+ All Categories
Home > Documents > 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December...

70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December...

Date post: 03-May-2018
Category:
Upload: hathuan
View: 238 times
Download: 2 times
Share this document with a friend
12
1 Addis Ababa, Ethiopia ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም. በሚሊየም አዳራሽ በተከናወነ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የወንዶችና ሴቶች የእግር ኳስ ቡድን አባላት የአሥር ሚሊዮን ብር፤ ለወንዶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጉዞ ወጪ ደግሞ አሥር ሚሊዮን ብር፤ በድምሩ ሃያ ሚሊዮን ብር ሰጥተዋል። የሚድሮከ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው በሽኝት በዓሉ ላይ ለጨረታ የቀረበውን አንድ የስፖርት ትጥቅ በአንድ ሚሊዮን ብር በማሸነፍ በቴክኖሎጂ ግሩፑ ስም በመግዛት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሣለኝ አስረክበዋል፡፡ አቶ አብነት ገ/መስቀል ለብሔራዊ ቡድኑ ሙሉ የስፖርት ትጥቅ ገዝተው በእለቱ አበርክተዋል፡፡ ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 13, Issue No. 70 December 2012 — January 2013 u¨<eØ Ñ뉋” Inside Pages 4 4 4 4 4 4 4 4 4 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO ወደ ገጽ 2 ዞሯል ዩኤኤም ኃ. የተ. የግል ማ. ዘመናዊ የተሽከርካሪ....................5 Earth science is said vital for Africa’s ...........................6 ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአነስተኛና ጥቃቅን ........................7 ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ በጥራት..........8 ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በሚያመርትበት ለገደምቢ አካባቢ......8 የመቻሬን ግቢ በአንድ ሰዓት እይታ ...................................9 Arabic Summary .......................................................10 General Knowledge.....................................................11 መልዕክት ከሲኢኦ ..........................................................12
Transcript
Page 1: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

1Addis Ababa, Ethiopia

ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም. በሚሊየም አዳራሽ በተከናወነ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የወንዶችና ሴቶች የእግር ኳስ ቡድን አባላት የአሥር ሚሊዮን ብር፤ ለወንዶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጉዞ ወጪ ደግሞ አሥር ሚሊዮን ብር፤ በድምሩ ሃያ ሚሊዮን ብር ሰጥተዋል።

የሚድሮከ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው በሽኝት በዓሉ ላይ ለጨረታ የቀረበውን አንድ የስፖርት ትጥቅ በአንድ ሚሊዮን ብር በማሸነፍ በቴክኖሎጂ ግሩፑ ስም በመግዛት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሣለኝ አስረክበዋል፡፡

አቶ አብነት ገ/መስቀል ለብሔራዊ ቡድኑ ሙሉ የስፖርት ትጥቅ ገዝተው በእለቱ አበርክተዋል፡፡

ከሊቀመንበሩ ማኅደርVolume 13, Issue No. 70 December 2012 — January 2013

u¨<eØ Ñ뉋”

Inside Pages

4

4

4

4

4

4

4

4

4

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

70

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

ዩኤኤም ኃ. የተ. የግል ማ. ዘመናዊ የተሽከርካሪ....................5 Earth science is said vital for Africa’s ...........................6ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአነስተኛና ጥቃቅን ........................7ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ በጥራት..........8ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በሚያመርትበት ለገደምቢ አካባቢ......8

የመቻሬን ግቢ በአንድ ሰዓት እይታ ...................................9Arabic Summary .......................................................10General Knowledge.....................................................11መልዕክት ከሲኢኦ ..........................................................12

Page 2: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

2

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

የሽልማቱ ሥነ-ሥርዓት በተከናወነበት ወቅት

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆነው ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወጪ ንግድ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች መካከል ባካሄደው ውድድር አንደኛ በመውጣቱ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ንግድ ባንኩ በወጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው የላቀ የውጭ ምንዛሪ ላስገኙ 175 ባለሀብቶች ጥር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. በሸራተን ሆቴል ባዘጋጀው የደንበኞች ቀን በዓል ላይ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማ ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ በማስገኘት ከተካተቱት አምራቾች ውስጥ አንደኛ ሆኖ ብልጫ በማግኘት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች ቀን በዓል ላይ ሽልማት አግኝቷል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሠርና የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማ. ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሽልማቱን ከንግድ ባንኩ የቦርድ ሊቀ መንበርና በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን እጅ ተቀብለዋል፡፡

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ ወርቅ በማምረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ለሀገሪቱ ዕድገት አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ ግዙፍ ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል፡፡

MIDROC Gold Mine P.L.C., a member of the MIDROC Ethiopia Technology Group companies received a special Award in recognition of excellence in earning considerable foreign currency by standing first among more than 175 export customers of the Commercial Bank of Ethiopia.

Dr. Arega Yirdaw, CEO of MIDROC Ethiopia and General Manager of MIDROC Gold Mine P.L.C., received the certificate and trophy from H.E. Ato Bereket Simon, Government Communication Affairs Office Head with ministerial portfolio and Chair of the Bank’s Board of Directors on an Exporters Day organized by CBE held on February 5, 2013 at Sheraton Addis.

MIDROC Gold . . .ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን . . .ከገጽ 1 የዞረ

Page 3: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

3

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

Page 4: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

4

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

Page 5: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

5

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ዩናይትድ የአውቶሞቢል ጥገና አገልግሎት ኃ. የተ. የግል ማ. ዘመናዊ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት

መመርመሪያ መሣሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አካል የሆነው ዩናይትድ የአውቶሞቢል ጥገና አገልግሎት ኃላ. የተ. የግ. ማኀበር የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ብቃት መመርመሪያ ዘመናዊ መሣሪያ ከጀርመን ሀገር በማስመጣት እና የተከላ ሥራ በማከናወን የፌዴራል የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሣሁን ሀ/ማሪያም በተገኙበት አስመረቀ፡፡

