎችን ጽፌያለሁ፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኝነት ከዚያ ጀምሮ ያደገ ሙያ ነው፡፡

ወደ ቶክሾው ስንመጣ ለምሳሌ ክዊን ላቲቫ ዘፋኝ ናት፡፡ የራሷ ቶክሾውም አላት፡፡ ሌሎችም እንደዚያው፡፡ እኔም የራሴ ቢኖረኝ ብዬ አልም ነበር፡፡ ኢቢኤስ ቲቪ ሲመጣ ፕሮግራሞች ይፈልግ ነበርር፡ ከባለቤቶቹ ጋር ተገናኝተን ለመጀመር አሰብኩኝ፡፡ በወቅቱ አልበሙ ትንሽ ያዝ ስላደረገና ልጀምር አልቻልኩም ነበር፡፡ ከቆይታዎች በኋላ ጀመርኩኝ፡፡

ጥያቄ፡- የፕሮግራሙ ፎርማት ምንድነው? ዮሴፍ፡- ሲጀመር የታዋቂ ሰዎች የህይወት ሂደት ምን ይመ

ስላል፣ አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ታዋቂ አይሆንም፡፡ እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እዚያ እውቅና ላይ የደረሱበት መንገድ እንዴት ነው? የሄዱበት መንገድ ለሌሎች መማሪያ መሆን በሚቻልበት መልኩ ማቅረብ ነው፡፡

ስለ አርቲስቶቹ የነበረን ገፅታ ጥሩ ስለነበር አርቲስት ከተጠቀምንበት በጣም ብዙ ነገር የማድረግ አቅም አለው፡፡ ብዙ ነገር ማድረግ ይችላል፡፡ የአርቲስቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያልታዩ ማንነቶችን እያሳዩ ያለውን መንፈስ ሊቀየር የሚችል መንፈስ ይዞ ነበር የተነሳው፡፡ ያንንም ስናደርግ የታመሙት፣ የተጎዱ፣ የተረሱትን፣ የትኛቸው ያሉት ብለን የመጠየቅ መንፈስ ይዘን መጣን፡፡ ከዚያም የበዓለት ዘመድ ጥየቃ የሚል ፕሮግራ ጀመርን፡፡ እያልን አሁን ያሉት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ፕሮግራ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ፣ ከቋንቋ አጠቃቀም ጀምሮ፣ ከአቀማመጥ፣ በእያንዳንዱ ነገር ከልጅ እስከ አዋቂ የሚከተለው የቤተሰብ ፕሮግራም እንደሆነ ነው እየሰራን ያለነው፡፡

ጥያቄ፡- ምን ያህል ፕሮግራሞች ሰራችሁ? ዮሴፍ፡- እስካሁን ዓመቱን ሙሉ ስንሰራ ነበር፡፡ ሶስት ልዩ የ

በዓል ፕሮግራሞች ሰርተናል፡፡ ለአዲስ ዓመት፣ ለገና እና ለፋሲካ፣ ከእነሱ ሌላ በእርግጠኝነት ከ3-4 ፕሮግራሞች ካልሆነ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ነበር ስናቀርብ የነበረው፡፡ ስኬታማ ያደረገንም ፕሮግራም ያለመድገማችን ነው፡፡ ዓመቱን ሙሉ አዲስ ነገር እያሳየን ነው እዚህ የደረስነው፡፡

ጥያቄ፡- ሰዎችን መርዳት እና ማገዝ የፕሮራሙ አካል እንዴት ልታደርገው ቻልክ?

ዮሴፍ፡- ሰዎችን የማገዝና የመርዳት ነገር አሪፍ ፕሮግራም አዘጋጅ ስለሆንክ ወይም እውቀት ስላለህ ስለዚህ ብቻ ሳይሆን ልብ ይፈልጋል፡፡ አንተ ትንሽ በመስጠት የምትደሰት ከሆንክ ያንን ትሰራለህ፣ ለምሳሌ 5 ብር ኖሮህ 1 ብር በመስጠት የምትደሰት ከሆንክ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ትሰራለህ፡፡ እንደዚህ አይነት ልብ ከሌለህ የፈለገው ጎበዝ ጋዜጠኛ ብትሆን አትሰራውም፡፡ ይሄ የልብ ነገር ነው፡፡

ጥያቄ፡- የማንአልሞሽ ቤተሰቦች ህይወትን በፕሮግራም ላይ ለማቅረብ ምን አነሳሳህ?

ዮሴፍ፡- የእኔ ታላላቆች ወይም በዘመዶቼና ቤተሰቦቼ በተለይ በዳግማይ ትንሣኤ ወቅት ‹‹አክፋይ›› በሚባለው ስነ ስርዓት ውስኪ እና በግ ይዘው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄ የክብር መገለጫ ነውና ያንን ሃሳብ ይዤ ነው ወደዚህ ያመጣሁት፡፡

ፕሮግራሙ ላይ በዓል (ጆሲ... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

ኪነጥበብ ጤና ሕይወት ስፖርት

“የእናቶች ምርቃት ለእኔ ሕይወት ሆኖኛል”

ክፍት የሥራ ቦታHelp Wanted

P-T Office Clerk: Vadnais Heights law firm is looking for a part- time office clerk with good organizational skills who is preferably

fluent in both English and Amharic. Job Duties: This position will include general office duties includ-ing open and closing files, light phone communications with Am-haric speaking clients, calendaring, filing, ensuring files are well

organized and the ability to assist with overflow work when needed. Salary Information: $10.00 per hour, 20 hours per week.

Please email your resume to [email protected].

Page 16: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 16

4ቱ የካፌን የጤና ችግሮች እና መፍትሄው

በዚህ ቢዚ ሕይወት መቼና እንዴት መመገብ እንዳለብዎ እንንገርዎከኢሳያስ ከበደ

ሰው ምግብ ለምን ትበላለህ? ሲሉት ህፃኑ እንዳይርበኝ፣ አዋቂው ለመኖር፣ እንደኔ ያለውም ለመዝናናት፣ ስፖርተኛውም ለጥንካሬ ይሉናል፡፡ የሕክምና ባለሙያውስ?

ያነጋገርናቸው አንድ የህክምና ባለሙያ ለመንደርደሪያ ያህል ምግብን መቼ እንዴትና ምን መመገብ እንዳለብን ከመግለፅ ጀምረው በዓለም አቀፍና ከህክምና ደረጃ አንፃር ተቀባይነት እያገኙ ስለመጡት የምግብ አይነቶችና ከገበታ እየተወገዱ ስላሉት የምግብ አይነቶች እንደሚከተለው ያስረዱናል፡፡ መልካም ቆይታ፡፡

ምግብ ለምኔ?ምግብ ህይወት ነው! ምግብ መመገብ ያለብን አንድም ለህፃ

ናት ዕድገት ጠቃሚ ነው፡፡ ከአይነትና ይዘት በተለይም ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማግኘት አለባቸው፡፡ ሌላው ሰውነታችን በሚያደርገው ውስጣዊና ውጫዊ እንቅስቃሴዎች ኃይል (ካሎሪ) ያስፈልገዋል፡፡ ካሎሪን ማግኘት ከምግብ የምናገኘው ተጨማሪ ጥቅም ነው፡፡ ሌላው ሰውነታችን እያረጀ በየጊዜው እራሱን እየተካ ያድሳል፡፡ ይህን ሂደት ይደግፋል፡፡ አካላችን በተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ እንዳይጠቃ እና በህመም ከተጎዳም ለማገገም ይረዳል፡፡ ስለዚህ ምግብ በአግባቡ ከተወሰደ ከላይ የጠቀስናቸውን ጥቅሞችና መንፈስን ዘና የማድረግ ጥቅሞች ከምግብ እናገኛለን፡፡

ምግብ በውስጡ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል፡፡ እነሱም ማይክሮ ኒውትሪየንትስ እንደ ፕሮቲን ስብና ካርቦሃይድሬት የምንላቸውን ሲሆን በተጨማሪም ጥቃቅን ይዘት ያላቸው ቫይታሚ

ኖች ማእድናትን ያጠቃልላል፡፡ ምግብ ስንል ከእይታ አንፃር ቁሳዊ ባህሪውን ቀያይሮ በማቅረብ እንጠቀምበታለን፡፡ በጠጣር (በፈሳሽ) መልክ እንደየሰዉ ፍላጎት፣ ባህልና ልምድ በተለያየ ሁኔታ ይቀርባል፡፡ እነዚህ ልዩነቶች ቢኖሩም በምግብ ውስጥ ያለው ይዘት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከዕድሜ፣ ፆታ፣ ከስራ ሁኔታ፣ ከሰውነት አቋምና የጤና ሁኔታ አንፃር መጠቀም የሚያስፈልገው የምግብ ይዘት ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ህፃናት ፕሮቲን ያለው ምግብ በብዛት እንዲጠቀሙ ይመከራሉ፡፡ ከበድ ያለ ጉልበት ስራ የሚሰሩ ሰዎች ኃይል እንዲያገኙ በካሎሪ የበለፀጉ ምግቦች ያስፈልጓቸዋል፡፡ ነፍሰጡር ሴቶች አይረን፣ አትክልት፣ ፍራፍሬዎችን ማግኘት አለባቸው፡፡

በአማካይ አንድ ሰው ምን ያህል ምግብ መመገብ አለበት?

በመጀመሪያ እንደየስራ ባህሪው እና እንደ ጤንነት ሁኔታው መታየት ያለበት ሆኖ በመካከለኛ ዕድሜ የሚገኝ አንድ አዋቂ የሚባል ሰው በአማካይ ወንድ ከሆነ

በቀን እስከ 200 ሺ ኪሎ ካሎሪ መውሰድ የሚጠበቅበት ሲሆን ለሴት ደግሞ እስከ 1800 ኪሎ ካሎሪ መውሰድ አለባት፡፡ የካሎሪ

መጠን ልዩነት የወጣው በብዛት ወንዶች በአካል መጠን ስለሚበልጡና በጉልበትና ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ስለሚገኙ ነው፡፡ ነገር ግን እንደየሰዉ የተለያየ የአመጋገብ ልዩነት መጠን ሊኖር እንደሚችልም ይጠበቃል፡፡ ቁርጥ ያሉ ነጥቦችን ማስቀመት ግን ይከብዳል፡፡ የሰው ገቢና አቅም የተለያዩ የምግብ አይነቶችን የማግኘትን ሁኔታም ይወስነዋል፡፡

የአንድ ሰው የምግብ ይዘት መጠን ምን መሆን አለበት የሚለውን ስንመለከት ከሚመገባቸው ምግቦች ውስጥ የፕሮቲን ውጤቶች 20% አነስተኛውን ይይዛሉ፡፡ የስብ ሁኔታም ከ30% መብለጥ የለበትም 50% ካርቦሃይድሬት ይዘት እንዲኖው ይመከራል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የፕሮቲን እና የስብ መብዛት የጤና ጠንቆችን ስለሚያስከትል ነው፡፡ ከእንስሳት ጋር የሚገኙ ፕሮቲኖችን የሚወስዱ ሰዎች ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚያጋልጡ በየጊዜው የሚወጡ ጥናቶች ይ

ጠቁማሉ፡፡ ለምሳሌ የጡት ካንሰር፣ የፕሮስቴት ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር የመሳሰሉት የእንስሳት ስጋን በብዛት በሚጠቀሙ ሰዎ

ች ዘንድ የሚስተዋል የጤና ችግር መሆኑ ተዘግቧል፡፡ ስለዚህ አነስተኛ ፕሮቲን መውሰድ በበለጠ ይመከራል፡፡ የስብዕና ካርቦሃድሬት መጠንም ከሰውነታችን መጠንና የስራ እንቅስቃሴ አንፃር መመጠን ይገባል፡፡

አትክልትና ፍራፍሬዎች ከ100% ምን ያህሉን መያዝ አለባቸው

እነዚህ በመደበኛ ደረጃ ከተቀመጡት ፕሮቲን ስብና ካርቦሃድሬት በተጨማሪነት ምግብነት የሚወሰዱ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የምግብ ፍላጎት እስካለው ድረስ አትክልትና ፍራፍሬ ሊመገብ ይችላል፡፡ እነዚህ ዋና ሳይሆኑ ተጨማሪ ምግቦች ናቸው በንፅህና ከቀረቡና ከተያዙ ጥቅም እንጂ ጉዳት አያስከትሉም፡፡

እንዴትና መቼ እንብላ?አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ከሚበላ ይልቅ ከፋፍሎ

በተወሰነ የሰዓት ልዩነት ትንሽ ትንሽ ቢመገብ ጥሩ ነው፡፡ ለሰውነታችን የምግብ መፍጨት ሂደት እንዲቀል ያደርጋል፡፡ ለሰውነት ጤና አንድ ሰው በቀን ከአራት እስከ ስድስት ጊዜ መመገብ እንዳለበት ይመከራል፡፡ በእኛ አገር ብዙዎች የሚመገቡት በቀን ሶስት ጊዜ ነው፡፡ ይህም በዋነኝነት ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ሲሆን በህክምና የሚመከረው ቢያንስ አራተኛ የመክሰስ ሰዓትን መጨመር እንዳለበት ነው፡፡ ይህም ጊዜውን ጠብቆ ምግብ እንዲዋሃድ እንዲፈጭና እንዲሰራጭ ያደርገዋል፡፡

ለሰውነታችንም አስፈላጊውን ጥቅም ይሰጣል፡፡ የሰዓት ሁኔታውን ለይቶ ማስቀመጥ ካስፈለገም አንድ ሰው በቀን ያለውን ጊዜ ብናካፍለው በሶስት እና (መመገብ... ወደ ገስጽ 19 የዞረ)

በቋንቋ የተነሳ መንጃ ፈቃድማውጣት ተቸግረዋል?

Global Translation & Interpreterበቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል?

በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር አለ፤

አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

Tajajila AfaanOromoos Nikennina !

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን2400 Minnehaha Avenue Suite - 204

Minneapolis, MN 55404

(612) 275-0970በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት

የትርጉም ሥራ ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

አንድ ስኒ ቡና ለንቃት ሁለትና ሶስት ድብን ብሎ በመተኛት የካፌይን ተፅዕኖ ሲገለፅ

በተለያዩ አጋጣሚዎች ስራ፣ ጥናትንና በአጠቃላይ ለነቃ ውሎ ስንል ካፌይን ብለን የምንጠራውን ኬሚካል የያዙ መጠጦችንና ምግቦችን እንወስዳለን፡፡ በተለይም የዚህ ኬሚካል በብዛት መገኛ የሆኑትና በደከመንና በዛልን ወቅት ከድብርትና ከዱካክ ወጥተን ነቃ እንድንል የምንጠጣቸው ቡና፣ ሻይና የተለያዩ ለስላሳ መጠጦች ዋነኛ ተጠቃች ናቸው፡፡ ካፌይን አዕምሮን የሚያነቃቃ ሲሆን ከላይ ከጠቀስናቸው መጠጦች በተጨማሪ በሌሎች መግቦች ውስጥ ለምሳሌ በብስኩቶችና በቸኮሌቶች ውስጥ እንደዚሁም በአንዳንድ መድኃኒቶች (ለምሳሌ በራስ ምታት መድሃኒቶችና ማስታገሻዎች) ውስጥ በሰፊው የሚገኝ ነው፡፡ በአገራችንም በተለያየ መልኩ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች የሚወሰድ ነው፡፡ በብዙ ሰዎች በመወሰዱና በመለመዱም በተለያዩ ባለስልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ሳይቀር በ‹‹እፅ›› መልክ የሚወሰድም ነው፡፡ ነገር ግን ካፌይን መውሰድና ሱስ ውስጥ መግባት ከጤና ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡

አንድ ስኒ ቡና ከ100 እስከ 150 ሚሊ ግራም ካፌይን በውስጡ ይይዛል፡፡ ሻይ የዚህን ሲሶ ያህል ካፌይን ሲኖው፣ በአንዳንድ መድሃኒቶች ይህንን ያህል ካፌይን የመገኘት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል፡፡ በለስላሳ መጠጦች፣ በጣፋጭ ከረሜላዎችና ቸኮሌቶች ውስጥ እንደዚሁም በብስኩቶችና በሻይ ውስጥም በብዛት መኖሩ ህፃናት ልጆችም ሳይቀሩ በቀላሉ ሊወስዱት ይችላሉ፡፡

በዓለም ዙሪያ በአማካይ በቀን ውስጥ ከ80 ሚሊ ግራም በላይ ካፌይን በየቀኑ ይወሰዳል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከካፌይን ጋር የተያያዙ አራት አይነት የጤና ችግሮች አሉ፡፡

1. የካፌይን ስካር (ኢንቶክሲኬሽን) ይህ ስካር የሚጀምረው ከ250 ሚ.ግ በላይ ካፌይን ከተ

ወሰደ በኋላ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች ጭንቀት፣ የህሊና መረበሽ፣ መቁነጥነጥ፣ መነጫነጭ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማላብ፣ የሆድ መረበሽ፣ የሽንት መብዛት፣ እንቅልፍ ማጣትና በእግርና በእጅ ጣቶች ላይ የመወረር አይነት ስሜቶች መፈጠር ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የተወሰደው ካፌይን ከ1000 ሚ.ግ በላይ ከሆነ የአፍ መኮላተፍ፣ የሃሳብ መደነጋገር፣ የልብ ትርታ መዛባት፣ ወፈፍ ማድረግ፣ የሌለና የማይታይ ብርሃን መታየት ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ የካፌይን ብዛቱ ከ10,000 ሚሊ ግራም (10 ግራም) በላይ ካለፈ ግን ድንገተኛ ሞት ሁሉ ሊከተል ይችላል፡፡

2. ካፌይን ሳይወሰድ ሲቀር የሚከሰት ህመምበዚህ ጊዜ የህመሙ አይነትና መጠን ከሰው ሰው እንደሚ

ወሰደውና እንዳስለመዱት ብዛትና የልምድ ጊዜ እርዝመት ይለያያል፡፡ የተለመደው ካፌይን ሲቀር ከሚታዩ ምልክቶች መካከል ራስ ምታት፣ ጭንቀት ወይም መደበት፣ ድካም ወይም መፍዘ

ዝ፣ ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ካፌይኑ ከቀረ ከ12 እስከ 24 ሰዓታት ውጥ የሚጀምሩ ሲሆን በሁለተኛው ቀን የሚብሱ ነገር ግን በአንድ ሳምንት ውስጥ ተመልሰው የሚጠፉ ናቸው፡፡

3. የእንቅልፍ መቃወስና ጥልቅ የሆነ ጭንቀትመረበሽ፣ መነጫነጭ፣ መቁነጥነጥ ወይም በአንድ ቦታ ረጋ

ብሎ አለመቀመጥን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በተለይም የመርበትበትና በሆነው ባልሆነው መደንገጥ ያለባቸው ሰዎች ካፌይን በብዛት ከወሰዱ በኋላ በሽታው ሊነሳባቸው ይችላል፡፡ ስለዚህም በተቻለ መጠን ህመማቸው እንዳያገረሽባቸው ብዙ ካፌዬን መውሰ

ዳቸውን መቀነስ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡

በእንቅልፍ ላይ የሚያመጣውን ለውጥ ስናይ ደግሞ ቶሎ እንቅልፍ እንዳይመጣ ካደረገ በኋላ በቀጣይነት ለረዥም ጊዜ መተኛት አለመቻልና በማለዳ ከእንቅልፍ መንቃትን የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡

የመፍትሄ እርምጃዎችየካፌይን አጠቃቀምን ለመቀነስ ወይም እስከ መጨረሻው ለ

ማቆም የመጀመሪያ እርምጃው ምን ያህል ካፌይን በቀን እንደሚወሰድ እና በምን አይነት መንገድ እንደተወሰዱ (በመጠጥ፣ በምግብ፣ በመድሃኒት…ወዘተ) እንደሚወስዱ ለይቶ ማወቅ፡፡

ከዚህ በኋላ በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ የካፌይን አወሳሰዱን በመቀነስ በሳምንታት ውስጥ የሚፈለገው የተሻለ የመፍት

ሄ ደረጃ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ጋር አብሮ ካፌይን የሌላቸውን መጠጦችንና ምግቦችን ለይቶ አውቆ እነዚህኑ በምትክ መውሰድን ልማድ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ካፌይን መውሰድ በድንገት በሚቆምበት ጊዜ የሚከተሉትን ህመሞችንና የድብርት ስሜቶች ሲከሰቱ ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡

ለዚህም ነው አንድ ስኒ ቡና ጥሩ ንቃትን ለመፍጠር ያስችላል፡፡ ነገር ግን ሁለት ሶስት እያልን ስንደጋግም የአንጎላችን የመላመድ ብቃት እየጨመረ ይመጣና በንቃት ከመቆየት ይልቅ ድብን ወዳለ የእንቅልፍ ዓለም ውስጥም ያስገባል፡፡ ይህም የካፌይን ተፅዕ

ኖ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የሚፈፅመው ድርጊትም ጭምር ነው፡፡ በአጠቃላይ የካፌይን አጠቃቀማችንን ከምንወዳቸው ምግቦችና መጠጦች አንፃር መጠኑን በመቆጣጠር መቀነስ ሲልም እስከመተው ደረጃ መድረስ እንችላለን፡፡

CAFFEINE SIDE EFFECTS & SAFETY

Caffeine is LIKELY SAFE for most adults when used appropriately. Caffeine can cause insomnia, nervousness and rest-lessness, stomach irritation, nausea and vomiting, increased heart rate and res-piration, and other side effects. Caffeine can make sleep disorders in patients with acquired immunodeficiency syndrome (AIDS) worse. Larger doses might cause headache, anxiety, agitation, chest pain, and ringing in the ears.

