+ All Categories
Home > Documents > ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር...

ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር...

Date post: 17-Nov-2020
Category:
Upload: others
View: 2 times
Download: 0 times
Share this document with a friend
71
ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገ ራት የሚከተለውን ጉዳይ አሳውቋል፡፡ ወደ አገ ሪቷ በሚላኩ የአደራ ደብዳቤዎች ጥቅል መልዕክቶች እና .ኤም .ኤስ መልዕክቶች ላይ በሙሉ የተቀባይ ደንበኛ ሞባይል ስክክ ቁጥር እንዲኖር በማድረግ እንዲላኩ ይህም ተቀባይ ደንበኛን በአጭር የ ፅሁፍ መልዕክተ እንደመጣለት ለማሳወቅ ወቅቱን የጠበቀ እደላን ለማቀላጠፍ እንዲሁም ለማደል ከራ የሚሰጡ ማስታወቂያዎችን ለመቀነስ እንደሚረዳ ገ ልፃ Dል፡ ፡
Transcript
Page 1: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 3

የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት

የሚከተለውን ጉዳይ አሳውቋል፡ ፡

ወደ አገሪቷ በሚላኩ የአደራ ደብዳቤዎች ፣ ጥቅል መልዕክቶች እና

ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶች ላይ በሙሉ የተቀባይ ደንበኛ ሞባይል ስክክ

ቁጥር እንዲኖር በማድረግ እንዲላኩ ይህም ተቀባይ ደንበኛን በአጭር

የፅሁፍ መልዕክተ እንደመጣለት ለማሳወቅ ፤ ወቅቱን የጠበቀ እደላን

ለማቀላጠፍ እንዲሁም ለማደል ሙከራ የሚሰጡ ማስታወቂያዎችን

ለመቀነ ስ እንደሚረዳ ገልፃDል፡ ፡

Page 2: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 5

የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ በጉምሩክ መፈተሽ የሚገባቸው መልዕክቶ

ሙሉ በሙሉ ካልተሞሉ ወይም በትክክል ካልተሞሉ የከስተም ዲክላሬሽን

ፎርሞች (CN22 ወይም CN23) ጋር እየደረሱት እንደሆነ

አሳውቋል፡ ፡ ይህም በጉምሩክ አገልግሎት ላይ ችግር እየፈጠረ

በመሆኑ መልዕክቶች እዚያው የሚዘገዩበትን ሁኔታ ፈጥሯል፡ ፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ፖስታ አስተዳደሩ በደብዳቤ አሰራር ህግ

አንቀፅ 152 መሠረት ወደ ኢንዶኔዢያ መልዕክቶች ሲላኩ ከዚህ

በታች የተዘረዘሩት መረጃዎች ተሟልተው እንዲላኩ ጠይቋል፡ -

- በ CN22 እና CN23 የሚሞሉ መረጃዎች በሙሉ በእንግሊዝኛ ፣

በፈረንሳይኛ ወይም በባሃሳ ቋንቋ መሞላት ይኖርበታል፤

- ስለሚላከው ዕቃ ዝርዝር እና ሙሉ ገለፃ የእያንዳንዱን መልዕክት

ዋጋ ጨምሮ መሰጠት ይኖርበታል

- የላኪ እና የተቀባይ የስልክ ቁጥር በCN23 ፎርም ላይ መሞላት

ይኖርበታል (ከተገኘ)

- ማኝኛውም አስፈላጊና ደጋፊ ዶክመንቶች (ኢንቮይስ ፣ የኢምፖርት

ወይም ኤክስፖርት ፍቃድ እና የመሳሰሉት) ተያይዘው መላክ

ይኖርበታል፡ ፡

Page 3: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 7

የዩክሬይን ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡ የዩክሬይን መንግስት ለጊዜው Donetsk እና

Luhansk Oblasts በሚባሉ ክልሎች ላይ ሙሉ በሙሉ ሆነ

በከፊል ስልጣኑን ተግባራዊ ማድረግ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ያለ

በመሆኑ ከ20 November 2014 ጀምሮ የዩክሬይን ፖስታ

አስተዳደር ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች የሚታደሉ መልዕክቶችን

የማይቀበል መሆኑን አሳውቋል፡ ፡ ወቅታዊ የተደረገ የክልሎች ዝርዝር

እና የፖስታ ኮዶቻቸው ከዚህ በታች ባለው አድራሻ የሚገኝ መሆኑን

ገልፃ Dል፡ ፡ http://ukrposhta.ua/en/robota-

ukrposhti-v-doneckij-ta-luganskij-

oblastyax.

የዩክሬይን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራት ከላይ

ወደተጠቀሱት ክልሎች የሚተላለፉ አለምአቀፍ መልዕክቶችን

እንዳይልኩለት በትህትና እየጠየቀ ሆኖም ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ

እነ ዚህን መልዕክቶች በፖስት ሪስታንቴ መላክ የሚችሉ ሲሆን

መልዕክቶቹ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ እንደሚገባቸው አሳስቧል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም

- በዩክሬይን መንግስት ቁጥጥር ስር ያለ መልዕክቱ የሚታደልበት

አካባቢ መጠሪያ

- የወረዳው/አውራጃው (district) መጠሪያ

- የክልሉ (region) መጠሪያ

- የአዳይ ፖስታ ቤት መጠሪያ

- ፖስት ኮድ

- የአዳይ አገር መጠሪያ

- የተቀባይ ደንበኛ መደበኛ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 7 ይመልከቱ፡ ፡

Page 4: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 19

የዩራጓይ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ያሳስባል፡ ፡ ወደ ዩራጓይ ለሚልኳቸው መልዕክቶች ከዚህ በታች በተገለፀው የዓለም

አቀፍ መልዕክት መስሪያ ማዕከል ኮዶች እንዲጠቀሙ አሳውቋል፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪም

የዓለም አቀፍ ሂያጅ መልዕክት ማዘጋጃ ማዕከላት ኮዶችንም አሳውቀዋል፡ ፡

የመጪ መልዕክቶች ማዘጋጃ ማዕከል ኮዶች

ኮድ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ

መጠሪያ

የሚቀበለው የመልዕክት ዓይነ ት

UYMVDA MONTEVIDEO CPP

APERTURA

ደብዳቤ እና የታተሙ ፅሁፎች (የአየር

መልዕክቶች እና የሳል መልዕክቶች)

UYMVDE MONTEVIDEO UNIDAD

CONTENEDORES

ባዶ የመልዕክት ሸራዎች

UYMVDH MONTEVIDEO CP INT

EMS LC/AO

- አነ ስተኛ ጥቅሎች እና ጥቅሎች

- ኢ.ኤም.ኤስ

የመጪ መልዕክቶች ማዘጋጃ ማዕከል ኮዶች

ኮድ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ

መጠሪያ

የሚያዘጋጀው የመልዕክት ዓይነ ት

UYMVDB MONTEVIDEO CAMBIO

AEREO

ደብዳቤ ፣ የታተሙ ፅሁፎች ፣

አነ ስተኛ ጥቅሎች እና ጥቅሎች

(የአየር መልዕክቶች)

UYMVDD MONTEVIDEO

ENCAMINAMIENTO

AEREO

ደብዳቤ ፣ የታተሙ ፅሁፎች እና

አነ ስተኛ ጥቅሎች (የአየር

መልዕክቶች)

UYMVDE MONTEVIDEO UNIDAD

CONTENEDORES

- ባዶ የመልዕክት ሸራዎች

UYMVDH MONTEVIDEO CPINT

EMS LC/AO

- አነ ስተኛ ጥቅሎች እና ጥቅሎች

(የአየር መልዕክቶች)

Page 5: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

- EMS

የዩራጓይ ፖስታ አስተዳደር የህብረት UYMVDF የሚባለውን መልዕክት ልውውጥ ቢሮውን

የዘጋ በመሆኑ መልዕክቶች ወደዚያ እንዳይላኩ አሳስቧል፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 20

የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ከህብረቱ አባል አገራት በCN 15

ያልተደገፉ ወይም የተሟላ መረጃ ካልያዘ CN 15 ሌብል ጋር

ተመላሽ መልዕክቶች እየደረሱት መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

በመሆኑም የሃንጋሪ ፖስታ በደብዳቤ አሰራር ሬጉሌሽን አንቀጽ RL

151.8 እና በጥቅል መልዕክት አሰራር ሬጉሌሽን አንቀጽ RC

144.5 መሠረት CN 15 በሚጠይቀው መልኩ መልዕክቱ ያልታደለበት

ምክንያት ተገልጾ እንዲላክለት ጠይቋል፡ ፡

Page 6: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 21

የሴኔጋል ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ከ5 ጃንዋሪ

2015 ጀምሮ አዲስ ፖስትኮድ ተግባራዊ ማድረጉን አሳውቋል፡ ፡

አዲሱ ፖስትኮድ ባለአምስት ዲጂት ሲሆን ይህም መልዕክቱ

የሚታደልበትን ፖስታ ቤት እና የፖስታ ማደያ ዞኖችን የሚገልጽ

ነው፡ ፡ የአድራሻ አፃፃፉም ከዚህ በታች በተቀመጠው ምሳሌ

መሰረትመሆን እንደሚገባው አሳስቧል፡ ፡

Ms Madeleine Tounde Mr Bouya KA

BP 1534 24 Avenue de

la gare

27000 Ziguinchor 10000

Dakar

SENEGAL SENEGAL

አባል አገራት ትክክለኛ የፖስት ኮድ ማግኘት የሚፈልጉ

ደንበኞቻቸውን በፖስታ አስተዳደሩ ድረ-ገፅ

(http://www.laposte.sn/laposte/trouver_co

depostal.php) ላይ የሚገኘውን የፖስት ኮድ ማፈላለጊያ

በመጠቀም ማግኘት የሚችሉ መሆኑንና ትክክለኛ አድራሻ መጠቀማቸውንም

እንዲያረጋግጡ እንዲደረግ ጠይቋል፡ ፡

Page 7: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 22

የሴኔጋል ፖስታ አስተዳደር ለህብቱ አባል አገራት ወደ ሴኔጋል

የሚላኩ መልዕክቶች አድራሻ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቁልፍ

መረጃዎችን መያዝ እንደሚገባቸው ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ

- የላኪ ሙሉ ስምና አድራሻ

- የተቀባይ መደበኛ ወይ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር እና የኢ-ሜይል

አድራሻ (ከተገኘ)