ጥር 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው ግቢ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በተካሄደበት ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ ሀገራችን ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበች ባለችበት ወቅት በተሸከርካሪ አደጋ ምክንያት ኢኮኖሚያችን እንዳይጎዳ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያ ይዞ የተነሳው ዓላማና ተግባራዊነቱ የመንግስትን ዕቅድ አጋዥ መሆኑ ይታመናል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ያለው ሥራ የተሸከርካሪ አደጋን በመቀነስ በልማታችን ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተግባር በመሆኑ በቀጣይም በጋራ የምንሠራበትን ሂደት ያፋጥናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሲኢኦ ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው በሀገራችን ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ ተሸከርካሪዎች ከድህነታችን አኳያ በአጭር ጊዜ የሚወገዱ ባይሆንም ቀስ በቀስ እስኪቀየሩ ድረስ ደህንነታቸውን በመጠበቅና በማስተካከል ለአገልግሎት የሚበቁበትን ሥልት መቀየሱ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ሲኢኦ አያይዘውም በቀጣይ ጊዜ ከባለሥልጣኑ ጋር ባለው መልካም ግንኙነት በመኪና ማሽከርከር ሂደት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስና ብቁ አሽከርካሪዎችን ለማፍራት ዘመናዊና በመሣሪያ የታገዘ የማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለመክፈት ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው ከመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የቀረበውን መሥፈርት በሚገባ በማሟላት የዘመናዊ የቴክኒክ ምርመራ ማካሄጃ መሳሪያ ተከላ በማከናወን፣ የምርመራ አገልግሎት የሚሠጡ ባለሙያዎችን በማሠልጠንና በማስመረቅ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል፡፡

ቃሊቲ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ግቢ የተተከለው ይኸው ዘመናዊ መሣሪያ የመሪ ግራና ቀኝ መጐተትን (Side slip tester)፣ የአረግራጊ (Shock absorber) ፍተሻ፣ የአክስል ንቅናቄ፣ የፍሬን ብቃት መፈተሻ (Roller Brake Tester)፣ የጭስ መጠን (Emission tester)ና የመብራት (Head Light Tester) ፍተሻን እስከ 20 ቶን የአክስል ክብደት ላላቸው ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች የምርመራ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሲሆን፣ ለሃያ ሠራተኞችም የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡

መሣሪያው የተሽከርካሪዎች ምርመራ በሚያካሂድበት ወቅት መርማሪ ባለሙያዎች የቅደም ተከተልና ሌሎች ስህተቶች እንዳይፈጽሙ መከታተያ ቼክሊስት የተዘጋጀና መቆጣጠሪያ ካሜራ የተተከለ ሲሆን፣ ማንም ተገልጋይ ቅሬታ ቢኖረው ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች የሆኑት የሚድሮክ ሲኢኦ ማኔጅመንትና ሥራ አመራር አገልግሎት፣ የሁዳ ሪል እስቴት፣ የኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች እንዱስትሪ፣ የዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ፣ የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ የዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ መሐንዲሶችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የመሣሪያውን ተከላ በመተባበር ማካሄዳቸው ታውቋል፡፡

ኩባንያው በቀጣይም በተመሣሣይ ዘመናዊ መሣሪያ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በክልል ከተሞች ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ለማካሄድና በዘመናዊ መሣሪያ የተሟላ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ት/ቤት ለማቋቋም ዝግጅት ማጠናቀቁ ተጠቁሟል፡፡

ዩናይትድ የአውቶሞቢል ጥገና አገልግሎት ኃላ. የተ. የግ. ማኀበር የመኪና ጥገና፣ የአካል ለውጥ፣ የባትሪ ሽያጭ፣ አዳዲስና ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች መሸጥ፣ የኢንጀክሽን ፓምፕ እድሳት እንዲሁም የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አንዱ የሆነ ዘመናዊ ኩባንያ ነው፡፡

UAM inaugurates vehicle inspection test lane

United Auto Maintenance P.L.C, a member of MIDROC Ethiopia Technology Group companies inaugurated vehicle technical inspection test lane built on its premises on January 15, 2013.

Federal Transport Authority Director General Kassahun Haile-Mariam said on the occasion that the low level technical capacity of vehicles has been a major cause for traffic accidents. In this regard, ensuring the technical capacity of vehicles has an important role to lessen the accidents.

Ato kassahun indicated that the company also through strengthening its capacity can be a model for other private companies engaged in providing the service.

MIDROC Ethiopia CEO, Dr. Arega Yirdaw on his part said that members of the MIDROC Ethiopia Technology Group Companies have been taking a leading position in assisting the country’s economic endeavors.

The CEO indicated that as part of the technology group's effort, UAM has finalized preparations to provide annual vehicle inspection test lane services in accordance with the standards set by the Ethiopian Road and Transport Authority.

UAM P.L.C. General Manager Ato Ephrem Abera on his part said that the company would provide the service using its new modern machine imported from Germany at a cost of over five million birr.

The inspection service includes visual inspection pit, slide slip tester, shock absorber tester, axle play tester, roller brake tester and emission tester.

The company will also launch licensing service in the near future.

While inaugurating the inspection test lane

Page 6: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

6

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

Earth science is said vital for Africa’s development

The 24th Colloquium of African Geology (CAG) conference was held at the Millennium Hall in Addis Ababa Ethiopia from 8-14 January 2013 under the theme “40 years of GSAF (1973-2013); Earth sciences solutions to African Development Challenges”. It was conducted together with the 14th congress of the Geological Society of Africa (GSAF) and the 40th anniversary of GASF.

The conference was officially opened with the presence of the Minister, Ministry of Mine, W/ro Sinknesh Egigu.

MIDROC Ethiopia Chief Executive Officer and MIDROC Gold Mine General Manager, Dr. Arega Yirdaw made a plenary presentation on the topic of MIDROC Gold’s experience in the mining sector.

MIDROC Ethiopia Technology Group was a diamond sponsor and MIDROC Gold Mine was among platinum sponsors for the

conference.

The objectives of the conference are : to promote understanding of the earth sciences and improve standards of earth science education and research in Africa, to provide a forum for discussion and dissemination of information across national boundaries among scientists, associations and institutions engaged in African geology and earth resources as well as to improve natural hazards assessment and disaster mitigation.

Large number of earth scientists from 60 countries attended the CAG 24 which was organized by the Ethiopian Geo-sciences and Mineral Engineering Association (EGMEA) in collaboration with government and non-government organizations.

ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ለመረዳት ከመንግሥት ኃላፊዎች እንዲሁም

የየኩባንያዎቹን ሃላፊዎች በማነጋገር የሥራ አቅጣጫዬን ቀይሼ ድርጅቶቹን

ለማስተዳደር ሃላፊነቱን ተረከብኩኝ›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ ከቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ

ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ሁለት ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው

ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው ስለ አየር መንገድ

አገልግሎት መስፋፋት፣ ከውጭ ስለሚገቡና በኢንቨስትመንት ስለሚሠማሩ

ኢትዮጵያውያን ጉዳይ፤ በከተማ ግብርና ህግ ላይ ከዚያ ባለፈም በግል

ጉዳዮች ላይ አርኪ ውይይቶች አድርገው እንደነበር ይገልፃሉ፡፡

ዶ/ር አረጋ ሃያ ኩባንያዎችን መምራት እንደማይከብድ ሌሎችም ቢጨመሩ

መምራት እንደሚቻል ይናገራሉ፡፡ ‹‹ዋናው ነገር አንድ ጊዜ ኩባንያዎቹ

ሥራቸውን ማከናወን የሚችሉበት የአሠራር ሥርዓት ከተዘረጋላቸው

ሁሉም በዚያ ሥርዓት መመራት ብቻ ነው፡፡ አስቸጋሪው ሊመሩበት

የሚችሉትን ሥርዓት በትኩረት የመዘርጋቱ የመጀመሪያው ደረጃ ላይ

ነው፡፡ ከዚያ ራሳቸው እያዳበሩት ይሄዳሉ፡፡ ሌሎች ኩባንያዎች ሲጨመሩ

በአመራር ደረጃ ብቁ የሆኑ ሰዎችን የመምራት ኃላፊነት በመሥጠት

አመራሩን ይከፋፈላሉ፡፡ ኩባንያዎቻችን ከአምስት ወደ ሃያ ያደጉትም

በየወቅቱ የሚወጡ የመንግሥት መመሪያዎችና ደምቦችን የተከተሉና

ለሥራ ተደጋጋፊነት እንዲኖራቸው ሲባል ነው›› በማለት መልሰዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ከሼክ ሙሐመድ ጋር እየተገናኙ ስለ ሥራውና ስለ ኩባንያዎቹ

ይመካከሩ እንደሆነም ሲገልፁ፡- የባለሀብቱ ትልቁ ሀብቱ እምነቱ ነው፡፡

በመታመንህ ሥራህን በአግባቡ እንድትሠራ ያደርግሀል፡፡ በሰዎች መካከል

ያለው ግንኙነት ለሥራህ ወሳኝ ነው፡፡ አለቃ ሲኖር የአለቃን ስሜትና

ፍላጐት መገንዘብ ግዴታ ነው፡፡ ሼክ ሙሐመድን ስንመለከት በእምነት

ለቀቅ አድርጐ ‹‹ሥራህን ሥራ!›› የሚል አለቃ ነው፡፡ የምናመርተውን፣

የምንሸጠውንና የምናስገባውን ገቢ ምን ያህል እንደሆነ የሚጨቃጨቅ

አለቃ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል የሼክ ሙሐመድ ተቃራኒ የሆነ አለቃ

ለእያንዳንዷ ጉዳይ ሪፖርት እንዲቀርብለት በመጨቃጨቅ ሥራ መሥራት

የሚቻልበትን ጊዜ በመሻማት ውጤታማ ሥራ እንዳይሠራ የሚያደርግ

አይጠፋም፡፡ ይህ ውጤታማ አያደርግም፡፡ መረጃ ሰብሳቢ ያደርጋል እንጂ!

እኔ ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ ሀገሬን እንዳገለግል ዕድሉን የፈጠረልኝ

ሼክ ሙሐመድ በመሆኑ መናገር ከምችለው በላይ ዕድለኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ

የማመሰግንበት ቃላቶች እንኳ ያጥሩኛል፡፡ ለጋራ ሀገራችን ‹‹እንረዳዳ

አብረኸኝ ሁን›› ያለኝ አለቃዬ ስለምሰራው ሥራ አንድ ቀን ጥያቄ ጠይቆኝ

አያውቅም፡፡

«ከምግብ ሽሮ፤ ከመጠጥ ሚሪንዳ፤ ከሠራተኛ በራሱ ነገሮችን ፈጥሮ

ለመሥራት የሚንቀሳቀሰውን፤ መጽሐፍ ማንበብ፣ ተራራ ለተራራ መኪና

መንዳት፣ የሀገር ቤቱን ሁኔታ እየተዘዋወሩ መቃኘት የምወዳቸው ሲሆኑ፤

አልኮል መጠጦችን ግን ሞክሬያቸው አላውቅም፡፡ የሥራ ፍልስፍናዬ

ሥራን መሥራት ነው፤ ሥራ ያስከብራል፣ ማንነትን ያንፃል፣ ከአልባሌ

ቦታ ይከለክላል፣ ቤተሰብን እንድትመራ ያደርጋል፤ ሥራ ባህል መሆን

አለበት፡፡ ማንም ሰው የሀይማኖት ልዩነት ሳይኖር ሥራን ማክበር አለበት።

የህይወት መሠረት በመሆኑ!» ብለዋል።

በትምህርቱ በኩልም «ሀገሮች ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱት የተማሩትን በቶሎ

ሰብስበው ሥራቸውን በመሥራታቸው ነው፡፡ ትምህርት ለማንም ሰው

ለሆነ ሁሉ የተሰጠ ዕድል ነው፡፡ አክብሮ ለያዘው ማንነት የሚለካበት ነው።

በእኔ አስተሳሰብ ትምህርት መለኪያ የሌለው የመጨረሻው ሀብት ነው፡፡

ለልጆቼ የሚሠጣቸው ስጦታ ትልቁ ትምህርት ነው፡፡» ሲሉ ተናግረዋል።

‹‹ሀገራችን ወደፊት ለማደግ የተዘጋጀ መሠረት አላትን?›› ብለን ስንጠይቅ

መልሳችን አዎን! ነው፡፡ የመሬቷ አቀማመጥ፣ የአየር ጠባይዋ፣ ባህልዋ

የሚወደድና እግዚአብሔርን የሚፈራ ሕዝብ ያለበት ሀገር ነች፡፡ ስለዚህ

ወደፊት ሀገሮች ሊበላለጡ የሚችሉት በወታደራዊ ኃይል ሳይሆን በአእምሮ

ዕድገትና በኢኮኖሚ ይሆናል ያኔ ሀገራችን ትበልጣለች ብዬ አስባለሁ፡፡

የሰው ልጅ በሕይወቱ የተሳካ ነገር ሁሉ ሊፈፅም አይችልም ጐደሎ ነገር

ሊኖር ይችላል፡፡ በሕይወቴ ማድረግ የሚገባኝን አስተዋፅዎ ለማድረግ

እየጣርኩ ነው ብዙዎቹ ተሳክተውልኛል፡፡ ሙከራዎቼ አመርቂ ናቸውና››

ብለዋል።

ተፈፀመ!