Large doses may be UNSAFE and can cause irregular heartbeats and even death.

Special Precautions & Warnings:Pregnancy and breast-feeding: Caffeine is

POSSIBLY SAFE in pregnant or breast-feeding women in daily amounts of less than 200 mg. This is about the amount in 1-2 cups of coffee. Consuming larger amounts during pregnancy might increase the chance of miscarriage and oth-er problems. Caffeine passes into breast milk, so nursing mothers should closely monitor caffeine intake to make sure it is on the low side. Caffeine in large amounts is POSSIBLY UNSAFE during breast-feeding. Caffeine can cause sleep distur-bances, irritability, and increased bowel activity in breast-fed infants.

Anxiety disorders: Caffeine might make these

conditions worse. Use with care.Bipolar disorder: Too much caffeine might

make this condition worse. In one case, a 36-year-old man with controlled bipolar disorder was hospitalized with symptoms of mania after drinking several cans of an energy drink contain-ing caffeine, taurine, inositol, and other ingredi-ents (Red Bull Energy Drink) over a period of 4 days. Use caffeine with care and in low amounts if you have bipolar disorder.

Bleeding disorders: There is concern that caffeine might aggravate bleeding disorders. Use caffeine with care if you have a bleeding disorder.

Heart conditions: Caffeine can cause irregular heartbeat in sensitive people. Use caffeine with caution.

Diabetes: Some research suggests that caf-feine may affect the way the body uses sugar and might worsen diabetes. But the effect of caffein-ated beverages and herbs has not been studied. If you have diabetes, use caffeine with caution.

Diarrhea: Caffeine, especially when taken in large amounts, can worsen diarrhea.

Irritable bowel syndrome (IBS): Caffeine, es-pecially when taken in large amounts, can worsen diarrhea and might worsen symptoms of IBS.

Glaucoma: Caffeine increases the pressure in-side the eye. The increase occurs within 30 min-utes and lasts for at least 90 minutes after drink-ing caffeinated beverages.

High blood pressure: Consuming caffeine might increase blood pressure in people with high blood pressure. However, this effect might be less in people who use caffeine regularly.

Weak bones (osteoporosis): Caffeine can in-crease the amount of calcium that is flushed out in the urine. If you have osteoporosis or low bone density, caffeine should be limited to less than 300 mg per day (approximately 2-3 cups of cof-fee). It’s also a good idea to get extra calcium to make up for the amount that may be lost in the urine. Older women with an inherited disorder that affects the way vitamin D is used should use caffeine with caution. Vitamin D works with cal-cium to build bones. (Source: WebMed Megazine)

Page 17: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 17

የጤና ሞግዚት አዘጋጅ፦ ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

ከኤችአይቪ የሚያድኑ መድሃኒቶች ተገኝተዋል የሚባለው እውነት ነው?ውድ አዘጋጅ፡- የ21 ዓመት ወጣት ሴት ስሆን በአሁኑ ወቅት በግል ኮሌጅ ውስጥ በመማር ላይ እገኛለሁ፡፡ የምኖረው ጥሩ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦቼ ጋር ነው፡፡ ከወንድ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ የጀመርኩት

ከአራት ዓመት በፊት ማለትም ገና የ17 ዓመት ወጣት በነበርኩበት ጊዜ ነው፡፡ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ እንዴትና መቼ እንደተያዝኩ አላውቅም። ክብረ ንፅህናዬን ከገፈፈው ከመጀመሪያው የወንድ ጓደኛዬ በተጨማሪ እስካለፈው ዓመት ድረስ ከአራት የተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነትን ፈፅሜያለሁ፡፡ በስሜት የተሞላሁ በመሆኔ በግንኙነት ወቅት ኮንዶም የመጠቀም ጥያቄ አቅርቤ አላውቅም፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ሁለተኛው የወንድ ጓደኛዬ በጠና ታሞ መሞቱን በመስማቴና አንድ ጓደኛዬም ልጁ የሞተው በኤች.አይ.ቪ መሆኑን ስትነግረኝ ተጠራጥሬ በምስጢር ባደረኩት ምርመራ ቫይረሱ በደሜ ውስጥ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁሉንም ነገር በፀጋ ተቀብዬ ከቫይረሱ ጋር በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡ እንደ ቀድሞው መቅበጤንም ትቻለሁ፡፡ ውጤቴን ከሰማሁ በኋላ ላለፈው አንድ ዓመት ወሲባዊ ግንኙነት አላደረግኩም፡፡ ሲዲ ፎሬ በጣም ያልወረደ በመሆኑ በየጊዜው የምጎበኛት ሐኪም ፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እንድጀምር አላዘዘችኝም፡፡ ያም ሆኖ በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በቫይረሱ መጠቃቴ ሁሌም ያሳዝነኛል፡፡ በየጊዜው በኢንተርኔት አማካኝነት ስለ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ የሚወጡ ጥናታዊ ፅሑፎችንም እከታተላለሁ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ፅሑፍ ቫይረሱ የሚጠፋበት እና ሰዎች ከኤድስ ነፃ የሚሆኑበት ጊዜ በጣም ሩቅ እንደማይሆን በመግለፁ ውስጤ በተስፋ ተሞልቷል፡፡ አሁን ልጠይቅህ የፈለኩትም ይህንኑ በሚመለከት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ውስጥ ቫይረሱን በከፍተኛ ደረጃ ሊከላከሉ እና ሊያጠፉ የሚችሉ መድሃኒቶች ተፈጥረዋል ይባላል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው? እውን ከኤድስ መዳን ወይም መፈወስ የሚቻልበት ጊዜ እየመጣ ይሆን? ቫይረሱን በቅድመ ክትባት ለመከላከል የሚቻልበት ሳይንሳዊ ዘዴ ተገኝቷል የሚባለውስ እውነት ነው? እባክህን በእነኚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ስጠኝ፡፡ - ሠላማዊት አስታጥቄ

ማሳሰቢያበዘ-ሐበሻ የጤና አምዶች ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ ለማስተማሪያነት እና ግንዛቤ ለመስጠት እንጂ እንድትታከሙበት አይደለም። ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ህመም ሲሰማ ወደ ዶ/ር ጋር በመሄድ

በዶ/ር ትዕዛዝ እንድትታከሙ አደራ እንላለን።

የግጥም ጉባዔ

የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፡- ጥንቃቄ በጎደለው ወሲባዊ ግንኙነት ምክንያት በዚህ የወጣትነት ዕድሜሽ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በመያዝሽ አዝነናል፡፡ ይሁን እንጂ ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ ተገኘ ማለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመኖር ወደ አለመኖር ትሸጋገሪያለሽ፣ ማለት እንዳልሆነ ተገንዝበሽ እንድትፅናኚ እንጠይቅሻለን። ይህንን የምንልሽ ከባዶ ሜዳ ተነስተን ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በመሰራጨት ላይ የሚገኙት የፀረ.ኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩትን ዕድሜ አስገራሚነትና ባልተጠበቀ መልኩ እያራዘሙት በመሆናቸው ነው፡፡ እናም በአሁኑ ወቅት አንድ ሰው በሚያደርገው ምርመራ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ ቢያረጋግጥ እንኳን ስለ ሞት አይጨነቅም፡፡

በእርግጥ እስካሁን ድረስ ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ከደም ውስጥ ማጥራት የሚችል መድሃኒት የለም፡፡ ይህም ማለት ቫይረሱን ከአንድ ሰው አካል ውስጥ ማጥፋት የሚችል እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማረጋገጫ የተሰጠው መድሃኒት አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ በኤች.አይ.ቪ ህክምና ውስጥ በየጊዜው አስገራሚ የሆኑ ዕድገቶችና መሻሻሎች እየተፈጠሩ ሄደዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚደረጉት የህክምና ክትትሎችና መድሃኒቶች ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ህይወት እየታደጉት ይገኛሉ፡፡ እነኚህ ሁኔታዎች የታማሚዎችን አዕምሯዊ እና አካላዊ ሁኔታዎች በማደስ ላይ ናቸው፡፡

በአውሮፓ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከቫይረሱ እየተፈወሱ ስለመሆናቸው የሚናፈሰውም ወሬ ቢሆን እውነትነት ያለው ይመስላል፡፡ ከእነኚህ ከኤች.አይ.ቪ መፈወሳቸው ከተነገረላቸው ሰዎች መካከል ‹‹የበርሊኑ ታማሚ›› (The Berlin Patient) በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው ራሞር ብራውን ይገኝበታል፡፡ በእርግጥ የበርሊኑ ታማሚ ጉዳይ በአውሮፓ ውስጥ በሚገባ የሚታወቅና ጥልቀት ያለው ጥናትም የተካሄደበት ነው፡፡ ታማሚው እንደተባለውም ከበሽታው መፈወሱ ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሳይንስ ለዚህ ሰው የመፈወስ ጉዳይ እስካሁን ድረስ እውቅና ሊሰጠው አልፈለገም፡፡

የበርሊኑ ታማሚ ከበሽታው በመፈወሱ ምክንያት በአሁኑ ወቅት የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶችን በመውሰድ ላይ አይደለም። በእርግጥም በቲሞቲ ብራውን ውስጥ የሚገኘው የቫይረሱ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱ ተረጋግጧል፡፡ ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙም እንደማንኛውም ጤነኛ ሰው የተሟላ ነው፡፡

ከበርሊኑ ታማሚ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ጉዳዮች እዚህም እዚያም በመታየት ላይ ናቸው፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ የፀረ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ፈውስን ማግኘታቸው በስፋት ይወራል፡፡ በውጭ ሀገር ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ቫይረሱን በተሻለ ሁኔታ ማዳከም እና የሲዲ 4 መጠንን ለማሳደግ መቻሉ እየተነገረ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሳይንቲስቶች በእነኚህ ሁኔታዎች አልተዘናጉም፡፡ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከደም ውስጥ ለማስወገድ የሚችለውንና ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የሚሰጠውን መድሃኒት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ሳይንቲስቶች የመፈወሻ መድሃኒቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡ የተላላፊ ቫይረሶችና ተለዋጭነት ያላቸው ህመሞች 21ኛው ኮንፈረንስ በቦስቶን ከተማ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ሳይንቲስቶች የገለፁት ምንም እንኳን ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚችለው መድሃኒት እስካሁን ባይፈጠርም ህክምናውን በሚመለከት ከፍተኛ መሻሻሎች መታየታቸውን ገልፀዋል። እነኚህ መሻሻሎች የተገኙት ደግሞ ቫይረሱ በደም ውስጥ እንዴት ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደሚችል እና እንዴትስ ሊጠፋ እንደሚችል ተጨማሪ ዕውቀቶች በመገኘታቸው ነው፡፡

ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ፈውስ ያገኙ ሰዎችን በሚመለከት ከጀርመኑ ታማሚ በተጨማሪ ሌሎች አጋጣሚዎችም ተስተውለዋል፡፡ ከእነኚህም አጋጣሚዎች መካከል አንዲት በሚሲሲፒ ውስጥ የምትኖር ህፃን ትገኝበታለች፡፡

ዴቦራ ፔርሱር የተባለች በጆንስ ሆፕኪንስ ሆስፒታል ውስጥ የምትገኝ ሐኪም ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ ውስጥ ከሚገኝ እናት የተወለደችውን ህፃን በሚመለከት ስትገልፅ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በሚያደርገው የህክምና ጥበብ ባለመታገዟ በተወለደችበት ወቅት ህፃኗ በቫይረሱ መያዟን ታረጋግጣለች። በመሆኑም ህፃኗ በሚሲሲፒ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የህፃናት ሐኪም ቤት ውስጥ እንድትቆይና ከተወለደች ከ30 ሰዓታት በኋላ የአንታየርትሮቫይ

ራል ህክምና እንድትጀምር ተደረገ፡፡ ከህፃኗ ጨቅላነት አንፃር ይህ ህክምና አደገኛነት ሊኖረው ይችል

ነበር፡፡ ይሁንና ህይወቷን ለማትረፍ ይህንን ህክምና ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ ስላልነበረ ሕፃኗ ለ18 ወራቶች ያህል በሆስፒታሉ ውስጥ ተኝታ የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናውን ስትከታተል ቆየች፡፡ በመጨረሻም ማለትም ከ18 ወራት በኋላ ቤተሰቧ በመልካም ጤንነት ላይ የምትገኘውን ህፃን ከሆስፒታሉ አውጥተው ወደ ቤታቸው ይዘው ሄዱ፡፡

የፀረ.ኤች.አይ.ቪ ህክምናውንም አቆመች፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ህፃኗ ወደ ሆስፒታሉ ተመልሳ ምርመራ ስታደርግ በደሟ ውስጥ የነበረው የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጥፋቱ ተረጋገጠ፡፡ አሁን ህፃን ዲቦራ የሶስት ዓመት ህፃን ስትሆን ከቫይረሱ ነፃ ሆና ጤናማ ኑሮን በመኖር ላይ ትገኛለች፡፡ ይህም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመካሄድ ላይ የሚገኙት የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናዎች ፈዋሽ መሆናቸውና ህፃናት ጊዜው ከማለፉ በፊት ህክምናውን ካገኙ ከበሽታው ሊፈወሱ እንደሚችሉ ያመለክታሉ፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ህክምናቸውን የተከታተሉ በርካታ ህፃናት እየተፈወሱ መሆናቸውም ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ በታች ያቀረብነው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ሰዎች ከኤች.አይ.ቪ የሚፈወሱ ስለመሆናቸው የሚተርክ ነው፡፡

ዶ/ር ማስ አር ዩሱፍ የስሪ ላንግ ብሔራዊ የህክምና አገናኝ ተቋም ምክትል ዳይሬክተር እና የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው፡፡ በስሪላንካ ፒታ ኮቴ ሆስፒታል በፍልስፍና እና በነርቭ ህክምና ላይ ጥናት ያደረጉት ዶ/ር ዮሴፍ በናቹራፓዚ እና በማግኔቲያዊ ህክምና ሰፊ ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ዶክተሩ በቅርቡ ኮሎምቦን በጎበኙበት ወቅት ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጋር እየተካሄደ ያለውን ትንቅንቅ በሚመለከት ከአንድ የህክምና መፅሔት ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ እኛም ቃለ መጠይቁን በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፡፡ ጠያቂያችንም ከቃለ ምልልሱ ግንዛቤ እንደምታገኚ እንገምታለን፡፡

ጥያቄ፡- ኤች.አይ.ቪ ሰዎችን የሚያጠቃው እንዴት ነው?መልስ፡- ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃው ተፈጥ

ሯዊውን የበሽታ መከላከል ሲስተም ነው፡፡ ቫይረሱ የአምዩኒ ሲስተማችንን ካዳከመ በኋላ በተለያዩ በሽታዎች እንድንጠቃ ያደርገናል። አንድ ሰው ሁለት አይነት ቲ ሴሎች አሉት። አንደኛው ቲ ሴል ሲዲ 4 የተባለ ሞሉክዩል በላዩ ላይ የያዘ ሲሆን የዚህ ሞሉክዩል ተግባር ደግሞ ወደ ሰውነታችን የሚገባውን ቫይረስ በመከላከል ማስወገድ ነው፡፡ ሁለተኛው በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ሞሎክዩል ሲዲ 8 የተባለው ነው፡፡ የዚህኛው ሞሎክዩል ተግባር በበሽታ የተጠቁ ሴሎችን ማስወገድና ፀረ ቫይረስነት ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ማምረት ነው። እነኚህ ሁለት የሞሎክዩል አይነቶች ናቸው፡፡ በተቀናጀ መልኩ ሰውነታችን በአንድጀንስ፣ በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፈንገስ እና ከመሳሰሉት ህመም አምጪ ህዋሳት እንዳይጠቃ የሚያደርጉት።

ኤች.አይ.ቪ በሲዲ 4 ሞሉክዩል ጋር በመጣበቅ ቫይረሱ ወደ ውስጥ ገብቶ ሴሎችን እንዲበክል ያደርጋል፡፡ በእርግጥ አንድ በውስጡ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ያለበት ሰው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰማው ለተወሰኑ ዓመታት በጤነኛነት ሊቆይ ይችላል፡፡ ምክንያቱ

ም በቫይረሱ በየቀኑ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የሲዲ 4 ቲ ሴልስ በቫይረሱ ቢደመሰስም የዚያኑ ያህል ቁጥር ያላቸው ሞሉክዩሎችን ሰውነታችን ስለሚያመርትና የተደመሰሱትን ስለሚተካ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ኤች.አይ.ቪ ያለ ጥርጥር ኤድስን ያስከትላል ማለት ይቻላል?

