+ All Categories
Home > Documents > LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

Date post: 14-Apr-2018
Category:
Upload: leaimero
View: 257 times
Download: 2 times
Share this document with a friend
34
7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7 http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 1/34  አእምሮ መጽሔት፥ የነሐሴ/August እትም -ቅጽ I- ቁጥር  – 05/08-7  አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም  – I-05/08-7
Transcript
Page 1: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 1/34

ለ አእምሮ መጽሔት፥ የነሐሴ/August እትም -ቅጽ I- ቁጥር  – 05/08-7

ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም  – I-05/08-7

Page 2: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 2/34

 

*

ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም  – I-05/08-7 

ለ አእምሮ  –  Le’Aimero © መጽሔት 

http://leaimero.com 

ሰሞኑ ጽሁፎችና ሰነዶች/ Recent Articles

  ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም  – I-05/08-7   ፀጋ፥ብርሃን 

  ዘመነ፥ብርሃን / Enlightenment   ግ ብ ፅ / ምን ሊያስተምረን መጣ ? 

  ዘ ጋርዲያን / The Guardian 

  ዓለም እንዴት ሰነበተች? 

  “ራዕይ ራዕይ …. “ዶቸ ቬለ የጀርመን ራዲዮ፤ ውይይት   ውርሰ፥ቅርስ 

  የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ደብዳቤ ፣ ለንጉሠ፥ነገሥቱ (1965) 

  Ethiopia to Yemen – The Most Dangerous Journey on Earth (BBC) 

Page 3: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 3/34

ፀጋ፥ብርሃን 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

ፀጋ፥ብርሃን 

ሲያይዋት ትንሽ ናት።ጠጋ ብለው ሲተነትንዋት ይህ ነው የማይባል ትልቅ ነገርነች። 

ሳይታሰብ ብቅ ትላለች።ቆይታም ሳትወድ ትጠፋለች። ወዳጆቹዋ በነፍስ ግቢናበነፍስ ውጪ ሰዓት ብዙ ናቸው።የልባቸውን ያደርሱ ቀን ግን ተራ በተራ እነሱእሱዋን እነደማያውቁዋት ጨርሶ ይከዱዋታል። 

ከመሣፍንቶች ጋር አንድ ጊዜ አብራ ትቆማለች። „አብዮተኞችም“በጣምአድርገው ያስጠጉአታል።አክራሪዎቹም ያቅፉአታል። ፋሽሽቶቹም እነደኮሚኒስቶቹ አላማቸውና ፕሮግራሞቻቸው ላይ ከፍ አድረገውያስቀምጡአታል።

ሥልጣን ላይ ሲወጡ ደግሞ ብዙዎቹ መልሰው እንደ የሚፋአጅ የፍም እሳት፣እርግፍ አድረገው ሁሉም ይጥሉአታል። በእግራቸው ቢረግጥዋት -ይረግጡዋትል- ደስተኛ ናቸው። 

ለወረሪ ጠላት መቼም እንደ ሱዋ „አመቺ“ ነገር የለም። በእሱዋ ስም ይዘምታል።በእሱዋም ስም ገንዘብ ይሰበሰባል። ሰውን ወደ ጦር ሜዳ መሰብሰብ ይቀላል።

ወጣቶች ልጆችም ዕውንት መስሎአቸው ሕይወታቸውን እሰከ መሰዋት ድረስይሄዳሉ። ተንኮልኛ አታላዩም፣ ይህን ሰለሚያውቅ እሱዋን ያስቀድማል። 

Page 4: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 4/34

የዋሁም „ዕውነት“ ነው ብሎ ይህን የሚሉ ሰዎችን ሳይጠይቅና ሳይመራመርዓይኑን ጨፍኖ ይከተላቸዋል። ሳያውቅ የገባበትን ጣጣና መንጣጣ አደገኛ መሆኑን የሚረዳው ግን ነገር ከእጁ ከአመለጠች በሁዋላ ላይ ነው።… ሲደርስበትደግሞ ብዙ ነገር አልፎአል። 

ልቡን አንዴ የሰጣቸው ደግሞ፣ ቢያታልሉትም „አሜን“ ብሎ ተቀብሎ ምንተ-ዕፍረቱን ሸፋፍኖ ውስጥ ውስጡን እየተቃጠለ፣ አንገቱን ደፍቶ ይከተላቸዋል። 

የተቀረው ዓይኑን እሰከሚከፍት ድረስ በጭፍን መንገዱ አለጥያቄ አብሮይጓዛል። የደረሰበት ቀን ግን ወደ ሁዋላ ማለትም እሱንም ይከብደዋል። 

ይህን ቀስቃሾቹ በደንብ ያውቃሉ።ይህን ተንኮለኛ አደራጆቹ በደንብ

ይጠቀሙበታል። 

ማናት ይህቺ፣ አንዳንዴ በሦስት አንዳንዴ በአራት ፊደል የምትጻፈው፣ ነገር ? 

ከመሣፍንቱ እስከ ተራ አወናባጁ?… ከፋሽሽቱ እሰከ ኮሚኒስቱ ፣ ከአናርኪስቱእሰከ ሽፍታው፣…ከቅኝ ገዢው እስከ…ባሪያ ነጋዴው ድረስ የሚያነሱዋት ቃል? 

ሊበርቲ ናት?… ወይስ አርነት?… ነጻነት ናት ወይስ ነጻ- ሰው?…ጥበብ? …ብርሃንናዕውቀት? ወይስ ጨለማ?…

ሞሰሊን ኢትዮጵያን ሲወር ያስቀደመው ቃል ቢኖር „…የሥልጣኔ ሚሺን፣…ኢትዮጵያን ከባርንት ለማውጣት የታቀደ ዘመቻ… ሲቭላይዚንግ ሚሽን..“የሚለውን ቃል:- ለማስታወስ ወርውሮ ነበር። የወረራ ዘመቻውንም ያ ፋሽሽትየሰየመውም በዚሁ ግሩም ቃልና ጥሪው ነበር። 

ሌኒንና ስታሊን፣ ማኦና ካስትሮ፣ ከእነሱ በሁዋላ የተነሱት ሥፍር ቁጥርየሌላቸው „ነጻ-አውጪዎች፣ እስከ መገንጠል የሚለውን ትግላቸውን“ የቀየሱት፣

ያራመዱት፣ የልባቸውን ያደረሱት፣ በዚህች „አርነት“ በምትባለው ቃል ነበር። 

በሌላ በኩል በአፍሪካና በደቡብ አሜሪካ በሕዝቡም ላይ ተነስተው የጨፈሩትወታደሮች ያራገቡት „ሥርዓትና ቃል…“ ሌላ ሳይሆን ይኸው፣„…አርንትን፣..ነጻነትን፣ እኩልነትን፣ ሰበአዊ መብት፣ …ዲሞክራሲን “ነበር። የወታደሩመንግሥት፣ ደርግም ብሎታል።„እናመጣላችሁዋለን…“ በሚለው ውሸት ዙሪያእስከ አሁን ድረስ ብዙዎች ቆመዋል።

የ20ኛው ክፍለ ዘመን የውሸት ፖለቲካም በብዙ አካባቢ የተመሰረተው ፣በዚሁ

አታላይ ቃል ላይ ነው። እላይ ከተጠቀሱት ቡድኖችም ውስጥ አንዳቸውምየገቡበትን ቃላቸውን እስከ አሁን ድረስ አላከበሩም።

Page 5: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 5/34

እንግዲህ ነገሩ ያላው እነሱ ጋ ሳይሆን እኛው ጋ ነው።

„ነጻነትን፣…በሌላው አካባቢ እንደሚባለው፣ ሊበርቲን፣…ጥብብን፣ ብርሃንናዕውቀትን…“ እባካችሁ ስጡን፣ እባካችሁን አምጡልን ብለን፣ ማንንምየምንጠይቀው ነገር ሳይሆን ፣ እኛው ነጥቀን የምንወስደው ነገር ነው።

መሬት ላይ የወደቀውን ነገር ብድግ አድርጎ የእራሳችን ማድረጉ ደግሞ ወንጀልአይደለም። ለዚህ ደግሞ ዕውነቱን ለመናገር፣ „ግብ ግብም፣ጦርነትም”

የሚባለው ነገር ውስጥ መሄድ አያስፈልግም ። 

ማመዛዘናና ነገሮችን መመልከት፣… ማሰብና ያሰቡትን ነገር መናገር፣… መጻፍናመወያየት፣ መከራከርና መተቸት፣ እኛ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ወይምአቴኢስቶች እንደሚሉት „ከተፈጥሮ“ ያገኘነው ፀጋና ስጦታ ነው። ለምንአምባገነኖች ይህቺን መብት ይፈሩአታል? 