- የአዳይ ፖስታ ቤት ፖስት ኮድ

Page 8: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 23

የቻይና ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት እንስሳትና

እጽዋት እንዲሁም የእንስሳትና እፅዋት ተዋጽኦ/ውጤቶችን ወደ ቻይና

ማስገባት የማይቻል መሆኑን ገልፃDል፡ ፡

ከላይ የተገለጹት እቃዎችን የያዙ የአለም አቀፍ ደብዳቤዎች ፣

ጥቅሎች ወይም ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶችን በክሎዝድም ሆነ በኦፕን

ትራንዚት በቻይና በኩል ማሳለፍ የማይቻል መሆኑን ጨምሮ

አስረድቷል፡ ፡

እንዳይተላለፉ የተከለከሉ መልዕክቶች ዝርዝር መረጃ በዋናው

የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ላይ አባሪ ተደርጎ የተላከ መሆኑን

እንገልፃለን፡ ፡

Page 9: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 30

የሲንጋፖር ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ቫፖራይዘር

(ኤልክትሮኒክ ሲጋራዎች፣ ኤሌክትሮኒክ ፒፓዎች እና የመሳሰሉትን)

እንዲሁም የሺሻ ሞላሰስ የተፈለጉበት ምክንያት ግምት ውስጥ ሳይገባ

ወደ አገሪቱ ማስገባት የማይቻል መሆኑን ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ቫፖራይዘሮች በላኪ ደንበኞች እንደ መጫዎቻ/አሻንጉሊት ፣

የኤሌክትሪክ ዕቃ ፣ የኤሌክትሪክ መለዋወጫ ወይም እንደ ዩ.ኤስ.ቢ

መሳሪያ ተደርገው የሚወሰዱ/የሚጠሩ በመሆኑ በፍተሻ ተገኝተው

ከሚያዙ ይልቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና እነ ዚህን

ዕቃዎች መላክ እንደማይቻል አስፈላጊውን መመሪያ እንዲሰጣDቸው

ፖስታ አስተዳደሩ አሳስቧል፡ ፡

Page 10: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 32

የአውስትሪያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ከእንስሳት ህክምና እና ከፋይቶሳኒታሪ/ከእጽዋት ጤና ጋር ተያያዥ

የሆኑ መልእክቶችን ተቀብሎ የማያስተናግድ መሆኑን እና ወደ ላኪ

አገር ተመላሽ የሚያደርግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

Page 11: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 32

ይመልከቱ፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 33

የቤላሩስ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት አለም አቀፍ

የአየር መልዕክቶች ማስተናገጃ አዲስ ኦፊስ ኦፎ ኤክስቼንጅ በኮድ

ስሙ MINSK AMU የተባለ መክፈቱን ይህም ከ1 December

2014 ጀምሮ ዋጋ ላላቸው የደብዳቤ መልዕክቶች አገልግሎት መስጠት

የጀመረ መሆኑን ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

በዚህም መሠረት አባል አገራት ወደ ቤላሩስ ዲስፓች ሲልኩ ከዚህ

ቀጥሎ የተዘረዘረውን የአለም አቀፍ መልዕክት ማስተናገጃ መጠሪያ

ኮድ እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡ ፡

Office of

Exchange/ኦፊስ

ኦፍ ኤክስቼንጅ

IMPC ኮድ Mail category/የመልዕክት ዓይነት

MINSK EMS BYMSQA EMS

MINSK PCI BYMSQB መተማመኛ ኖቶች/ Verification notes

MINSK PI 2 BYMSQC ሁሉም የደብዳቤ መልዕክቶች (non-

priority)

MINSK PI 3 BYMSQD ጥቅል

MINSK PI 5 BYMSQE ባዶ ሸራዎች

Page 12: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

MINSK PI 6 BYMSQF ከቻይና፣ ከሆንግ ኮንግ እና ከሲንጋፖር

ለሚላኩ ደብዳቤ መልዕክቶች (priority,

S.A.L.) ብቻ

MINSK PI 4 BYMSQI ከሩሲያ እና ካዛኪስታን ለሚላኩ ደብዳቤ

መልዕክቶች (priority, S.A.L., nonpriority)

ብቻ MINSK PI 7 BYMSQK ከሩሲያ እና ካዛኪስታን ለሚላኩ ጥቅል

መልዕክቶች (airmail, S.A.L., surface) ብቻ

MINSK AMU BYMSQL ለአየር መልዕክቶች

MINSK

AMUPI2

BYMSQG ለሁሉም የደብዳቤ መልዕክቶች (priority, S.A.L.)

ሰርኩላር ቁጥር 38

የታይላንድ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ አሳውቋል፡ ፡ የተወሰኑ የህብረቱ አባል አገራት የኢ.ኤም.ኤስ

ማደያ ዋጋ መጨመራቸውን ለማሳወቅ የዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት

ቢሮ ሰርኩላርን እንደመጀመሪያ ዘዴ አድርገው እየወሰዱ መሆኑን

ተረድቷል፡ ፡

የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክት ማደያ ዋጋን ወይም የክፍያ ስርዓትን

ከማሻሻል ጋር በተያያዘ ከፖስታ አስተዳደሮች ጋር የሚኖር ጭቅጭቅን

ለማስቀረት የታይላንድ ፖስታ አስተዳደር በኢ.ኤም.ኤስ ማደያ ታሪፍ

ላይ ያለውን አቋም እንደሚከተለው ገልፃDል፡ ፡

Page 13: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

የታይላንድ ፖስታ አስተዳደር የሚከተሉት ሁኔታዎች ካልተሟሉ የታሪፍ

ማሻሻያዎችን አይቀበልም፡

1. የኢ.ኤም.ኤስ ማደያ ታሪፍን ለማሻሻል የፈለገ ፖስታ

አስተዳደር አዲሱ ታሪፍ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚታሰብበት

ጊዜ ቀደም ብሎ ለታይላንድ ፖስታ አስተዳደር ማሳወቅ

ይኖርበታል ይህም በሁኔታው ላይ ለመወያየት እና የሁለትዮሽ

ስምምነት ላይ ለመድረስ በቂ ጊዜ እንዲኖር ያደርጋል፡ ፡

2. በሁለቱ አካላት መካከል ስምምነት ላይ መደረስ ይኖርበታል

፤ የስምምነቱም በጽሁፍ የሰፈረ መሆን እና መጠናቀቅም

ይጠበቅበታል፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 39

የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ከ

March 2015 ጀምሮ በሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት ወደ

Anguilla, Antigua እና Barbuda, Aruba,

Curaçao እና Sint Maarten, Barbados,

Bonaire, Dominica, Guadeloupe, Jamaica,

Martinique, Saint Christopher (St Kitts)

እና Nevis, Saint Croix, Saint Lucia, Saint

Thomas, እንዲሁም Trinidad እና Tobago የሚላኩ

Page 14: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

መልዕክቶችን ተቀብሎ የሚያስተላልፍ/ትራንዚት የሚያደርግ መሆኑን

አሳውቋል፡ ፡

ለበለጠ መረጃ አባል አገራት ከዚህ ቀጥሎ ባለው አድራሻ፡

Ms Elizabeth Frías

ኢ-ሜይል ([email protected]