መልስ፡- አንድ አዋቂ ሰው ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ በኋላ ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይሰማው ለ8 ዓመታት ሊቆይ ይችላል፡፡ ለህፃናት ደግሞ አማካይ ጊዜ 2 ዓመታት ነው፡፡ ይህም ሆኖ አንዳንድ አማይዋሎጂስቶች ሞሎኪያሮች፣ ባዮሎጂስቶች፣ ቫይኖሎጂስቶች፣ ባዩኬሜስቶች እና ማይክሮባዮሎጂስቶች ኤች.አይ.ቪ ከመደበኛው በሽታ አስተላላፊ ቫይረስ ምንም የሚለይበት ነገር እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡ በእነኚህ ተመራማሪዎች እምነት መሰረት ኤች.አይ.ቪ ኤድስን አያከስትልም። ለዚህ እምነታቸው የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ኤድስ የባህሪ በሽታ እንጂ በኤች.አይ.ቪ የሚከሰት አይደለም የሚል ነው፡፡ በእነኚህ ጠበብቶች እምነት መሰረት ኤድስ የሚከሰተው በአሙዩኒ

ሲስተም ውስጥ በሚከሰት በርካታ የመዛባት ሁኔታዎች ምክንያት ነው፡፡ እነኚህም ሁኔታዎች በወሲባዊ ግንኙነት ምክንያት በሚተላለፉ ህመሞችና በበርካታ የቫይረሱ ጥቃቶች ወዘተ… እንጂ በኤች.አይ.ቪ የሚከሰት እንዳልሆነ ለማሳመንም ይሞክራሉ። በዚህም ሆነ በዚያ አንድ ሰው በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ሲያዝ ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙ እየመነመነ ይሄዳል፡፡ ይህ ሁኔታም እንደ የሣምባ ምች፣ ካፓሲ ሰርኮም፣ ሰውነትን ለሚያከሳ በሽታ፣ ለተቅማጥ እና ለሌሎችም አደገኛ በሽታዎች ያጋልጠናል፡፡ እነኚህ በሽታዎች ደግሞ ሰውን የመግደል አቅም ያላቸው ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- በእርስዎ ቲዩሪ መሰረት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምክንያት ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙ የወረደውን ሰው የጤንነት ሁኔታ እንዴት ማሻሻል ይቻላል?

መልስ፡- የወደቀን የኢሚዩኒ ሲስተም ለማነቃቃት በሰው ላይ ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ መድሃኒቶችን በትንሹ እየሰጡ በማከም በሰውነት ውስጥ ያለውን ፊዚዮሎጂካል ሚዛን ማስተካከል የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ በመርፌ ነርቭን እየወጉ የማከም ዘዴ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ አንዴ ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት ማግኘት ከተቻለ እና የአሲድ ጂኒክ ሁኔታን በሰውነታችን ውስጥ ወደ አልካሊ ጂኒክ መለወጥ ከተቻለ በሽታን የመከላከል አቅማችን እየተጠናከረ ይሄዳል፡፡ ይህንን ለውጥ መፍጠር የምንችለው ደግሞ በናቹር ፓቲክ ሳይንሳዊ ዘዴ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰውነታችን ማንኛውንም በሽታ ለመዋጋት የሚችልበትን ተፈጥሯዊ ጥንካሬ እያገኘ ይሄዳል፡፡ በመሰረቱ እኛ ሰዎች የምንኖረው (ኤችአይቪ... ወደ ገጽ 19 የዞረ)

እነሆ ረመዳን መጣ...

እስቲ ከሙሐመድ አወል እንጉርጉሮ እንቀነጫጭብ እንግዲህ . .

. “ ቢስሚላሂ ብዬ ታጥቄ ልጥመድየሃድራውን እርሻ እንድለማመድበኒዕማው አሽቅሬ ደሞ ለሃምድ

. . .ዋሪዳው ታስነሳኝ ቀለምና መድ

ወደ ማእናው ባሕር እስቲ ልራመድበኢባዳው መርከብ ዋና ልላመድጠና ይላል ምጡ እስተሚለመድ

ሳይቅላላ አይለቅም ሳያቅመደምድ

. . .ቢስሚላሂ ብዬ መድሑን ልቀድሰውየሙስጠፋን ዝና የዚያን የደግ ሰው

ተዳር እንኳን ቢሆን ሃዱን ባላደርሰውቢያግዘኝ ጌታዬ አልቀርም ሳልቀምሰው

በፈድሉ ወደኔ ፈይዱን ቢመልሰው . . .

ዝቅዝቄን ቀለሜን እስቲ ልመልሰውአልሐምዱሊላሂ ገለታ ይድረሰው

. . . “ . . . (ምንጭ: ከመሐመድ አወል እንጉርጉሮ መንዙ

ማ የተቆነጠረ)

Remoteሳገኝሽ ደስታ ነውጨዋታ ያምረኛልስጠፊ እከፋለሁሀሳብ ይገባኛልአሁንስ እንጃልኝ

ገብተሽ በመውደዴአንቺ ሴት ለሙዴ

Remote ሆንሽ እንዴ? ቶማስ ወልዴ

አዳምና ጥበቡበመጀመሪያ አዳም ሳተ

ከገነትም ተጎተተአዳም ከገነት ሲባረርእነሆ እርቃኑን ነበር

ብርዱ፣ ውርጩ አንዘፈዘፈውዶፉ፣ ጠሉ ወረደበት

ይንዠረገገውን አይተውአእዋፍ አራዊት ሳቁበትይሄኔ አዳም ተማረረተማረረና ተመራመረተመራምሮም አልቀረጋቢ መስራት ጀመረጅማሬውን ወደደ

ተጀምሮ እስኪፈጠምየእድሜውን ግማሽ ወሰደ

ያሳዝናልጋቢውን ጨርሶ ሲቋጭገላው ብርዱን ለመደ::

ከበውቀቱ ስዩም

ሰው..... መሆንሰውን ለመታደግ ክብሩን ለመጠቅ

ከሂወት ፈተና ሰውን ለማላቀቅግዴታ አይሆንም ሰውን በዘር ማወቅዝምድናም ባይኖረን ወይንም ጋብቻለመርዳት በቂ ነው ሰው መሆኑ ብቻ

እ ሙ

የተደበቀችይቱአደን ሽሽት ተደበቅኩ

ተፈጥሮዬን ግን አልገደልኩ፤ግና ከተደበኩበት ሳለሁየተሸሸገች ቆንጆ አየሁ፤“የምርጥ አዳኝ ብቃቱ

ሳይሆን ሌሊት ማድባቱቀን የሸሸጋትን ማግኘቱ!”

ሄኖክ ስጦታው

በምን ይሆን የዳንኩ?ትላንት አመም አርጎኝ

የራስ ምታት ይዞኝበአንዲት ቅጠል ቢጤ ዳብሰሽው ግንባሬንሞት፣ ሞት ያሰኘኝን አጣሁት ህመሜን፡፡

እኔ ግን ያልገባኝ ነገረ-ብሂሉበአንቺ ነው የዳንኩት ወይስ በቅጠሉ?

ሰሎሞን ሞገስ(ፋሲል)እውነትን ስቀሏት፣መጽሐፍ፣ 2001ዓ.ም

የጦጢት ስታይልቆይ፣ ቆይ አንተ፣ ጠብቅ!

እንደዚያ አይደለም፤ምን ያስቸኩልሃል?ቆየኝማ ልስተካከል!

እህ … ቆይ፣ ኧረ ቆይ፣የሽቦ አጥሩ ላይ ልንጠልጠል፤

እሾሁ ግን እንዳይወጋኝ …ኧረዲያልኝ!

“ሊያጌጡ ይመላለጡ”፥አለች እመት ጉሬዛ፥ነፍሷን ይማረውና።

እውነቷን ነው!እሷስ ሃቁን ተናግራ አለፈች፤

መጥኔ ለኔ!እስኪ ለማነኛውም፥

ፎቶዬን ማንሳትህ ካልቀረእንግዲህ በደንብ አንሳኝ …

አዎን … አሁን ትንሽ ተረጋጋህ፤እንደዚያ ነው … በል አንሳኝ!

ቀጭ፣ ብልጭ አርገው፤ለልጅ ልጆቼ

ሞቼ እንዳልሞትባቸው።ጸዳ ያለ ምስል፥

ያ ነው የኔ ስታይል!

Page 18: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 18

Page 19: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 19

ኤችአይቪ... ከገጽ 17 የዞረ በርካታ ጎጂነት ካላቸው እና ከሌላቸው ህዋሳት ጋር ነው። በሳ

ይንሳዊ ግምት መሰረት አንድ ሰው በአንድ ሰዓት ውስጥ ከ14 ቢሊዮን በላይ ፓቶጂነሶችን ወደ አየር ይለቃል፡፡ ይሁንና በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው የአምዩኒ ሲስተም በየሴኮንዱ ውስጣችንን ከእነኚህ ህዋሳት የማንፃት ተግባር ያከናውናል። ኤች.አይ.ቪ ኤድስን በመዋጋቱ ሂደትም ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ መፈጠር አለበት።

ጥያቄ፡- እንደ ሆሞፓዚ፣ ፓልም ዲያግኖሲስ ቴክኒኮች፣ ማግኔቶራፒ፣ አዩርቪዳ እና ሌሎችም የህክምና አይነቶች ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ወደ ማዳን ሊያደርሰን ይችሉ ይሆን?

መልስ፡- በእርግጥ የመርፌ ነርቭን እየወጉ የማከሙ ዘዴ ከሌሎች ናውትሮፓቲክ የህክምና ዘዴዎች ጋር በመቀናጀት ቫይረሱ ባለበት እንዲቆምና የአምዩኒ ሲስተማችንንም ሊያሳደግ ይችላል። ሁሉም ችግር የሚመጣው በራሱ በቫይረሱ ሳይሆን ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅም ሲዛባ ነው፡፡ ፊዚዮሎጂያዊ የህክምና ዘዴ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅምን ካጠናከረ ቫይረሱ ራሱን እየወለደ ለመራባት አይችልም። ይህም ሁኔታ የመራባት ባህሪውን ያሳጣዋል፡፡ አንዳንድ ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጤነኛ እና የተረጋጋ ህይወት በመኖር ላይ የሚገኙትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ጥያቄ፡- በአጭሩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ የመፈወስ ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ነው?

መልስ፡- አንድን በኤች.አይ.ቪ ኤድስ የተያዘ ሰው የሚያድነው ብቸኛው መድሃኒት የገዛ ራሱ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም መጠናከሩ ነው፡፡ ሌሎች የህክምና ዘዴዎች አምዩኒ ሲስተምን ለመንከባከብና ቫይረሱ እንዳይራባ ለማድረግ ብቻ የሚከናወኑ ናቸው፡፡ ይህ ህክምና የህመምተኛው አምዩኒ ሲስተም ከቫይረሱ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመድሃኒቶቹም ጋር ተስማምቶ ያለ ችግር እንዲያድግ ያደርገዋል፡፡ ይህ እውነት ያለው ነገር ነው። በመሆኑም ሐኪሞች በቅድሚያ ማድረግ ያለባቸው ነገር የህመምተኛው ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም እንዲያድግ ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ህመምተኛው ወይም ህመምተኛዋ ወደ ሙሉ ፈውስ በሚያደርሳቸው ጎዳና ላይ እንዲጓዙ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሚዩኒ ሲስተምን ሳያሳድግ የሚካሄድ ማንኛውም የህክምና ዘዴ ህመምተኛውን ከሞት ሊያድነው አይችልም፡፡

ጥያቄ፡- ነርቭን በመርፌ በመውጋት ከሚካሄደው ህክምና በተጨማሪ ሌላ ኤች.አይ.ቪ ኤድስን በተሻለ ሁኔታ ሊከላከል የሚችል መድሃኒት አግኝተዋል?

መልስ፡- በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ኪንግደም የሆምፓዝ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ፒተር ቻፕል የፈጠሩትን መድሃኒት በጥቅም ላይ ለማዋል በሙከራ ላይ እገኛለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ይህ መድሃኒት ከአሁን በፊት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህመምተኞች ላይ ተሞክሯል? ውጤቱስ ምንድነው?

መልስ፡- አዎን! ግን ሙከራውን ያደረኩት እኔ ሳልሆን ዶ/ር ቻፕል ናቸው። ዶ/ር ቻፕል በኢትዮጵያ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጋር በሚኖሩ 200 ሰዎች ላይ ባደረጉት ሙከራ አስደናቂ ውጤት

ተገኝቶበታል፡፡ በእርግጥ እስካሁን ያለውን ሁኔታ ከክሊኒካል ሙከራ የዘለለ አይደለም። ግን አዲሱ መድሃኒት እጅግ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ የሰውነትን የሲዲ 4 መጠን ከማንኛውም ጤነኛ ሰው ጋር ለማስተካከል የተቻለ ሲሆን የህመም ስሜቶችም መቀነሳቸው ተረጋግጧል፡፡

ጥያቄ፡- ይህ ከሆነ ታዲያ መድሃኒቱ ከሙከራ አልፎ በመላው ዓለም በስፋት ጥቅም ላይ ለምን አልዋለም?

መልስ፡- መድሃኒቱ እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ ያልዋለው ገንዘብና አስፈላጊው ትብብር ስለተነፈገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዶ/ር ቻፕል መድሃኒቱን የበለጠ ለማሻሻል ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ እኔም በዶክተሩ የተፈጠረውን መድሃኒት በማሻሻል ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ የሚፈውስ መድሃኒት የመፍጠር ሙከራዬን ገፍቼበታለሁ፡፡

መመገብ... ከገጽ 16 የዞረበአራት ሰዓት ልዩነት ውስጥ እንዲመገብ ይመከራል፡፡ በዚህ

አጋጣሚ የአንድን ሰው አመጋገብ መጠን የሚወስነው ፍላጎቱና አቅሙ ነው፡፡ በሌላው በኩል የሰውነቱ ሁኔታም ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ፍላጎት ከሌለው እና ከጠገበ ሰውነቱም የሚፈልገውን አቋምና የጤና ሁኔታ ከያዘ (ከመጠን) ያለፈ አመጋገብ ምግቦች መኖራቸው ሰውነትን አላስፈላጊ የስብ ክምችት እንዲኖረው ያደርጋሉ፡፡ በዚህ የተነሳም ስብ በደም ስር ግድግዳዎች በመጣበቅ የደም ስሮችን በማጥበብ ለልብ ድካም፣ ለነርቭ፣ ለኩላሊት፣ የጉበትና ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ሊኖር የሚገባው የስብ (ኮሌስትሮል) መጠ

ን ምን ያህል ነው?በሰውነት ውስጥ ሊኖር የሚገባው ኮሌስትሮል 200 (mg/dc)

ዲሲ ሊትር ማነስ አለበት፡፡ ነገር ግን ኮሌስትሮል ስንል ሁሉም የስብ አይነቶች ጎጂ አይደሉም፡፡ አዋቂ ሰዎች ሰውነት ውስጥ ከ200 (mg/dc) ዲሲ ሊትር ስብ ከበለጠ አይነቱን በመለየት ጎጂውን የስብ አይነት እንዲቀንሱት ህክምናው ይመከራል፡፡ ለምሳሌ ኤልኤል የሚባለው የስብ አይነት ለጤና ጠንቅ ነው፡፡ በመሆኑም ሰውነታችን ክምችት እንዳይኖረው መከላከል አለብን፡፡ አንድ ሰው ምግብ መብላት ያለበት ከሚሰራው ስራ አንፃር መሆን ይገባዋል፡፡ ብዙ ጊዜ በከተሞች አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች የተለያዩ ምግቦችን የማግኘት አጋጣሚና አቅሙ ስለሚኖራቸው የሰውነት ክብደታቸው ከአቋማቸው ጋር አይመጣጠንም፡፡ በተለይም በቢሮ ውስጥ እና ጭንቅላት የሚጠይቁ (አካላዊ እንቅስቃሴ ብዙ የማይፈልጉ ስራዎች ቁጭ ብለው ስለሚያከናውኑ በመሆናቸው በሆድ አካባቢ ቦርጭ (ትርፍ ሰውነት) ይስተዋልባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎችም ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በአንፃሩ በገጠር የሚኖሩ ወገኖቻችን የሚመገቡት የሚያስፈልጋቸውን ያህል በመሆኑ በተጨማሪም የተለያዩ ጉልበት ስራዎችን በመስራታቸው የተጠቀሙትን ምግብ በቀላሉ ወደሚያወጡት ኃይል ተቀይሮ ስራ ላይ ስለሚውል የስብ ክምችት በሰውነታቸው ውስጥ አይገኝም፡፡ አካላቸው ቀልጠፍ ያለና ጠንካራ ነው፡፡ በጤናማ ረገድ በቀላሉ ለበሽታ አይጋ

ለጡም፡፡ (ካላቸው አካላዊ አቋም ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና ችግሮች አይስተዋሉባቸውም)

በከተማ የሚኖሩ ሰዎች ያላቸው እንቅስቃሴ ውስን ነው፡፡ በእግር ከቤት ወደ ስራ ከመሄድ ይልቅ በትራንስፖርት ከዛም ቢሮ መቀመጥ እና አመጋገብ ላይ ስራ ላይ ከሚያውሉትና ከሚያስፈልጋቸው በላይ ይመገባሉ፡፡ ይህም እየጎዳቸው ይመጣል፡፡ ጣፋጭና ስብ የበዙባቸው ምግቦች መረር ሲልም አልኮል ስለሚወስዱ ከውፍረት ጋር የተያያዙ በሽታዎች እንደ ወረርሽኝ እየተስፋፉ በመሆኑ ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ አመጋገባችን ከምንሰራው ስራና ከምናደርገው እንቅስቃሴ ጋር መመጣጠን አለበት፡፡

ከአመጋገብ ጋር የተገናኙ የጤና ችግሮች የትኞቹ ናቸው?ምግብ መመገባችን ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ያመዝናል፡፡ አንዳ

ንድ የምግብ አይነቶች ግን የሰውነትን መቆጣት በመቀስቀስ ጤናችንን ሊያቃውሱት ይችላሉ፡፡ ከተለያዩ የምግብ አይነቶች የሚነሳው አለርጂ ከዚህ አንፃር ተጠቃሹ ሲሆን ብዙ ጊዜ በሰውነት ላይ ሽፍታ እና የማሳከክ ሁኔታዎችን ይፈጥራ፡፡ ከፍተኛ የስኳርና የስብ ይዘት ያላቸው ምግቦች ከማዘውተር የተነሳ ስኳር ህመም እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡ ከፍተኛ ክብደት ከመጨመር ተያያዥ በሽታዎች ይመጣሉ፡፡ ከሚፈለገው መጠን ያነሰ የአመጋገብ ልምድ ያላቸው ሰዎች ደግሞ ደካማ እንዲሆኑ በቀላሉ ለበሽታ እንዲጋለጡ ስለሚያደርጋቸው ኢንፌክሽኖች እና ሌሎች ህመሞች ያጠቋቸዋል፡፡ ስለሆነም የተመጣጠነ እና የተመጠነ ምግብ በተቻለ አቅም ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ኢትዮጵያውን የሚመርጡት ምግብ የእንስሳት ተዋፅኦ ነው፡፡ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርበው እና ለግብዣ የሚታዘዘው ክትፎ ቀይ ወጥ ጥብስ ወዘተ… ከቀለም ለውጥ የዘለለ የምግብ ንጥረ ነገር አይስተዋልበትም፡፡ እንደውም አትክልትና ፍራፍሬዎች ለጠረጴዛ (ብፌ) ማስጌጫነት ታስበው የቀረቡ ይመስላሉ፡፡ ተጋባዥም ጋባዥም ብዙ ትኩረት አይሰጧቸውም፡፡ ከሳይንስ አንፃር የስጋ ተዋፅኦ አይነቶችን ከመቀያየር ይልቅ የይዘት ለውጥ ማድረግ ጤናማና ጠንካራ ሰውነት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ከምግብ ማመጣጠን በተጨማሪ ወቅታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግም ተገቢ ነው፡፡