አንድ አምባገነን ሥልጣኑን መከታ አድርጎ ብዙ ነገሮችን „አታድረጉ ብሎ አንድን

ሕዝብ ሊከለክል“ ይችላል። ማሰብን ግን እሱ ጨርሶ መከልከል ይችላል?በምንም ዓይነት፣ ማሰብን መከልከል አይችልም። በምን አቅሙ ነው፣ የአንድሰው ጭንቅላት ውስጥ ገብቶ ሊከለክል የሚችለው? ይህማ አስቸጋሪ ነው። 

አእምሮ ያሰበውን፣ የታሰበውንስ ቀና ሐሳብ ከሌላው ጋር ለመነጋገር (ምንምዓይነት ሥልጣን ቢኖረው) ማንም ሰው ማንንም ሊያግደው አይችልም ። 

እንግዲህ አሁን ያለነው፣ በዚህ „ፀጋ-ብርሃን“/ዘመነ፥ብርሃን በሚለው ጽሑፋችንእሱን አንስቶ መመልከቱ ላይ ነው። አምባገነኖች የእያንዳንዱን ግለሰብ ነጻነት፣

ለምን እንደጦር እንደሚፈሩ በየጊዜው አንስተን እንመለከተዋለን። 

Page 6: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 6/34

እንግዲህ ይህ አንደኛው   አርዕስት ነው።  

ሁለተኛው  ስለ ጋርዲያን ጋዜጣ ነው።የምዕራቡ ዓለም ስለ ሚኮራበት ስለ ፕሬስነጻነት፣ ስለዚያም አታሚዎች ፍተሻ ፣ስለ ጋርዲያን ጋዜጣ ነው። ቻይና በዚህ

ጉዳይ ላይ ምን እንዳለች አስተያየቱዋን ፈልገን ለማውጣት አስበን ነበር።አልተሳካልንም። ግን አገላብጣችሁ እንደምታዩት የሌሎቹም አስተያየት ቀላልአይደለም። 

ሦስተኛው   አርዕስት„ ….እኛ ጥቁሮች እራሳችንን በእራሳችን፣ ተመካክረንናተቻችለን ተፈራርቀን መግዛት ስለ አልቻልን፣ የዱሮ ጌቶቻችን ነጮች መጥተውይግዙን…“ በሚለው አዲስ ጥሪ ላይ ያተኩራል።

ይህ ደግሞ ምን እንበላው „…ያሳዝናልም። ያስቃልም። ያቃጥላልም።ይኮረኩራልም። ….“ ወቸ ጉድም ያሰኛልም። 

በተጨማሪም አወዛጋቢ ሰለሆነው የግብፅ ጉዳይ ያለንን አስተያየትና፣ እንዲሁም ስለ  ውርሰ፥ቅርስ ለመነሻ  ያህል  የደረሰንን  ሰነደንና  የሰዓሊው  የእስክንድር ቦጎስያን ማስታወሻችንንም ተመልከቱት። 

ዋና አዘጋጁ 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

 ——————–  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013 

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Page 7: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 7/34

ዘመነ፥ብርሃን / Enlightenment 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

ማንም ሊያግደው የማይችለውየተፈጥሮ ጸጋ! የተፈጥሮ መብት! 

በትክክል ስለ ነጻ ሰውና ስለነጻነት፣ስለ ማሰብና ስለ አለ ፍረሃት መነጋገር፣ ስለእነሱም መጻፍና መመራመር የተጀመረው:- እንደገና በትክክል ነገሩንለማስቀመጥ “ ስለ ባሪያ ሳይሆን ስለ ነጻ ሰውና ስለነጻነት“ (ይህ መነገር ያለበትአስፈላጊ ቦታ ነው) ስለዚህ ጉዳይ ማሰብና መነጋገር የተጀመረው በጥቂት ሰዎችየጥናት ክበብና የጽሕፈት ቢሮ ውስጥ ነው። 

የደረሱበት ውጤትና ተመክሮዎች፣ ታትሞና ተባዝቶ፣ለሰዎች መበትን በአውሮፓየተጀመረው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ነው። 

የዚህ ጥናት ውጤት የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች እጅ ይገባል።ቆየት ብሎተማሪዎቻቸው ቀበል አድርገውት በየአለበት፣በመጀመሪያ በዘመዶቻቸውናበጓደኞቻቸው መካከል አሰራጭተውታል። 

እንደሚባለውና ብዙዎቹ እንደሚገምቱት የጀርመኑ ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንትአይደለም „ስለ ዘመነ- ብርሃን፣ስለ ጸጋና ስለ ጧፍ ልጆች፣… ስለ ጨለማው

ዓለም „ የመጀመሪያውን የአካዳሚ ጽሑፍ የጻፈው።ያስተማረው። የተነተነው።

ለካንት አስተማሪዎቹና የቅርብ ጓደኞቹ ናቸው፣ አርዕስቱንም፣ሁኔታውንም ለእሱየእንግሊዘኛ ቋንቋ በደንብ ለማያውቀው ፈላስፋ በሁዋላ ያስተዋወቁት። 

ካንት ግን አለጥርጥር ትላልቅ ጽሑፎች አውጥቶ የዘመኑን ሰዎችና ከዚያ በሁዋላየተወለዱትን ትውልዶች፣ ስለ ሞራልና ስለ ኤትክ፣ስለ የሰው ልጆች አብሮየመኖር ዘይቤ፣ ስለ የዓለም ሰላም፣ ስለፍትህና ፍርድ ብዙ ነገሮች

አስተምሮአል።

Page 8: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 8/34

እንግዲህ የኢንላይትሜንት :- የዘመነ- ብርሃን ትምህርት ፣ ዋና አባት ካንትሳይሆን የእንግሊዙ ፈላስፋው ጆን ሎክ ነው። 

ሎክ ይህን ዕውቀት የሰበሰበው፣ከቡዙ ጊዜ ጥናት በሁዋላና እሱ እራሱ ከአየውና

ከአገኘው ተመክሮ ተነስቶ ነው። ግሩም ጥያቄዎችን ለእራሱና ለሌሎቹምበማቅረቡና ለእሱም ጊዜ ወስዶ ከፍተኛ አተኩሮስ ሰጥቶ፣ በመልስ ፍለጋውምላይ በመጠንከሩም ነው። 

ከጓደኞቹ ጋር አብሮ እየተገናኘ በአደረገው የረጅም አመታት የጥናት ጊዜ በሁዋላእሱ እንደሚለው „…የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ሁሉም ብዙ ተንከራተው“ እንደነበር በተወልን ማስታወሻው ላይ ያስታውሳል። 

በእርግጥም ጆን ሎክ ከጓደኞቹ ጋር በየጊዜው እየተገናኘ በጋራ በሚያካሄደውየጥናትና የምርምር ድካም ፣ እሱ እንደሚለው፣ የተሳሳተ መንገድና የተሳሳተፍንጭና ዱካ ተከትለው የማይሆን ቦታ ደርሰው ነበር። 

ግን አስተዋዩ ሎክ፣እሱ እራሱ እንደሚለው፣ ያን ጎዳና ጥሎ በ1689ዓ.ም(እ.አ.አ) „አንዳንድ አመለካከቶች፣ በፖለቲካና በሃይማኖት፣እንዲሁምበአስሰተዳደር ላይ…“በሚለው አርዕስት ሥር የራሱን አመለካከቶች ጽፎአደባባይ ላይ ሳያወጣው ለተወሰኑ አመታት ሐሳቦቹን አስቀምጦታል። 

ሎክ እሱን በሚያበረታተውና መልሶም በሚጠይቀው በፖለቲከኛው በሁዋላየመኳንንት ማዕርግ አግኝቶ ግራዝማች የተባለው አንቶኒ ኤሽሌ ኩፐር፣በእሱምክንያት የአመለካከት አቅጣጫውን ሊቀይር ችሎአል።

ግራዝማቹ የኤርል ኦፍ ሻፍትስበሪ”.. እስቲ ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ አሰበህጻፍልኝ..“ ብሎ ይጠይቀው እንደነበር ይጠቀሳል። ትውውቃቸው በሰኔ/ሐምሌ1666 አካባቢ ነው። 

የእሱና የአብዛኛው የጧፍና የብርሃን ልጆች የትግል አቅጣጫም „ …የሰውንልጆች፣ በሙሉ በዚያውም የእንግሊዝን ኑዋሪዎች“ እነሱ እንደሚሉት“…ከሮማው ሊቃነጳጳስ የባርነት ዘመን ነጻ -ለማውጣት ምን እናድርግ ?“ የሚለው„ጥያቄና የትግል ብልሃት“ የጉዞአቸውን አቅጣጫ እነደወሰነውና እንደቀየረውእነሱም፣አረጋግጠው ተናግረውታል ።

በአጭሩ ሎክ የሮማውን ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳስ የበላይነት፣ እንደሌሎቹእንግሊዞችና የሰሜን አውሮፓ ተወላጆች እሱ የማይቀበል ሰው ነበር።

እንዲያውም „በቫቲካን ሥር ሁኖ የካቶሊክን ሃይማኖት ተከትሎ መኖርንእንደባርነት“ የሚያይ ሰው ነበር። በዚህ አመለካከቱም ብቻውን አልነበረም። 

Page 9: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 9/34

ዘግየት ብለን እነደምናየው የሎክ ትምህርቶችና አመለካከቶች በፈረንሣይ እናበአሜሪካን አብዮት፣ከዚያም በሁዋላ እነሱ እራሳቸው ወደው በነደፉትናበተቀበሉት ሕገ- መንግሥት ላይ እንዲሰፍር ተደርጎአል።

በጀርመኑ በ1848 እና እንደገና ከዘውድ አገዛዝ በሁዋላ ተነድፎ በወጣው በ1918የጀርመኑ የቫይመር ሕገ-መንግሥት ላይ የጆን ሎክ መሰረታዊ አስተሳሰቦችአብሮ ተጠቃሎ እንዲቀመጥም ተደርጎአል። 

የዓለም ሕዝብ በፋሺዚምና በኮሚኒዚም ተዋክቦና በሚሊዮን የሚቄጠሩ ሰዎችበዚያ ጦስ ተጨፍጭፈው ከአለቁ ወዲህም፣ ከዚያ በተገኘው ተመክሮም“አረመኔዎች ተመልሰው እንዳይመጡ በተነደፈው የጋራ ሐሳብም ላይ” የጆንሎክ መሰረታዊ ሐሳቦች መነሻ ሁነው „ዓለም አቀፋዊው የሰባአዊ መብት አዋጅ“