ስልክ ቁጥር : 809–534–5838, ኤክስቴንሽን ቁጥር 211

or 89–763– 0512

በማግኘት መጠየቅ የሚቻል መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 40

የቤላሩስ ፖስታ አስዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

Page 15: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

የጥቅል ፣ አነ ስተኛ ጥቅልና የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶችን እደላ

ለማቀላጠፍ ፖስታ አስተዳደሮች ደንበኞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ

መረጃዎችን እንዲሞሉ እንዲጠይቁ አሳስቧል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ

- የተቀባይ ስልክ ቁጥር

- በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ RC 151 እና በደብዳቤ አሰራር

ህግ አንቀጽ RL 156 መሠረት በCN 22 እና CN 23 ላይ

የሚጠየቁ መረጃዎችን በሙሉ በእንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ ቋንቋ

እንዲሙሉ

- ስለሚላከው ዕቃ ይዞታ ሙሉ እና ዝርዝር መረጃ ከዕቃዎቹ ዋጋ

ጋር መሞላት እንደሚገባ አሳስቧል፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 44

Page 16: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

የካዛኪስታን መንግስት ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል አገራት

የሚከተውን ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡

በቀን 22 December 2014 በሰርኩላር ቁጥር 221

እንደተገለፀው ካዛፖስት "Kazpost" የኢ.ኤም.ኤስ አገልግሎት

የሚሰጥ እና በዩፒዩ ኮንቬንሽን መሠረት የሚጠበቁ ግዴታዎችንም

የሚፈጽም መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

Page 17: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 45

የሆንግ ኮንግ “ቻይና” ፖስታ አስተዳደር ይሰጠው የነ በረውን

የሂያጅና መጪ ፈጣን ደብዳቤ መልዕክት አገልግሎት ከ1 April

2015 ጀምሮ ያቋረጠ መሆኑን እያሳወቀ ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮም

ሆነ በኋላ የሚደርሱትን ፈጣን የደብዳቤ መልዕክቶች እንደተራ

መልዕክት የሚያስተናግዳቸው መሆኑን ገልፃDል፡ ፡

Page 18: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 49

የፊንላንድ ፖስታ አስተዳደር ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል

አገራት ከ1 ጃኑዋሪ 2015 ጀምሮ የስም ለውጥ ያደረገ ሲሆን

የስም ለውጡም ከ Itella Posti Oy ወደ Posti Ltd

መሆኑDን ገልፃል፡ ፡

የቢዝነ ስ መታወቂያ ቁጥሩ (0109357–9) ሲሆን ይጠቀምበት

የነ በሩት ስልክ ቁጥሮች እና የጎዳና አድራሻዎች አለመቀየራቸውን

የኢ-ሜይል አፃፃፍ ፎርማቱ

[email protected] እንዲሁም የድርጅቱ

ድረ-ገጽ www.posti.fi መሆኑን ከዚህ ጋር በተያያዘም የስም

ለውጡ ከድርጅቱ የመጠሪያ ስም በስተቀር የዓለም አቀፍ የሂሳብ

አካውንቶቹን የማይነ ካ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

Page 19: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 50

የሳውዲ አረቢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ወደ

ሳውዲ አረቢያ በሚላኩ መልዕክቶች ውስጥ ሽቶ መላክ የተከለከለ

መሆኑን አያሳወቀ ሽቶ የያዙ መልዕክቶችን በምንም አይነት ሁኔታ

የማያድል በመሆኑ ለላኪ ደንበኛ ተመላሽ የሚያደርግ መሆኑን

አሳውቋል፡ ፡

Page 20: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 52

የቬትናም ፖስታ አስተዳደር ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል

አገራት የሚከተለውን ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ወደ ቬትናም በተለይም ወደ ሆቺሚኒ የመልዕክት ልውውጥ ማዕከል

(IMPC code: VNSGNA) በሚላኩ መልዕክቶች ሌብል (CN 35

ወይም CP 84 እና CN 38 ዴሊቨሪ ቢሎች) ላይ የሚቀመጡ

የአውሮፕላን በረራ ቁጥር እና ሌሎች ከዲስፓች ጋር ተያያዥ የሆኑ

ዳታዎች መልዕክቱን በትክክል ጭኖ ከሚወጣው አውሮፕላን ጋር ተዛማጅ

መሆን እንዳለባቸው አሳውቋል፡ ፡

አግባብነት ያለው የመረጃ መጣጣም ከአየር መንገዱ ጋር ሊኖር

እንደሚገባ እያሳሰበ ይህ አስፈላጊ ሁኔታ ሳይሟላ ሲቀር አየር

መንገዱ መልዕክቱ ለምን በትክክለኛው አየርመንገድ እንዳልተላከ

እንዲያብራራ ይጠየቃል፡ ፡

በመሆኑን በዚህ ሳቢያ መልዕክቶች የሚዘገዩበት እድል የሚፈጠር

መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

Page 21: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 56

የሳይፕረስ ፖስታ አገልግሎት ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለው

ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡

ፖስታ አስተዳደሩ ለሁሉም አይነ ት መልዕክቶች የሚጠቀመው ለአንድ

ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ ሸራዎችን በመሆኑ አባል አገራት እነ ዚህን

ባዶ ሸራዎች ለሳይፕረስ እንዳይመልሱ አሳውቋል፡ ፡

ሆኖም ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ሸራዎችን ለሳይፕረስ ለሚላኩ

ዲስፓቾች መጠቀም የሚችሉ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

Page 22: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 57

የፓፑዋ ኒው ጊኒ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት

የመልዕክት እደላን ለማቀላጠፍ እና ለትክክለኛው ደንበኛ ለማደል

እንዲረዳ ወደ ፓፑዋ ኒው ጊኒ በሚላክ በእያንዳንዱ መልዕክት ላይ

ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቁልፍ መረጃዎች እንዲፃፉ ጠይቋል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም

- የፖስታ ሳጥን ቁጥር

- የገጠር ወይም ከተማ ስም

- ፖስትኮድ

- የአገር ስም

- የተቀባይ ስልክ ቁጥር እና ኢ-ሜይል አድራሻ /ከተገኘ/

ሰርኩላር ቁጥር 58

የሲውዘርላንድ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት

በሲውዘርላንድ በኩል በአዲኮቨርት ትራንዚት ስለሚላኩ መልዕክቶች

ስርዓት/ሂደት የሚከተለውን ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡

ደብዳቤ

Page 23: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

በሰርኩላር ቁጥር 220/2014 እንዳሳወቀው በደብዳቤ አሰራር ህግ

አንቀጽ RL 176 መሠረት ወደ ሌይቸቴንስቴይን

/Liechtenstein/ ለሚላኩ መልዕክቶችን የኦፕን ትራንዚት

አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡ ፡ በደብዳቤ አሰራር ህግ

አንቀጽ RL 211 መሠረት ለቆጠራ ወቅት ሲባል፤ በአዲኮቨርት

ትራንዚት ወደ Liechtenstein የሚላኩ መልዕክቶች በ CN

65 ቢል ተደግፈው መላክ ይኖርባቸዋል፡ ፡

የሲውዝ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት በ2015

ትራንዚት ኮምፔንዲም በምድብ 1 እና 2 ላይ በክፍል V ለተዘረዘሩ

መዳረሻ አገሮች የሚላኩ የትራንዚት አዲኮቨርት መልዕክቶችን

የሚቀበል መሆኑን አስታውሷል፡ ፡

ጥቅል

በኦፕን ትራንዚት ወደ Liechtenstein ለሚላኩ አነ ስተኛ

መጠን ጥቅል መልዕክቶችን አገልግሎት ይሰጣል፡ ፡ በጥቅል አሰራር

ህግ አንቀጽ RC 172.3 እና RC 176.2 መሠረት ጥቅሎች በ

CP 87 ቢል መካተት ይኖርባቸዋል፡ ፡

ኢ.ኤም.ኤስ

የስዊዝ ፖስታ አስተዳደር ወደ Liechtenstein የሚላኩ

ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶችን ተቀብሎ መስራቱን የሚቀጥል ሲሆን እንደ

ከዚህቀደሙ ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶች በኢ.ኤም.ኤስ ዲስፓች

ለሲውዘርላንድ መላክ ይኖርባቸዋል (በአዲኮቨርት ትራንዚት

አይላኩም)፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 63

Page 24: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

የኩራካኦ (CURAÇAO) ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት

ከ1 February 2014 ጀምሮ ከ Nieuwe Post

Nederlandse Antillen N.V. ወደ Cpost

International N.V.የመጠሪያ ስም ለውጥ ያደረገ መሆኑን

አሳውቋል፡ ፡

የፖስታ አስተዳደሩ ስልክ ቁጥሮች እና የፖስታ አድራሻዎች

ያልተቀየሩ መሆናቸውን የኢ-ሜይል አድራሻ ግን ማለቂያው

@cpostint.com መሆኑን እንዲሁም የፖስታ አስተዳደሩ

ዌብሳይት አድራሻ www.cpostinternational.com

መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

የድርጅቱን ሎጎ ከዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 63 ላይ

ይመልከቱ፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 73

የአፍጋኒስታን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራትን በደብዳቤ

አሰራር ህግ አንቀጽ RL 203.4 መሠረት በይዞታቸው ስር የሚገኙ

የድርጅቱ ንብረት የሆኑ ባዶ ሸራዎችን እንዲመልሱለት ጠይቋል፡ ፡

Page 25: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 74

የማዳጋስካር ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ወደ ማዳጋስካር ተልከው የሚታደሉ መልዕክቶች እደላ ለማቀላጠፍ

እንዲረዳ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ የአድራሻ መረጃዎች አስፈላጊ

መሆናቸውን አሳስቧል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ

- የተቀባይ ደንበኛ ሞባይ እና መደበኛ ስልክ ቁጥር እንዲሁም

የኢ-ሜይል አድራሻ (ከተገኘ)

- የአዳይ ፖስታ ቤት ፖስት ኮድ

- የላኪ ሙሉ ስም እና አድራሻ

ሰርኩላር ቁጥር 76

የጅቡቲ ፖስታ አስተዳደር ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል

አገራት ለደንበኞች SMS የመላክ አገልግሎት እና የመልዕክት

ትራኪንግ (Mail Tracking Service) አገልግሎት

መጀመሩን አሳውቋል፡ ፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የመልዕክት ጥራትን ፣ ብቃትን እና

የመልዕክት አሰራር ፍጥነ ት ከማሻሻል አንፃር የስልክ ቁጥር እና

Page 26: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

የፖስታ ሳጥን ቁጥር ወደ ጅቡቲ በሚላኩ የአደራ መልዕክቶች ፣

ጥቅሎች እና የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶች በሙሉ እንዲፃፍ ጠይቋል፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 78

የኮሪያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ከ1 August 2015 ጀምሮ በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመበት ያለው

ባለ 6ዲጂት የፖስት ኮድ ስርዓት በባለ 5ዲጂት ስርዓት የሚለወጥ

መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡

አዲሱ ፖስት ኮድ ከነባሩ ፖስት ኮድ ጋር የማይመሳሰል በመሆኑ

ሁለቱንም ፖስት ኮዶች በአንድ ጊዜ መጠቀም የማይቻል በመሆኑ አባል

አገራት ከ1 August 2015 ጀምሮ የሚልኳቸው መልዕክቶች

አዲሱን የፖስት ኮድ አድራሻ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስቧል፡ ፡

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ይመልከቱ፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 80