ቀድሞ በመደበኛነት (በዋነኛነት) ሲጠቀሱ የነበሩ የምግብ አይነቶች የስብና ፕሮቲን እንዲሁም ካርቦሃድሬት ይዘታቸው በመጠኑ አለመሆኑ በበለፀጉት እና በማደግ ላይ በሚገኙ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ በብዛት በመወሰዳቸው ከመጠን ያለ ክብደት ብሎም ከፍተኛ ስጋት እየሆኑ ለመጡ የማይተላለፉ የረጅም ጊዜ በሽታዎች እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡ ስኳር፣ ኩላሊት፣ ልብ፣ ደም ግፊትና የመሳሰሉት በሽታዎችም በስፋት እንዲከሰቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዓለም ገበታም ከዚህ የተነሳ እንዲጠብ ተገዷል፡፡ አራቱ ነጫጭ መርዞች ‹‹ስኳር፣ ጨው፣ ጮማ እና ነጭ የስንዴ ዱቄት (ፍርኖ ዱቄት)›› ከሚያስከትሉት የጤና ቀውስ አንፃር ከዓለም የምግብ ዝርዝር እንዲቀነሱ (እንዲሰረዙ) እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ በሌላው በኩል እንደ ተጨማሪ ምግቦች ይወሰዱ የነበሩ አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች የመደበኛ ምግቦችን ቦታ በመያዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጥናቶችም አትክልትና ፍራፍሬ ለረጅም ዕድሜ፣ ጥንካሬና አካላዊ ጤ

ና እንደሚረዱ በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡

ካንሰር... ከገጽ 14 የዞረበካንሰሩ የሚጠቁት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። ከቅድመ የማህፀ

ን አፍ ካንሰር ወደ ዋናው የማህፀን አፍ ካንሰር ያለው ሂደት በርካታ ዓመታትን ይወስዳል፡፡ ይህም ሆኖ አንዳንዴ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ዋናው ካንሰር ሊከሰትም ይችላል፡፡ በብዙዎች ሴቶች የቅድመ ካንሰር ሴሎች ያለ ምንም የህክምና ክትትል ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ በአንዳንድ ሴቶች ግን ቅድመ ካንሰሩ ወደ እውነተኛውና ገዳዩ ካንሰርነት ሊቀየር ይችላል፡፡ በመሆኑም በቅድመ ካንሰር የለውጥ ጊዜ ውስጥ የሚደረግ ምርመራ እና የህክምና ክትትል ዋናው ካንሰር እንዳይከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡

የቅድመ ካንሰር ለውጦች በማህፀን ውስጥ እንደሚገኙት የሴል አይነቶች ሁኔታ የተለያዩ ናቸው፡፡ ይህንን የለውጥ ሂደት ማወቅ የሚቻለው ደግሞ በማይስክሮኮፕ አማካኝነት ሴሎችን በመመልከትና በመመርመር ነው፡፡

ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የማህፀን አፍ ካንሰሮች ቦስክዋሞስ ሴል ካርኪኖማስ ወይም በአዴኖካርሲኖማስ የሚከሰት ቢሆንም ሌሎች የማህፀን አፍ ካንሰሮችም ይኖራሉ፡፡ እነሱም በህክምናው ቃል ሜላኖማ፣ ሳርኮማ እና ላይምፓማ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፡፡

የማህፀን አፍ ካንሰርን መከላከል ይቻላል?በአብዛኛው ዋና ዋናዎቹ የማህፀን አፍ ካንሰሮች በቅድመ ካን

ሰር ለውጥ የሚከሰቱ በመሆናቸው ይህ የካንሰር አይነት እንዳይስፋፋ ማድረግ የሚቻልባቸው ሁለት መንገዶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ዘዴ የቅድመ ካንሰሩን ሂደት በማወቅ ወደ ዋና ካንሰርነት እንዳይቀየሩ መከላከል ሲሆን ሁለተኛው መንገድ ደግሞ የቅድመ ካንሰር ለውጡ እንዳይከሰት በመከላከል ነው፡፡

የማህፀን አፍ ካንሰርን ለመከላከል ዋነኛው ዘዴ ካንሰሩ ወይም ቅድመ ካንሰሩ መኖሩን በምርመራ በማረጋገጥ እንዲወገድ በማድረግ ነው፡፡ በተለይም የቅድመ ካንሰሩ ለውጥ ወደ ዋናው ካንሰርነት እንዳይለወጥ መከላከል እጅግ ጠቀሜታነት አለው፡፡

ዋና ዋና ምክሮች- እያንዳንዷ ሴት ዕድሜዋ 21 ዓመት ከሞላበት ጊዜ ጀምሮ የ

ማህፀን አፍ ምርመራ ማድረግ ይኖርባታል፡፡ ዕድሜያቸው ከ21-29 የሆኑ ሴቶች ቢያንስ በየሦስት ዓመቱ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ - ከ30 ዓመታቸው ጀምሮ የHPV እና የPAP ምርመራዎችን በቅንጅት ቢያንስ በየአምስት ዓመቱ ማድረጋቸው አስፈላጊ ነው፡፡

- ሌላው አማራጭ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 65 የሆኑት ሴቶች የPAP ምርመራን ብቻ በየሶስት ዓመቱ ማድረግ ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ የማህፀን አፍ ካንሰርን መከላከል የሚቻለው በአብዛኛው ሂደቱ ከቅድመ ካንሰርነት ወደ ዋናው ካንሰርነት ከመለወጡ በፊት ቢሆን ይመረጣል ይላሉ የህክምና ባለሙያዎቹ፡፡

ለፈለጉት የጤና ዘገባ Tenaadam.com

Page 20: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 20

ትግራይ.... ከገጽ 3 የዞረ

መንሰራፋቱ እና አብዝሃው የበይ ተመልካች መሆኑ፣ የአዲሱን ትውልድ ልብ በህወሓት ላይ ካሸፈተው ውሎ ያደረ ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ከወደ ሸገር ተጋንኖ የሚወራውን ያህል ባይሆንም፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን በመውደድ ብቻ ድርጅቱን የሚደግፉ እንደነበሩ አይካድም፤ ግና፣ ይህም ቢሆን የሰውየውን ህልፈት ተከትሎ ታሪክ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡ ሌላኛው የተቃዋሚውን ጎራ ያጠናከረው ምክንያት ከቀዳሚዎቹ ሁሉ የከፋ አምባገነን እንደሆነ የሚነገረው የአባይ ወልዱ ካቢኔ፣ በሙስናና መልካም አስተዳደር እጦት የሚቀርብበት ወቀሳ ነው፡፡ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ደግሞ ‹‹ነፃ አውጪ››ውን ህወሓት እና መቀሌን ለሁለት ከፍሎ የማይተዋወቁ ዓለሞች አድርጓቸዋል ወደሚል ድምዳሜ ያደርሳል፡፡ ይህም ሆኖ ህወሓት በየትኛውም የትግራይ መሬት ተቃዋሚ ፓርቲ የመንቀሳቀስ ዕድል እንዳይኖረው ከጫካው ትግል ጀምሮ፣ በድርጅታዊ ቋንቋ ‹‹የትግራይ መሬት ከአንድ ፓርቲ በላይ መሸከም አይችልም›› የሚለውን ያልተፃፈ ሕግ ለማስፈፀም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፤ ለአፈናው ቀንበር መክበድም ቀንደኛው መነሾ ይህ ነው የሚለው ጭብጥ የተጋነነ አይደለም፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ስዩም መስፍን እና ፀጋዬ በርሄ፡- መቀሌ፣ አጽብሃ ወአብርሃ፣ ውቅሮ፣ አዲግራት፣ ፈረስ ማይ፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ሽሬ እንደስላሴ፣ አላማጣ እና ማይጨው ከተሞች ተገኝተው ከነዋሪዎቹ ጋር ስብሰባ በመቀመጥ፤ እንዲሁም ከነበለት፣ ማይቅነጣል፣ ዕዳጋ ዓርቢ፣ እንዳባጉና እና ሽራሮን ከመሳሰሉ ወረዳዎች ደግሞ የተወሰኑ ግለሰቦችን በተወካይነት ወደ መቀሌ በማስመጣት ‹‹ችግራችሁ ምንድን ነው? አለ የምትሉትን ቅሬታና የጎደለውን ነገር በሙሉ ንገሩን?›› በሚል መንፈስ የተቀኙ ጥያቄዎችን በማቅረብ ውይይት አካሄደው እንደነበር ይታወሳል፤ በዚህ ስብሰባም ሕዝቡ በርካታ ችግሮችን ከመዘርዘሩ ባለፈ፣ በአብዛኛዎቹ መድረኮች ስሜት የፈነቀላቸው አረጋውያን ሳግ እየተናነቃቸው ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊጠቃለል የሚችል ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ሰምቻለሁ፡-

‹‹እናንተ ክዳችሁናል! ለ17 ዓመታት ልጆቻችንን በጦርነት ማግዳችሁ ስታበቁ፤ ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀማችሁት ነገር የለም፡፡ እንዲያውም በሌሎች ክልሎች ላይ በሚገኙ ወገኖቻችንን ላይ በምታደርሱት በደል በጠላትነት እንድንመለከት ነው ያደረጋችሁን፡፡ ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ አናምናችሁም!!››

የቀድሞዋ የድርጅቱ የአመራር አባል አረጋሽ አዳነም ‹‹እነዚህ ሰዎች (የህወሓት መሪዎች) የምር ኢትዮጵያን ይወዳሉ ወይ? የሚል ጥያቄ ተብላላብኝ›› ማለቷን ‹‹የትግራይ ሕዝብ፣ ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ›› መጽሐፍ ገፅ 81 ላይ መገለፁ የአዛውንቶቹን አባባል ያስረግጣል ብዬ አስባለሁ፡፡

የሆነው ሆኖ እነ አባይ ፀሀዬ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ቅሬታ ይዘው (በርግጥ መጀመሪያውኑም ችግሩ ስለመኖሩ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም)፣ ከክልሉ ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ ጋር ተወያይተውበት ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት አባይም በድርጅታዊ መዋቅር የቀድሞ አለቆቹ እቢሮው ተገኝተው አንድ በአንድ የዘረዘሩለትን ችግር ካደመጠ በኋላ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፡- ‹‹እናንተ ያነጋገራችሁት ተቃዋሚ-ተቃዋሚውን ብቻ እየመረጣችሁ ነው፤ የመጣችሁትም ልክ እንደ ተቃዋሚዎች እንከን ፍለጋ ነው››፡፡

መቼም ከዚህ የበለጠ አስገራሚ የፖለቲካ ቀልድ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር ሄዶ ሄዶ አንድምታው ‹‹ህወሓት እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም›› የሚል የልዩነት መልዕክት ይኖረዋልና ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመለስ ህልፈት ማግስት ‹‹የአዲስ አበባው›› እና ‹‹የመቀሌው›› ተብሎ ለሁለት መከፈሉ ሲነገር የነበረው የህወሓት የውስጥ መተጋገል ገና መቋጫ ላለማግኘቱ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል (በነገራችን ላይ እነ አባይ ፀሀዬ በብዙ ሺህ ቅጂዎች የታተመ መጠይቅ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በትነው የነበረ ሲሆን፤ በቅርቡ ደግሞ የተሞላው መጠይቅ ተሰብስቦ ወደ አዲስ አበባ መላኩን ሰምቻለሁ፡፡ ይሁንና ውጤቱ ምንም ይሁን ምን አዲስ ነገር ይኖራል ብዬ ግን አላስብም፤ ምክንያቱም ከአስራ ሶስት ዓመት በፊት በዋነኛ መሪዎቿ አንደበት ‹‹ህወሓት ከአናቷ በስብሳለች›› ተብሎ ከተመሰከረባት ክፉ ህመሟ አለመፈወሷ ዛሬም በገሀድ ይታያልና)

የትግራይ እጣ-ፈንታበአስከፊው የትጥቅ ትግል ያለፈው የአካባቢው ነዋሪ፣ በህወ

ሓት ላይ የነበረው ተስፋ መሟጠጡን የሚያስረግጥልን፣ ከላይ ያየነው የመቀሌ ገፅታ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎች ለጉምቱ የድርጅቱ ታጋዮች ያቀረቡት ብሶት ብቻ አይደለም፤ አርሶ አደሩም በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ በስቃይና በድህነት ኑሮውን የመግፋቱ ጉዳይ ጭምር እንጂ፡፡ በተለይም መሬትና ማዳበሪያ ወሳኝ የፖለቲካ ካርድ ሆነዋል፡፡ ማዳበሪያው በክልሉ በጀት የሚገዛ ቢሆንም፣ በዱቤ የማከፋፈሉን ስራ የሚያሳልጠው ደደቢት ብድርና ቁጠባ ነው፡፡ ብዙሃኑ አርሶ አደርም ከዚህ ተቋም በዱቤ የገዛውን ማዳበሪያ መክፈል ባለመቻሉ በዕዳ የመያዝ ክፉ ዕጣ-ፈንታ ይገጥመዋል፡፡ ስለዚህም ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ሚስቱንና ልጆቹን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ለልመና አሰማርቶ በሚያገኘው ገንዘብ እንደምንም ዕዳውን ከፍሎ፣ የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት መያዝ የሚችልበትን አጋጣሚ ማመቻቸት፤ ወይም ከህወሓት ጎን በመቆም ዕዳው ተሰርዞለት፣ የሴፍቲኔት ተጠቃሚም ሆኖ

በጭቆና አገዛዝ ውስጥ ማዝገም ነው፡፡ ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታትም የሰሜን ኢትዮጵያ መልከዓ-ምድር ይህን በመሰለ ፍርሃትና በአንድ ርዕዮተ-ዓለም ተጠርንፎ ማደሩን ማን ይክደው ይሆን?

የመጪው ጊዜያት የብቻ ፍርሃት…በዚህ አውድ የማነሳው የትግራውያን ከባድ ፍርሃት፣ ከክፉ

ው የህወሓት አስተዳደር ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በሀገሪቱ በነቢብ ገዥ-ፓርቲ ተደርጎ የሚታሰበው ኢህአዴግ መሆኑ ባይስተባበልም፣ ግንባሩን የፈጠሩት አራቱ ድርጅቶች በፖለቲካዊ ተፅእኖም ሆነ በአንዳንድ መንግስታዊ ቁልፍ ኃላፊነቶች ላይ እኩል ውክልና ያሌላቸው መሆኑ አያከራክርም፤ ይህንን ያፈጠጠ ሀቅ አምኖ አለመቀበሉም መፍትሔውን ሊያርቀው እንደሚችል መዘንጋት የለብንም፡፡ ለማሳያም እንደ ኢህአዴግ ባለ አምባ-ገነን አገዛዝ ውስጥ ከምንም በላይ ወሳኝ የሆኑት የደህንነት እና የመከላከያ ሠራዊቱ አወቃቀር በህወሓት የበላይነት መሆኑን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊም በመከላከያ ውስጥ ያለውን ፍትሓዊ ያልሆነ ውክልና ከማመኑም በዘለለ፣ በበረሃው ዘመን ታጋዩ በአብላጫው የህወሓት አባል የነበረ መሆኑን እንደ ምክንያት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ በአናቱም ድርጅቱ በመሀል ሀገር ያጣውን ድጋፍ ለማካካስ፣ ራሱን የትግራይ ብሔረተኛ አስመስሎ ከማቅረቡም ባለፈ፣ እንዲህ አይነት ከፋፋይ መንፈሶች እንዲናኙ በርትቶ ለመስራቱ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፤ ‹‹እኛ ከሌለን የትግራይ ህዝብ ለአደጋ ይጋለጣል›› ከሚለው አፍራሽ ቅስቀሳው አልፎ፣ በ97ቱ ምርጫ ወቅት የኢንተርሃሞይ ጨዋታን ወደ ክርክሩ መድረክ ያመጣበትን አውድ እና በ2002ቱ ምርጫ አንድነትን ወክሎ በተምቤን ለመወዳደር የቀረበውን አቶ ስዬ አብርሃንም ሆነ አረና ፓርቲን ለማጥላላት የተጠቀመበትን ፖለቲካ መጥቀሱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በቅርቡ የሙስሊሙ መንፈሳዊ መሪዎችም ምርምራ የተደረገባቸውም ሆነ ስቅየት የደረሰባቸው በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ መርማሪዎች መሆኑን ለፍርድ ቤት መናገራቸው ተጨማሪ ማሳያ ነው፤ መቼም የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊዎች፣ ከሌሎች ብሔሮች የተገኙ መርማሪዎችም ሆነ ጨካኝ ገራፊ የፖሊስ አባላት አጥተው አይመስለኝም፤ እንዲህ አይነት አመለካከት በሕዝብ ዘንድ እንዲሰርፅ የሚሹ ፖለቲከኞችን ትዕዛዝ ማስፈፀም እንዲቻል እንጂ፡፡ ይህ እውነታም በአንዳንድ ቦታዎች ድርጅትንና ሕዝብን ቀላቅሎ ለጅምላ ፍረጃ ማጋለጡ አሌ አይባልም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ በክልሉ ላይ ብሔራዊ ሥጋት ፈጥረው ሕዝቡን አማራጭ አልባ አድርገው ድርጅቱን እንደጋሻ እንዲመለከት ቢያስገድዱ አስገራሚ አይሆንም፡፡

ሳልሳዊ ወያኔበብላታ ኃይለማርያም ረዳ ፊት-አውራሪነት በ1935 ዓ/ም ት

ግራይን በአፄው ላይ እንድታምፅ ያነቃቃው የወያኔነት እንቅስቃሴ፤ በያኔዋ የአፄው የክፉ ቀን ወዳጅ ታላቁ ብሪታኒያ ማበር ጭምር ሲቀለበስ፤ በክሽፈቱ ፅንስ ውስጥ ሌላ ትውልድ እንደሚገነግን ግልፅ ነበር፡፡ እናም የእነ ኃይለማርያምን ኢትዮጵያዊነት ጨፍልቀው የተነሱት እነ ስብሐት ነጋ፣ ያን ብርቱ የማህበረሰብ ክፍል ሰቆቃ ጠምዝዘው ከማህበረ-ባህሉ የተጣረሰ መንገድ መርጠው ሸገር ሲደርሱ፤ እነርሱኑ ካፈራ መሬት፣ የተቀለበሰውን ዳግማይ ወያኔ ረግጦ የሚነሳ ትውልድ እንደሚመጣ ዘንግተው ሰንብተዋል፡፡ ይሁንና ከላይ በመግቢያዬ የጠቀስኩትን የወልቃይቱን ትምህርት ቤት ኩነት በወቅቱ በቦታው የነበረው መምህር ሀጎስ አርዓያ (ስሙ የተቀየረ) እንደተረከልኝ፣ ራሳቸውን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ብለው በሚጠሩ ነፍጥ-አንጋች ፋኖዎች የተፈፀመ የመሆኑ እውነታ የህወሓትን የተሳሳተ ግምት ያስረግጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ የሳልሳዊ ወያኔ ወኪል እንደሆነ እየታመነ የመጣ የሚመስለው ስብስብ ሁመራ፣ ወልቃይትና ሽሬን በመሳሰሉ ከባቢዎች እንዳሻው የመንቀሳቀስ አቅም መገንባቱ ይነገራል፡፡ ድርጅቱ ከአስራ ሶስት አመት በፊት ወደ ኤርትራ በተሰደደው የህወሓት ሰው ፍሰሀ ኃይለማርያም ተድላ አስተባባሪነት መመስረቱ ይታወሳል፡፡ እንደ ትህዴን እምነት መሪው ፍስሀ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ መንግስት ደህንነቶች ነው የተገደለው፤ ከዚያን ጊዜም ወዲህ ሌላኛው የህወሓት አባል የነበረው ፀጋዬ ሞላ አስገዶም ከግማሽ መቶ ሺ አያንስም የሚባለውን ታጣቂ እንቅስቃሴ እየመራ እንደሆነ ንቅናቄውን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ድርጅቱ ለፕሮፓጋንዳ ሥራው የራሱ ቴሌቪዥንና ራዲዮ፤ እንዲሁም ‹‹መጽሔተ ብስራት›› የተሰኘች በአማርኛና ትግርኛ የምትዘጋጅ የህትመት ውጤት እንዳለው ይታወቃል፡፡