ሊታወጅም ችሎአል። ንቁ የሕግ አዋቂ የኢትዮጵያ ልጆችም አብረው የጥቁሩንሕዝብ ወክለው የ1948ቱን አዋጅ ነድፈዋል። እንደሚባለው “የነጮች አዋጅ”ሳይሆን አብረው እንደአባልነታቸው አጽድቀዋል። “የአረመኔዎች አገዛዝ ተመልሶእንዳይመጣ” -ይህ ነው የዓለም አቀፉ አዋጅ- ይህ ነው የጀርመኖች ከሒትለርበሁዋላ የወጣው አዲሱ ሕገ-መንግሥት ይዘት “…የሰው ልጆች ሁሉበተፈጥሮአቸውና በሕግ ፊት  እኩል ናቸው የሚለውን መሰረተ ሐሳብተንተርሶ፣… ማንም  ሰው የሌላውን ሰው መብትናሰበአዊ ክብሩን ሊደፍረውም ሊረግጠውም አይችልም …”ብሎ ያግደዋል።

ከዚያም ስለ መብቱ፣ከግል ሀብት  እስከ የግል እምነቱ፣ ስለ መናገርናመጻፍ ነጻነቱ፣…ፍርድና ፍትህ፣ ስለ ተቃውሞ መብቱ… ይዘረዝራል። 

ሎክ በምርምር ዘመኑ „ ብዙ የተለያዩ አስተሳሰቦችና እምነቶች በአሉበት በአንድሕብረተሰብ ውስጥ እንዴት ተቻችሎና ተከባብሮ መኖር ይቻላል?“ የሚለውንጥሩ መጣጥፉን (በ1667እ.አ.አ) ጽፎ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን፣ አብሮ ለመኖርአስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን አስፍሮልናል።

ሰውዬው ” ባለ ግርማው አብዮት Glorious Revolution” የሚባለውየእንግሊዞች አብዮት ከመፈንዳቱ በፊት የስደት ዓለምን በነጻው ሆላንድቀምሶአል።

በጽሑፉም የአንድ መንግሥት ወይም የአንድ አስተዳደር ዋና „ዓላማና ኃላፊነቱ፣ጸጥታና ሰላም በዜጎቹ መካካል ማረጋገጥ፣ ሰው የፈለገውን ሃይማኖትእንዲከተል መልቀቅ እንጂ ከዚያ አልፎ ያ አስተዳደር በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ገብቶ ሰዎች እንዴት መኖር እንዳለባቸው፣ማንን ማምለክ እንዳለባቸው፣… በማንሃይማኖታዊ አባት ሥር መተዳደር እንዳለባቸው መወሰን ቀርቶ፣ እዚያ ውስጥአልፎ ተርፎ ገብቶ ማብኳት አንድ መንግሥት የለበትም „ ይላል።

Page 10: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 10/34

በእሱ እምነት „መንግሥት በዚህ ጉዳይ አያገባውም“ባይ ነው። ከዚሁ ጋርፈላስፋው ሎክ አንድ ሰው፣አንድ ሕዝብ የፈለገውን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣እራሱመርጦ ሊከተል ይችላል።” 

ይህን ማድረግ በእሱ እምነት „ሀገር እንዳይበታተን ይጠቅማል“ ባይ ነው።ንጉሡ  ግን የእንግሊካን እንጅ የካቶሊክ ሃማኖት ተከታይ ፍጹም መሆንየለበትም ይላል። ቅራኔ ይታይበታል? አይደለም። 

የጆን ሎክ ጉዞ በዚህ አቅጣጫ ጀርመኖችም ከሮማው የቫቲካን ካቶሊክቤተክርስቲያን ለመላቀቅ ከአደረጉት ከማርቲን ሉተር የፕሮቴስታን እንቅስቃሴምጋር በጥብቅ ይመሳሰላል ። 

ግን ደግሞ የፈላስፋው አመለካከቶች፣ከዚያም አልፎ ይሄዳል። “መለኮታዊ ነኝ”የሚለውን የአንድ ንጉሥ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝን እንደ ሮማው ካቶሊክቤተክርስቲያን እሱንም ያቃወማል።

ብረሃን ልጆች፣ የንጉሰ ነገሥቱን ዙፋንና ዘውድን ሳይተቹና ሳይነኩ በዚያ ላይያቆማሉ ብሎ መገመት ስህተት ነው። በ1680 „…መለኮታዊው የንጉሡ ሥልጣን…“በሚለው ጽሑፉ ሎክ ስለ የሥልጣን ገደብ በንጉስ ላይ አንስቶከዚሁ ጋር ራመድ ብሎ ስለ ነጻነትና ስለ እኩልነት፣ ስለፍትህና ዳኝነት፣ ስለ

የፓርላማ መብትና ገደብ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ፣ ምን መምሰል አለበት?ብሎ ወደ መዘርዘሩ ይራመዳል። 

እንግዲህ ይህ ሰው ቆየት ብሎ በቀጥታ እኛን የሰው ልጆችን(የትም እንሁን የት፣እስላም እንሁን ክርስቲያን፣ አሕዛብ እንሁን፣ኮሚኒስት ወይም ሶሻሊስት…)በቀጥታ ሁላችንም ሰለሚያሳስበውና ስለሚያስጨንቀው በሥራም ላይ ውሎሌላ ቦታ ማየት ስለ ምንፈልገው “ …ስለ በነጻ-የመኖር መብት፣…ስለ ነጻ-ሰውመብት፣ ስለ የግል ሀብት፣ በእሱም የሰው ልጅ ስለ አለው መብት…“ ፈላስፋውጆን ሎክ አንስቶ መልስ ይሰጣል። 

ንጉሠ ነገሥቱ ሕግ ከጣሰ? ብሎ ይጠይቃል። ሕዝቡም መብቱን በመንግሥት፣በገዢ መደብ ከተገፈፈ? ምን እናድርግ ይላል። ፈላጭ ቆራጩ ጉልበተኛ ገዢ አልሰማም ከአለ? ….ያኔ ሕዝቡ፣ ሰበአዊ መብቱ ተገፎ ተገዢ ባሪያ እንዳይሆን፣ፈላስፋው „…እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በተፈጥሮ የሰጠውን መብቱንለማስከበር፣ላለማስነጠቅ መነሳት“ አለበት ብሎም ያስተምራል። 

ካንት በአስተማሪዎቹና በአብሮ አደግ ጓደኞቹ የጆን ሎክን ከእንግሊዘኛ ወደ

ጀርመንኛ የተተረጎመውን ጽሑፍ አገላብጦ እላይ እንዳልነው ወፋፍራምመጽሓፍትን በሁዋላ ጽፎልናል።

Page 11: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 11/34

የአሜሪካንንና የፈረንሣይ አብዮት አባትና አዋላጆች በሕገ-መንግሥታቸው ላይ„ስለ ምርጫ፣ ….“ የሎክን ሓሳቦች መሰረት አድርገው ወደ ዲሞክራቲክ ሥርዓትከአንድ መቶ አገር የበለጡ መንግሥታት ተሸጋግረዋል። እንደተባለው ከ1948 ቱየተባበሩት መንግሥታት አዋጅ ወዲህ “ለሰበአዊ መብት መታገል፣ ለነጻ-ፕሬስመሟገት፣ ለግል ሀብት መቆም፣መምረጥና መመረጥ፣መተቸት፣ፊልም መቅረጽናመጸሕፍቶች ማተም …” እንደ ወንጀል አይቆጠርም። የሎክ ትምህርት ውጤትይህ ነው።

ይህን ሐሳብ ግን :- ይህ ነጥብ ሲነሳ የሚቆጡ ደግሞ የሚበሳጩ አይጠፉም- እነሌኒንና እነ ስታሊን፣ ማኦና ሖዲጃ፣ ፖልፖትና ካስትሮ፣ ኢሳያስና መንግሥቱኃይለ ማሪያም…ቆጥረን አንጨርሰውም፣ ተነስተው ….ይህን ሐሳብ ውድቅአድረገው „አምባገነን ሥርዓታቸውን“ (መውደቃቸው ላይቀር) በገዛ

ወገኖቻቸው ላይ መስርተዋል።

እዚሁ “የቶታሊቴሪያንና የአምባገነኖች የአስተሳሰብ” ማጥ ውስጥ ገብቶ አልወጣያለው ሰው ቁጥር ሌላ ቦታ እየቀነሰ ሲመጣ እኛ ጋ ተበራክቶአል። ይህ ዕውነትነው? 

ጆን ሎክ ፈላስፋው „ስለ አእምሮ ነጻነት አመጣጥ „ ጽፎአል። ወዳጄ! 

በአንዴ ሁሉን ነገር ዘርግፎ ማስቀመጥ አይቻልም። በቂ ጊዜ ወደፊት ስለ አለንቀስ ብለን እንመለስበታለን። ቀስ ብለን እንደርስበታለን። 

አንድ ጥያቄ ግን አንስተን ጉዳዩን እዚህ ላይ ለጊዜው እናሳድራለን። ለምንድነውየኢትዮጵያ ምሁር እንደዚህ ዓይነቱ፣ እነደ ሎክ ያሉ ፈላስፋዎች ላይአተኩሮአቸውን ሳይጥሉ እንዲያው „…በላብ አደሩ አምባገነን ሥርዓት፣በዚያፍልስፍና ተማርከው….“ ” …በሌኒን እና በስታሊን ፣… በማርክስና በማኦትምህርት” ላይ ዓይናቸውን ጥለው እሰከ አሁን ድረስ እዚያው ላይ ብዙዎችየቀሩት? ለመሆኑ እነሱስ ዛሬ ስንት ናቸው? 

…የሰው ልጆች:-ሁለተኛው ጥያቄ- ዕድሜ ልካቸውን ሊገዛቸው የሚፈልገውን“አንድ አምባገነን ሥርዓት” ምን ያህል ጊዜ ዝም ብለው ይቀበሉታል?…ይሸከሙታል?

በሌላ በኩል „ በተፈጥሮ ያገኘነውን የነጻነት መብት“ እሱን ማን ሊያግደውይችላል? ለምን ድነው “ስለሃይማኖት ነጻነት፣… ስለየተለያዩ ሃይማኖቶችበኢትዮጵያ ተቻችለው መኖር” በየጊዜው እያስታወሱ መናገር የሚያዘወትሩ

ሰዎች፣ ለምን ስለ የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች እንደዚሁ ተቻችሎ መኖርየማይናገሩት? 