በፖስታል ኮንቬንሽን አንቀጽ 34 መሠረት የዓለም አቀፉ ፖስታ

ህብረት ኦፕሬሽን ካውንስል በ April 2015 የስብሰባ ፕሮግራሙ

የ2016 የቤዚክ ኤይር ኮንቬያንስ ታሪፍ 0.624 ሺህኛ SDR

ወይም 0.000624 SDR በኪሎግራም (ከአጠቃላይ

ክብደት/Gross weight) እና በኪሎሜትር እንዲሆን መወሰኑን

አስታውቋል፡ ፡

Page 27: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ይህም ታሪፍ ተለዋጭ ማሳሰቢያ እስኪሰጥ ድረስ ተግባራዊ እንደሚሆን

ጨምሮ አስታውቋል፡ ፡

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 80

ይመልከቱ፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 84

የቤላሩስ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት

የደብዳቤመልዕክት ዲስፓች አዘገጃጀት ጋር በተያያ ሚከተለውን

አስተያየት መስጠት ይፈልጋል፡ ፡

ደክመንት የያዙ የደብዳቤ መልዕክቶች (LC) እና አነ ስተኛ ጥቅል

መልዕክትን የያዙ የደብዳቤ መልዕክቶች (AO) ለየብቻ ዲስፓች

ተዘጃቶላቸው ቢላኩ የመልዕክት ስራው እንዲቀላጠፍ የሚያደርግ

መሆኑንና ይህ አይነ ቱ የዲስፓች አዘገጃጀት ዕቃ ያልያዙ የደብዳቤ

መልዕክቶች በጉምሩክ ሳይፈተሸ በቀጥታ እንዲያልፉ የሚያደርግ

በመሆኑ በፍጥነት እንዲታደሉ እንደሚያደርግ ገልፃ Dል፡ ፡

Page 28: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 88

የስፔን ፖስታ አስተደዳደር ከህብረቱ አባል አገራት በጉምሩክ ተፈትሸው የሚያልፉ

መልዕክቶች ትክክል ካልሆነ ወይም ካልተሟላ የጉምሩክ ዲክላሬሽን ሌብል (CN22 ወይም

CN23) ጋር በተደጋጋሚ እየተላኩለት መሆኑንና ይህም ለጉምሩክ አሰራር አስቸጋሪ

ከመሆኑም ባሻገር የመልዕክት ስራው ላይ መዘግየትን እያስከተለ መሆኑን ለህብረቱ አባል

አገራት ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

በስፔይን የጉምሩክ አሰራር ህግ መሠረት የጉምሩክ ፍተሻ የሚፈልግ ዕቃ የያዙ ማንኛው

አይነ ት ዓለም አቀፍ መልዕክቶች (ጥቅል፣ አነ ስተኛ ጥቅል እና ኢ.ኤም.ኤስ) በCN22

ወይም CN23 የከስተም ዲክላሬሽን ተደግፈው መላክ ይኖርባቸዋል፡ ፡

ትክክለኛ ካልሆነ ወይም ካልተሟላ የጉምሩክ ዲክላሬሽን ሌብል ጋር የሚላኩ መልዕክቶች

በጉምሩክ ተቀባይነ ት የሌላቸው በመሆኑ ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ተቀባይ ፖስታ አስተዳደር

ያልተሟሉ መረጃዎችን እንዲያሟላ ፤ የተሳሳቱ መረጃዎችንም እንዲያስተካከል የሚደረግ

ሲሆን ይህም የመልዕክት ስራው እንዲጓተት የሚያደርግ በመሆኑ በመልዕክት ጥራት ላይ

ቀጥተኛ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል፡ ፡

በመሆኑም የስፔን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራት CN22 እና CN23

የከስተም ዲክላሬሽን ሌብሎች በትክክል መሞላታቸውን እያረጋገጡ ጠይቋል፡ ፡ በደብዳቤ

አሰራር ህግ አንቀጽ RL156 እና በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ RC151 መሰረት

ከዚህ በታች የተዘረዙ መረጃዎች በጉምሩክ ዲክላሬሽን ሌብል ላይ መሙላታቸውን ማረጋገጥ

አስፈላጊ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

- ፎርሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሞላቱን

- የእቃው ይዘት ሙሉ ዝርዝር መረጃና የእያንዳንዱ እቃ ትክክለኛ ዋጋ

- ከተቻለ የላኪና የተቀባይ ደንበኞች ስልክ ቁጥሮች

- ማንኛውም አስፈላጊ ዶክመንቶች (ኢንቮይስ ፣ የላኪ እና አስመጪ ፍቃድ፣

የሳኒታሪ ሰርተፊኬት እና የመሳሰሉት) በላይኛው የመልዕክቱ አካል ላይ

መለጠፉን

Page 29: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 89

የአንጎላ ፖስታ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሱ መረጃዎችን በሚላኩ

ጥቅሎች ላይ ማስፈር አስፈላጊ መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት ማሳወቅ

ይፈልጋል፡ ፡

- የላኪ እና የተቀባይ ሙሉ አድራሻ

- የእቃው ብዛት እና የእናዳንዱ ዕቃ ዋጋ እንዲሁም የኢንቮይሱ

አጠቃላይ የዋጋ ድምር

ከላይ የተገለፀው መረጃ ሳይካተት ሲቀር የጉምሩክ ፍተሻ ስራው የሚዘገይ

መሆኑን እና ለእቃው/ለመለልዕክቱ ግምታዊ ዋጋ የሚሰጥ መሆኑን

ገልፃ Dል፡ ፡

Page 30: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 91

የአዘርባጃን ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለው

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

የመልዕክት እደላ ጥራትን እና የጉምሩክ ፍተሻ/ቁጥጥር ስራን

ለማቀላጠፍ አባል አገራትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጉዳዮችን

እንዲያሟሉ በትህትና ጠይቋል፡ ፡

- በCN 23 ከስተም ዲክላሬሽን ፎርም ላይ የተቀባይ ደንበኛ ሙሉ

ስም እና አድራሻ እንዲሁም ስልክ ቁጥር (ከተገኘ)

እንዲያሰፍሩ፡ ፡

- በዓለም አቀፉ ፖስታ አሰራር ህግ በተለይም በደብዳቤ አሰራር

ህግ አንቀጽ RL 156 እንዲሁም በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ

RC 151 መሠረት የCN 23 እና CN 22 ከስተም ዲክላሬሽን

ፎርም ላይ የሚጠየቁ መረጃዎች በአግባቡ ተሞልተው እንዲላኩ፡ ፡

Page 31: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 94

የጃማይካ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ጠይቋል፡ ፡

ወደ ጃማይጀካ ተልከው በሚታደሉ መልዕክቶች ላይ የተቀባይ ደንበኛ ቀጥታ

ወይም ሞባይል ስልክ ቁጥር (ከተገኘ) በማስፈር መላክ እንደሚገባ

እያሳሰበ ይህም የጃማይካ ፖስታ አስተዳደር የተቀበላቸውን መልዕክቶች

ለደንበኞች መልዕክት እንደመጣላቸው በአጭር ጽሁፍ መልዕክት (SMS)

በማሳወቅ መልዕክቶቹን ሳይዘገዩ ማደል እንደሚያስችለው እንዲሁም

የማኑዋል አድቫይሶችን ቁጥር ለመቀነ ስ እንደሚያግዘው ገልፃ Dል፡ ፡

Page 32: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 95

የካዛኪስታን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ጠይቋል፡ ፡

ወደ ካዛኪስታን ተልከው በሚታደሉ በሁሉም አደራ ደብዳቤዎች እና ጥቅል

መልዕክቶች ላይ የተቀባይ ሞባይል ስልክ ቁጥር (ከታወቀ) ላኪ ደንበኞች

አንዲያሰፍሩ እዲያደርጉ ፤ ይህም ተቀባይ ደንበኞችን በአጭር የጽሁፍ

መልዕክት (SMS) ፖስታ እንደመጣላቸው ለማሳወቅ የሚረዳና ወቅታዊ

የመልዕክት ዕደላ ስራን የሚያቀላጥፍ እንዲሁም የዕደላ ሙከራ

ማስታወሻዎችን (አድቫይሶችን) አስፈላጊነት ለመቀነ ስ የሚየስችለው

መሆኑን ጨምሮ ገልፃ Dል፡ ፡

Page 33: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 96

የኖርዌይ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት በኮፐንሃገን

አለማቀፍ የመልዕክት ማዕከል ይጠቀምበት በነበረው የ IMPC ኮድ (IMPC

code: DKCPHK) ላይ ለውጥ ያደረገ መሆኑን ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ከ10 June 2015 ይህ IMPC ከደብዳቤ መልዕክት በተጨማሪ የጥቅል መልዕክቶችንም የሚያስተናግድ ይሆናል፡ ፡

የፖስታ ቤቱ IMPC ኮድ እና መጠሪያ ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መሠረት የተለወጠ መሆኑን ያረጋግጡ፡ ፡

IMPC ኦፕሬተር ኮድ ፡ NOA

IMPC ኮድ: DKCPHZ

IMPC ባለ 12 ካራክተር ስም፡ CPH ETOE NOA

IMPC ባለ 32 ካራክተር ስም፡ COPENHAGEN Z ETOE NOA

ከዚህ ቀደም የነ በረው IMPC ኮድ እና ተያያዥ ስሞች በቀጣይ የማያገለግሉ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