ትህዴን የመረጠው የትግል ስልት ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ሙግት ወደጎን ትተን፣ ኢትዮጵያን የሚመለከትበት መንገድ አስደማሚ ነው፡፡ በ1993 ዓ.ም አጋማሽ በለቀቀው የፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለጸው፣ ዓላማው ‹‹አንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው››፤ የንቅናቄው ጠንከር ያለ የክልሉን የድጋፍ መሰረት ስናስተውል፣ የአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ የትግራዋይ ዋነኛው መለዮ መሆኑን ያስረግጥልናል፡፡ ‹ትግራይ የኢትዮጵያ መፈጠሪያ መሬት ናት› የሚለው የስብስቡ ድምፅ፣ ‹‹ትላንት የተፈጠረች›› ከሚለን ህወሓት ጋር ያለውን ተፃርሮሽ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ ፕ/ር መሳይ ከበደም፣ ከሳምንት በፊት በበተኗት መጣጥፍ ለድርጅቱ ቡራኬያቸውን እንዲሰጡት ያስገደዳቸው፣ ይኸው የአንዲት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊነት ምስረታ ናፍቆት ይመስለኛል፡፡ አንቀፅ 39፣ ኢትዮጵያውያን እንዲበታተኑ የሚያደርግ በከፋፍለህ ግዛ የመገንጠል ፖሊሲ የተቀኘ እንደሆነ የሚከራከረው ንቅናቄው፣ ‹‹የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት የሚያምን ነው›› ሲል ህወሓት የማያውቃትን ትግራይ ይነግረ

ናል፡፡ መሪው ፀጋዬ ሞላም ‹‹የትህዴን አላማ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄም ለመመለስ እንደሚታገል›› አበክሮ ይሟገታል፡፡ የሆነው ሆኖ የ17ቱ ዓመታት መራር የትጥቅ ትግል ዋና ገፈት ቀማሽ በሆነች ምድር፣ ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ ‹‹ዱር ቤቴ!›› ማለታቸው ስለህወሓት ክሽፈት ‹‹ግዛቴ›› በሚለው መሬት በግላጭ መታወጅን ይመሰክራል፡፡

በመጨረሻም የለውጡ መንፈስ በመላ ሀገሪቱ እንዲናኝ ከትህዴን የጠቀስኳቸው መሰል መንፈሶች ጋር የሚስማማ አረዳድ ያለው አረና እና በስሩ የተሰባሰቡት ወጣቶችም ሆኑ የብሔሩ ልሂቃን፣ የትግራይን የመከራ መስቀል የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ግፉዓንም እንዲጋሩ የማሳመን ሥራ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በርግጥ ይህን መሰል የተንሸዋረረ አረዳድ ለመኖሩ ዋነኛው መነሾን ትህዴን በፖለቲካ ፕሮግራሙ እንዲህ ሲል መግለፁ መዘንጋት የለበትም፡-

‹‹ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ወያኔ (ማሌሊት) ለትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ጠበቃ መስሎ በመቅረብ በሌሎች ሕዝቦች ላይ እየፈፀማቸው ባሉ ግልፅና ስውር ወንጀሎች ሳቢያ የትግራይ ሕዝብ በገዛ አገሩ በአይነ-ቁራኛና በጥርጣሬ እንዲታይ ማድረጉ ነው፡፡››

ያለፈው አልፏል፤ በመጪው ጊዜያት ይህን ፍርሃት አሸንፎ ትግርኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ የለውጡ አካል ለማድረግ፣ ለሥርዓት ቅየራው የሚካሄደው ትግል ዘርን መሰረት ያደረገ አግላይ የመከራ መስቀልን በጋራ ለመሸከም ዝግጁ መሆንን የሚያካትት ሊሆን ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም ጠረጴዛው ላይ ያለው ምርጫ ሁለት ብቻ ነውና፤ ወይ አብሮ መውደቅ፣ አልያም በህብረት መነሳት፡፡ እስከዚያው እነ አባይ ፀሐዬን ከደርግ የሰማይ እሩምታ የከለሉ የትግራይ ተራሮች፣ ለትህዴን ጓዶችም እንደማይጨክኑ በመተማመን እናዘግማለን፡፡

ቴዲ አፍሮ .... ከገጽ 6 የዞረ

አንዱ አድርጎ ቴዲን እንደመረጠው ተሰማ፡፡ቴዲም ከሶስት ወራት በላይ በአዲስ አበባና በኬኒያ እየተመላለሰ የሙዚቃ ስራውን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ ተነግሯል፡፡ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ብራዚል እየተካሄደ የሚገኘውን የዘንድሮውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት በማድረግ እንደተለመደው ግዙፍ የቢዝነስ ተቋም የሆነው ኮካ ኮላ በተለያዩ ድምጻውያን ሙዚቃዎችን አዘጋጅቶ ራሱን እያስተዋወቀ ነው፡፡ ሙዚቃዎቹ የተሰሩት በብዙ ዓይነት ቋንቋዎችና ከተለያዩ ሀገራት በተውጣጡ ድምጻውያን ሲሆን የተቀረጹት በኮካኮላ ስቱዲዮ /Coke Studio/ ነው፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የተመረጡ ድምጻዊያን የሠሩት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አፊሲያላዊ የኮካ ኮላ ሙዚቃ ‹‹The world Is our›› /አለም የኛ ናት/ የሚል ርዕስ አለው፡፡ ይሄንን ሙዚቃ በድምፅ ለመስራት ከተመረጡት በርካታ ዘፋኞች መካከል ኢትዮጵያዊው ቴዲ አፍሮ ይገኝበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ አካባቢ ቴዲ ለሙዚቃ ኮንሠርት ወደ ኳታር ባቀናበት ወቅት ከኮካ ኮላ ካምፓኒ ስልክ ተደውሎ በዓለም ዋንጫው ሙዚቃ ላይ እንዲሳተፍ ተጠየቀ፡፡ በዚህ መሠረት ከሌሎች አፍሪካውያን ድምጻውያን ጋር በጋራ ካቀነቀነው ዘፈን በተጨማሪ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራና በግሉ የተሳተፈበት ሙዚቃ በኮካ ኮላ ስቱዲዮ መቀረጹ ተነገረ፡፡ ሙዚቃውም በ2014 የመጀመሪያ ወራት ላይ ለህዝብ እንደሚቀርብ ተገልጾ ነበር፡፡ ይሁንና በተባለበት ጊዜ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አልተለቀቀም፡፡

በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን የተሰሩ ዘፈኖች ግን በይፋ ተለቀው እየተደመጡ ይገኛሉ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራው የቴዲ ዘፈን ግን መዘግየቱ ሳያንስ በቅርቡ ደግሞ ሙዚቃው ከነአካቴው ከስቱዲዮ እንደማይወጣ ተሰማ፡፡ ይህን ተከትሎ ቴዲ አፍሮ በድረገጹ ላይ ወጣ በተባለ ጽሁፍ ድርጊቱን ኮነነ፡፡ የኮካ ኮላ ካምፓኒ ድርጊት ‹‹ሀገራችን ያዋረደ›› ጭምር መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚከታተለው ገለጸ፡፡ የኮካ ኮላ ዘመቻ በአብዛኛው የዓለም ክፍል የሚታወቀው ኮካ ኮላ በዓለም ላይ 200 ከሚበልጡ ሀገሮች ውስጥ ፋብሪካውን ተክሎ በቀን ከ1.7 ቢሊዮን በላይ የሚሆን ጠርሙስ ኮካ ይሸጣል፡፡ መመረት የተጀመረበትን 128 ኛ ዓመት በማክበር ላይ ያለው ኮካ ኮላ ካለፈው ጥር አንስቶ እስከ መጋቢት ባለው ሶስት ወራት ብቻ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አትርፏል፡፡ ኮካ ኮላ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ተቃውሞዎች ገጥመውት የሚያውቁ ሲሆን ሁሉንም በማይበገረው የገንዘብ ሀይሉ አሸናፊነቱን አረጋግጦ ነው የተወጣው፡፡ ከአረብ እስራኤሎች ጦርነት በኋላ በአረቡ ዓለም በታየው የፀረ እስራኤል ዘመቻ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአብዛኛዎቹ አረብ ሀገራት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ለፍልስጤሞች ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ጥረዋል፡፡ አረቦቹ ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ብቻ ሳይወሰኑ ፊታቸውን ወደ ፔፕሲ አዙረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ይህ ዘመቻ የኮካ ኮላን ገበያ የሚፈታተንና ከገበያ የሚያስወጣ ስላልነበረ በማስታወቂያው ላይ ባፈሰሰው ከፍተኛ በጀት የዓለማችን ቀዳሚ ለስላሳ መጠጥነቱን አስከብሮ ለመቆየት ችሏል፡፡ እ.እ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ ላይም የህንድ ገበሬዎች ኮካ ኮላ ለማሳችን የሚያስፈልገንን ውሃ ተሸማብን በማለት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ተቃውሟቸውን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በዓመት 11 ቢሊዮን ዶላር ለማስታወቂያ ብቻ የሚያወጣው ኮካ ኮላ ንፁህ የመጠጥ ውሃን በማውጣትና ዙሪያ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚመድበውን ማህበራዊ በጀት ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር በማሳደግ ራሱን ከህንድ አርሶ አደሮች ዘመቻ ተከላክሏል፡፡

የኮካ ኮላ የአቀማመም ምስጢር ድብቅነቱን ተከትሎ ሱስ አ

ስያዥ ቅመም እንዳለውና ለጤናም አደገኛ ስለመሆኑ የተወራበት ጊዜ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶም ሰዎችን ሱስ የሚያሲይዝ የኮኬይን ቅመም እንዳለው ሲነገር ኮካ ኮላ ግን ይህ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡ያም ሆኖ ኮካ ኮላ አሁንም

ድረስ በብዙ ሀገሮች ውስጥ ተወዳጅ መጠጥ ቢሆንም እንደ ሰሜን ኮሪያ በርማና ኩባ አይነት ሀገሮች ኮካ ኮላ ፋብሪካ በሀገሮቻቸው እንዲቋቋም ያልፈቀዱ ሀገራት ናቸው፡፡እ.ኤ.አ በግንቦት 8 ቀን 1886 በአትላንታ ጆርጂያ ለራስ ምታት መድሃኒት ይሆናል ብሎ መድሃኒት ቀማሚው ጆን ኤስ ቴምበር ከካካዋ ፍሬ በሶዳ ውሃ በጥብጦ ያዘጋጀው ኮካ ኮላ የተባለው መጠጥ ይኸው ዛሬ በመላው ዓለም ይጠጣል፡፡ በወቅቱ ድካምንና ራስ ምታትን እንዲሁም ድብርትንና የወንዶችን የወሲብ ፍላጎት ያነሳሳል በሚል የተቀመመው ኮካ ኮላ በአዲስ መልኩ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ምስጢራዊነቱን ጠብቆ መመረት ከጀመረ እነሆ ዘንድሮ 120 ዓመታት ሆኖታል፡፡

ዘመቻ ‹‹ኮካ አትጠጡ››የድምጻዊው አድናቂዎችና በሁኔታው ስሜታችን ተነክቷል ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ድረገፆች አማካኝነት በኮካ ኮላ ካምፓኒ ላይ መቀየማቸውን የሚያሳዩ ምስሎችንና ጽሁፎችን ለጠፉ፡፡ የካምፓኒውን ምርቶች ባለመጠጣት ተቃውሞአቸውን ለማሰማት ዛቱ፡፡ በተግባር ጉዳዩ ለመፈጸሙ

ማረጋገጫ ባናገኝም በቴዲና በኮካ ኮላ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አበሳጭቷቸው ከኮካ ምርቶች የታቀቡ ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ግን አያዳግትም፡፡ በተለይ በማህበራዊ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ሲጻፍ የነበረውን ‹‹ፀረ-ኮካ›› ዘመቻ የቅስቀሳ መልዕክቶች ስንመለት የተባለው ድርጊት መጨረሻው የት ነው እንድንል ይገፋናል፡፡ የሙዚቃው አለመለቀቅ ‹‹ሀገራችን ከመናቅ›› የመጣ ነው ከሚል ሀሳብ ጋር አያይዞ ድምፃዊው ቅሬታውን መግለጹ ተቃውሞውን እንዲደምቅ አድርጎታል፡፡ በቴዲ አፍሮ የግል ድረገጽ ላይ ወጣ የተባለው መግለጫ እንዲህ ይላል፡፡‹‹ስለ ዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ የተሰጠ መግለጫ ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም ‹‹ቴዲ አፍሮ›› ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ ሚርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ሲደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ ግንኙነቱን ሚጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባ እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ ወጥቶ ህዝብ እንዲያውቀወው እንደቻለ ቢያስገርመንም አሁን ለመገንዘብ እንደቻልነው የቴዲ ከኮካ ጋር ያለው ግንኙነት ኢትዮፒካል ንክ

በተሰኘ የሀገር ውስጥ የኤፍ.ኤም ሬዲዮ የመዝኛ ፕሮግራም አዘጋጆች አማካኝነት ያወጀው እና በሚያስገርም ሁኔታ ለኮካ የቲቪ ሥራም አድናቆቱን በመስጠት ያረጋገጠው የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ምስክር ሙሉጌታ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡

ያለጥርጥር በኮካ ኮላ ስም ቴዲ አፍሮ ለኮካ የቴሌቪዥን ስራ በማገናኘት እና በዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ተነሳሽነቱን የወሰደው የብራንዱ ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ እኛም ጥያቄን ውድ አገራችንን በመላው የዓም ዋንጫ ተመልካቾች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታ የትኩረት እይታ ስር የሚያውላት በመሆኑ እና በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ከንዋኔ ግዙፍ ቁጥር ያለው የዓለም ህዝብ ዘንድ የአገራችንን እና የህዝባችንን መልካም ገፆች ለማሳየት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ከተሟጠጠ በኋላ ነበር፡፡በመጨረሻም ምንም እንኳን በጉዳዩ ጭብጥ ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ስለተያዘው አቋም የተወሰነ መግባባት ላይ መድረስ ቴሌኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚገኙበት ቃል ተገብቶበት የተዘጋጀ ቢሆንም ውይይቱ ሙያዊ በሆነ መልኩ ያልተዘጋጀ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ አለመግባባት እንዳይከሰት ለማድረግ የጋራ መፍትሔ ለመሻት ሳይሆን ቅንነት በጎደለው መልኩ የኛን ሐሳብ ለመረዳት ነበር፡፡ ቴሌኮንፈረንሱ ሆነ ተብሎ ህጋዊ ወኪል የሆነውን ሥራ አስኪያጃችንን በጭብጦቹ ላይ ለመወያየት እንዳይሳተፍ በማግለል መካሄዱ በራሱ ሂደቱ በቅን ልቦና ላይ ያለተመሰረተ መሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡ በመሆኑም የአርቲስቱ አድናቂ ለሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ አገር ዜጎች በሙሉ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረንን ግንኙነት ያቋረጥን መሆናችንን ለመግለፅ መገደዳችን እያዘንን ስንገልፅ የዓለም ዋንጫ እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የወሰደውን እርምጃ በድጋሚ እንዲያጤነው ያደርግ ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪያችንን ስናቀርብ ብሔራዊ ጠርዝ ባለው እና በውድ አገራችን፤ በህዝባችን እና አድናቂዎቻችን ላይ ጭምር የተቃጣውን የፈሪ እና ሀገር ወዳድነት የጎደለው አሳፋሪ የክህደት እና ክብር የሚያጎድፈውን ተግባር ግን ይቅር ላለማለት ወስነናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የተጠናቀቀውን ሥራ እንዲያሰራጨው እና እንዲለቀው ግፊት ማድረጋችንን እንደምንቀጥልበት ለአድናቂዎቻችን እያረጋገጥን ከዚህ ጎን ለጎንም ከሁኔታዎች ጋር አግባብነት ያላቸው ሰላማዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የሁለቱንም ወገኖች ገፅታን እና ጥቅምን የሚጎዳ ማናቸውም ውዝግብ በማስቀረት በአድናቂዎቻችን የተጣሉብንን አደራ መተማመን እና እምነት ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡›› ቢቀር ምን ይቀርበታል? ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ከኮካ ኮላ የቀረበለትን ጥያቄ በደስታ ተቀብሎ የዓለም ዋንጫውን የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ተቀርጿል፡፡ ታድያስ መጽሔት ከአሜሪካ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ሙዚቃው እንደማይለቀቅ ከተነገረ በኋላም ኮካ ለድምጻዊው ተገቢውን የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ የተቀረፀው ሙዚቃ ንብረትነቱ የኔ ብቻ ነው የሚለው ግዙፉ የለስላሳ መጠጥ ካምፓኒ ለጊዜው ዘፈኑ ባይለቀቅም ለድምፃዊው ግን ተገቢውን ነገር እናደርጋለን የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከተመለከትነው ቴዲ ሙዚቃው ባለመለቀቁ ምንም አይቀርበትም ማለት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ድምጻዊው ከሚያገኘው ገንዘብ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም ፊት የምትታወቅበትን ዕድል አጥታለች፡፡ ቴዲም ቢሆን የደከመበት ሙዚቃ ከስቱዲዮ አለመውጣቱ ምቾት ይነሳዋል፡፡ ለምን ብሎ መጠየቁም ተገቢ መሆኑን የብዙዎቹ አድናቂዎች ሀሳብ ነው፡፡

‹‹ሾላ በድፍን››ኮካ በዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ራሱን ለማስተዋወቅ የ

ሚረዱ ሙዚቃዎች ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ደቡብ አፍሪካ ላይ ለተከናወነው የዓለም ዋንጫ ‹‹waving Flag›› በሚል ርዕስ ሶማሊያዊው ድምጻዊ ኬናንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ድምፃውያን አሰርቷል፡፡

በወቅቱ ይህ ሙዚቃ ተወዳጅ እንደነበር ይታወሳል፡፡የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር አጋር የሆነው ኮካ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ማጀቢያ የሚሆን ሙዚቃ በራሱ ስቱዲዮ መቅረጽ የጀመረው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡ ሳምባ በሚባለው የብራዚሎች ባህላዊ የሙዚቃ ስልት የተሰራው ‹‹The World Is Our›› የተሰኘው ሙዚቃ በተለያዩ ሀገራት ሙዚቀኞችና በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ ሙዚቃ ዋና አቀንቃኝ በትውልድ ብራዚላዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆነው ዴቪድ ኮሬይ ሲሆን ካለፈው መስከረም ጀምሮ ከ90 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተዘዋውሮ ሙዚቃውን መድረክ ላይ ተጫውቷል፡፡

በዲቪድ ኮሬይ በዋናነት የተሰራው ይህ የኮካ ኮላ ሙዚቃ በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን በተለያዩ ቋንቋዎች ተቀርጾ ለጆሮ በቅቷል፡፡ ከስቱዲዮ ያልወጣው የቴዲ አፍሮ ብቻ ነው፡፡ ለምን? እስካሁን መልስ የለውም፡፡ የኮካ ኮላ ሰዎች ከአትላንታ ሰጡት በተባለው መግለጫና ቴዲ አፍሮ በድረ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ሙዚቃው ስላለመለቀቁ እንጅ በምን ምክንያት እንደሆን አይጠቅሱም፡፡ ነገሩ ‹‹ሾላ በድፍን›› ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉም ነገር በፊት ሙዚቃው ያልተለቀቀው በምን ምክንያት ነው? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