Page 12: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 12/34

ለምንድነው ስለ “ብሔር/ብሔረሰቦች እኩልነት  በኢትዮጵያ አለ” ብለውየሚናገሩ ሰዎች፣ ስለ “ሰበአዊ መበት፣ ስለ ግለሰብ ነጻነት፣ ስለ ነጻ-ፕሬስአስፈላጊነት ግልጽ በሆነ ቋንቋ የማይናገሩት? 

መልሱንም እንግዲህ ቢቻል ወደፊት በጋራ መልስ ብለን እንመለከተዋለን። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል 

ግ ብ ፅ / ምን ሊያስተምረን መጣ ? 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

„ጠላት“? አንድ ግራ የሚያጋባ ቃል! 

„አብዮት“፣- ፈረንሣይ አገር አንዴ እንዳደረገቸው- በኢትዮጵያ ልጆቹዋን ቅርጥፍአድርጋ በልታለች። ግብጽ ላይ ደግሞ -አንዱ የጀርመን ጋዜጣ እንደ ጻፈው-ይህቺ ጨካኝ አብዮት ብቅ ብላ „ወንድሞቹዋን“ ከእህቶቹዋ ጋር ጠብሳ፣ ዋጥአደርጋችዋለች።“

ነገ ደግሞ – ይህን ዛሬ ማን ያውቃል- አንዱን ቀቅላ እንደ ልማዱዋ ትበላለች።ምናልባት -ይህን ማሰቡ ያስፈራል- እናትና አባትዋን አሳዳ…ትጨርስም ይሆናል። 

ወሬው እንደተሰማ፣ ዜናው ከካይሮ እንደተስፋፋ(-የአገሬን ልጆች መቼምበዚህቺ ድፍረታቸው እወደቸዋለሁ፣ በዚህችም ችሎታቸው አደንቃቸዋለሁ -)ቶሎ ብለው፣  “… ሙርሲ ይህን ቢያደርግ፣ የእስላም ወንድማማቾች ያን

ቢያደርጉ፣ ወታደሩ ለአገሩና ለሕዝቡ ቢያስብ፣ አንድ ላይ ተቀምጠው ቢነጋገሩኑሮ፣….ሁለቱም ሦስቱም፣አራቱም ወገኖች የጋራ መንገድ ቢፈልጉ፣እረ ቢያንስ

Page 13: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 13/34

በትንሹ ቢከባበሩ፣… አስታራቂ ሽማጋሌዎች እንኳን መኻላቸው ቢገቡ…ይህ ሁሉእነሱ እነደሚሉት ትርምስና ደም መፍሰስ፣ሞትም ላይ በአልደረሱም ነበር…“፣ይላሉ። 

እንደዚህ ዓይነቱን ቀና ሐሳብ ከሚሰነዝሩት ሰዎች መካከል፣መገመትእንደሚቻለው ኢህአዴግን የሚደግፉ ሰዎችም (ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግንሌላ ነገር ያነሳሉ) እንደ ተደመጠው፣ እነሱም ይገኙበታል። 

አዲስ የተፈጠረው የግብጹ ውስጣዊ የፓለቲካ ሁኔታ ግልጽ አድርጎ የሚያሳየንአንድ ነገር ቢኖር (ምን ግብጽ ብቻ!… ጠቅላላው መካከለኛው ምሥራቅ)፣እንዴት አድርጎ፣  አለመደማመጥ፣ በጠላት አይን ከመሬት ተነስቶ መተያየት፣…የሁዋላ ሁዋላ፣ ቀስ እያለ፣ ከባድ ችግር ውስጥ አንድን ሀገርና አንድን ሕዝብ

እንደሚከት ቁልጭ አድረጎ፣ያስተምረናል።ያሳየናል። 

እንዴት አድርጎም ስለ „ሀገር አስሰዳደር ብልሃትና ዘዴ፣ ምንም ነገር አለማወቅ“፣ ምን ያህል መመለሻ የሌለው እሳት ውስጥ አንድን ሕዝብና እንድን ሀገር፣በጥቂት ሰዓታት፣በትንሽ ጊዜ፣ በቅጽበት፣ እነሱንጨምሮ እንደሚበታትንማስተዋል የሚችል ሰው ቢኖር፣ የግብጽ ሁኔታ፣ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።ያስተምራል።

ስለ የተለያዩ የሰው ልጆች በህሪና ተፈጥሮ ቅንጣት ያህል እነኳን ደክሞለመረዳት አለመቻል፣ አለመሞከርም ገፍትሮ መጨረሻ ወደ ሌለው የማይታወቅሁኔታም ውስጥ እነደሚከት፣ የግብጽ ግርግር ያስተምራል።ተጠንቀቁም ብሎይመክራል። 

ሀ 

ግብጽ አብዮቱን በአካሄደች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንደዚህ ትሆናለች ብሎየገመተ ሰው የለም።

ግብጽ የገባችበት ሁኔታና ችግር ደግሞ ማንኛውም አገር -የአስተዳደር ብልሃትንከአላወቀበት፣ ምክንያቱ እላይ ተገልጸአል- ዓይኑ እያየ፣ ነገ ሰተት ብሎ፣ ያ!ሀገርና ሕዝብ ሊገባ ይችላል።

ሌላም ትምህርት የግብጹ ሁኔታ ጥሎልን ሄዶአል። 

እሱም „ወታደሩ“ በግብፅ ሀገር (በሌላው ዓለም እንደምናውቀው)፣ „ በፖለቲካስር የሚተዳደር የሀገር መከላከያ ተቋም „ ሳይሆን፣ ይህ የጦር ሠራዊቱ እራሱንየቻለ(እስከ ዛሬ የምናውቀው አራት ተቋሞችን ብቻ ነው፣እሱም…የሕግማውጫ፣የሕግ መወሰኛ፣ ነጻ-ፍርድ ቤትና ነጻ- ጋዜጣን/ሜድያ…) „አምስተኛው፣

Page 14: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 14/34

የሕብረተሰቡ በዚያውም ፖለቲከኞቹንና የፖለቲካ አቅጣጫን የሚቆጣጣሪኃያል ኃይል“ ሁኖ ዘንድሮ ብቅ ብሎአል።

እንደሚባለው የግብጽ የጦር ኃይል፣ ዱሮንም ቢሆን „በአገሪቱ ውስጥ፣

በመንግሥት ስር የራሱ የሆነ “ልዩ መንግሥት“ ገና ዱሮ እንደ አቋቋመ፣የአደባባይ ምሥጢር ሁኖ ይነገርለታል።

የእራሱም የሆነ የተለያዩ እንዱስትሪ፣ምርት የሚያመርቱ የግል ፋብሪካዎች፣የንግድ ድርጅቶች፣የሕንጻ ተቋራጮች፣ የጉዞ ወኪሎችና የቱርስት ድርጅቶች፣ከእነሱ ጋር በየቀኑገንዘብ„የሚያትምበት“ ሆቴሎች፣ባንኮች፣ሠራዊቱ አሉት። 

„ሲሶ መንግሥት ነው“ ማለት፣አንድ ተመልካች እንዳለው፣  ይቻላል። ይህ

በግብጽ እንደሆነም እርግጠኛ ሁነው ብዙዎቹ ይናገራሉ።እንደዚህ ዓይነቱ የአሰራር ዘይቤምና ሐሳቡም ተስፋፍቶ ወደ ሌሎች የአፍሪካግዛቶችም እንደዘለቀና፣  አንዳንዶቹ የአፍሪካ የጦር ኃይሎች፣ ባንክ ቤቶችለመክፍት፣ ፋብሪካ ለመመስረት፣ የሕንፃ ተቋራጭ ለመሆን ዝግጅት ላይእንደሆኑ የአውሮፓ ጋዜጣዎችም ይጽፋሉ። 

ምን ይታወቃል፣ በዚህ በያዝነው በ21ኛው ክፍለ-ዘመን የግብጽ ጉዞ ተከታይአግኝቶ፣ እኛም ከሌሎች የአፍሪካ ሀገርና መንግሥታት ጋር ወደዚያው(ደርግእንዳልገዛን ሁሉ) እንደገና ተመልሰን እናመራ ይሆናል። 

በርካሽ የወር ደመወዝ የጦር ፋብሪካውን፣ሆቴሉን … በጉልበት ሥራየሚያንቀሳቅሱለት፣ነገሩ ከተነሳ ላይቀር „…ወጣት ወታደር እና ሰላይ ሁነውየሚቀጠሩት ልጆች“ እንደሆኑም ይጠቀሳል።

ሐሳቡ ከየት መጣ? ማነው የዚህ ዓይነቱ አሰራር አባቱ?