ከጐንደር እንኮዬ መስክ . . .ከገጽ 12 የዞረ

Page 7: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

7

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአነስተኛና ጥቃቅን የሥራ ዘርፍ ያሠለጠናቸውን ሙያተኞች አስመረቀ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆነው ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል. ኩባንያ ወርቅ ከሚያመርትበት ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ የተውጣጡ አሥር ወጣቶችን በመመልመል በአነስተኛና ጥቃቅን የሥራ ዘርፍ በማሠልጠን ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም. አስመረቀ፡፡

ኩባንያው ወጣቶች በማኅበር ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲሰማሩና ለሌሎች ዓርአያ እንዲሆኑ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ካሉበት ወረዳ ወደ አዲስ አበባ በማጓጓዝ ለ9 ሣምንታት በድንጋይ ጠረባና ንጣፍ (ኮብል እስቶን) እንዲሁም ማኅበራቸውን በስኬት መምራት የሚያስችላቸውን የሙያ ሥልጠና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ ሦስት አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ሥልጠና ማስተባበሪያ ቢሮና ከከፍተኛ 20 ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋም ጋር በመተባበር በቂ ዕውቀት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፣ ሠልጣኞች ወደ ወረዳቸው ተመልሰው የአካባቢያቸውን ወጣቶች በማሠልጠን ዕውቀቱን ማስፋፋት የሚያስችላቸውን ብቃት እንዳገኙ ተገልጿል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሲኢኦና የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ለተመራቂዎቹ የምሥክር ወረቀት በሠጡበት ወቅት ሠልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን ዕውቀት በተግባር እንዲያውሉ በተከለለላቸው ቦታ በብቃት ሠርተው ማየታቸውን እንዳረጋገጡ ገልፀው፤ ወደ ወረዳቸው ሄደው በጥራት እንዲሰሩና ወደ ከፍተኛ ደረጃ የልማት ሥራ እንዲሸጋገሩ ሙሉ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል። ለሠልጠኞች ለማኅበራቸው የሥራ መነሻ የሚሆን የካፒታል ድጋፍ ከመሰጠቱ በተጨማሪ በነፍስ ወከፍ የኪስ ገንዘብ ተሠጥቷቸዋል፡፡

የከፍተኛ 20 ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋም ምክትል ዲን ወ/ሮ አዱኛ ካሴ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል. ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረዳው የዚህ አይነቱን የልማት ሥራ ለማስፋፋት ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉ ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ሀላፊነቱን እየተወጣ በመሆኑ ለወደፊቱም የእኛም ድጋፍ አይቋረጥም ብለዋል፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል. ኩባንያ ቀደም ሲል 25 ተማሪዎችን በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በማዕድን ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ትምህርት እንዲያገኙ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን፤ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለወጡ የወረዳው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጠቀም ያለ የገንዘብ ድጋፍና ውጤታቸው ለዩኒቨርሲቲ ያበቃቸው የወረዳው ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚጓጓዙበት ሙሉ ወጪያቸውን መሸፈኑ ይታወሳል፡፡

ሠልጣኞችና መምህራኖች በምረቃው ቀን

ሠልጣኞች የምሥክር ወረቀት ሲቀበሉ

Page 8: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

8

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆነው ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር የሚያመርታቸው ምርቶችና የሚሠጣቸው አገልግሎቶች ጥራትን ማዕከል እንዲያደርጉና ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር ለሠራተኞች ስለ ጥራት በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ሠጠ፡፡

ኩባንያው ከጥር 14-17 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ባዘጋጀው ሥልጠና ሠራተኞቹ ስለጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት፣ ስለ መልካም ምርት አመራረት ሥርዓት፣ ስለጥሬ ዕቃ አቅርቦት፣ አቀማመጥና ቁጥጥር፣ ስለ ተረፈ ምርት አወጋገድ፣ ስለ ፋብሪካ ልዩ ልዩ ክፍሎች አያያዝ፣ ስለ ቤት አያያዝና የግል ንጽህና አጠባበቅ በባለሙያዎች የታገዘ ሥልጠና አግኝተዋል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጰያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ወቅት ኩባንያዎቹ ጥራትን ማዕከል በማድረግ የሚሠጡት አገልግሎት የተሟላ ሲሆን፤ ተወዳዳሪነትን በፍጥነት እያሳደገ

ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር በጥራት አሠራር ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሠጠ

ተፈላጊነትን እንደሚጨምር አስታውቀዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ በዴይላይት ኩባንያ የተጀመረው ጥራትን ማዕከል የማድረግ ተግባር በኮርፖሬት ሴንተሩ እንደ ማዕከል ተቋቁሞ በሁሉም ኩባንያዎች ተግባራዊ እየሆነ መስፋፋት እንዳለበት ዕቅድ መያዙንና ሂደቱ መጀመሩን ጠቁመው፣ በየኩባንያዎቹ አሠራር ጥራትን ለማስረጽ በሙሉ ኃይላችን መንቀሳቀስና የደንበኞቻችንን ፍላጐት ማርካት ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስፋው ገ/ሥላሴ በበኩላቸው የኩባንያውን የአመራረትና የአገልግሎት አሠጣጥ የጥራት ደረጃ ለማሳደግ ይህንን መሰሉ ሥልጠና ውጤታማ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ዴይላይት ልዩ ልዩ የለስላሳ ጠርሙሶችንና ብርጭቆዎችን በማምረት እንዲሁም የኤሌክትሪክና የኤሌክትሪክ ምህንድስና ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማ ወርቅ በሚያመርትበት ለገደምቢ አካባቢ የሚገኙ የዲዶላ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኙ ተደረገ