‹ኮካ ሀገሪቷን ደፍሯል?›ቴዲ አፍሮ በርካታ አድናቂዎች ካሏቸው አትዮጵያዊያን የሙ

ዚቃ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ለኮካ ኮላ ሙዚቃ ሊሠራ ነው ተብሎ ሲነገር እንደ አንድ በሀገር ኩራት ተቆጥሮ በመገናኛ ብዙሀን ሲዘወርለት ነበር፡፡ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ተጠግቶ ከነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጋር ተነጻጽሮ ሲቀርብ ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የሚወክለው›› የሚል መንደርደሪያ ከስሙ በፊት መጠቀስ ጀምሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሙዚቃው አለመለቀቁ በዚያ ሁሉ ሙቀት ላይ በረዶ እንደ መጨመር ነው፡፡ ለዚያምነው (ቴዲ አፍሮ... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

Page 21: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 21

ስፖርት

የናይኪና አዲዳስ ጦርነትፊፋ ለ64ቱ ጨዋታ 33 የመሐል ዳኞችና 57 ረዳት ዳኞችን

መርጦ አዘጋጅቷል። ከ33ቱ የመሐል ዳኞች አፍሪካ፣ እስያ፣ የሰሜ

ንና ደቡብ አሜሪካ ካሪቢያን ዞን አምስት- አምስት ዳኞችን ሲያስመርጡ ላቲን አሜሪካ 6፣ ኦሽኒያ በ 2፣ አውሮፓ በ10 ዳኞች ተወክለዋል። በዚህ ሻምፒዮና ታዋቂዎቹ አርቢትሮች የሆኑት እንግሊዛዊ

ው ሃዋርድ ዌብ፣ ጣሊያናዊው ኒኮላ ሪዞሊ፣ አርጀንቲናው ኔስተር ፒታናና ብራዚላዊው ሳንድሮ ሪቺ መካተታቸው ታውቋል።

በዚህ ሻምፒዮና ላይ የጐል መስመር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል። ውሳኔዎች ሁሉ ፍትሃዊና ትክክለኛ እንዲሆኑ የጐል መስመር ቴክኖሎጂው ከፍተኛ ጥቅም አለ

ው ሲሉ ሮልፍ ዲትሪች የተሰኙ የጀርመን ካምፓኒ ባለሙያ ተናግረዋል። የጐል ኮንትሮል 14 ከፍተኛ ፍጥነት ባላቸው ካሜራዎች የሚመራ ሲሆን፤ 7ቱ (የዓለም ዋንጫ.. ወደ ገጽ 13 የዞረ)

አንዳንድ እውነታዎች ስለዓለም ዋንጫ የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞችን ተዋወቁ

ይህን አምድ ሊሊ ሞገስ ከአፕል ቫሊ ና እና ዳኒ ከሚኒያፖሊስ ያዘጋጁታል

ከሊሊ ሞገስ በዘንድሮው 20ኛው የአለም ዋንጫ የእግር ኳስ ተንታኞች ለ

ላቲኖቹ አርጀንቲናና ብራዚል የማሸነፍ ቅድሚያ ሰጥተዋቸዋል። የኳስ ሐገሯ ብራዚል የጁሊየስ ሪመት ዋንጫን ካስቀረች ወዲህ ዋንጫ የማስቀረት ዕድል ያላቸው ብራዚል፣ አርጀንቲናና ጀርመን ሲሆኑ፤ ተንታኞቹም የሁለቱ የላቲን ሐገሮች ዕድል ሰፊ መሆኑን እየተናገሩ ይገኛሉ። አርጀንቲና በ1978 እና 86፣ ብራዚል በ1994 እና በ2002 ጀርመን በ1974 እና 1990 የዋንጫ ባለቤት በመሆናቸው የዘንድሮውን ዋንጫ ያነሳ ቡድን ሁለተኛውን ታሪክ ይሰራል። አርጀንቲናና ጀርመን ብራዚል 2 ጊዜ በማስቀረት በታሪክ ብቸኛዋ ልዕለ ኃያል (የእግርኳሷ አሜሪካ) እንዳትሆን ከፊቷ የቆሙ ሃገሮች ሆነዋል። ስለእነዚህ 3ቱ አገራት ትንሽ መረጃ እናካፍላችሁ፡፡

ብራዚልምድብ 1፡- ብራዚል፣ ክሮሺ

ያ፣ ሜክሲኮና ካሜሮንአዘጋጅ አገሯ ብራዚል በፊ

ሊፕ ስኮላሪ እየተመራች ካካ፣ ሮቢንሆና ሮናልዲንሆ ጐቾን የመሰሉ ኮከቦችን ሳታካትት ሻምፒዮናው ላይ እየፋለመች ትገኛለች። አሰልጣኝ ስኮላሪ ሮማሪዮን አሰናብተው አወዛጋቢ ውሳኔ የወሰኑበትን የ1994 የአለም ዋንጫ ክስተትን ዳግም ከስተዋል። ከውድድሩ ውጪ የህብረተሰቡ የተቃውሞ ማዕበል እየናጣት ያለችው ብራዚል፣ ባላለቁ ስታዲየሞቿም ስትተች ከርማለች። ይህን በተመለከተ አስተያየቱን የሰጠው የቀድሞ የቡድኑ ኮከብ ዚኮ ‹‹የብራዚላዊያን ተቃውሞ መነሻው በኢኮኖሚው ብቻ ሳይሆን በቡድኑ እምነት ስለሌላቸው ነው።›› ሲል ፍሬድ የተባለው አጥቂ በበኩሉ ‹‹መድፈን ያለብንን ቀዳዳ የደፈን አይመስለኝም›› ሲል በስኮላሪ ቡድን እምነቱ እንደሌለው ገልጿል። ያም ቢሆን ብራዚል ብራዚል ነችና የአለም ዋንጫውን ለማስቀረት ጠንክራ እንደምትገባ ይጠበቃል። በአለም የቡድኖች የደረጃ ሰንጠረዥ 3ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ለ6ኛ ጊዜ በማሸነፍ የማይደፈር ታሪክ ለመስራት ከሁልዮ ሴዛር እስከ ዴቪድ ሉዊዝ፣ ከቲያጐ ሲልቫ እስከ ዳኒ አልቬዝ፣ ከራሚሬዝ እ

ስከ ኦስካር፣ ከናይማር እስከ ፍሬድ ከሃልክ እስከ ፓውሊንሆ ድረስ ለ20ኛው የአለም ዋንጫ በብራዚሎች የተወደሩ ጦረኞች ሆነዋል። ብራዚል በ67 ጨዋታ ድል በማስመዝገብ 210 ጐል አስቆጥራ በስኮላሬ አመራር መበርታቷን አሳይታለች።

አርጀንቲናምድብ 6፡- አርጀንቲና፣ ናይጄሪያ፣ ኢራንና ቦስኒያበፊፋ የደረጃ ሠንጠረዥ 5ኛ ደረጃ የምትገኘው የአሌሳንድሮ

ሳቤላ ስብስብ የዋንጫ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል። አርጀንቲና

የላቲን አሜሪካ ማጣሪያ በ1ኛነት በመፈፀም የሻምፒዮናው ጠንካራ ተፋላሚ መሆኗን አውጃለች። የበርካቶችንም የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። ቡድኑ በአጥቂው መስመር አስፈሪ ሲሆን፤ 5ቱ አጥቂዎች ሊዮኔል ሜሲ፣ ሰርጂዮ አጉየሮ፣ ጐንዛሎ ሄግዌን፣ ቫዝኩዌል ላቬዚና ሮድሪጐ ፓላሲዮ በጋራ በዘንድሮ የውድድር አመት ብቻ 120 ጐሎችን ማስቆጠራቸው የአገሪቱን የፊት መስመር አስፈሪ አድርጐታል። በተደጋጋሚ ጊዜ የኳስ ኮከቦችን በማፍራት የምትሞገሰው አርጀንቲና 28 አመት የሞላው የዋንጫ ድርቅ ለማስወገድ ጠንክራ እንደምትገባ አሰልጣኙ ሳቤላና ሜሲ ተናግረዋል። ‹‹የሊዮኔል ሜሲን ትክክለኛ ብቃት መውጣት ከተቻለ አርጀን

ቲና ድል ልታስመዘግብ ትችላለች።›› ሲሉ ዚኮ ተናግሯል። ከ5ቱ አጥቂዎች ውጪ ከሰርጂዮ ሮሜል እስከ ኤዝኩዌል ጋራይ፣ ከፓውሎ ዛባሌታ እስከ ሪካርዶ አልቬዝ፣ ከማርቲን ዲ. ሚቸልስ እስከ አንሄል ዲ. ማርያ ድረስ ለአርጀንቲና ድል ብራዚል የደረሱ ኮከቦች ናቸው። አሰልጣኙ አሌሃንድሮ ሳቤላ የታክቲክ እውቀታቸው የሚወራላቸው ባለሙያ በመሆናቸው አርጀንቲና ተስፋ ያደረገችውን ዋንጫ ትወስዳለች እየተባለ ነው።

ጀርመን

ምድብ 7፡- ጀርመን፣ ጋና፣ ፖርቱጋልና አሜሪካበዮአኪም ሎው ምርጥ የአሰልጣኝነት ብቃት የሚመራው የ

ጀርመን ብሄራዊ ቡድን በፊፋ የሐገራት ደረጃ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በአለም ዋንጫው ተስፋ አለው የተባለለት ቡድን ሆኗል። በማጥቃት ላይ በተመሰረተ አጨዋወቱ በርካታ ደጋፊዎችን ያፈራው የጀርመን ቡድን ምናልባት ቢተች በተከላካይ መስመር እንደሆነ ይነገራል። ጀርመኖች ቡድናቸው እንደባየር ሙኒክና ባርሴሎና በመቀባበል ላይ ባመዘነ አጨዋወት ምድብ ሁለት ላይ ትልቅ ገድሏን ትከስታለች ተብሎ ይገመታል። 7 ጊዜ ለፍፃሜ አ

ልፈው 3 ጊዜ ባለድል ሆነዋል። ከ1930 እና ከ1950 ውጪ በሻምፒዮናው ላይ አልታጡም። በማጣሪያ ውድድሩ 9 አሸንፋ 1 ብቻ ወጥታ የመጣችው ጀርመን በስብስቧ ብርታት የበርካቶችን ይሁንታ አግኝታለች። በርካቶች ጀርመኖች ግማሽ ፍፃሜ ድረስ ይጓዛሉ እያሉ ነው።

ጀርመን በ20ኛው የአለም ዋንጫ የብራዚልን የዋንጫ ፍላጐት ለማበላሸት ይችላሉ ከተባሉ 2 የአውሮፓ ሐገራት መሐል አንዷ ናት። ነገር ግን የተከላካይ ክፍሉ ድክመትና ከአማካይ ክፍሉ ጋር የመናበብ ድክመቱ ለበርካቶች ስጋት ሆኗል። ከማኑኤል ኑ

የር እስከ ፊሊፕ ላህም፣ ከፔር ሜርትሳከር እስከ ባስቲያን ሸዋንስታይገር፣ ከቶኒ ክሮስ እስከ ማሪዮ ጐትዝ፣ ከሜሱት ኦዚል እስከ ቶማስ ሙለር ድረስ የማንቻፍት ስብስብ ዋንጫውን ሊወሰድ እንደሚችል ተነግሮለታል።አውሮፓውያኑ ደቡብ አ

ሜሪካ ላይ አይችሉም

በዓለም ዋንጫው የ20ኛ የውድድር ጉዞ አውሮፓዊ የሆነ ሃገር ደቡብ አሜሪካ ተጉዞ ዋንጫ ወስዶ አያውቅም። በላቲን በተዘጋጀው ሻምፒዮና ብራዚል፣ አርጀንቲናና ዑራጓይ ውጪ ዋንጫ የወሰደ ሐገር አለመኖሩ ለጀርመንና ስፔን

ስጋት ሆኗል። በተለይ የላቲኖቹ ኮከቦች (ብራዚል፣ አርጀንቲናና ዑራጓይ) ዋንጫው ከአህጉራቸው እንደማይወጣ እየዛቱ ነው።

የተንታኞች ግምት: ብራዚላዊው ዚኮ ከሦስቱ ሃገራት ውጪ ምንም እንኳ በመጀመሪያው ዙር ከዓለም ዋንጫው ለተሰናበተችው ለስፔን ግምት የሰጠ ባለሙያ ሆኗል። የቢቢሲ ተንታኞች የሆኑት እንግሊዛዊያኑ ጋሪ ሊንከር እና ፊል ኔቪል ለአርጀንቲና፣ አለን ሺረርና ክሪስ ዋድል ለብራዚል የማሸነፍ ዕድል ሰጥተዋል። የሚገርመው 4ቱም እንግሊዛዊያን ለሦስቱ አናብስት (ለሐገራቸው ቡድን) ግምት አለመስጠታቸው ነው። እነርሱ ገመቱም አልገመቱም እንግሊዝም ጉዞዋ ያማረ አልሆነም።

የዓለም ዋንጫን ማን ያነሳል? - እግር ኳሳዊ ትንበያ

1. ስታዲዮ ጆርናሊስታ ማሪዮ ፊልሆ (ማራካኛ)በ1950 እንደተገነባ የሚነገርለት የሪዮ.ዴ. ጄኔሮው ስታዲየ

ም በአንድ ወቅት 200ሺ ተመልካችን አስተናግዷል፡፡ ዑራጓይ ብራዚልን 2 ለ1 ረትታ ለብዙዎች ብራዚላዊያን ሞት ምክንያት የሆነችበት ፍፃሜ የተካሄደው በዚህ ስታዲየም ነው፡፡ ሪዮ 2ኛዋ የቱሪስት መስህብ ከተማ ስትሆን ማራካኛ ደግሞ ለደጋፊዎች መስህብ የሆነ ስታዲየም ተደርጐ ይቆጠራል፡፡ 73,531 ተመልካች የሚይዘው ማራካኛ በአሁኑ ወቅት የብራዚል ትልቁ ስታዲየም ነው፡፡ በአለም ዋንጫው አርጀንቲና ከቦስኒያ፣ ስፔን ከቺሊ፣ ቤልጂየም ከሩሲያ፣ ኢኳዶር ከፈረንሳይ እንዲሁም 2ኛ ዙር፣ ሩብ ፍፃሜና የዋንጫውን ጨዋታ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

2ኛ. ስታድ ናሲዮናል68,009 ተመልካች የሚይዝና በሀገሪቱ በ

ትልቅነቱ 2ኛ የሆነ ስታዲየም ነው፡፡ በብራዚሊያ ከተማ የሚገኘው ይኸው ስታዲየም የ2013 የፊፋ ኮንፌዴሬሽን ካፕ መክፈቻ ጨዋታ ተስተናግዶበታል፡፡ ስዊዘርላንድ ከኢኳዶር፣ ኮሎምቢያ ከኮትዲቯር፣ ካሜሮን ከብራዚል፣ ፖርቱጋል ከጋና፣ አንድ 2ኛ ዙር፣ አንድ ሩብ ፍፃሜና ለደረጃ የሚደረጉ ግጥሚያዎችን ያስተናግዳል፡፡

3. አሬና አማዞኒያበ2013 የተገነባ ስታዲየም ሲሆን፤ የበፊት መጠርያው ስታዲ

ዮ ቪቫልዳኦ ነበር፡፡ በአማዞን ጫካ ውስጥ የተገነባ በመሆኑ ለተመልካቹ መስህብ ሆኗል፡፡ ከውድድሩ በኋላ የሙዚቃ ኮንሰርትና ባህላዊ ፕሮግራሞች እንደሚካሄዱበት ታውቋል፡፡ 42,377 ተመልካች የሚይዝ ሲሆን፤ ሬስቶራንትና ፓርኮች ይገኙበታል፡፡ በአለ

ም ዋንጫው እንግሊዝ ከጣሊያን፣ ካሜሮን ከክሮሽያ፣ አሜሪካ ከፖርቱጋል፣ ሆንዱራንስ ከስዊዘርላንድ ይጫወቱበታል፡፡

4. ስታዲዮ ማኔይሮ

ኮሎምቢያ ከግሪክ፣ ቤልጂየም ከአልጄሪያ፣ አርጀንቲና ከኢራን፣ ኮስታሪካ ከእንግሊዝ እንዲሁም የ2ኛ ዙር ጨዋታዎች ይስተናገዱበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አትሌቲኮ ማኔይሮና ክሩዜሮ የተሰኙ ክለቦች ይጫወቱበታል፡፡ 57,483 ተመልካች የሚይዝ ሲሆን፤ የዛሬ 49 አመት /በ1965/ መገንባቱ ይነገርለታል፡፡

5. አሬና ዲ ሳኦፓውሎበከተማው ከሚገኙት 3 (ስታዲየም.. ወደ ገጽ 13 የዞረ)

ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ይህንን መድረክ የከፈተልኝን ዘ-ሐበሻን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። በመቀጠልም የሚኔሶታ ሕዝብን በተለይም የስሞል ቢዝነስ ባለቤት የሆኑትን ኮንፈረንስ ሲኖረን ማስታወቂያ ለመለጠፍ ወይም እቃ ለመግዛት ስገባ በፈገግታና በፍቅር ስለሚያስተናገዱኝ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ። በዚህ አጋጣሚ ፒያሣ ማርኬት፣ ሰንሻይን የውበት ሳሎን፣ አዲስ ማርኬት፣ ሸጋ፣ ሸበሌ፣ ኢትዮማርኬትና አዲስ ትራቭልን ሳለመሰግን አላልፍም።

ለመሆኑ በየወሩ ዘ-ሐበሻ ላይ መል ዕክት እንድታስተላለፊ ያነሳሳሽ ወይም የገፋፋሽ ነገር ምንድን ነው?