እሱን እነተውና „አብዮት ልጆቹን የምትበላው ለምንድነው?“ ብለን እንጠይቅ።ለ 

ቡዳ ስለሆነች አይደለም። ወይም የአብዮት „ዓይኑዋ „ ከሩቁ ስለሚወጋምአይደለም። ወይም ደግሞ አብዮት „…ደም ማሽተት፣ደም ማፍሰስ“ስለምትወድም አይደለም። 

አብዮት ልጆቹዋን ትበላለች የሚባለው በአንድ ነገር ነው። 

እሱም በአንድ ሀገር የሚኖሩ፣ ነገር ግን የተለያዩ አመለካከቶችና አቋሞችየሚያራምዱ፣ኃይሎች፣… እንበል ጥቂት ቡድኖች፣የፖለቲካ ድርጅቶች:-

Page 15: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 15/34

አቋማቸው ሊጻረርም ይችላል- „ በጠላትነት በደመኛ ጠላትነት መተያየት „የጀመሩ ሰዓት“ ፣ ያኔ! ነገር ተበላሸቶ፣”አብዮት ልጆቹዋን ለመብላት” ቢላዋን ትስላለች፣ድስቱዋን ትጥዳለች፣ ጠበንጃዋንትወለውላለች፣ ማለት ነው።

ቀደም ሲል „ሰውን ለመሰብሰብ ሆን ተብሎ የተወረወረ አይዲኦሎጂ የሚዋገውጠላት“ ያስፈልገዋል ብለናል።

አለበለዚያ ያ ድርጅት እንደ ምትሃት፣ ለአፍዝ አደንግዝ፣ ተከታዮቹንለመሰብሰብ የቀነጠሰው ቅጠል፣ ያን ቢል ይህን ቢያደርግ የመከተለው “ጀሌ”መሰብሰብ ሰለማይችል፣ድካሙ ሁሉ ከንቱ ሁኖ አይሰራለትም። 

ግን የተመኘው ከሰራለት ያኔ ! እነዚህ „በጠላትነት የሚተያዩና የሚፈላለጉ“ቡድኖች ፊት ለፊት፣ የተገናኙ ቀን ደግሞ „…ደመኛ ጠላቶች“ ስለሆኑየሚገላግላቸው ነገር (ይህ የታወቀ ነው) አንድ እርምጃ ብቻ ነው። እሱም አንዱሌላውን ቀድሞ (ሻለቃ መንግሥቱ ብሎት ጨርሶታል - ለምሳ ያሰቡንን ቁርስአደረግናቸው…እንዳለው) መግደልና መገዳደል ብቻ ነው።

ይህ ብዙ ቦታ ተደጋግሞ ታይቶአል።

እራሱ የቅርቡ የኢትዮጵያ ታሪክም ምስክር ነው።… ለመድገም:- ደረግና የደርግአባሎች እርስ በራሳቸው፣ ደርግና መሣፍንቱ፣ ኢህአፓና መኢሶን፣ ወያኔናሻቢያ፣ሻቢያና ጀበሃ፣ ደርግና ወያኔ፣ደርግና ሻቢያ፣ ኦነግና ወያኔ….ወያኔናአባሎቹ…ወዘተ፣እነዚህ ሁሉ እንደ ዕውር ተያይዘው ተናንቆዋል። ይህም ማየትለሚፈልግ ሰው ቋሚ ምስክሮች ናቸው።

ችግሮቻቸውን፣ በአንድ ዓረፍተ-ነገር ለመናገር ለመፍታት የሞከሩት በኃይል፣ ያውም በጥይት ነው። 

ለምንድነው በአውሮፓ ወይም በሰሜን አሜሪካ እንደዚህ ዓይነቱ“ጥላቻና የደምማፍሰስ ጭካኔ፣ በጠላትነት የመተያየት መንፈስና ሓሰቦች“ በዚያ አካባቢ፣በመካከላቸው ዛሬ የማይታየው?

ለምንድነው የምሥራቅ አውሮፓው፣ ጸረ-ኮሚኒስትና ጸረ-አምባገነኖች የሕዝብእንቅስቃሴ – ከአለ የሩሜኒያው ቻውቼስኮ የሞት ፍርድ በስተቀር – አንዲትጥይት ሳትተኮስ በሰላም ያለቀው?ለምንድነው ለሁለት ተከፍለው ከአርባ አመትበላይ ይኖሩ የነበሩ የጀርመን ወታደሮች ጠበንጃቸውን ጥለው በውህደቱ

ቀን የተቃቀፉት?

Page 16: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 16/34

ከ500 ሺህ በላይ የሆኑ በደንብ የታጠቁ የራሺያ ወታደሮች ጓናቸውንአንዲት ጥይት ሳይተኩሱ ጠቅልለው የጀርመንን መሬት የለቀቁት? 

ይህን መረዳት የምንችለው“ጠላት“ የሚለውን ቃል አውሮፓያኖቹና አረቦቹ፣

ኢትዮጵያና አሜሪካኞቹ፣ ቻይናና ሕንዱ፣ እሥራኤልና ኢራኩ፣… እነዚህ ሁሉአገሮች የሚያዩበትን ዓይንና ግምት፣ ጠጋ ብሎ መመልከት አስፈላጊ ነው።

የሚያዩበት ዓይናቸው የተለያዩ ናቸው። ፍጹም ሌላ በመሆኑም ችግራቸውንየሚፈቱት በተለያዩ መንገድ ነው። 

በአውሮፓና በአሜሪካን የፖለቲካ ፍልስፍና „ጠላት“ ተብሎ የሚታየው፣እነደጠላትም የሚቆጠረው „ ሀገር አቋርጦ፣ድንበር ሰብሮ፣ ጦር መዞ፣ ወታደር

አሰልፎ የሁሉም እናት ሀገር የሆነቺውን መሬት ይዞ ባሪያ ለማድረግ የተነሳውን፣የሚነሳውን ወራሪ ኃይል ብቻ ነው።

ሌላውስ ? ለየት ያለ የፖለቲካ አቋም የሚያራምደውስ? ሥልጣን ላይለመውጣት ተቀናቃኝ ሁኖ የፖለቲካው መድረክ ላይ ብቅ የሚለውስ ቡድን?…ድረጅት?…ተቺውስ?ጸሓፊ ጋዜጠኛውስ?… እነሱ በአውሮፓና በአሜሪካ „ጠላት“አይደሉም። በጠላት ዓይንም፣ እርስ በእራሳቸው አይተያዩም።

ሥልጣን ላይ ያለውን፣በሌላ በኩል እንበል አንድ የገዢን መደብ፣ ሕዝቡ በምንዓይን እነሱን ያያቸዋል?

ሐ 

እሱም ቢሆን፣ ይህኛው ገዢው ክፍል በምንም ዓይነት፣ በምዕራብ አውሮፓ ሆነበአሜሪካ „ተቃዋሚ“ እንጂ „ጠላት፣ ደመኛ ጠላት“ አይደለም። 

ይህን የመሰለ የፖለቲካ ጥበብና ዕውቀት አውሮፓውያኖች ፈልገው ያገኙት

ደግሞ ወደ ታሪክ መለስ እንበል፣ ከጥንታዊ ግሪክ፣  ከአቴንስ ፍልስፍና እንከእነሱም ሥልጣኔ ነው። 

ሁለተኛው „ጠላትህን እንደ እራስህ አድርገህ ውደደው“ ከሚለው ከክርስትናትምህርትም ነው። ሶስተኛው በተጨማሪ ከሮማ ሕግ ነው። 

አቴናውያን በነበራቸውና በአገኙት የምርምር ነጻነት „..ዓይን ለዓይን፣ጥርስለጥርስ „ የሚለውን የሓሙራቢን ሕግ (እስከ አጼ ምኒልክ ድረስ እኛ አገር ይህሕግ፣አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ይታይ ነበር) ከጥቅሙ ለአንድ

ሕብረተሰብ፣ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እሱን ጥለውት ለመሄድ፣ ለየት ያለ መንገድእነሱ ፈልገው ፣ መርጠው ወስደዋል።

Page 17: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 17/34

ከእሱም ጋር „…በሰው ልጆች ዘንድ ቂም በቀልን ለማስቀረት ፣… ለፈሰሰው የአባት ወይም የወንድም ደም ፤… ልጅ የአባቱን ደም መበቀል አለበት“የሚለውን ልማድ ( የጣሊያን ማፊያ አሁንም ድረስ ያደርገዋል) እነሱ ገና ዱሮ፣እንደዚህ ዓይነቱን ልማድ አስቀርተዋል። ለምን? ምን ታይቶአቸው ነው ይህንያደረጉት? 

ይህ አካሄድ “ አንዱ አድፍጦ አንዱን መበቀል…ዞሮ ዞሮ መጨረሻ ወደሌለውየበቀል ኣዙሪት“ ትውልዱን እንደ ሚከት እንደከተተም መለስ ብለው ስለተገነዘቡት ነው። ይከታል። ደግሞም ከቶአቸዋል። 

ስለሚከትም ከዚያ „ባህልና ልማድ፣እንዲሁም ከጥንታዊ ሕግጋት“ ለመላቀቅየወሰዱት እርምጃ ወሳኝ እና በጣም የሚደነቅ መንገድ ነው። 

ከክርስቶስ ልደት በፊት እነዚህ ግሪኮች የደነገጉት ሕግ „የሁለት ጠበኞችን ጉዳይበግዲያም ሊሆን ይችላል… ይህን ውዝግብ ችሎት ተቀምጦ፣ የሚመለከተው፣የተበዳዩ ቤተሰብ ሳይሆን፣…. ዳኛና ፍርድ ቤት ነው ብለው ደንግገዋል። 

“ …ያ እሱ በእኔ ዘመድ ላይ ስለአደረገው ወንጄል፣ እኔ አጻፋውን በተመሳሳይመልኩ፣ በልኩ እሱ እንዳደረገው፣ እኔም በዚያው መልክ መልሼ ልገደለውእችላለሁ“ ብሎ መነሳት እንደማይችል -ይህ ነው እንግዲህ የአቴኖች ችሎታ-

በሕግ፣እሱ ይህን ማድረግ እንደማይችል እነሱ ከልክለዋል። „ቂም በቀልእርምጃውንም“ ማንም ከመሬት ተነስቶ እንዳይወስድ አግደውታል።

እንዴት አድርገው ነው ሕዝቡ እንደዚህ ዓይነቱን አዲስ አሰራር፣…የዱሮውንባህሉንና ልማዱን ጥሎ፣ በቀላሉ፣ ያኔ ጋዜጣና ራዲዮ፣ ቴሌቭዠንም በሌለበትዘመን እንዲቀበለው ያደረጉት? 