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ወርቅ በሚያመርትበት በለገደምቢ ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲዶላ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውሀ እንዲያገኙ የሚያስችል ተግባር አከናወነ፡፡

በወረዳው ቀደም ሲል ለመጠጥ የሚሆን ውሃ ባለመኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆነ ከብቶቻቸው በመጠጥ ውሃ እጦት ችግር ላይ መውደቃቸውን በመረዳት ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ 25 ሺህ ሊትር ውሃ መያዝ የሚችል ማጠራቀሚያ በማዘጋጀት ንፁህ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

ከ100 ሺህ ብር በላይ የወጣበት ይህ የውሃ ማጠራቀሚያ፤ የሚድሮክ

ወርቅ ማዕድን አንደርግራውንድ ማይን ዴቬሎፕመንት ኤንድ ፕሮዳክሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አያሌው ተበጀ እና የሻኪሶ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሮቤ በራቆ በተገኙበት ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ተመርቆ በዲዶላ ቀበሌ ለሚገኙ ሁሉም ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

ኩባንያው ቀደም ሲል ከብቶቻቸው የምግብና የመጠጥ ውሃ እጦት ችግር በገጠማቸው ወቅት ሳር በመኪና እንዲሁም ውሃ በቦቴ በማመላለስ ህይወታቸውን እንዳዳነላቸው ያስታወሱት የወረዳው ነዋሪዎች፤ አሁን ደግሞ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በማግኘታችን ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው ብለዋል፡፡

በጥራት አሠራር ላይ ሥልጠና በተሰጠበት ወቅት

Page 9: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

9

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

የመቻሬን ግቢ በአንድ ሰዓት እይታ

ከሜክሲኮ ወደ ሣር ቤት ከዚያም ወደ ብሥራተ ገብርዔል የሚወስደውን መንገድ ሲያያዙ ካናዳ ኤምባሲን በስተግራ እያዩ ጥቂት ተጉዘው መቻሬ ኮርፖሬት ሴንተርን ያገኙታል፡፡ ‹‹መቻሬ›› ይህ በሰፊው የተንጣለለው ምድረ ግቢ መጠሪያ ስሙን ያገኘው ወልድያ ከተማን ከሚያዋስናት ሰፊው የመቻሬ ሜዳ መጠሪያ ነው፡፡

በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር ዘወትር ከጠዋት ማለዳ አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ የሰው ልጅ ሊሰራው የሚገባ ተግባር ሁሉ ይከናወንበታል፡፡ እንዲያው የአንዱን ቀን የጥቂት ሰዓታት ቅኝቱን ማየት ብቻ ሁልጊዜም ተግባራቱ ያው መሆናቸውን መገንዘብ ያስችላል፡፡

የትራንስፖርት እጦቱንና የትራፊክ ጭንቅንቁን ተቋቁሞ ከማለዳ ጀምሮ ወደ መቻሬ ግቢ የሚተምመው ሠራተኛ ግቢውን የገበያ ሥፍራ ያስመስለውና በስራ ሠዓት ደግሞ ሁሉም ወደ ቢሮው ስለሚከተት ሰው አልባ ግቢ ያስመስለዋል፤ ግቢው በፀጥታ ይዋጣል፡፡ ይህ ማለት ሠራተኞች በሙሉ በሥራ ገበታቸው ተሰማርተዋል ማለት ነው፡፡ ምናልባትም የአንዳንድ ሰዎች እንቅስቃሴ ቢታይ እንኳ ለሥራ ጉዳይ ከአንዱ ኩባንያ ወደ ሌላው የሚዘዋወሩ ብቻ ይሆናሉ፡፡

የጥበቃ ሠራተኞች ቢሮዎች በየዋናና አስፈላጊ ቦታዎች መኖር፣ የመኪኖች አቋቋም ሥርዓት፣ የግቢው የትራፊክ ምልክቶች አጠቃቀም፣ የሠራተኞች መጓጓዣ መኪኖች በረድፍ ተሰልፈው ሲገቡና ሲወጡ ዋናውን መንገድ እስኪይዙ ያለው ሥርዓት አይንን ይማርካል፡፡

በግቢው የሚገኙ ሠራተኞች በአንድ አይነት ሪባን መታወቂያቸውን በአንገታቸው ማንጠልጠላቸው፣ አብዛኛው ወንዶች ሠራተኞች ከሰኞ እስከ ሐሙስ ሙሉ ልብስ ከነክራባቱ መልበሳቸው ለግቢው ሥርዓት ውበትን ሠጥተውታል፡፡

ማለዳ በሥራ ገበታቸው የተገኙት የግቢው የጽዳት ባለሙያዎች ከቢሮ እስከ ምድረ ግቢው ድረስ ጽዳታቸውን ያከናውናሉ፡፡ የጥበቃ ሠራተኞች የሚገቡትን መኪኖች ማስተናገድና የግቢውን ሥርዓት መጠበቅ የሥራ ድርሻቸው ነው፡፡

በመቻሬ ግቢ የሚድሮክ ሲኢኦ ማኔጅመንት እና አመራር አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማ.ን ጨምሮ ስምንት ያህል ኩባንያዎች ማለትም ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን፣ ዘመናዊ የሕንፃ ኢንዱስትሪ፣ ኮምቦልቻ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ፣ ሁዳ ሪል እስቴት፣ ትረስት የሰው ኃይልና አገልግሎት ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስና ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ኃላ.የተ.የግ.ማ. እንዲሁም የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነው መቻሬ ክሊኒክ የየዕለት ተግባራቸውን ያከናውናሉ፡፡

በተለይም መቻሬ ክሊኒክ ከሁሉም ኩባንያዎች ጤናቸው የተጓደሉ ታማሚዎች በቅርቡና በተቀላጠፈ ሁኔታ ሙሉ ህክምና የሚያገኙበት የጤና ተቋም ነው፡፡

ዋናውና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 20 ኩባንያዎችን የሚመራው የሚድሮክ ሲኢኦ ማኔጅመንት እና አመራር አገልግሎት የግቢውን ሰፊ የሥራ ድርሻ የያዘ ሲሆን፤ ኩባንያዎቹ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውንና ሀላፊነታቸውን መወጣታቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡

በሲኢኦ ቢሮ በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት በየሥራ ዘርፎቻቸው ማለትም ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና ፕሬዚዳንት፣ ፕሪንሲፓል ማኔጅመንት ኦፊሰር ኮርፖሬት ገቨርነንስ፣ ኮርፖሬት ማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት፣ ፕሪንሲፓል ማኔጅመንት ኦፊሰር ኮርፖሬት ኢንጂነሪንግ ኳሊቲና ቴክኖሎጂ፣ ፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሰር ሰብ ግሩፕ ኤ ካምፓኒስ፣ ፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሰር ሰብ ግሩፕ ቢ ካምፓኒስ እና ፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሰር ሰብ ግሩፕ ሲ ካምፓኒስ በሚል የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡

የመቻሬ ግቢ ሠራተኞች ከሥራ በኋላ በምሳ ሰዓታቸው የሚመገቡበትና የካፊቴሪያ አገልግሎት የሚያገኙበት የመመገቢያ አዳራሽና አገልግሎት በበቂ ሁኔታ በመደራጀቱ አብዛኞቹ ሠራተኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በግቢው ሠራተኞች በቡድን ተደራጅተው እግር ኳስ፣ የእጅ ኳስና ሌሎች የስፖርት አይነቶችን የሚያከናውኑባቸው ሜዳዎች ከየትኛውም የከተማችን ስፍራ ይልቅ በመቻሬ ሜዳ የተሟሉ ናቸው፡፡

የመቻሬ ግቢ ዘርፈ ብዙ ግልጋሎት ሠራተኞችን ተጠቃሚ ያደረገ በመሆኑ ሠራተኞች የሚፈልጉትን ነገር ለመግዛት ረጅም ርቀት እንዳይሄዱ ታስቦ ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ኃላ.የተ.የግ.ማ. ሁሉንም ሸቀጦች በማቅረብ እዚያው ስፍራ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡

ከማለዳው ጀምሮ የሠራተኞችን በደህና ወደ ሥራቸው መምጣታቸውን፤ ማታ ደግሞ ሥራው ሲያበቃ በሠላም ወደ ቤታቸው መጓጓዛቸውን፤ የግቢውን የዕለት ሁኔታ የሚከታተሉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሲኢኦ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ከቢሮ የአመራር ሥራቸው በተጓዳኝ የሠራተኞች ደህንነት ቅድሚያ ትኩረታቸው ነው፡፡

ይህ የአሠራር ሁኔታ ለአዲስ ሰው ያስገርም ይሆናል እንጂ ለለመደው ያው የዘወትር ተግባር በመሆኑ አያስደንቅም፡፡ የዕለቱ ቋሚ ተግባር ነውና!

የመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ

Page 10: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

10

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

Page 11: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

11

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

GENERAL KNOwLEDGE

The first moon walker

Neil Armstrong made history in 1969 when he planted his feet — and a flag — on the moon.Armstrong fell in love with flying at a young age. By 15 he was already taking lessons. He picked up odd jobs around his

hometown to pay for flight time in a small airplane. He got his student’s flying permit, at 16, before he got his driver’s license.

In college, he trained as an aeronautical and aerospace engineer. In this field, people learn how to design and control not only aircraft but also jets and other propulsion systems.

But before he could finish college, Armstrong was called up for military service. He signed on to become a Navy fighter pilot. He flew 78 combat missions in Korea. During one, his plane was hit and he had to parachute out. It was an event that could have killed him. But it didn’t frighten him off of flying. Instead, he went back to school and finished his studies. Then he joined a federal agency that would become the National Aeronautics and Space Administration, or NASA.

Armstrong standing in front of an X-15 space plane that he test piloted. Credit: NASA .There, for 17 years, Neil Armstrong held a number of different jobs. He started as a test pilot for many pioneering aircraft. These included the X-15, an experimental vehicle that could zoom through the atmosphere at more than 4,000 miles per hour! He made seven flights on that space plane, at one point reaching an altitude of 63,198 meters (207,500 feet). That’s about six times higher than today’s standard jumbo jets. And he didn’t just pilot the X-15. He also worked closely with the aircraft’s engineers and designers to improve the plane’s flight controls. In all, Armstrong flew more than 200 different models of aircraft, including jets, helicopters and gliders.

That all changed in 1962 when Armstrong joined NASA’s astronaut corps. Suddenly, his focus became rocketry and space exploration. Within four years, he was given the command of the Gemini 8 spacecraft, from which he controlled the first successful docking, or linkup, of two vehicles in space.

But the highlight of his career was Apollo 11, that famous mission to the moon. And almost 1 in 5 people alive at the time shared in the excitement, watching as blurry television images showed Armstrong descending to the lunar surface.

His team’s landing module had set down in a region known as the Sea of Tranquility. Within 20 minutes, Aldrin joined him. There, the two took photos, collected moon rocks and set up some science experiments.

They also left mementos for future space travelers. These included a patch carrying the names of Virgil Grissom, Edward White and Roger Chaffee — Apollo 1 crew members who died in a launchpad fire. Armstrong and Aldrin also left medals inscribed with the names of Vladimir Komarov and Yuri Gagarin, two Russian astronauts (called cosmonauts) who died during space flights in 1967 and 1968. Finally, they left a small silicon disc that carried a miniature goodwill message from 73 world leaders (its message is so small that you would need a microscope to see the words).

Aldrin returned to the Eagle after 93 minutes on the moon’s

surface. Armstrong, the mission’s commander, stayed 40 minutes longer. He savored the last bits of this huge adventure. Then the pair rejoined Michael Collins aboard the Apollo 11 space capsule for their return trip home. In all, the team spent more than eight days in space and traveled 953,054 miles (more than 1.5 million kilometers).

And still their trip wasn’t really over. The men couldn’t step out of their space suits and rush to hug their families for another three weeks. Once back on Earth, the men had to remain in quarantine. It was a precautionary measure to make sure no one had picked up a dangerous germ during their lunar trek and carried it home.

After his Apollo 11 trip to the moon, Armstrong stayed on at NASA and eventually rose to become its deputy associate administrator, in Washington, D.C. Later, he became a college professor, teaching aerospace engineering. He then worked for several aerospace companies. It seems the man never could get enough of the idea of cruising through — and occasionally outside of — Earth’s atmosphere.