Page 34: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 97

የታላቋ ብሪታንያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የCN 08 አቤቱታዎች እና

የዘገዩ/የጠፉ መልዕክቶች አቤቱታዎችን መላኪያ ትክክለኛ ዝርዝር አድራሻን ማስታወስ

ይፈልጋል፡ ፡

ለደብዳቤ መልዕክት አቤቱታዎች የህብረቱ አባል አገራት CN08 አቤቱታዎች እና ሌሎች

ተያያዥ አቤቱታዎቻቸውን በኢሜይል አድራሻ

[email protected] እንዲልኩ ይህም ተመራጭ የመገናኛ ዘዴ

መሆኑን አሳስቧል፡ ፡ አቤቱታዎቹን ኢ-ሜይል ለማድረግ የማያስችሉ አስቸጋሪ ሁኔታ ከተፈጠረ

ትክክለኛው የፖስታ አድራሻ እንደሚከተለው ይሆናል፡ ፡

Royal Mail International Team P.O.Box 740 STOKE ON TRENT ST1 5XZ GREAT BRITAIN

አቤቱታዎች በፖስታ በሚላኩበት ወቅት በአደራ የአየር መልዕክት መላክ እንደሚገባ እና ቀደም

ሲል የቀረቡ አቤቱታዎች ወይም ተመሳሳይ አቤቱታዎች (duplicate

inquires/CN08) መላክ እንደማይገባ ከተላኩ ግን የመልስ አሰጣጥ ስራው ላይ

መዘግየትን የሚፈጥር መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

በተመሳሳይ ለጥቅል መልዕክት አቤቱታዎች IBISን (Internet Based Inquiry

System) መጠቀም የሚመረጥ ሰሆን ይህን ስርዓት ለመጠቀም የማያስችል አስቸጋሪ ሲሆን

CN08 ፎርሞች ከዚህ ቀጥሎ ባለው ኢ-ሜይል አድራሻ

[email protected] መላክ እንደሚቻል፡ ፡

ኢሜይል ለመጠቀም አስቸጋሪ ከሆነ ደግሞ በሚከተለው ፖስታ አድራሻ በአደራ የአየር መልዕክት

እንዲላኩለት ጠይቋል፡ ፡

Parcelforce Worldwide Enquiry Center Enquiries Manager 2 Denby Dale Road WAKEFIELD WF1 1AA GREAT BRITAIN

Page 35: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 100

የዚምባቡዌ ፖስታ አስተዳደር ሂያጅ ጥቅል ፤ ደብዳቤ እና ኢ.ኤም.ኤስ

መልዕክቶችላይ ላኪ ደንበኞች ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መረጃዎች ማሟላታቸውን

እንዲያረጋግጡ የህብረቱ አባል አገራት ጠይቋል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ

- የተቀባይ ሞባይል ስልክ ቁጥር እና ኢ-ሜይል አድራሻ (ከተገኘ)

- በCN 22 እና CN 23 ላይ የተጠየቁ መረጃዎች በሙሉ መሞላታቸውን

- ሙሉ እና ዝርዝር የመልዕክቱ ይዘት ከዕቃው ዋጋ ጋር

ከላይ የተገለፁት መረጃዎች ሲሟሉ የጉምሩክ ፍተሻ ስራን የሚያቀላጥፍ

መሆኑን አስረድቷል፡ ፡

Page 36: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 101

የፊንላንድ ፖስታ አስተዳደር በዓም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል አገራት

ይዞታ ስር ሊገኙ የሚችሉ የፖስታ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ ባዶ

ጀሸራዎችን እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡

ሰርኩላር ቁጥር 103

የዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት በ20015.1 ባደረገው የፖስታል ኦፕሬሽን

ካውንስል (POC) ስብሰባ በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ጀነ ራል

ሬጉሌሽን አንቀጽ 104.9.2 መሠረት በደብዳቤ እና ጥቅል ሬጉሌሽን

ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሃሳቦችን በመመርመር እንዲጸድቁ ያደርጓል፡ ፡

እነ ዚህም ማሻሻያዎች በዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ላይ የቀረቡ ሲሆን

ተግባራዊ የሚሆንበትም ተገልፃ Dል፡ ፡

Page 37: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 104

የቬትናም ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

በሃኖዪ እና ሆቺሚንህ የሚገኙ ሁለት የመልዕክት ልውውጥ ቢሮዎቹን መጪ

መልዕክቶችን በመረከብ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ወደቦች እንዲያሰራጭ

የወሰነ መሆኑንና ግቡም ፈጣን የመልዕክት እደላን መፍጠር መሆኑን

ገልፃ Dል፡ ፡

በመሆኑም የቬትናም ፖስታ አስተዳደር በዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር

ቁጥር 104 አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ፖስትኮድ

መሠረት መልዕክቶችን በመዘርዘር ወደ ትክክለኛው የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ

እንዲልኩለት ጠይቋል፡ ፡

Page 38: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 105

የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ቁጥራቸው ብዙ የሆነ በቂ አድራሻ የሌላቸው

አደራ እና ተራ የደብዳቤ መልዕክቶች እየደረሱት መሆኑን ለህብረቱ አባል

አገራት አሳውቋል፡ ፡ እነ ዚህ መልዕክቶች የቤት ወይም የጎዳና ቁጥር

የሌላቸው ሲሆን የተቀባይ ስልክ ቁጥር ፤ ከተማ እና ፖስት ኮድ ብቻ

የተፃፈባቸው መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡

የደንበኞችን አቤቱታ ለማስቀረት የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ላኪ ፖስታ

አስተዳደሮች በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL 125.3.3 ላይ

የሰፈረውን ድንጋጌ እንዲያሟሉ ጠይቋል፡ ፡

ከላይ የተገለፀውን ድንጋጌ ባለመከተል የሚላኩ መልዕክቶችን የሃንጋሪ

ፖስታ አስተዳደር የማያድል መሆኑንና መልዕክቶቹንም ከ CN15 ሌብል

ጋር ለላኪ አገር ተመላሽ የሚያደርግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

Page 39: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 106

የኮሎምቢያ ፖስታ አስተዳደር (Servicios Postales Nacional S.A 4–

72) የመልዕክት ፍሰትን ፣ የመልክት ለማዘጋጀት የሚወስደውን ጊዜ እና የዕደላ

ፍጥትን ለማሻሻል መልዕክት የሚልኩና የሚቀበሉ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮዎችን ያዋቀረ

መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት አሳውቋል፡ ፡

ፖስታ አስተዳደሮችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የዓለም አቀፍ መልዕክት ማዘጋጃ

ማዕከሎች/international mail processing centres (IMPCs)

ኮዶችን እንዲቀሙ ጠይቋል፡ ፡

IMPC

ኮድ

IMPC ስም የመልዕክት

ምድብ

የመልዕክት

ዓይነ ት

የመልዕክት

ፍሰት

የማዕከሉ

አገ/ት

COBAQA BARRANQUILLA Surface

non-

priority

and

surface

priority

ጥቅል፣

ደብዳቤ፣

ኢ.ኤም.ኤስ

እና ባዶ

ሸራዎች

መጪ መልዕክት ብቻ

መልዕክት ልውውጥና መልዕክት ክፍል

COBOGC BOGOTA C IMPORT EXCHANGE OFFICE

Air,

S.A.L.,

surface

non-

priority

and

surface

priority

ጥቅል፣

ደብዳቤ፣

ኢ.ኤም.ኤስ

እና ባዶ

ሸራዎች

መጪ መልዕክትና ትራንዚት መልዕክት

መልዕክት ልውውጥና መልዕክት ክፍል

COBOGG BOGOTA G EXPORT EXCHANGE

Air,

S.A.L.,

surface

ጥቅል፣

ደብዳቤ፣

ኢ.ኤም.ኤስ

ሂያጅ መልዕክትና ትራንዚት

መልዕክት ልውውጥና መልዕክት

Page 40: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

OFFIC non-

priority

and

surface

priority

እና ባዶ

ሸራዎች

መልዕክት ክፍል

ሰርኩላር ቁጥር 107

የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት እ.ኤ.አ 2009 በተላከው

ሰርኩላር ቁጥር 33 ላይ ያሳወቀውን ጉዳይ ማስታወስ ይፈልጋል፡ ፡

የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ወደ Timor-Leste (Dem. Rep) ለሚላኩ

መልዕክቶች የትራንዚት አዲኮቨርት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ሆኖም ግን ከቲሞር

ሌስቴ ውጭ ወደ ሌላ አገር የሚላኩ መልዕክቶች ሲደርሱት እንደሚስሴንት መልዕክት

በመቁጠር ክፍያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡

በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL 211.1.5 መሠረት የኢንዶኔዢያ ፖስታ ለህብረቱ

አባል አገራት እንደየአገሩ ምድብ ከዚህ በታች በተገለፀው የሚሴንት ታሪፍ መሠረት

ክፍያ የሚጠየቁ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

የመዳረሻ አገር የማጓጓዣ ክፍያ ታሪፍ

ሃንድሊንግ ክፍያ

ተጨማሪ ክፍያ

አጠቃላይ የሚሴንት መልዕክት ክፍያ

ምድብ

አገራት በኪ.ግ (SDR)

በኪ.ግ (SDR)

በኪ.ግ (SDR

)

በኪ.ግ (SDR)

1 ደቡብ ምስራቅ ኤሲያ አባል አገራት

1.804 0.195 2 3.999

2 ኤሲያ-ፓሲፊክ 3.492 0.195 1 5.687

3 አፍሪካ 6.926 0.195 2 9.121

4 አውሮፓ 7.566 0.195 2 9.761

5 ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ

10.185 0.195 2 12.385

Page 41: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 109

የሊብያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፤

በ3 August 2011 በተደረገው የአገሪቱ ትራንዚሽናል ካውንስል

አዋጅ ከዚህ በፊት Libyan Arab Jamahiriya ተብሎ ይጠራ

የነ በረው የአገሪቱ መጠሪያ ስም ወደ "Libya" የተቀየረ መሆኑን

እንዲሁም የአገሪቱ ብሔራዊ ሰንደቃላማም የተለወጠ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