በቲያትር ጫዋታ ነው። መድረኩ ላይ በሚታየው ድራማ ነው። „….ትረጀዲ-አሳዛኝ ጨዋታዎችን“ በመጫወትና እሱንም ሰው አይቶ እንዲነጋገርበት፣

እንዲከራከርበት በማድረግም ነው። ቀስ እያሉ ሕዝቡን በዚህ ዘዴ ማስተማርችለዋል።

በየአደባባዩ ቀንም ሆነ ማታ ማታ መድረክ ላይ በሚጫወቱትየቲያትር ትራጀዲ ”ሚስቱን ስለገደለ፣ አንድ የልጆች አባት” ይተረካል። ይነሳል።ሚስት ባሉዋን… ወንድም በወንድሙ ላይ ያካሄደውን የግዲያ ሙከራ፣በመድረኩ ላይ ተመልካቹ ፍርዱን በሁዋላ እንዲሰጥ ይደረጋል። የወንድሙዋገዳይ ፍቅረኛዋ ሆኖም ይገኛል።

Page 18: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 18/34

እንግዲህ ቤተሰብ እንዳይበትን፣ ሰው በቂም በቀል ተናንቆ እንዳያልቅ፣ ጉዳዩንየሚከታተሉ ዳኞች ተቀምጠው፣ ችሎት፣ ጉዳዩን የሚመለከት፣ መድረኩ ላይ፣በትራጀዲ ጨዋታው ላይ ይጠራል።

አማልክቶቹ በፍርድ አሰጣጡ ላይ እንዲሳተፉበት ይደረጋል። ጎረቤቶችአስተያየታቸውን እንዲሰነዝሩበት ይጠየቃል።…

የግድያው መነሻ ምክንያት ምንድነው? ተብሎ እዚያው መድረኩ ላይይመረመራል። ሲወድቅ ነው የሞተው ወይስ በተሰነዘረበት ጩቤ፣ ተብሎይጠየቃል። ባሉዋን የገደለቺው ሴትዮ እሱዋ ብትገደል (ልጁዋ ነው የአባቱንደም መበቀል ያለበት) ሌሎቹን ማን ያሳድጋል ተብሎ ጉዳዩ ይታያል። ልጁስውድ እናቱን ለመግደል ፈቃደኛ ነው ወይ? ተብሎም ይጠየቃል። 

መ 

ይህንንና ይህን የመሳሰሉ ኃይለኛ የትራጀዲ ድራማዎች „ ፍርድ መስጠት“ የነጻፍርድ ቤት ኃላፊነት እንጂ፣ ማንም ከመሬት ተነስቶ በሰው ልጆች ሕይወት ላይመፍረድ እንደማይችል፣ አቴኖች አስተምረውበታል።

ይህም ታሪካዊ የሆነ -በሁዋላ ዓለም አቀፋዊ እርምጃ – በሕግ በደንብ ተደንግጎእንዲወጣም ተደርጎአል። 

እንግዲህ በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ በፖለቲካ ጥያቄ ሆነ፣ በምርጫ“ማጭበርበር”…ሌላም ነገር ለሆን ይችላል- ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑየፖለቲካ ድርጅቶች ሸንጎ ውስጥ ሆነ ከሸንጎ ውጭ ከአልተግባቡ ፣ „ጉዳያቸውንጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ዳኞች እንዲያዩትና ፍርዳቸውን እንዲሰጡ – እዚህ ይደረጋል።“ 

በግብጽና በኢትዮጵያ፣ወይም ሌላ ቦታ… በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ውዝግብ

ሲነሳ፣ በተለይ አንድ መሪ ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ፣ ሰውን ሁሉ ከሥራው አባሮበእራሱ ሰዎች ሲተካ (ፕሬዚዳንት ሙርሲ ይህን አደረገዋል ኢትዮጵያም ውስጥተካሂዶአል) ያኔ እንደዚህ ዓይነቱን፣ ሰው ከሥራው ሲባረር፣ ይህን እርምጃ፣በሠለጠነው ዓለም፣ይህን እርምጃ የሚያግደው „ችሎት የተቀመጠው ነጻ- ፍርድቤት“ ነው እንጅ ወታደሩ፣ፖሊሱና የአየር ኃይሉ ባለደረቦች አይደሉም።

በግብጽ እንዳየነው ወታደሩ መሳሪያውን ይዞ አደባባይ ወጥቶ የእራሱን ፍርድሰጥቶ፣ሰልፈኞች ላይ ተኩሶአል። ፕሬዚዳንቱንም አስሮአል። ሌሎቹን አርፋችሁ

ተቀመጡ ብሎአል። 

Page 19: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 19/34

እንግዲህ ከዚህ አንጻር ነው የግብጽን ውስጣዊ ፖለቲካ፣ በዚያውም የሌሎቹንአፍሪካ ሀገሮች፣ የኢትዮጵያንም ውስጣዊ ውዝግቦችና ችግሮች ማየትየሚቻለው። 

„የጠላትን፣… የደመኛ ጠላትን ትርጉም በአንድ ሕብረተሰብ፣ “በደንብአለመረዳት ያንን ሀገር፣…አንድን ሕዝብ፣ ሳይታሰብ መጨረሻ ወደ ሌለውእልቂት እንዴት እንደሚወስደው፣ የግብጽም፣ የኢትዮጵያም፣ የኮንጎም፣የሱማሌም የናይጄሪያም፣ ውስጣዊ ሁኔታዎች ሕያው ምስክሮች ናቸው።

በሌላ በኩል የኔልሰን ማንዴላ የፖለቲካ እርምጃ „ዘረኛ የነበሩ ነጮቹንማንከባከብና ማቀፍ“ እራሱን የቻለ ትልቅ (በጠላት ትርጉም ላይ)ትምህርትይሰጣል። 

„ጠላት“ ማለት እንድገመው፣ ባሪያ አድርጎ ለመግዛት ከውጭ የሚመጣ ወራሪኃይል ብቻ ነው። የፖለቲካ ተቃዋሚና ተቀናቃኝ ድርጅቶች „ጠላት „ ሳይሆኑየሀገር ልጆች ናቸው። ሕገ -መንግሥቱም በትክክል በሥራ ቢውል የመቃወምመብታቸውን ያረጋግጥላቸዋል።  

ከጠላት ጋር የሚደረገው ፍሊሚያ ጦር ሜዳ ይለይለታል። ለየት ያለ የፖለቲካአቋምና የፖለቲካ ፕሮግራም ከሚያራምደው ጋር ያለውን ልዩነት የሚፈታው

ደግሞ፣ እኛ እዚህ እንደምናውቀው፣ ሕዝብ ፊት ቀርቦ በሚካሄደው፣ በክርክር፣በውይይት፣ በመጨረሻም፣በምርጫ ሂደት፣ በወረቀት ነው። ወይም ደግሞውዝግብ ሲነሳ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው። 

„ገዢው መደብ፣ አልሰማም ብሎ እምቢ ከአለ ደግሞ፣ (በጦርነት ሳይሆን)በሕዝብ አመጽ በተቃውሞ ሰልፍ፣ ከቦታው እንዲነሳ የደረጋል። ወጣ ወረደወሳኙ ሰበአዊ መብቶች ፣ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ይከበራሉ ወይስ አይከበሩምነው።  የግለሰብ ሰበአዊ መብቶችን አምባገነኖች ለምን እንደማይቀበሉት(ሌላውን ነገር ሁሉ ፣  የብሔር እኩልነትና የሃይማኖትን እኩልነት እንቀበላለንይላሉ) የሚያጠያይቅ ነገረ ነው። ታቦታችን ላይ የሙሴ ጽላት ላይ “አትግደል” ይላል። 

ከግብጽ የምንማረውም እሱኑ ነው።  ከሣቴ ብረሃን ሣልሳዊ © ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Page 20: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 20/34

ዘ ጋርዲያን / The Guardian 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

ዘ ጋርዲያን / The Guardian 

[1] የዛሬ 5000 ዓመታት ይህችን የነፃነት መልክት የነደፏት አስተዋዮች ምንኛ በደነቃቸው! 

*** 

ብዙ ሐተታ አቅራቢ ጸሓፊዎች የኤድዋርድ ስኖውድንን መረጃ ሰነዶች እንቀማለን ብለው የ ጋረዲያንንመዝገብ ቤት አለማዘዣ ስለፈተሹት የጸጥታ ፖሊሶች እዚህ አውሮፓ ጽፈዋል።  

እራሱ ዘ ጋርዲያን የደረሰበትን ችግር ከመካከለኛው ክፍለ-ዘመን ከኢንኩዜሽንፍርድና ምርመራ ጋር አያይዞት የሚከተለውን አረፍተ ነገር ለአንባቢዎቹ እንደዚህ አድረጎ አስፍሮአል።

„…እሰከ ዛሬ ድረስ ቀልዳችሁብናል። አሁን ግን ይበቃችሁዋል። የመጣነውምሰነዱን ለመውሰድ ነው።´ 

በነዚህ ቃላቶች ነበር የብሪታኒያ መንግሥት በኢንተርኔት ክፍለ-ዘመን አስገራሚየሆነውን የሳንሱር ቁጥጥር በእኛ ላይ ለመክፈት የቃጣው። በዝግጅትክፍላችንም ጋዜጣችን የሰበሰበውን መረጃዎች የጸጥታ ፖሊሶቹ ልክ እንደየቀድሞው የስፓንያን መጽሐፍ አቃጣዮች፣ በደስታ ዓይን ነበር፣  እነሱም

ተዝናንተው ሰነዶቻችን ሲወድሙ ይመለከቱት የነበረው።የስኖውድን መረጃዎች በዓለም ዙሪያ እንደተበተኑ ብንነግራቸውም እንኳን፣ከደስታቸው የተነሳ ይህን እርምጃችንን ሰምተው ከቁም ነገርም አልቆጠሩትም።የፈለጉት በመጥፎ መናፍስት ተያዙ የተባሉትን ሰዎች በእሳት ሲቃጠሉ ማየቱንብቻ ነው። ሌላ እነሱ የፈለጉት እኛ ይህን የቃጠሎ ድርጊታቸውን እንድናከሽፍነበር።…እኛ ግን አውቀን ደስ እንዲላቸው ለቀቅንላቸው …“ ዘ-ጋርዲያን ይላል።