After his death, Armstrong’s family issued a statement. They said, in part: “While we mourn the loss of a very good man, we also celebrate his remarkable life and hope that it serves as an example to young people around the world to work hard to make their dreams come true, to be willing to explore and push the limits, and to selflessly serve a cause greater than themselves.”

Observes NASA Administrator Charles Bolden: “As long as there are history books, Neil Armstrong will be included in them, remembered for taking humankind’s first small step on a world beyond our own.”

Astronaut Neil Armstrong’s official portrait for the Apollo 11 mission to the moon. Credit: NASA A little more than 43 years ago, an American astronaut climbed down the ladder of his lunar landing module — the Eagle — and became the first human to touch the moon’s surface. As he steadied himself, he said: “That’s one small step for a man, one giant leap for mankind.” Around the globe, an estimated 530 million people watched on their televisions…

A little more than 43 years ago, an American astronaut climbed down the ladder of his lunar landing module — the Eagle — and became the first human to touch the moon’s surface. As he steadied himself, he said: “That’s one small step for a man, one giant leap for mankind.” Around the globe, an estimated 530 million people watched on their televisions as Neil Armstrong uttered those now-famous words. On August 25, this American hero died at age 82.

“Neil was among the greatest of American heroes — not just of his time, but of all time,” said President Barack Obama. “When [Armstrong] and his fellow crew members lifted off aboard Apollo 11 in 1969, they carried with them the aspirations of an entire nation.” These men showed the world “that with enough drive and ingenuity, anything is possible,” the president added. And these brave individuals “delivered a moment of human achievement that will never be forgotten.”

As a mark of respect for Armstrong and what his achievements represented, President Obama ordered that flags throughout the country and at U.S. embassies abroad be lowered to half-staff on the day Armstrong is buried.

Source:- from Internet

Page 12: 70 - midroc-ceo.com · ሼህ ሙሐመድ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ... Issue No. 70 December ... ተወያይተዋል፡፡ በተለይም የመጨረሻው ውይይታቸው

12

MIDROC NewsletterVolume 13, Issue # 70 December 2012 — January 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ዶ/ር አረጋ ይርዳውDr. Arega Yirdaw

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣ ሚድሮክ ኢትዮጵያChief Executive Officer, MIDROC Ethiopia u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)

Address: Office of the Chief Executive Officer, MIDROC EthiopiaFax: +251-11-371-5988 / 372-4977P.O. Box: 5787, Addis Ababa EthiopiaE-mail: [email protected]: www.midroc-ethiotechgroup.com

mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR

ከጐንደር እንኮዬ መስክ - አሜሪካ - ከዚያም መቻሬ ሜዳ!

ጐንደር ከተማ እንኮዬ መስክ በሚባለው ስፍራ ተወለዱ፤ የቄስ ትምህርታቸውን በግምጃ ቤት ማሪያም ፊደል በመቁጠር ጀመሩ፤ የቄስ ትምህርቱ ሲያልቅ በጐንደር ፋሲለደስ ዙሪያ በተቆረቆሩ በግምጃ ቤት ማሪያምና በእልፍኝ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በድቁና አገለገሉ፡፡

ከጓደኞቻቸው ጋር ዋርካ በመልቀም፤ በጥምቀት በዓል የቤተክርስቲያን ልብስ በመልበስና ቃጭል በመያዝ ታቦት አጅበው መጓዝ፣ በአንገረብና በቃሀ ወንዝ ውሃ ዋና ለመልመድ መድከማቸው የልጅነት ትዝታዎቻቸው ናቸው፤ የያኔው ታዳጊ አረጋ ይርዳው የዛሬው ዶ/ር አረጋ ይርዳው፡፡

የፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን 98.1 ሬዲዮ ጣቢያ የእንግዳ ፕሮግራም ላይ ከአዘጋጁ ጋዜጠኛ ጋር በሦስት ክፍል ያደረጉት ቃለ ምልልስ ብዙ ጉዳዮችን የዳሰሰ ነበር ሁሉንም ለማቅረብ የመጽሔታችን ገጽ ገደበን፤ ይሁን እንጂ ዋናውን ጭብጥ ሀሳብ እንደሚከተለው አቀረብንላችሁ!

ታዳጊው አረጋ ይርዳው በልጅነቱ የቤተክርስቲያን ትምህርት ሲማር

የበላዮቹን መምህራኖች ለመሆን ተመኘ፤ ወደዘመናዊው ትምህርት ሲገባ

ደግሞ የሚያስተምሩትን የዘመናዊ ትምህርት አባቶቹን ለመሆን አሰበ፤

ታዲያ የትኛውን ይጨብጥ ይሆን?

በዚህ ሂደት ከቄስ ትምህርት ቤት ወደ ዘመናዊ አስኳላ የተሸጋገረው

ታዳጊ የቄስ ትምህርቱ መሠረት ሆኖት በዘመናዊ ትምህርት ቤት የሦስተኛ

ክፍል ተማሪ ሆኖ ጀመረ፤ ጐበዝ ተማሪ ስለነበርም በአመቱ ክፍሉን

በማጠፍ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሆነ፤ ከዚያም ስድስተኛና ሰባተኛ ክፍልን

አጠናቅቆ በአራት አመታት ውስጥ ስምንተኛ ክፍል ደረሰ፡፡

የእርሱ ጉብዝና ለትምህርቱ መቀላጠፍ መንገድ ሆነና በአጭር አመታት

የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ላይ ተቀመጠ፤ በዚህ መሀል የአንደኛ ደረጃ

ተማሪ ሆኖ ስድስተኛ ክፍል ያገኛት ጓደኛው የትዳር አጋሩ እንድትሆን

አስቦ በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ወቅት በሀገሩ ባህል መሠረት በትዳር

ተጣመሩ። በሠርጋቸው ዕለት ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-

አሙዲ ጓደኛ ነበሩና ሚዜ ሆነው የሠርጉ አድማቂ ሆኑ፡፡

አሁን ታዳጊው አረጋ ትዳር መስርቷል፡፡ ታዳጊ የሚባልበትን ጊዜ አልፏልና

የክብር መጠሪያ ማዕረጉን እያስቀደምን ዶ/ር አረጋ እያልን ወጋችንን

እንቀጥላለን፡፡

ዶ/ር አረጋ ከ1953 - 1956 ዓ.ም. በወይዘሮ ስህን ት/ቤት ትምህርታቸውን

ሲከታተሉ ጠንካራ ተማሪ በመሆናቸው ለዩኒቨርሲቲ የሚያበቃቸውን

ውጤት በማግኘት አጠናቀቁ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለመጀመር ባለቤታቸውን ይዘው አዲስ