Page 42: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 110

የዴንማርክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ወደ ዴንማርክ

የሚላኩ መጽሄቶች እና ጋዜጣዎች የያዙ የደብዳቤ መልዕክቶች በCN

22 የጉምሩክ ዲክላሬሽን ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲሁም

ከመሰራጨታቸው በፊት በጉምሩክ እንዲፈተሸ አዲስ የወጣው የአገሪቷ

ብሔራዊ ህገደንብ እንደሚያስገድድ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ይህ ህገደንብ ከ 1 July 2015 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሆነ

ተገልፃ Dል፡ ፡

Page 43: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 114

የናይጄሪያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የፖስታ አስተዳደሩ

ንብረት የሆኑ በይዞታቸው ስር ሊገኙ የሚችሉ ባዶ የኢ.ኤም.ኤስ

ሸራዎችን በተቻለ ፍጥነ ት እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡

በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL 203 መሠረት ፖስታ አስተዳደሮች

ወደ ናይጄሪያ የሚልኳቸውን የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክት ዲፓቾች በናይጄሪያ

ፖስታ አስተዳደር ሰማያዊ ሸራዎች በመጠቀም መላክ የሚችሉ መሆኑን

አሳስቧል፡ ፡

በተጠቀሰው ጊዜ ሸራዎቹ የማይመለሱለት ከሆነ በደብዳቤ አሰራር ህግ

አንቀጽ RL 203 ተ.ቁ 9 እና 10 ላይ በተጠቀሰው መሠረት እነዚህን

ሸራዎች ለመተካት ያወጣውን ወጪ ለመሸፈን ፖስታ አስተዳደሩ ክፍያ

የሚጠይቅ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

Page 44: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 115

የዩናይት ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፖስታ አስተዳደር ከአሜሪካ በስህተት

የተላኩ በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ኮንቬንሽን አደገኛ ዕቃዎች ተብለው

የተፈረጁ መልዕክቶች ሲደርሱ በተሻሻለው ከዚህ በታች በተገለጸው የኢ-

ሜይል አድራሻ ሪፖርት እንዲያደርጉለት ለህብረቱን አባል አገራት

አሳውቋል፡ ፡

ፖስታ አስተዳደሮች ከላይ የተጠቀሱት ዓይነ ት ጉዳዮች ሲያጋጥሙ

የመልዕክቶቹን CN 13 መረጃዎች (የላኪና የተቀባይ ስም ፣

የመልዕክቱን ሬጂስተር ቁጥር እንዲሁም የመልዕክቱን ይዘት ዝርዝር መረጃ

ጨምሮ) በኢሜይል አድራሻ [email protected] ሪፖርት

እንዲያደርጉለት ጠይቋል፡ ፡

Page 45: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 116

የዩናይት ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፖስታ አስተዳደር የመጪ አደራ መልዕክቶች

አገልግሎት አሰጣጡ ገጽታ ላይ ለውጥ የሚያደርግ መሆኑን ለህብረቱ አባል

አገራት ማሳወቅ ይወዳል፡ ፡

ከ1 October 2015 ጀምሮ በዩፒዩ ሰፕሊሜንታሪ ሪመነሬሽን

ፕሮግራም ለሚሳተፉ አገሮች ብቻ የመጪ መልዕክቶች ትራኪንግ እና የእደላ

መረጃ በwww.usps.com እንዲታይ የሚደረግ ሲሆን ለሌሎች አገሮች

ግን መረጃው በፖስታ አስተዳደሩ ድረገጽ ላይ የማይታይ መሆኑን

ገልፃ Dል፡ ፡

Page 46: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 118

የራሺያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ከዚህ በታች

የተዘረዘሩ 5 የመልዕክት ልውውጥ ቢሮዎቹን የዘጋ መሆኑን ማሳወቅ

ይፈልጋል፡ ፡

- MOSKVA PCI–1 (RUMOWB);

- MOSKVA PCI–1 SURFACE (RUMOWH);

- MOSKVA PCI–4 (RUMOWI)

- MOSKVA MINSK AMB (RUMOWP)

- MOSKVA PCI–15 (RUMOWK)

ከ1 August 2015 ጀምሮ የደብዳቤ መልዕክቶች አዲስ ወደተከፈተው

የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ በሚከተለው አድራሻ መላክ እንደሚኖርባቸው

ገልፃ Dል፡ ፡

MOSKVA PCI–21 (IMPC code: RUMOWS)

Marushkinskoye settlement

near Sharapovo village

MOSCOW

102975

Page 47: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 119

የአርሜኒያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ በጉምሩክ ሊፈተሹ የሚገባቸው ዕቃዎችን የያዙ

መልዕክቶች ካልተሟላ ወይም ትክክለኛ መረጃ ካልያዙ CN 22 እና CN

23 ከስተም ዲክላሬሽን ፎርሞች ጋር እየተላኩለት እንደሆነ ይህም

በጉምሩክ አሰራር ላይ ችግር ከመፍጠሩም ባሻገር የመልዕክት ስራው ላይም

መዘግየትን እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፃ Dል፡ ፡

በአርሜኒያ የጉምሩክ አሰራር ህግ መሠረት ማንኛውም በጉምሩክ ተፈትሾ

ማለፍ ያለበትን ዕቃ የያዘ ዓለም አቀፍ መልዕክት (ጥቅል፣ አነ ስተኛ

ጥቅል እና ኢ.ኤም.ኤስ) በCN 22 እና CN 23 ከስተም ዲክላሬሽን

መደገፍ ይኖርበታል፡ ፡

በዚህም መሠረት የአርሜኒያ ፖስታ አስተዳደር ላኪ ፖስታ አስተዳደሮችን

በደብዳቤ አሰራር ህግ አነ ቀጽ RL156 እንዲሁም በጥቅል አሰራር ህግ

አንቀጽ RC151 ላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ሟሟላት እንደሚገባቸው

በተለይም ፡ -

- በCN22 አና CN23 ከስተም ዲክላሬሽን ላይ የሚጠየቁ መረጃዎች

በአንግሊዝኛ ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በተቀባይ አገር ተቀባይነ ት ባለው

ቋንቋ መሞላት እንዳለበት

- የእቃው ይዘትና የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በተሟላ እና በትክክል መግለጽ

- የላኪ እና የተቀባይ ስልክ ቁጥር (ከተገኘ) በCN 23 ፎርም ላይ

ማስፈር

- ማንኛው አስፈላጊ የሆነ ጠቃሚ ዶክመንት(ኢንቮይሶች ፣

የላኪ/የአስመጪ ፈቃድ ፣ የጤና ሰርተፊኬት ወዘተ…) በመልዕክቱ

ውጫዊ አካል ላይ አያይዞ መላክ እንደነሚገባ አሳውቋል፡ ፡

Page 48: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 121

የኪርጂዝስታን ትራንስፖርት እና መገናኛ ሚኒስቴር ከKyrgyz

Pochtasy እና Kyrgyz Express Post በተጨማሪ ሦስተኛ

Trans Asia Express CJSC የተባለ አዲስ ፖስታ አስተዳደር

በዓለም አቀፍ የፖስታ ኮንቬንሽን መሠረት እንዲሰራ ፈቃድ የሰጠ መሆኑን

ለህብረቱ ዓባል አገራት አሳውቋል፡ ፡

Trans Asia Express CJSC በኪርጂዝስታን ውስጥ የመጪ እና

ሂያጅ ደብዳቤ እና ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አድራሻውም

የሚከተለው ነው፡ ፡

15 Razzakov Street

720040 BISHKEK

KYRGYZSTAN

Tel: +996 312 986 612

+996 555 588 547

E-mail: [email protected]

ከዚህ ጋር በተያያዘ በTrans Asia Express CJSC የሚሰጡ

የስራ መረጃዎች በቅርቡ በደብዳቤ እና ጥቅል ኮፔንዲየሞች ላይ በህብረቱ

ድረገጽ አማካኝነ ት እንዲገኙ የሚደረግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 121 ይመልከቱ፡ ፡

Page 49: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 122

የዲሞክራቲክ ፒፕልስ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮሪያ ፖስታ አስተዳደር ለሪፐብሊክ

ኦፍ ኮሪያ መላክ ያለባቸው ዲፓቾች/መልዕክቶች በስህተት እየደረሱት

እንደሆነ ለህብረቱ አባል አገራት ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

ወደ ዲሞክራቲክ ፒፕልስ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮሪያ የሚላኩ ዲስፓቾች

“PYONGYANG, IMPC code KPFNJA” የሚል ሌብል ሊኖራቸው

እንደሚገባ ገልፃ Dል፡ ፡

ክሎዝድ ዲፓቾችን መላክ ያልቻሉ ፖስታ አስተዳደሮች የቻይና ፖስታ

አስተዳደርን በማማከር ትራንዚት አዲኮቨርት አገልግሎት ማመቻቸት የሚችሉ

መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

Page 50: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 124

የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የድርጅቱ እንብረት

የሆኑ በይዞታቸው ስር የሚገኙ ባዶ ሸራዎችን እንዲመልሱለት ጠይቋል፡ ፡

ባዶ ሸራዎች ወደ NPKK 1005 የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ (IMPC

code: HUBUDA) በተላኩበት ተመሳሳይ ሩት እንዲላኩ አሳስቧል፡ ፡

እነ ዚህ ሸራዎች ሳይመለሱ ከቀረ በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL

203.9 እና 10 መሠረት የመተኪያ ዋጋ ክፍያ የሚጠይቅ መሆኑን

ገልፃ Dል፡ ፡

Page 51: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 125

የቬንዙኤላ (ቦሊቫሪያን ሪፐብሊክ) ለህብረቱ አባል አገራት ከዚህ በታች

ከተዘረዘሩ አገራት ጋር የአየር መልዕክት ግንኙነ ት የሌለው በመሆኑ

ተለዋጭ መሳሰቢያ እስኪሰጥ ድረስ ለእነ ዚህ አገሮች በብትንም ሆነ

ክሎዝድ ትራንዚት የሚላኩ መልዕክቶች የማይቀበል መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