ከላይ የተጠቀሰውን ጥያቄ ከብዙ አቅጣጫ ይቀርብልኛል። ጥያቄውም ምስጋናና አበረታችን በሆነ አስደሳች ቃል የተሞላ ነውና ጥያቄውን ከልብ አመሰግናለሁ። እኔ ወደዚህ ወደ ሚኒሶታ የመጣሁት በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ማርች 20/1993 ዓ.ም ነበር። አሜሪካንም የመጣሁት የልጅነት ሕልሜን እግዚአብሔር አሳክቶልኝ የሥነ መለኮት ለመማር ነበር። የመጀመሪያ ዲግሪዬን ያጠናቀቅሁት በክሮስ ካልቸራል ሚሽን እና በፓስተራል ሲሆን በ2011 ደግሞ በቤተክርስቲያን አመራር ማስተርስ አጠናቅቄያለሁ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በቤተክርስቲያን አመራር ዶክትሬቴን እየተከታተልኩ ነው። እግዚብሔርን ለመውደድ ወይም ለማገልገል ከፍተኛ ትምህርት ባያስፈልግም ለ እኔ ግን እግዚአብሔር ፍላጎቱንና ዕድሉንም ሰጥቶኛልና በ እግዚአብሔር ፀጋና ባገኘሁት ትምህርት ሕዝቤን ለማገልገል ያለኝን ጉጉት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ።

አሁን ወደ ዋናው ቁምነገር ልመለስና ለምን በዘ-ሐበሻ ወራዊ መልዕክት እንደማስተላልፍብ በአጭሩ ልነገራችሁ።

የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ በ2009-2010 አሰቃቂ ራዕይ አየሁ። ያየሁትም በጣም ከማሳዘኑ የተነሳ ዕረፍትን የሚሰጥ አልነበረም። ይኸውም ቁጥራቸው የማይታወቅ ኢትዮጵያውያን በትልቅ ገደል ታጭቀው በሕይወት እያሉ በሲኦል ጣር ሲማቅቁና ሲጮኹ አየሁ። የመከራቸውም መጠን ከሚችሉት በላይ ከመሆኑ የተነሳ እጃቸውን ወደ ላይ እያወራጩ የመውጣት ፍላጎታቸውን ያሳዩ ነበር።

እኔም ያየሁት ስቃይ ዝም የሚያሰኝ ስላልነበር ለብዙዎች ጉዳዩን ገለጽኩላቸው። በተለይም ደግሞ በ እግዚአብሔር እርዳታ በየቀኑ መጸለይ ጀመርኩ።

እግዚአብሔር ራዕይን ሲሰጥ ምሪትንም ይሰጣል። በመሆኑም ሕዝቤን በእግዚአብሔር ቃል የማጽናናበት የማበረታታበት መንገድ ሰጠኝ። ራዕዩንም የሰጠኝ አምላክ ከ እኔ ይልቅ ለፈጠረው ሕዝብ ስለሚገደው ብዙዎችን በምክርና በተለያዩ ሁኔታዎች እንዳገለግላቸው ረድቶኛል፤ እየረዳኝም ነው።

ንግግሬን ከመቋጨቴ በፊት ዘ-ሐበሻን እጅግ አድርጌ ማመስገን እፈልጋለሁ። ሕዝባችንን በፀሎትና በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ሳይሆን በምክርና በተቻላችሁ ሁሉ ለማገልገል የምትተባበሩኝን ሁሉ ከልቤ አመሰግናለሁ። ከዘ-ሐበሻ መልዕክቶችን በማንበብ የምታበረታቱኝ ሁሉ ምስጋናዬ በ

ጣም የላቀ ነው።በጸሎት ከኛ ጋር መተባበር የምትፈልጉ፡

በ1901 Portland Ave S, Minneapolis MN 55404 ታገኙናላችሁ። በየቀኑ የፀሎት ጊዜ ከ10:00am እስከ 12:00pm

የጸሎት አምልኮ የቃል ጊዜ፦ረቡዕ በ6pm (ለየት ያለ የወጣቶች ፕሮግራም አለን)ዓርብ - 6:00p – 8:00p እሁድ፡ 5:00p – 7:00pm

አስተያየት፣ ድጋፍ፣ ምክር፣ ትብብርን ማበርከት የምትፈልጉ በተጠቀሰው አድራሻ ልታገኙኝ ትችላላችሁ።

በዓለም ዙሪያ የተሰማራችሁ ወገኖች ሆይ፤ አይዟችሁ።በመዝሙር ዳዊት 68:31 መሰረት ወደ እግዚአብሔር እጃችንን እንዘርጋ። የሰማይና የምድር ፈ

ጣሪም ፀሎታችንን ሰምኖ ሊረዳንና ሊታደገን ይችላል። ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ጎብኝቶ በ እኛም ለዓለም ዘርን ሁሉ ሊጎበኝ እንደተነሳ እርግጠኛ ነኝና በርቱ።

ፀሎት የምትፈልጉ፤ ወይም ጥያቄ ያላችሁ፦ከፓስተር ደስታዬ ክራውፎርድ

በ612-225-8269 ይደውሉ።

“በየወሩ መልዕክቴን በዘሐበሻ በኩል የማስተላልፈው ራዕይ ታይቶኝ ነው” - ፓስተር ደስታዬ

አህመድ... ከገጽ 1 የዞረ

በዓሉን በንግግር የከፈተው የዘ-ሐበሻ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ የዘ-ሐበሻን አመሰራረትና ዓላማዋን አስረድቷል። “ዘ-ሐበሻ በሱዳን የ1 ዓመት የ6 ወር የስደት፣ በሊቢያ የ3 ወር እስርና በቱርክ የዓመት ከግማሽ የስደት ሕይወት ውስጥ ታስባ በሚኒሶታ የተቋቋመች የመረጃ ምንጭ ናት” ያለው ጋዜጠኛው “እነዚያ በስደት የቆየሁባቸው ሃገሮች ውስጥ የነበረው ፈተና በአሜሪካን ሃገር እንዲህ ያለውን ጠንካራ ሚዲያ ለመፍጠር ምክንያት ሆኖኛል” ሲል ገልጿል።

ስለዘ-ሐበሻ ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ፕሮፌሰር ሰለሞን ጋሻው ባደረጉት ንግግርም ዘ-ሐበሻ በሚኒሶታ ካለው ኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያሳየ የመጣውን ጠንካራ ተሳትፎ አድንቀው ዘ-ሐበሻን ለማጠናከር ሁሉም እንዲረባረብ ጠይቀዋል። በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፕሬስ አፈናና የወቅቱን ወቅታዊ ጉዳዮች የዳሰሱት ፕሮፌሰር ሰለሞን ጋሻው “ዘ-ሐበሻ ከፖለቲካው ጉዳይ በተጨማሪም እንደ ጤናዳም ያሉ በህክምና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ድረገጾችን በመጨመር ሕብረተሰቡን እያስተማረ ነው” ካሉ በኋላ ዘ-ሐበሻ በኢትዮጵያ እንዳይታይ በመንግስት የታገደ ድረገጽ ቢሆንም መረጃዎቹ ግን ሕዝቡ ጋር በተዘዋዋሪ መንገድ እንደሚደረሱ አስታውሰዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የነበረው ታዋቂው አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ “እስካሁን ድረስ የምታዩኝ በኢሳት ፈንድራይዚንግ ላይ ነበር። ኢሳትን አቋቁመን የልባችንን ተንፈስ እያልን ነው ያለነው። አሁን ለዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት እንድገኝ ጥሪው ሲቀርብልኝ የመጣሁት ትልቁ ምክንያት ሔኖክ በወጣትነት እድሜው ሰው ሃገር ላይ መጥቶ እንደማንም ሕይወቱን መኖር ሲችል ለሃገሬ ያገባኛል በሚል የበኩሉን ጥረት ዘ-ሐበሻን በመክፈት እያደረገ መሆኑን ስመለከት እንዲህ ያለ ጥረት በሰው ሃገር ላይ ሆነው የሚያደርጉ ወጣቶችን ለማገዝ ካለኝ ፍላጎት ነው” ብሏል። ታማኝ በዕለቱ ለዘ-ሐበሻ ማጠናከሪያ የሚውል የተዘጋጀውን የጨረታ ፕሮግራም የመራ ሲሆን በስፍራው የነበረው የዘ-ሐበሻ ደጋፊም በንቃት በመሳተፍ ድጋፉን አሳይቷል።

የዚህ ፕሮግራም አንዱ አካል የነበረው የዓመቱ የሚኒሶታ ምርጥ ሰው ሽልማት የነበረ ሲሆን በዚህም በከተማችን ላለፉት 25 ዓመታት እየተሰራጨ ያለውን የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ በማገልገል ለወገኖቹ ትልቁን ሥራ የሰራው ጋዜጠኛ አህመድ ዋሴ ሽልማቱን ከታማኝ በየነ እጅ ተቀብሏል። ስለአህመድ ሕይወትና ሥራ አቶ ዘውዴ በስፋት ጠለቅ ያለ መረጃ ያቀረቡ ሲሆን በስፍራው የነበረው ሕዝብም ሽልማቱ ይገባዋል ሲል የዘ-ሐበሻን ምርጫ አድንቋል። አህመድ ከሽልማቱ በኋላ ባደረገው ንግግር “ሽልማቱ ለኔ ይገባኛል ብዬ አላስብም። በዚህ ከተማ በንግዱም ዘርፍ፣ በሌላውም ነገር ሕዝቡን እያገለገሉ ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ይህ ሽልማት ለኔ ሳይሆን ለነርሱ ነው የሚገባው። ሆኖም ግን ዘ-ሐበሻ እኔን በመሸለሙ ደስ ብሎኛል፤ አመሰግናለሁ” ብሏል።

ዘ-ሐበሻን ያንብቡ! ጽፈው ያስነብቡ!

Page 22: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 22

በሊሊ ሞገስ

‹‹ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚያጠቁት የካንሰር አይነቶችና ስለመከላከያዎቻቸው በ

ሚገባ ማወቅ እፈልጋለሁ››

ከሁሉ አስቀድሜ የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩ ለማቀርብላችሁ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጡኝ በመተማመን ነው፡፡ በእርግጥ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ነኝ፡፡ ይሁን እንጂ እናቴ ከ5 ዓመት በፊት ማለትም የ16 ዓመት ታዳጊ በነበርኩበት ጊዜ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው በማህፀን ካንሰር መሆኑን ማወቄ በአጠቃላይ ለሴቶች ጠንቅ ስለሆኑት ካንሰሮች የማወቅ ፍላጎት እንዲኖረኝ አድርጎኛል፡፡ ስለ ገዳዮቹ ካንሰሮች ማወቀ ብቻ ሳይሆን በእነኚህ የካንሰር አይነቶች እንዳልጠቃ ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግም እፈልጋለሁ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች ባሰፈርኳቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ባለሙያዎችን በማማከር ጭምር ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ እንድትሰጡኝ እጠይቃለሁ፡፡ 1. ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚያጠቃቸው የካንሰር አይነቶች2. እኔም ሆንኩ ሌሎች በእነኚህ ካንሰሮች እንዳንጠቃ ማድረግ ስለሚኖርብን ጥንቃቄበአጠቃላይ ለሴቶች ጠንቅ ስለሆኑት የካንሰር አይነቶችና ስለመከላከያዎቻቸው በቂ የሆነ ማብራሪያ እንድትሰጡኝ እየጠየኩ፣ ዕድሜዬም 21 መሆኑን እገልፃለሁ፡፡ (ራሄል አበበ ነኝ)

የዶክተሩ ምክር፡- ካንሰር በአብዛኛው ከቤተሰብ የህክምና ታሪክ፣ ከምንከተለው የህይወት ዘይቤ እና ምርጫ እንዲሁም ከአካባቢው ሁኔታዎች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእርግጥ በቤተሰባዊ የጤና ታሪክ ምክንያት የሚከሰትን ካንሰር ለመቆጣጠር እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ በአካባቢ ሁኔታዎች ምክንያት የሚከሰተው ካንሰርም ቢሆን የመከላከል ዕድላችን አነስተኛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እንደ አመጋገብ፣ ክብደት፣ የእንቅስቃሴ ሁኔታ፣ ሲጋራ ማጨስና በመሳሰሉት ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ካንሰሮችን ለመከላከል ግን እንችላለን። ይህም ማለት ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ ካንሰርን ለመከላከል ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ማለት ነው፡፡

‹‹ካንሰርን የመከላከል እርምጃዎች በአብዛኛው በራሳቸው በሰዎቹ እጅ የወደቀ ነው፡፡ ሰዎች ብርቱ ጥንቃቄን ካደረጉ ራሳቸውን ከካንሰርም ሆነ ከሌሎች ከማናቸውም በሽታዎች መከላከል ይችላሉ›› ያሉት በኒውዮርክ ሲቲ በሚገኘው የስሎአን ኬተርንግ መታሰቢያ የካንሰር ማዕከል ውስጥ በጃይኖኮሎጂ የህክምና ዘርፍ ስፔሻል ሐኪም የሆኑት ሪቻርድ ባራካት ናቸው፡፡

እስካሁን ባለው ሁኔታ ከሶስት ሴቶች መካከል ሁለቱ በካንሰር የመያዝ ዕድል አይገጥማቸውም፡፡ ይህም ሆኖ ካንሰር በዓለማችን ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሴቶችን ያጠቃል፣ ይገድላልም፡፡ በ2008 ብቻ በአሜሪካ ውስጥ ከ700,000 በላይ የሆኑ ሴቶች በካንሰር በሽታ ተጠቅተዋል። ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ ከሚያጠቁት የካንሰር አይነቶች ደግሞ ከዚህ በታች የተጠቀሱት አምስቱ በዋነኝነት የሚጠቀሱና በገዳይነታቸውም የሚታወቁ ናቸው፡፡

1. የጡት ካንሰር (Breast cancer)ይህ የካንሰር አይነት ከሴቶች የካንሰር ጉዳዮች 20 በመቶው

ን ሲሆን በየዓመቱ በካንሰር ምክንያት ከሚሞቱት ሴቶች መካከል 15 በመቶ የሚሆኑትን የሚገድለው ይኸው የካንሰር አይነት መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከ8 ሴቶች መካከል አንዷ በዚህ የካንሰር አይነት እንደምትጠቃም ተረጋግጧል፡፡

2. የሳንባ እና የመተንፈሻ አካላቶች ካንሰር (Lung and bronchus cancers)

በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር አይነቶች ውስጥ 14 በመቶ የሚሆኑት የሚጠቁት በሣንባ እና በመተንፈሻ አካላቶች ካንሰር መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በየዓመቱ በካንሰር ከሚሞቱት ሴቶች መካከል 26 በመቶ የሚሆኑት ሟቾች ህመም ከዚሁ የካንሰር አይነት ጋር የተያያዘ እንደሆነም ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከ16 ሴቶች መካከል አንዷ በዚሁ የካንሰር አይነት ትጠቃለች፡፡

3. የትልቁ አንጀትና የፊንጢጣ ካንሰር (Colon and rectal cancers)

በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ህመሞች ውስጥ 10 በመ

ቶ የሚሆኑት ከትልቁ አንጀትና ከፊንጢጣ ካንሰር ጋር የተያያዙ ሲሆኑ ከካንሰር ሟቾች መካከል 9 በመቶ የሚሆኑትም በዚሁ የካንሰር አይነት የሚከሰት እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ በየዓመቱ በካንሰር ከሚሞቱት ሴቶች መካከል 26 በመቶ የሚሆኑት ሟቾች ህመም ከዚሁ የካንሰር አይነት ጋር የተያያዘ እንደሆነም ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከ16 ሴቶች መካከል አንዷ በዚሁ የካንሰር አይነት ትጠቃለች፡፡

4. የማህፀን ካንሰር (Uterine cancer)በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር አይነቶች መካከል 6 ከመ

ቶ የሚሆኑት የሚጠቁት በዚሁ የካንሰር አይነት ነው፡፡ በካንሰር ህመም ከሚሞቱት ሴቶች መካከል 6 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህመማቸው ከዚሁ የካንሰር አይነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ከ41 ሴቶች መካከል አንዷ በዚሁ የማህፀን ካንሰር አይነት እንደምትጠቃም ተረጋግጧል፡፡

5. የነጭ የደም ሴል ካንሰር በካንሰር ህመሞ ከሚጠቁ ሴቶች መካ

ከል 4 በመቶ የሚሆኑት ህመማቸው ከዚህ የካንሰር አይነት ጋር የተያያዘ ነው። በካንሰር ምክንያት ከሚሞቱት ሴቶች መካከል ደግሞ 3 ከመቶ የሚሆኑት የመሞታቸው ምክንያት ይኸው የነጭ የደም ሴል ካንሰር አይነት ሲሆን ከ53 ሴቶች መካከል አንዷ በዚሁ የካንሰር አይነት እንደምትጠቃም ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

6. የጡት ካንሰርየጡት ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ

ከሚያጠቁት የካንሰር አይነቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን ለዚህ ካንሰር መከሰት በዋነኛነት የሚጠቀሱት ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ዕድሜ፡- በጡት ካንሰር ከሚጠቁት ሶስት ሴቶች መካከል ሁለቱ ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ነው፡፡

ቤተሰባዊ ታሪክ፡- አንዲት ሴት እናቷ፣ እህቷ ወይም ልጇ በጡት ካንሰር የተያዘች ከሆነ እሷም በዚህ ካሰር የመያዝ እድሏ እጥፍ ይሆናል፡፡

የቆዳ ቀለም፡- ጥቁር ቀለም ያላቸው ሴቶች በጡት ካንሰር አንዴ ከተያዙ የመሞት ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ይህም ሆኖ ካንሰሩ ብዙውን ጊዜ ከጥቋቁር ሴቶች ይልቅ የሚያጠቃው ነጭ ቀለም ያላቸውን ሴቶች ነው፡፡ ምክንያቱም የነጮቹ ዕጢ በፍጥነት የሚያድግ በመሆኑ ነው፡፡

የጡት ህብረ ህዋሳት፡- የጡት ህብረ ህዋሳት አጀብ ብለው በብዛት የሚገኙ ከሆነ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

የጨረር ህክምና፡- ሴቶች ቀደም ሲል በደረታቸው አካባቢ የጨረር ህክምና አድርገው ከሆነ ዘግየት ብሎ በጡት ካንሰር ሊጠቁ ይችላሉ፡፡

- ከ12 ዓመት በፊት እና ከ55 ዓመት በኋላ የወር አበባ የሚያዩ ሴቶች በዚህ የካንሰር አይነት የመጠቃት ዕድላቸው ከፍ ይላል፡፡

- የሚያረግዙ ወይንም ከ30 ዓመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያረግዙ ሴቶች በጡት ካንሰር ሊጠቁ እንደሚችሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

- የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን መጠቀም ሌላው የጡት ካንሰርን የሚያስከትል ነገር ነው፡፡

- ለልጆቻቸው ጡትን የማያጠቡ- ከመጠን በላይ የወፈሩ እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች የ

ሚያዘወትሩ- በየቀኑ የአልኮል መጠጦችን በብዛት የሚጎነጩ (የኦክስፎር

ድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እንደሚያመለክተው ለሰባት ዓመታት ያህል በሳምንት ሶስት ቀን አልኮል ሲጠጡ የነበሩ 1.3 ሚሊዮን ሴቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ለጡት ካንሰር ተጋልጠዋል)

- ፅንስ ካስወረዱ በኋላ በዚሁ ምክንያት የሚከሰተውን ሕመ

ም ለማስወገድ ዳሶታይል ስቲበርስትሮል (DES) የተባለውን መድሃኒት የሚጠቀሙ።

- የወር አበባ መታየት ካቆመ በኋላ (ከ50 ዓመት በላይ) የሚደረግ የሆርሞን ህክምና፡፡

ለጡት ካንሰር መከሰት በዋነኛነት የሚጠቀሱት ምክንያቶች እንደሆኑ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

7. የሣንባ እና የመተንፈሻ አካላት ካንሰርእጅግ ገዳይ ናቸው ከሚባሉት የካንሰር አይነቶች መካከል በ

ዋነናነት የሚጠቀሰው የሣንባ ካንሰር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን የካንሰር አይነት በቀላሉ መከላከል ይቻላል። የሣንባ ነቀርሳ ካለባቸው ሴቶች መካከል 80 ከመቶ የሚሆኑት እንዲሁም ከወንዶች

ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት ሲጋራ ማጨስን በማቆም ብቻ ራሳቸውን ከዚህ ካንሰር ነፃ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በሣንባ ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከማያጨሱት ከ10 እስከ 20 ጊዜ በላይ የሰፋ ነው፡፡ ሌሎቹ ለሣንባ እና ለመተንፈሻ አካላት ካንሰር የሚያጋልጡት ምክንያቶች ደግሞ፡-