አበባ ገቡ፡፡ በተቆረጠላቸው በወር የ50 ብር ደመወዝ ቤት ተከራይተው

ኑሮአቸውን እየመሩ ትምህርታቸውን ተያያዙት፡፡ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ

ዘርፍ ለ6 ዓመታት ትምህርታቸውን ተከታትለው በጥሩ ሁኔታ ጨረሱ፡፡

ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለት አማራጮች

ነበሩዋቸው ወንጂ ስኳር ፋብሪካና የኢትዮጵያ አየር መንገድ፡፡ እነዚህ

ሁለቱም መሥሪያ ቤቶች በዩኒቨርሲቲ እያሉ የተግባር ልምምድ

ያደረጉባቸው ተቋማት ነበሩ፡፡ እርሳቸው ግን አየር መንገድን መርጠው

የኢንጂነሪንግ ክፍሉን ተቀላቀሉ፡፡ ጥቂት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ እንግሊዝ

ሀገር በሚገኘው ‹‹ክራንፊልድ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› በሚባለው

ተቋም ገብተው በአየር ትራንስፖርት ኢንጂነሪንግ ዘርፍ የማስትሬት

ዲግሪያቸውን አግኝተው ሀገራቸው ተመልሰው ወደ ሥራ ተሰማሩ፡፡

ከትምህርት መልስ በሥራ ዘርፍ ቆይተው ለሥራ አሜሪካ በሄዱበት

ሥራቸውን ሲያጠናቅቁ እርሳቸው ኑሮአቸውን እዛው አደረጉ፡፡ ይሁን

እንጂ አሜሪካ ለሥራ መሠማራት አስቸጋሪ የሆነበት ወቅት ስለነበር ለትንሽ

ጊዜ ተቸግረው ቆይተው የአውሮፕላን የተለያዩ አካላትን በሚያመርተው

‹‹ቦርጎርነር ዌስተርን ሀይድሮሊክስ ኩባንያ›› በጀማሪ ዲዛይን ኢንጅነርነት

ማገልገል ጀመሩ፡፡ እዚያ በየደረጃው አድገው የመሀንዲስ ክፍሉን

በማናጀርነት መርተዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ስለ ሼክ ሙሐመድ አጠቃላይ ሁኔታ ሲናገሩ፡- ‹‹ስለ ሼክ

ሙሐመድ ትልቅ ጥራዝ የሚወጣው መጽሐፍ መፃፍ ይቻላል፤ ሼክ

ሙሐመድ ቸር ነው፤ ትልቅ የሚጐረብጥ ነገር ቢያጋጥመው ሆደ ሰፊ

ስለሆነ ከባዱን ችግር ተሸክሞ ማለፍ የሚችል ነው፡፡ በሰዎች ላይ ያለውም

አስተያየት የተለየ ነው፤ ሰው እንዲጐዳ አይፈልግም፡፡ ሼክ ሙሐመድ

ውለታን የሚያከብር ሰው ነው፡፡ ውለታን አይረሳም፡፡ ሼክ ሙሐመድ

በባህርይው የንጉሥ ዓይነት ጠባይ አለው በእኔ አጠራር ኮምፓርትመንት

እለዋለሁ፡፡ እርሱ ሰዎችን እንደ ችሎታቸውና እንደ ጠባያቸው በተለያየ

ዘርፍ ባማረ አያያዝ ያስተዳድራቸዋል፡፡ ይህ የትልቅ ሰው መለያ ነው፡፡

የዚህ አይነት ባህርይ የነበራቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን

ነበሩ፡፡ ሼክ ሙሐመድ አብሮ ያደገ ከሆነ ከትንሽ እስከ ትልቅ፤ ደሀ ወይም

ሀብታም ሳይለይ አብሮ የሚያሳልፍ ነው፡፡

ሼክ ሙሐመድ የማይወደውም አለው፡፡ ሰው ቃሉን እንዲያከብር ይፈልጋል።

እርሱ ሊረዳው የሚፈልገው ሰው መሻሻል የማይፈልግ ሲሆን ያስከፋዋል።

ለሥራው እንቅፋት የሚሆነውና የተንዛዛ ቢሮክራሲያዊ አሠራርንም

አይወድም፡፡ እርሱ ቶሎ ሥራ እንዲፋጠንና ዕድገት እንዲያይ ይፈልጋል፡፡

ከዚህ ውጪ ሼክ ሙሐመድ ዘመድና ሀገርን የሚወድ ሰው ነው፡፡ ለዚህች

ሀገር ዕድገት ዕውን መሆን ጽኑ አቋም ያለው ሰው ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት እንዴት እንደተመለሱም ሲገልፁ ‹‹ቀደም ሲል ወደ ሀገር

ቤት የመምጣት ዕቅዱና ሀሳቡ አልነበረኝም፡፡ ሼክ ሙሐመድ በሀገር ቤት

የሚያደርገው የልማት ተሳትፎ እየተስፋፋ ሲመጣና በዋሽንግተንም ቢሮ

ከፍቶ እንቅስቃሴ ሲጀምር ስለተገናኘን ‹‹እኔ በሀገር ቤት በልማቱ ዘርፍ

እየተንቀሳቀስኩ ነውና አንተም ብትረዳኝ›› የሚል ጥያቄ ስላቀረበልኝ

በአንድ በኩል የቤተሰቤ ሁኔታና የለፋሁበት የሥራ ዘርፍ ሲያስጨንቁኝ

በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አጋጣሚ ገንዘብ እየከፈለች ያስተማረችኝን ደሀ

ሀገር ለመርዳት ይህ ዕድል ከየት ይገኛል የሚለው ሀሳብ አጣብቂኝ ውስጥ

ቢከተኝም ለጥቂት ወራቶች አሜሪካ ዋሽንግተን በሚገኘው በእርሱ ቢሮ

በመሆን ጥናቴን በማካሄድ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣትም ሀገር ውስጥ

ወደ ገጽ 6 ዞሯል


Recommended