አፍጋኒስታን ፤ አርሜኒያ ፣ አዘርባጃን ፣ ቤላሩስ ፣ ኮንጎ(ሪፐብ)፣

ኮትዲቫር፣ ኤርትራ፣ ጊኒ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ኮሪያ(ሪፐብ)፣ ሊባኖስ፣

ላይቤሪያ፣ ሊቢያ፣ ማያንማር፣ ሴራሊዮን፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣

ሱዳን፣ ሲሪያ፣ የመን እና ዚምባቡዌ፡ ፡

Page 52: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 127

የአየርላንድ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ የአየርላነድ መንግስት በዓይነ ቱ የተለየ ባለ

7 ዲጂት ፖስትኮድ ተግባራዊ ያደረገ መሆኑን ከ15 July 2015

ጀምሮ አዲሱን ፖስትኮድ በሁሉም አድራሻ ላይ መጠቀም እንደሚገባ

ገልፃ Dል፡ ፡ ወደአየርላንድ የሚላኩ መልዕክቶች ከዚህ በታች በተቀመጠው

የአድራሻ አፃፃፍ ምሳሌ መሰረት መላክ አለባቸው፡ ፡

Eason

80 Abbey Street Middle

DUBLIN 1

DO1 P8N3

IRELAND ከአዲሱ ፖስትኮድ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎች ሲኖሩ በሚከተለው አድራሻ

መጠየቅ ይቻላል፡ ፡

Karen Dwyer, Operations Director

Capital Business Support Service (Ireland) Limited

Block C

Maynooth Business Campus

Straffan Road

MAYNOOTH

CO KILDARE

W23 F854

IRELAND

Mobile: +353 87 949 2066

E-mail: [email protected]

Website: www.ericode.ie

Page 53: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 129

የፔሩ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

የፔሩ ጉምሩክ ለፔሩ ፖስታ አስተዳደር ወደ ፔሩ የሚመጡ የፖስታ

መልዕክቶች በበቂ ሁኔታ ባልተሞላ ወይም ተቀባይነ ት ከሌለው ከስተም

ዲክላሬሽን ጋር እየደረሱት እንደሆነ ይህም የፍተሻ እና መልዕክቱን ወደ

የሚፈለግበት ቦታ የማከፋፈል/የመላክ ስራ ላይ የማጓተት ችግር እየፈጠረ

መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

በዚህም መሠረት የፔሩ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት በጥቅል

መልዕክት አሰራር ህግ አንቀጽ RC 125 እና በደብዳቤ አሰራር ህግ

አንቀጽ RL 156 መሠረት በከስተም ዲክላሬሽን ፎርም CP 72 እና

CN 23 ተደግፈው የሚላኩ መልዕክቶች (ጥቅል ፣ ኢ.ኤም.ኤስ እና

ደብዳቤ) የሚፈለገውን ትክክለኛ እና የተሟላ የጉምሩክ መረጃ መያዝ

እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መረጃዎች በከስተም ዲክላሬሽን ፎርም ላይ

ሊሰፍሩ ይገባል፡ ፡

- የላኪ ስም እና አድራሻ

- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ (መደበኛ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ

ቁጥር እና ኢሜይል)

- የመልዕክቱ ይዘት ዝርዝር መረጃ ፣ ብዛት ፣ ክብደት እና ዋጋ

(የገንዘብ መጠሪያ ይገለፃል)

በሚላኩ መልዕክቶች ላይ የሚደረገውን የጉምሩክ ፍተሻ ስራን ለማቀላጠፍ

እንዲረዳ ፖስታ አስተዳደሮች ደንበኞቻቸው የጉምሩክ ዲክላሬሽን ፎርሞችን

እንዴት በትክክል መሙላት እንዳለባቸው ማሳወቅ እና ማረጋገጥ

እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡

Page 54: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 130

የኢኳዶር ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

በከስተም ቁጥጥር ስር የሚያልፉ ሁሉም መልዕክቶች (ጥቅል ፣ አነ ስተኛ

ጥቅል እና ኢ.ኤም.ኤስ) ግልጽ ባልሆነ ወይም ባልተሟላ ከስተም

ዲክላሬሽን ተደግፈው ሲደርሱ በመልዕክት ስራው ላይ መጓተትን የሚፈጥር

መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡

የከስተም ፍተሻ እና የመልዕክት እደላ ስራን ለማቀላጠፍ ላኪ ፖስታ

አስተዳደሮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መረጃዎችን የያዘ CN22/CN23

የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ፎርም እንዲልኩ ጠይቋል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ አድራሻ (ሙሉ ስም ፣ ስልክ ቁጥር)

- የመልዕክቱ ይዘት በዝርዝር ለምሳል አንድ አሻንጉሊት ፣ ሁለት ጥንድ

ሱሪዎች ፣ አንድ ሸሚዘው (ለስጠጦታ ፣ ለናሙና ወይም ለሌላ ጉዳይ

የተላከ መሆኑ ይገለፃል)

ይህ መረጃ በትክክል ወይም በአግባቡ ካልቀረበ መልዕክቱ ወደ መጣበት

አገር ተመላሽ የሚደረግ መሆኑን በተጨማሪም የመልዕክቱ ይዘት ግልጽ

ካልሆነ ጉምሩክ ተቀባይ ደንበኛ ደጋፊ ዶክመንቶችን እንዲቀርብ ለመጠየቅ

አድራሻውን የሚፈልግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 130 ይመልከቱ፡ ፡

Page 55: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 131

የፓራጓይ ፖስታ አስተዳር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ ወደ ፓራጓይ የሚላኩ መልዕክቶች በአሜሪካ

የአየርመንገድ እና ታምፓ በሚባል አየር መንገድ ተጭኖ መላኩን እንዲሁም

ከዲስፓቹ ጋር CN 38 መያያዙን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል፡ ፡

ይህም የመልዕክት ስርጭት ስራን እንደሚያቀላጥፍ ፣ በዕደላ ላይ

የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንደሚቀንስ እንዲሁም አጠቃላይ የመልዕክት ስራውን

እንዲሻሻል የሚያደርግና የደንበኞችንም እምነ ት የሚያጠነክር መሆኑን

ገልፃ Dል፡ ፡

Page 56: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 132

የቤልጂየም ፖስታ አስተዳደር በጉምሩክ የሚፈተሹ መልዕክቶች ትክክል

ባልሆነ እና ባልተሟላ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ጋር እየደረሱት መሆኑን

ለህብረቱ አባል አገራት አሳውቋል፡ ፡

ይህም ሁኔታ በፖስታ አስተዳደሩ ላይ ተጨማሪ ስራን እየፈጠረ በመሆኑም

መልዕክት ከመላክ እስከ ማደል ባለው የደንበኞች አገልግሎት ልምድ ላይ

አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡ በመሆኑም የቤልጂየም ፖስታ

አስተዳደር ላኪ ፖስታ አስተዳደሮች CN 22 እና CN 23 ፎርሞች

በትክክልና በተሟላ መልኩ መሞላታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል፡ ፡

በተጨማሪም ፖስታ አስተዳደሩ የህብረቱ አባል አገራት በደብዳቤ አሰራር

ህግ አንቀጽ RL 156 እንዲሁም በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ RC

151 ላይ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች በተለይም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት

መሟላታቸውን እንዲያረጋግጡ መክሯል፡ ፡

- በCN 22 እና CN 23 ፎርም ላይ የሚጠየቁ መረጃዎች

በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በስፓኒሽ ቋንቋ መሞላት

እንዳለባቸው

- የመልዕክቱ ይዘት ከእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ጋር በዝርዝር መገለጽ

ይኖርበታል

- ከተገኘ የተቀባይ ደንበኛ ስልክ ቁጥር በCN 23 ፎርም ላይ

ይሰፍራል

- ሁሉም አስፈላጊ ዶክመንቶች (ኢንቮይስ ፣ የላኪ ወይም የአስመጪነት

ፈቃድ ፣ የጽዳትና ጤና አጠባበቅ ሰርተፊኬት እና የመሳሰሉት)

ከመልዕክቱ ውጫዊ አካል ጋር ተያይዘው መላክ ይኖርባቸዋል፡ ፡

Page 57: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 133

የኢኳዶር ፖስታ አስተዳደር የአቤቱታ (CN 08) አያየዝ ስራን

ለማሻሻል እንዲያግዘው ለዚህ ስራ ብቻ የሚያገለግል የኢ-ሜይል አድራሻ

ያዘጋጀ መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

በመሆኑም የኢኳዶር ፖስታ አስተዳደር በቻለ መጠን የደንበኞች አቤቱታዎች

ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ እንዲላኩለት ጠይቋል፡ ፡

[email protected].

Page 58: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 134

የጣሊያን ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡

በቅርብ ጊዜ በፖስታ ኢንደስትሪ ሬጉሌሽን ላይ በተደረገው ለውጥ መሠረት

ከ October 1, 2015 ጀምሮ በምረቱ እና በዓለም አቀፍ ፖስታ

አገልግሎት ስራው ላይ ማሻሻያ የሚያደርግ መሆኑን ገልDፃል፡ ፡

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ፡

-

Page 59: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 136

የቬይትናም ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

ያሳውቃል፡ ፡

የአደራ ደብዳቤዎችን እና ጥቅል መልዕክቶችን የሚመለከቱ CN 08 እና

CN 48 ፎርሞች ከዚህ በታች ባለው አድራሻ መላክ እንዳለባቸው

ገልፃ Dል፡ ፡

1 Hanoi Customer Service

No. 75 Dinh Tien Hoang Str.