- ከሚያጨሱ ሰዎች ጋር መዋልና ማደር- ራይን ጋዝ- ኃይለኛ መርዝ (Arsenic) - ሬንጅ (Tar)- ጥላሸት (Soot)ጤናማ የሆኑ አመጋገብ፣ የአልኮል መጠጥ መቀነስና የአካል

ብቃት እንቅስቃሴን በእቅድ ማከናወን በሣምባ እና በመተንፈሻ አካል ካንሰር የመያዝ አጋጣሚን ይቀንሳል፡፡

የትልቁ አንጀት እና የፊንጢጣ ካንሰርበትልቁ አንጀት እና በፊንጢጣ ካንሰር ከሚጠቁት ሴቶች መ

ካከል 90 ከመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ50 በላይ ነው። ለዚህ የካንሰር አይነት የሚያጋልጡት ምክንያቶች ደግሞ፡-

- የግለሰቡ ወይም የቤተሰብ ከአንጀት ካንሰር ጋር የተያያዘ ህክምና በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ትናንሽ ነፍሳት፣ የሰውነት እብጠት

ና የሆድ ዕቃ ህመም- ልፍስፍስነት፣ - ሲጋራ ማጨስ- የአልኮል መጠጦች ሱሰኝነት- ከመጠን በላይ ሥጋ እና ስብነት የበዛባቸው ምግቦችን መ

መገብ እና አነስተኛ መጠን ያላቸው አትክልትና ፍራፍሬዎችን መውሰድ ናቸው፡፡

ይህንን የካንሰር አይነት ለመከላከል ቁልፉ ዘዴ በየጊዜው ምርመራ ማድረግ እና ፈጣን የመከላከል እርምጃ መውሰድ ናቸው። ትልቁ አንጀት እና ፊንጢጣ ከተጠቃ በኋላ የተጠቁት ሴሎች በአንጀት ውስጥ ለማደግ ከ10 እስከ 15 ዓመት ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም በየጊዜው የአንጀትና የፊንጢጣ ምርመራ የምና

ደርግ ከሆነ ችግሩ ወደ ካንሰርነት ከመቀየሩ በፊት ልንከላከለው እንችላለን፡፡

በቅርቡ የአሜሪካው ብሔራዊ የጤና ኢንስቲቲዩት ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ ካልሲየም እና የወተት ተዋፅኦ ምግቦች የአንጀትና የፊንጢጣ ካንሰርን ለመከላከል እንደሚያስችሉ ጠቁሟል። የጤና ኢንስቲቲዩት በ200,000 ወንዶችና በ200,000 ሴቶች ላይ ባካሄደው ለሰባት ዓመታት የዘለቀ ጥናት ካልሲየም የበዛባቸውን ምግቦች በየጊዜው መመገብ ይህንን የካንሰር አይነት ለመከላከል እንደሚያስችል አረጋግጧል፡፡

8. የማህፀን ካንሰርለማህፀን ካንሰር መከሰት በዋነኛነት የሚጠቀሰው ምክን

ያት የሆርሞን ለውጥ ነው፡፡ በተለይም ከአስትሮጂን ጋር የተያያዘ የሆርሞን ለውጥ ይህንን የካንሰር አይነት ሊያስከትል እንደሚችል ተረጋግጧል። በእንግሊዝኛ Uterine cancer ወይም Endometical ተብሎ ለሚጠራው የማህፀን ካንሰር በዋነኛነትና በመንስኤነት የሚጠቀሱት ምክንያቶች፡-- ከተለመደው አማካይ በላቀ ሁኔታ የወር አበባ መደጋገም- ለማርገዝ ያለመቻል- የኤስትሮጂን ህክምና መውሰድ- ከመጠን በላይ መወፈርና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች በብዛት መመገብ- ለጡት ካንሰር የሚወሰደውን ታሞክሲፈን የተባለውን መድሃኒት በፊትም ሆነ በአሁኑ ወቅት መውሰድ- የትናንሽ ዕጢዎች በማህፀን ውስጥ መከሰት- የዕድሜ መግፋት - የስኳር ህመም- ከአንጀት ካንሰር ጋር የተያያዘ ቤተሰባዊ የህመም ታሪክ- ከጡት ወይም ከኦቫሪያን ካንሰር ጋር የተያያዙ ግላዊ ታሪክ- የማህፀን ግድግዳ መወፈር ናቸው፡፡

የማህፀን ካንሰር የሚያጠቃው የትኞቹን ሴቶች ነው?

አብዛኛዎቹ በማህፀን ካንሰር የሚጠቁት ሴቶች ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ካንሰር ብዙውን ጊዜ የሚያጠቃው ዕድሜያቸው ከ45 እስከ 65 ባሉት ሴቶች ላይ ሲሆን ከጥቁር ሴቶች ይልቅ በነጭ ሴቶች ላይ እንደሚበረታም ተረጋግጧል፡፡

ለማህፀን ካንሰር መንስኤ የሚሆኑት ምንድናቸው?በአሁኑ ወቅት ለማህፀን ካንሰር በዋነኛነት የሚጠቀሱት

ምክንያቶች በግልፅ የሚታወቁ አይደሉም፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምክንያቶች ለአንዲት ሴት በዚህ አይነቱ ካንሰር መያዝ በምክንያትነት ሊጠቀሱ እንደሚችሉ ሳይንቲስቶች ተስማምተውበታል፡፡

- የሆርሞን መዛባት፡- በአነስተኛ ዕድሜ የወር አበባን የሚያዩ፣ በጣም ዘግይተው የወር አበባ ማየትን የሚያቆሙ (የሚያርጡ)፣ አርግዘው የማያውቁ፣ የሙሉ ጊዜ እርግዝና ያላጋጠማቸው ወይም ጥቂት ልጆችን ብቻ የወለዱ ሴቶች በማህፀን ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

- የቤተሰብ ታሪክ፡- እናቶቻቸው፣ እህቶቻቸው ወይም ሴት ልጆቻቸው በማህፀን ካንሰር የተጠቁ ሴቶች እነሱም በዚህ በሽታ የመያዝ ዕድል ሊገጥማቸው እንደሚችል ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቤተሰብ አባሎቻቸው በአንጀት ካንሰር የተጠቁ ሴቶች በማህፀን ካንሰር የመያዝ ዕድል ሊገጥማቸው እንደሚችል ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡

ከመጠን በላይ መወፈር፡- ከልክ በላይ የሚወፍሩ ሴቶች በማህፀን ካንሰር ሊያዙ ይችላሉ፡፡

የጨረር ህክምና፡- በሌላ የካንሰር አይነት ህመም ምክንያት በዳሌያቸው አካባቢ የጨረር (ካንሰር... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

የሴቶች ጤና/Womens Health

10ሩ ሴቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠቁት የካንሰር ዓይነቶች

Page 23: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 23

ለጅቡቲ ውሃ.. ከገጽ 7 የዞረሱማሊያ የመሰሉት የሰሜንና ምስራቅ አጎራባች ሀገሮችን በጋ

ራ በመሆን ልናሸንፋቸው የምንችላቸው ብዙ ጉዳዮች አሉን፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ለማጠናቀቅ ግን ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምነት ከታሪካዊ ጠላትነት ፍልስፍና ወጥታ ለታሪካዊ አጋርነት መመሥረት መሥራት ይኖርባታል፡፡ እነዚህ የሰሜንን እና ምስራቅ አጎራባች ሀገሮች ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሥራት አንድ ሰጥተው ሁለት የሚያገኙበት መሆኑን ማስጨበጥ ሲሆን ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ እነርሱ ሁለት ያገኙት ከኛ ተቀንሶ ሳይሆን አብረን በመሆናችን ከተገኘ ትርፍ መሆኑን አብረን ካልሆንን እኛም አንድ እነርሱም ሁለት አያገኙም የሚለውን ማስጨበጥ ይኖርብናል፡፡” ብዬ ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር ሲመዘን የሰሞኑ ለጅቡቲ የተሰጠው ውሃ እጅግ ጠቃሚ ጅምር አድርገን መውሰድ ይኖርብናል፡፡ ትግሉን አሁን ባለ ነባራዊ ሁኔታ ትክክል የሆነን ውሳኔ በመቃወም ሳይሆን ዘላቂ ጥቅም ልናረጋግጥ የምንችልበትን ነፃ የባህር በር የማግኘት መብታችንን ማረጋገጡ ላይ ይመስለኛል፡፡

ልክ ነው ጅቡቲ ትንሽ ሀገር ነች፡፡ ለኢትዮጵያ ግን የመተንፈሻ በር ነች፡፡ ዋነኛ መተንፈሻችን ጅቡቲ እንድትሆን ያደረጉን ደግሞ በትግራይ ነፃ አውጪ ስም ተደራጅተው ኢትዮጵያ የሚመሩ ያሉት ቡድኖች ናቸው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ በመቶ እጥፍ ከምንበልጣት ጅቡቲ ጋር በእኩል ደረጃ ልንደራደር አንችልም፡፡ በእኩል እንዳንደራደር ሀገራችንን ባህር በር አልባ ያደረጉን የትግራይ ነፃ አውጪዎች የሚያስከፍሉን ዕዳ ወደፊትም በዚህ የሚያበቃ አይመሰለኝም፡፡ በእኔ እምነት በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙት ሀገሮች ሁሉ ባለ ራዕይ መሪዎች በተመሳሳይ ወቅት መፈጠር ይህን ዕዳችንን ሊያሳጥረው ይችላል የሚል ቅን አመለካከት አለኝ፡፡

ቴዲ አፍሮ... ከገጽ 20 የዞረበማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ኮካ ኮላ አትጠጡ›› የሚሉ ኢትዮጵያ

ዊያን በብዛት ብቅ ማለታቸው፡፡ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያን ወክሎ ከተጋዘበና ሙዚቃው በስቱዲዮ ከተቀረጸ በኋላ እዚያው ታፍኖ መቅረቱ ‹‹ክብረ ነክ›› መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡ ‹‹ሀገር ተደፍራለች›› የሚሉ ሀሳቦች በስፋት እየተነሱ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ መንግስት እጁንእንዲያስገባ የጠየቁም ነበሩ፡፡ ጉዳዩ ግን የሁለት አካላት ስምምነት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሀገራዊ አጀንዳ ለመሆን ግን አይበቃም፡፡ ተራ የቢዝነስ ስምምነትና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ የውል መፍረስ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ፡፡

ኮካ ኮላ እንደአንድ የንግድ ተቋም ከድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ጋር የስራ ስምምነት አድርጓል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ተፈጻሚ ያልሆኑ ነገሮች ካሉ ቴዲ አፍሮ ህጋዊ ጥያቄ ማንሳት ይችላል፡፡ ይሄን ለማድረግም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡ እንዴት ተሠራ?ኮካ ኮላ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሙዚቃ መሪ ድምጻዊ አድርጎ የመረጠው ዴቪድ ኮሬይን ነው፡፡ ይህ ድምጻዊ ከተለያዩ ሀገራት ድምፃዊያን ጋር የየሀገራቱን ቋንቋ በመጠቀም በጋራ ሙዚቃውን ሰርቷል፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ድምጻውያን ጋር በዚያው ቁጥር ልክ አንዱን ሙዚቃ ደጋግሞ ተጫውቷል፡፡ ይሄን ዕድል ካገኙ ድምፃዊያን መካከል ቴዲ አፍሮ አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቅጅ የሆነውን ሙዚቃ ዴቪድ ኮሬይና ቴዲ በጋራ ቀርፀዋል፡፡ ኮካ ኮላ በተለያዩ ሀገራት የሙዚቃ ስቱዲዮዎች አሉት፡፡ የቴዲ አፍሮና የሌሎች አፍሪካውያን ድምጻዊያን ሙዚቃ የተቀረፀው ናይሮቢ በሚኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ሲሆን ጉዳዩን የሚከታተለውና የሚያስፈጽመው ደግሞ ማንዳላ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያው ግን ሙዚቃውን ‹የውሀ ሽታ› አደረገው፡፡መጨረሻው ምን ይሆን?

ለዚህ ጥያቴ ምላሽ መስጠት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ሙዚቃው ከስቱዲዮ እንዳይወጣ የተደረገበትን ምክንያት አለማወቃችን ከግምት ያለፈ እንዳንናገር ያስገድደናል፡፡ኮካ ኮላ ትልቅ የንግድ ስም ነው፡፡ በሀገራችን በብዛት ከሚዘወተሩ የለስላሳ መጠጦች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ድምጻዊ ቴዲ

አፍሮ ደግሞ ብዙ አድናቂዎች ካሏቸው የሙዚቃ ሰዎች አን

ዱ እንደመሆኑ መጠን ኮካ ኮላ በገበያው ላይ የሚደርስበትን ተጽዕኖ በመፍራት ችግሩን እልባት ይሰጠዋል ብለን መገመት እንችል ይሆናል፡፡በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ፀረ ኮካ›› ዘመቻ የጀመሩ የቴዲ አድናቂዎች የካምፓኒውን ስም ሊጎዱ የሚችሉ ሀተታዎችንም ደጋግመው እያስነበቡ ነው፡፡ ኮካ ለጤና ጠንቅ የሆነ ንጥረ ነገሮች እንዳሉት በመግለጽና የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ያልተለቀቀው ካምፓኒው ለኢትዮጵያ ካለው ንቀት የተነሳ መሆኑን በመዘርዘር አድማ እየቀሰቀሱ ነው፡፡

ይህን ስንመለከት ካምፓኒው በኢትዮጵያ ያለውን ተቀባይነት ላለማጣትና ስሙን ለመጠበቅ ሲል ‹የታፈነውን ሙዚቃ› ሊለቀው ይችላል፡፡ (ከቁምነገር መጽሔት የተወሰደ)

የአፍሪካ ቡድኖችን... ከገጽ 6 የዞረ ጋስኮኝ ተቆጣጥረውት ነበር፡፡በተለይ እንግሊዝ ጋስኮኝ ላይ

ተንጠልጥላ ጥሩ ለመምሰል ሞክራ ነበር፡፡ እንግሊዞች ከዚህ በፊትና አሁን ድረስ ከኋላ የተገኘውን ኳስ ለአጥቂ መጣልና ክሮስ በማድረግ የሚታወቁ ቢሆንም ጋስኮኝ በግሉ ይሄን እንዲቀይሩ ምኪንያት ሆኖ ነበር፡፡ ጋስኮኝ ደፋርነቱ ብቻ ሳይሆን ኳስ መቻሉ ከተከላካዮች ጋር ሄዶ በድፍረት ይቀበላል፡፡ ፊታቸውን አዙረው ለመሄድ ለተዘጋጁት እየጠራ ይሰጣል፡፡ እንደገና ይቀበላል፡፡ እንዲህ ሲያደርግ መሀል ሜዳው ከሁለት ወደ አራትና አምስት እያሳደገ የሰው ቁጥር እየጨመረ ወደ ፊት ፎርም ሆነው ስለሚሄዱ ማጥቃቱን በብዙ ቁጥር ከማሳደጉ ሌላ ባለጋራ ኳስ እንዳያገኙ አስችሎ ነበር፡፡ በታሪኳ እንግሊዝ ኳስ ተጫወተች የሚባለው ያኔ ነበር፡፡ይህም ጋስኮኝ ፎርም ባደራጋቸው ቅኝት ውስጥ በመግባታቸው ነው፡፡ ከዚያ በኋላ እነ ቤካም መጡ፡፡ ቤካም የመሀል ሜዳውን በቁጥር ማሳደግ ቀርቶ ያገኘውን በረጀሙ ለአጥቂ ሲጥል ጋዜጠኞችም አደነቁት ፡፡ያ ኳስ ግን እየመጣ እንግሊዝን ጫና ውስጥ እንደሚከታት እንዴት እንደጠፋቸው አስገራሚ ነበር፡፡ ጋስኮኝ መሀል ሜዳው ላይ ሁለት የነበሩትን ወደ አምስት ያሳድጋል፡፡

ቤካም መሀል ሜዳ አራት የነበሩት ወደ ሁለት ያወርድና ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ እንግሊዝና በእውቀት መጫወት እስከዛሬ ተጣልተው‹‹ጊዜ ከሚባክን ኳስ ይባክን››በሚለው ስልት ቶሎ ጎል ጋር ለመድረስ ያገኙትን ከየትም እየጠለዙና ተጠልዞ በሚመለሰው ኳስ እጠየተጠቁ አሉ ፡፡

………. ሰሞኑን አልጀሪያንም አየሁት፡፡አልጀሪያ ዘጠና ደቂቃ ሲከለከል ለአንድ አጥቂ እየጣሉ የተጣለለትም ሳያገኝ እንዲሁ ባከኑ፡፡መርተውም ተመርተውም ሲከላከሉ አፍሪካ የግርግር ቡድን እንደሆኑ እያስመሰከሩ ነው፡፡ በ12ተኛው አለም ዋንጫ ጀርመንን የመሰለ ሀያል ቡድን አልጀሪያ መጫወቻ አድርጎት ነበር፡፡ የተከላከለው ጀርመን ነበር፡፡አልጀሪያ 2ለ1 እየመሩ ያጠቁ ነበር፡፡አጥቂው መስመር ሳላ አሳድ፤ላካድራ ቤሉሚና ራባህ ማጃር እየተመራ በኳስ ቅብብል ጀርመንን አርበድበደውት ነበር፡፡የዛሬው አልጀሪያ ግን እነዚያን መምስል ቀርቶ ማስታውስ አልቻለም፡፡በተለያ አሳድን የመሰለ ቴክኒካል ተጫዋች አልጀሪያ ቀርቶ ለአፍሪካ እስካሁን አላፈራችም ፡፡ያሁኑ አልጀሪያ ፈጣንና ተከታካች ነው፡፡እንዲህ ሲባል ደግሞ ቀላል ነው ተብሎ በነሀሴ አዲስ አበባ ላይ የሚደረገው ግጥሚያ….ግን ያን ግዜ እንዴት ነው መግጠም ያለብን?

በሩጫ..በርግጫ…..በጡጫ..በቁንጥጫ…በቡጥጫ….ፈጣንና ጉልበትን ጠንከር ያሉ ስለሆነ ማስቸገራቸው አይቀርም፡፡ በተለይ ብቻ ለብቻ ካገኙ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ቤልጀም ኳስ ስለሚቀባበል ነው ያስቸገራቸው፡፡ቤሌጅየም በጉልበት ቢገባ አልጀሪያ ማሸነፍ ይችል ነበር፡፡አሁንም እኛ በጉልበት ላይ ከተመሰረትን አልጀሪያ ደስ ነው የሚለው‹‹በምፈልገወው መንገድ መጣችሁልኝ›› ብሎ ፈገግ ብሎ እንደሚቀበለን ነው፡፡የኛ ትልቁ ችግራችን የኛን ጠንካራ ነገርና የነርሱን ደካማ ነገር ሳናውቅ መግጠማችን ነው፡፡ አሁን እንደተለመደው በጉልበት ለመቋቋም መሞከራችን አይቀርም፡፡ በጉልበት አንችላቸውም ካሁኑ በኳስ ለመብለጥ መዘጋጀት ካልቻልን ያገኘውን ኳስ እየሰጠን ለመንጠቅ መሯሯጥ ነው፡፡……….

Page 24: Universal Realty Group - Zehabeshaልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤ ... ኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ

June 2014 I volume VI I No. 64 ሰኔ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 64 Page ገጽ 24

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር

ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

እርሶ የሺ እንጀራን ካልቀመሱ ደንበኞቻችንን ለምን እንደሚመገቡት ይጠይቋቸው፤

የኛ የጥራት ምስክሮቻችን ደንበኞቻችን ናቸው


Recommended