ቀደም ሲል ይኸው ጋዜጣ ” እነሱን የጎበኙ ነጭ ለባሽ ፖሊሶች፣ የጄምስ ቦንድፊልምን እንኳን በደንብ ያዩ ይመስላሉ” ብለው ቀልደውባቸዋል። 

Page 21: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 21/34

የጀርመኑ ጋዜጣ „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ ለምን ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ በሩንለፖሊሶቹ ከፈታችሁላቸው ብሎ ጋዜጠኞን ሲወቅሳቸው፣ የራሻው ፕራቭዳ(ይህ ይገርማል) ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ዓረፍተ-ነገር አምዱ ላይ አስፍሮአል። 

„ የጋዜጣው አዘጋጆቹ ያላቸው ምርጫ ውስን ነው። ወይ ሰነዱን አውጥቶእነዳለ ሁሉንም ማተም ነው። ወይም እነሱ እራሳቸው መረጃዎቹን ማውደም።ወይም ደግሞ ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሶ ከመንግሥት ጋር ጠበቃ ይዞ መሟገትነው።

በሦስተኛው አማራጭ ላይ የፍርድ ቤት ዳኞቹም ሰነዱን ማጥናት ስለ አለባቸውመረጃዎቹ ምን ምን፣ ነገሮችን እነደ አዘለም ማወቅ ይችላሉ። ወጣ ወረደ ይህከሆነ ዘ ጋርዲያን ከቅጣት አያመልጥም ነበር። ስለዚህ ቀላሉ እና በገንዘብ ደረጃ 

ርካሹ መንገድ፣ የጸጥታ ፖሊሶቹ እያዩ፣ ሰነዱን ማውደም ትክክልኛ ውሳኔ ነው።እንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት ደግሞ በጋርዲያን ታሪክ ፍጹም አስገራሚ ነበር።“ 

„አሁን የኮሚፒውተር ቀፎና ሆድቃውን ማቃጠልና መጨፍለቅ“ ኖይ ዙሪሸ ዛይቱንግ የተባለው የስውሲ ጋዜጣ እንደ አለው“… ምን ያደርጋል። በቀላሉ እኮጠቅ አድሮ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ኮፒዎችና ግልባጮቹን ማንም ሊደርስበትየማይችለበት አገሮችና መንደሮች ወይም አህጉሮች አሸጋግሮ ማስቀመጥይቻላል። ዋና አዘጋጁ አንድ ጥሩ ነገር ብሎአል። አስፈላጊ ከሆነ የተጠለፉትን

ንግግሮችና ሰነዶች ሁሉ ወደ አሜሪካን አገር አሸጋግሮ ከዚያ ሁኖ (በአሜሪካን የፕሬስ በጣም ነጻና ሊበራል ነው) ማተም ይቀላል ነው፣ ብሎአል።“ 

የኖርዌዩ ዳግስአቪሰን በተራው፣ የብርትሺን ጸጥታ ፖሊሶች እርምጃ አውግዞአል። 

„….እንዲያው ጉልበት ለማሳየት የተወሰደ እርምጃ ነው እንጂ ምንም ፋይዳየሌለው ነገር ነው። ኃይልን ለማሳየት የብርቲሽ መንግሥት አውቆ ሕግንተንተርሶ፣ አሳዛኝ የስልክ ጠለፋውን ድርጊት በዚህ ዘዴ አግዳለሁ ብሎመድከሙ ከንቱ ነው።… ሕገ-ወጥ ሥራቸው ከተንኮል  ሥራ የማይርቁትን፣ከእሱም የማይመለሱትን፣  … ጨካኝ፣  አረመኔ ገዢዎችን አለጥርጥር፣ በደንብያስታውሰናል። የጋርዲያን፣  ዋና አዘጋጁ የተናገረው ቃል ዕውነት አለው።የእንግሊዝ መንግሥት ህገ ወጥ ሥራ፣ አንድ የሚያሳየው ነገር ቢኖር፣ ስኖውዲንየሰበሰባቸው መረጃዎች ምን ያህል ትልቅና ከባድ ቁም ነገሮች እንዳዘሉ ያሳያል።“ 

ጉዳዩ ለስርቦቹ ጋዜጣ “ፖለቲካ“ ለሚባለው ቅጠል ” በጣም አሳፋሪ ድርጊት

ነው” ይላል። 

Page 22: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 22/34

„…የብሪታኒያ ጋዜጠኞች የምዕራቡ ዓለም እሰከ ዛሬ የሚኮሩበትን  የፕሬስነጸነት፣ ሳይፈሩ ከፍ አድርገው በማውለብለባቸው ጥሩ ሥራ እነሱ ሰርተዋል።የየናይትድ እስቴት ኦፍ አሜሪካና ታላቁዋ ብርታኒያ በዚህ  የሽብረ ፈጠራሥራቸው የዲሞክራሲ መሰረት የሆነውን የፕሬስ ነጻነትን ስም አጉድፈዋል።ጋዜጠኞቻቸው ሳይሆኑ እነሱ እራሳቸው በቀጠሩአቸው ሰላዮቻቸውመንግሥታቸውንና ሥርዓታቸውን፣ እነዚህ ሰዎች እንደሚያዳክሙባቸውአይገባቸው ይሆን?

…ስለዲሞክራሲ ምንም የማያውቁ፣  ጭላንጭሉም እንኳን ቢሆን ምኑምበማይታይበት አገር፣ የሚሰሩና የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች ከእንግዲህ ለእነሱወዮላቸው ማለት ይሻላል። በታላቁዋ ብርታኒያና በሌሎች የምዕራብ አገሮችየሚታየው የሳንሱር ቁጥጥር እነሱን፣ ዲሞክራሲ የሚረግጡትን መንግሥታት ፣

ይህ እርምጃቸው አደፋፍሮ ጋዜጠኞቻቸውን እንዲያዋክቡ የልብ ልብ -ተመልከቱ፣  እነሱንም፤  እያሉ- የፈለጉትን ለማድረግ ዕድል ይሰጣቸዋል።ያበረታታቸዋል።“

የቻይናን ጋዜጣዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንደጻፉ ለመመልከት ሞክረንሳይሳካልን ቀርቶአል።

[1] የነጻነት ሲምቦል (ca. 2350 B.C) / 

http://sumerianshakespeare.com/21101.html 

 ——————–  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Page 23: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 23/34

ዓለም እንዴት ሰነበተች? 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

ዓለም፣ የለም! አፍሪካ እንዴት ሰነበተች! 

ሕልም ወይስ ቅዠት? አንድ አፍሪካ ውስጥ እየታተመ የሚወጣ መጽሔት 

ነጮች መጥተው ይግዙን ብሎ ይለምናል! (1  

ዝነኛውን  „…ምኞትና  ሕልም“  ተብሎ  በታሪክ  ላይ  የተመዘገበውን  የቀሲስ ማርቲን  ሉተር  ኪነግ  የዋሽንግተኑ  ንግግር  ዘንድሮ  ሃምሳኛው  አመት 

በሚያከብርበት  ወራት  በአፍሪካ  ጥሩ  ስምና  ዝና  ያላቸው  የአህጉሪቱ  ምሁሮች የተገላቢጦሹን ጉዞ ይዘው„…ነጮች ተመልሰው በመዳፋቸው ሥር አሰገብተው 

በቅኝ ገዢነት ያስተዳድሩን“ የሚለውን ጥሪአቸውን እነሱ ለቀዋል። 

ይህን የመሰለ „ልመናም“ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማውና የተነበበው፣ „ቺሙሬንጋ 

CHIMURENGA Chronic“  በተባለው  በየአራት  ወሩ  እየታተመ የሚወጣው አንድ የአፍሪካ መጽሔት ላይ ነው። 

CHIMURENGA የባንቱ  ቃል  ነው።  በዚምባቡዌም  የመገበያያ  ቋንቋ  ይህ ቃል፣ ትረጉሙ፣ እዚህ ለእኛ  የተረጎመው „ዲ ቬልት“ የተባለው ዕለታዊ ጋዜጣ 

እንደሚለው „ አብዮታዊ ትግላችን“ ማለት ነው። 

በአጭሩ ይላል ጸሐፊው ይህ ቃል „…ለሰበአዊ መብቶች መከበር፣…ለፖለቲካ 

እኩልነት፣…ለፍርድና  ለፍትህ፣…ለማህበራዊ  ኑሮ  መሻሻል“ (ማመን  ከተቻለ)የቆመ ነው ይለናል። 

Page 24: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 24/34

„ቺሙሬንጋ“  በሁለት  ክፍለ-ዘመን  እንደተከፈለ  አስታውሶ፤ (አንደኛው 

በ19ተነኛው  ክፍለ-ዘመን  መጨረሻ   ላይ  ከእንግሊዝ  ቅኝ  ግዛት  ከብሪታኒያን መዳፍ ለመውጣት የተካሄደው የአመጽ ጊዜ ነው። 

ሁለተኛው በ1960 እና 70 ዓ.ም እአአ. የካሄደውን የነጻነት ትግል ዘመን ነው )

እሱን  ጋዜጠኛው  አስታውሶ፣  የአሁኑን  የቺሙሬንጋ  „ተግባርና  ሚና“  ወደ ማስረዳቱ ይሸጋገራል። 

ይህ  መጽሔት  በየአራት  ወሩ  ታትሞ  በደቡብ  እፈሪካና  በኬንያ  እንዲሁም በናይጄሪያ  ይበተናል።  በኢንተርኔት  ኦንላይንም  ማንበብ  ይቻላል። 

http://www.chimurengachronic.co.za/?s=Jean-Pierre+Bekolo 

ከመጽሔቱ ጀርባ በገንዘብ ዕርዳታ „ዲ ቬልት“ እንደሚለው „የጀርመኑ የባህል ማዕከል የጉተ ኢንስቲቲውት፣ የሓይንሪሽ ቦል የበጎ አድራጎት ድርጅትና የጀርመኑ 