Hoan Kiem District

HANOI

VIET NAM

Tel: +84 4 39392469

Fax: +84 4 39362578

E-mail: [email protected]

2 Hochiminh-City Customer Service

No. 125 Hai Ba Trung Str.

Ben Nghe Ward District 1

HOCHIMINH-CITY

VIET NAM

Tel: +84 8 38271352 or 38237785

Fax: +84 8 38237784

E-mail: [email protected]

Page 60: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 139

የሆንዱራስ ፖስታ አስተዳደር ወደ አገሩ የሚላኩለት ዲስፓቾች በሙሉ ለ EGUCIGALPA መልዕክት ልውውጥ (MPC code:

HNTGUA) ብቻ መላክ እንዳለባቸው እየገለፀ የፑኤርቶ ኮርቴስ መልዕክት ልውውጥ የተዘጋ መሆኑን አያይዞ ለህብረቱ አባል አገራት አሳውቋል፡ ፡

Page 61: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 140

የኬኒያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

አሳውቋል፡ ፡ በዩ.ፒ.ዩ ስታንዳርድ መሠረት መልዕክቶችን ለትክክለኛው

ደንበኛ መታደሉን ለማረጋገጥ ወደ ኬኒያ የሚላኩ ሁሉም ዓይነ ት

ደብዳቤዎች እና ጥቅል መልዕክቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቁልፍ

መረጃዎችን መያዝ እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ ፤ የፖ.ሳ.ቁ ፣ የፖስታ ቤቱን

መጠሪያ ፣ ክ/ሃገር እና አገርን ጨምሮ

- የአዳይ ፖስታ ቤት ፓስል ኮድ

- የላኪ ሙሉ ስም እና አድራሻ

- የተቀባይ ደንበኛ የስል ቁጥር እና ኢ-ሜይል (ከተገኘ)፡ ፡ ይህም

የመልዕክት አደላ መረጃ አያያዝን የሚያሻሽል መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

Page 62: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 143

የዩክሬይን ፖስታ አስተዳደር "Ukrposhta" በአባል አገራት ይዞታ

ስር ሊኖር የሚችል የድርጅቱ ንብረት የሆኑ ባዶ ሸራዎችን እንዲመለሱለት

ጠይቋል፡ ፡

እነ ዚህ ባዶ ሸራዎች ወደ KIEV P1–15 (IMPC code:

UAIEVK) የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ እንዲለመሱለት ጠይቋል፡ ፡

እነ ዚህ ባዶ ሸራዎች ሳይመለሱ ቢቀሩ በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL

203.9 እና 10 መሠረት ከሚመለከተው ፖስታ አስተዳደር የማካካሻ

ክፍያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡

Page 63: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 144

የማሌዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ

አሳውቋል፡ ፡ በአገሪቱ የጉምሩክ ህግ መሰረት እያንዳንዱ የፖስታ

መልዕክት የተቀባዩን ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና መሰል መረጃዎች መያዝ

ይኖርበታል፡ ፡

ካልተሟላ የአድራሻ መረጃ የሚደርሱ መልዕክቶች ለጉምሩክ ፍተሻ

የማይተላለፉ ወይ የማይታደሉ በመሆኑ ወደ ላኪ አገር እንዲመለሱ

የሚደረግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

የፖስታ መልዕክቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቁልፍ መረጃዎችን መያዝ

እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡

- የተቀባይ ሙሉ ስም ፤ ወይም የተቋም ሙሉ ስም

- የተቀባይ ሙሉ አድራሻ

- የተቀባይ ደንበኛ የስል ቁጥር እና ኢ-ሜይል (ከተገኘ)

- የመልዕክቱን ይዘት እና ዋጋ

በመሆኑም ፖስታ አስተዳደሮች CN 22 እና CN 23 ፎርሞች የተሟላ

መረጃ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡ ፡ ለበለጠ መረጃ

ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 144 ይመልከቱ፡ ፡

Page 64: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 145

የዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ አገራት

በኢ.ኤም.ኤስ መልዕክት የማደያ ክፍያ ላይ ለውጥ ያደረጉ መሆኑን እና

ይህም መሻሻያ ከ1 January 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን

ማሳወቃቸውን ገልፃ Dል፡ ፡

አውስትሪያ ፣ ባህሬይን፣ ኮስታ ሪካ፣ ዴንማርክ፣ ጂቡቲ፣ ፈረንሳይ፣

ጋና ፣ ብሪታኒያ፣ ሆንግ ኮንግ (ቻይና) እና ኢንዶኔዢያ ሲሆን ዝርዝር

መረጃው በዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 145 ላይ ይገኛል፡ ፡

Page 65: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 146

የአፍጋኒስታን ፖስታ አስተዳደር በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል

አገራት ይዞታ ስር ሊገኙ የሚችሉ የፖስታ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ ባዶ

ሸራዎችን እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡

Page 66: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 148

የብሪታኒያ ፖስታ አስተዳደር (ሮያል ሜይል) ለዓለም አቀፉ ፖስታ

ህብረት አባል አገራት ሮያል ሜይልን ለማነ ጋገር ለሚፈልጉ ደንበኞች

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልክ ቁጥሮች ያዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡

ለማንኛውም ዓይነት ጥያቄዎች ፣ እርዳታ እና ምክር ስ.ቁ +44 1752

387112.

የአድራሻ ለውጥ ላደረጉ እና ሮያል ሜይል መልዕክቶቻቸውን

እንዲያስተላልፍላቸው ለሚፈልጉ ደንበኞች ስ.ቁ +44 1782 668007

በሮያል ሜይል ኦንላይን ኦፕ ላይ ስለሚገኙ ምርቶችን በተመለከተ መረጃ

ለማግኘት ስ.ቁ +44 131 316 7483.

የሮያል ሜይል ፖስታ አስተዳደር ከላይ የተገለፁት ቁጥሮች የሚያገግሉት

ለደብዳቤ መልዕክቶች ብቻ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡

Page 67: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 151

የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን

ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ የመልዕክት እደላ እና የጉምሩክ ፍተሸ ስራን

ለማቀላጠፍ ላኪ ፖስታ አስተዳደር ደንበኞቻቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩ

አስፈላጊውን የአድራሻ መረጃዎችን በመልዕክቶች ላይ ማስፈራቸውን

እንዲያረጋግጡ አሳስቧል፡ ፡

- የተቀባይ ደንበኛ ሙሉ ስም እና የተሟላ አድራሻ ፤ ፖስታ ኮድን

ጨምሮ

- የተቀባይ ደንበኛ ቀጥታ እና ሞባይል ስልክ ቁጥር እንዲሁም የኢ-

ሜይል አድራሻ ከተገኘ

- የላኪ ደንበኛ ሙሉ ስም እና አድራሻ

Page 68: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 152

የፓፑዋ ኒው ጊኒ ፖስታ አስተዳደር በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል

አገራት ይዞታ ስር ሊገኙ የሚችሉ የፖስታ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ ባዶ

ሸራዎችን እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡

Page 69: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 154

የአውስትራሊያ ፖስታ አስተዳደር የመልዕክት ስራውን ለማሻሻል እና

የአነ ስተኛ ጥቅል መልዕክቶች እደላ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ የመልዕክት

ልውውጥ ቢሮዎችን በአዲስ መልክ ያደረጃ መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት

ያሳውቋ ል፡ ፡

ከ15 September 2015 ጀምሮ ላኪ ፖስታ አስተዳደሮች በተቻለ

አቅም E-format letter class mail (AO category)

ወይም አነ ስተኛ ጥቅል መልዕክቶችን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሠንጠረዥ

በተገለፀው አድራሻ መሠረት እንዲልኩ አሳስቧል፡ ፡

መድረሻ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ ኮድ

የመልዕክት ምድብ የፖስት ኮድ ኮድ (ከ እስከ)

ክልል/ግዛት

ሲድኒ AUSYDA Air LC/AO 0200–0299 New South

Wales (NSW)

and Australian

Capital Territory

(ACT)

AUSYDD

S.A.L. LC/AO

1000–1999

2000–2999

5000-5999

South Australia

(SA)

4000-4999 Queensland

(QLD) 9000-9999

0800-0899 Northern

Territory (NT) 0900-0999

ሜልቦርን

AUMELA

Air and S.A.L.

LC/AO

3000-3999

Victoria (VIC) 8000-8999

7000-7999 Tasmania (TAS)

ፔርት/Perth AUPERA Air LC/AO

6000-6999 Western

Australia (WA) AUPERD S.A.L. LC/AO

ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 154 ይመልከቱ፡ ፡

Page 70: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

ሰርኩላር ቁጥር 155

የሞሪሺየስ ፖስታ አስተዳደር ትክክለኛ የCN 08 አቤቱታ እና

የመልዕክት መዘግየት ወይም መጥፋት የሚመለከቱ ጥያቄዎች አላላክ ሁኔታን

ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አስተዳደር እንደሚከተለው ማሳወቅ

ይፈልጋል፡ ፡

ፖስታ አስተዳደሮች በሚከተለው መረጃ መሰረት መስራት ይኖርባቸዋል፡ ፡

1. ለደብዳቤ መልዕክት አቤቱታዎች - CN 08 ፎርም በሚከተለው

አድራሻ ኢ-ሜይል ይደረግ

[email protected]

2. የጥቅል መልዕክቶች አቤቱታ በIBIS መላክ ይኖርበታል

3. የኢ.ኤም.ኤስ አቤቱታ በሚከተለው ኢ-ሜይል አድራሻ መላክ

ይኖርበታል

[email protected]

Page 71: ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር ቁጥር 3 የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል

Recommended