የባህል ሽልማት ድርጅት…“ ሦስት ተቋሞች ይገኙበታል። 

በሚቀጥለውም  አመት፣እነደተባለው፣  በጀርመንኛ   ቋንቋም  ይኸው  መጽሔት ታትሞ ገበያ ላይ ይቀርባል። 

„አብዮታዊ ትግላችን“ የሚለው ቃል የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች የክሱ አግዳሚ ወንበር 

ላይ  አስቀምጦ  በአንባቢው  ፊት  „ይከሳቸዋል፣ያጋልጣቸዋል፣ይተቻቸዋል…“ብሎ  የሚገምት  ሰው  ከአሁኑ  ከአለ  ትንሽ  ቆየት  ብሎ  ወረድ  ብሎ  ጽሑፉን ሲያገላብጠው ደንግጦ አፉን ይይዛል። 

ከዚህ  በፊት  በተደጋጋሚ፣እንደ  የሥነ-ጽሑፍ  ኖቤል  ሽልማት  አሸናፊው  እንደ ወሌ  ሶይንካ  ያሉ  ሰዎች፣እንደ  የሰላም  ኖቤል  አሸናፊዋ  እንደ  የኬንያዋ  ተወላጅ 

ወይዘሮ  ዋንጋሪ  ማታይ፣እነዚህ  ሁሉ  “…አሁን  በየአለበት  ፈልቶ  የሚታየው የአፍሪካ ችግርና ችግሮች ሁሉ በአንደኛ  ደረጃ  ዋና ተጠያቂ የቀድሞው የአውሮፓ 

የቅኝ ገዢዎች ሳይሆኑ እራሳቸው የአፍሪካ መሪዎች ናቸው…“ ስለዚህ መታረም አለባቸው  ብለው  ነገሩን  ጨርሰውታል።  የዚህ  መጽሔት  አዘጋጆችም  አቋም በመጀመሪያ ላይ ላዩን ሲያዩት ይህንኑ ዓይነት መልዕክት ያዘለም ይመስላል። 

ግን የፊልም ዳይሬከተሩ የካሜሩን ተወላጁ፣በ1966 የተወለደው ጎልማሣው ጃን 

ፒዬር  ቢኮሎ  ለመጽሔቱ  በሰጠው  ቃል-ምልልስና  ቀስ  ብሎ  በወረወረው አስተያየቱ የሚገርምም የሚደንቅም ነገር አንስቶአል። 

Page 25: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 25/34

„ቅኝ  ገዢዎቹ  ተመልሰው  መጥተው  አፍሪካን  ያስተካክሉአት“  ይላል።  „እኛ  እራሳችን  ችግራችንን  ለመፍታት  አልቻልንም  „  ብሎም  የዕርዳታ  ጥሪውን  ወደ አውሮፓ ይለቃል። 

„…በግልጽ  እንናገር፣እኛ   ብቻችን  አልቻለነውም፣ስለዚህ  እነሱ  ብቻ  ናቸው 

ሚያውቁበት፣…ተመልሰው  ይምጡ„  ብሎም  ቅኝ  ገዢዎቹን  እንዲመጡለት ይለምናል። 

ጠያቂው:- „..ለመሆኑ  ካሜሩን  እንደገና  የቅኝ  ግዛት  መዳፍ  ውስጥ  ተመልሳ 

እንድትገባ ይሻሉ?..ይህንስ ይመኛሉ?“ 

ቢኮሎ:- „…ከሃምሳ ሁለት አመት የነጻነት አመት በሁዋላ መቀበል ያለብን አንድ ነገር ቢኖር የእራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚባለው ነገርና የነጻነት አይዶሎጂ፣ብሔራዊ አመጽ…እነዚህ ሁሉ ምንምአላመጡልንም። 

የዓለም አቀፉንም ሁኔታ፣… ግሎባላይዜሽንም ስንመለከተው፣ 

እኛን  አሁን  ወደፊትም  ወደ  ሁዋላም  ለመሄድ  የማንችልበት  ደረጃ   ላይ አድርሶናል። 

ዓላማችንና ግባችንን እንዳልመታን ግልጽ ነው። ይህን ብቻችን የማንወጣው ነገር ነው። ሁሉ ነገር ደግሞ አሁን ከአቅማችን በላይ ነው።“ 

ሌላ  ተጨማሪ  ጥያቄ:- „..በትክክል  ተረድቼዎታለሁ፣…ነጮች  ተመልሰው 

መጥተው (አፍሪካን) እንዲያሰተካክሉሎት ይፈልጋሉ?“ 

ቢኮሎ:- „  የቅኝ  ገዢዎች  ዓላማና  ፕሮጄክት  ግሩም  ነበር።ብዙ  ነገሮች  ላይ 

ደርሰናል።…ቀኝ  ገዢ  መሆን  ተቀባይነት  በአጣበት  ዘመን፣ያኔ  አይሮፕላኑን 

የሚያከንፈው ፓይለት ቀስ ብሎ ሽው ብሎ ጃንጥላውን ይዞ በመስኮት ፈትለክ አለ። 

ሌላው  እችልበታለሁ  ብሎ  መሪውን  ጨበጠ።ግን  ምኑንም  አያውቅበትም።ከነአካቴው (አይሮፕላኑን ይዞ) ወዴት እንደሚከንፍም ፕላን ስለሌው እሱ እረሱ 

አያውቅም።  ይመስለዋል“  ፤  ቀጥሎ  እንደአለው  „  …እራሱን  ሲያታልል 

የሚያደርገውን ሁሉ የሚያውቅ ይመስለዋል።…አንድ የሚያውቀውና የሚችለው ነገር ቢኖር፣ የሕዝብ ንብረትን ዘርፎ የእራሱን የግል ጥማት ብቻ ማርካት ነው።…የሐሰተኞችና የዋሾዎችም ቤት ነው።“ 

Page 26: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 26/34

እንደዚህ አድርጎ ጎልማሳው ጃን ፒዬር ቢኮሎ የአፍሪካን መሪዎች በጅምላ በንቀት ዓይኑ እየገረፈ ሙልጭ አደርጎ እነሱን እየተቸ ሲጓዝ፣ዞር ብሎ የነጮቹን የግዛት ዘመን ያደንቃል። 

„…ለባህላችንና  ለጥንታዊ  ቅርሳ  ቅርስ  ታሪካችን  መጠበቅ  እንኳን  ገንዘብና ሕንጻ“፣ እሱ እንደሚለው „ሰርተው  የሚሰጡን እነሱ  ነጮቹ ናቸው፣ …በዚህ የጃክ ሺራክን ሙዚየም በካሜሩን አመስግነን መቀበል ይኖርብናል። ቢያንስ በዚህ የበጎ  አድራጎት  ሥራ  ውረሰ  ቅርሳችን  እዚያ  ሳይጠፉ  ለትውልድ  ተጠብቆ 

እንዲቆይ  ተደርጎአል።…ግፋ  ቢል  የአፍሪካ  ገዢዎች፣የእስክስታ  ጭፈራ ቡድኖችን  አይሮፕላን  ጣቢያ  ድረስ  እየጠሩ  እነሱን  ማስጨፈር  ይችሉበታል።እሱም  ቢሆን  የነጮች  ሥራ  ነው።“ብሎ  አሽሟጦ  ወደ  ሌላ  አርዕስት፣ቢኮሎ 

ይሸጋገራል። 

ጠያቂው እንደገና :- „ አፍሪካውያኖች እራሳቸውን ማስተዳደር አይችሉም ነው 

የሚሉት?“ 

መልስ:- „…  እቅጩን  እንናገር  ከተባለ  ምንም  ነገር  ለመሥራት  አልተቻለም። 

ምኑም  ነገር አይሰራም።…ሞከርን፣ ደከምን፣…ከአቅም በላይ ስለሆነ፣ ምኑንም 

አልቻልንበትም።…እራስን  በራስ  መቻልና  ማስተዳደር፣  እኛን  ለመግዛት 

የተወረወረ የውሸታሞች የፖለቲካ ጨዋታ ነው።…የአለነው በትክክል ለመናገር የፖለቲካ እስር ቤት ውስጥ ነው፤ …ታዲያ ዝምታ እሰከ መቼ…!“ 

የቢኮሎ  ትንተና  እና  ግንዛቤ  „ሰምና  ወርቅ“  መልዕክት  ያዘለ  ነው  ብለው የሚገምቱ ሰዎች አይጠፉም።በሌላ በኩል ይህንኑ የእሱን መደምደሚያ ተከትለው 

„ጊዜው ደረሰ ብለው፣ ስንቃቸውን የሚያዘጋጁ ቅኝ ገዢዎችም ትንሽ አይደሉም።“ 

„ቀልድ  ነው።”  እንዳይባል  ልጁ  አይቀልድም።”ዞሮበታል”  እንዳይባል  ጤነኛ  ነው።ታዲያ ነገሩ ምንድ ነው። መልእክቱስ? 

ጥያቄዎች  ይነሱ  መልሶችም  ይደርደሩ፣  ቢኮሎ  እና  ከእሱ  ጋር  ይህን  የሚያስቡ 

ሰዎች  ፈልገው  ያገኙት  መፍትሔዎች  ለእኛ   ለኢትዮጵያውያኖች  “ትክክል  ነው” 

ማለት  አይቻልም።…  ያሳፍራል።  ይህ  ከሆነ  አባቶቻችን  ለአገራችን፣ለባንዲራችን፣ለሃይማኖታችን…  ለኢትዮጵያ  ነጻነት  ሲሉ  የሞቱላት  ሞት  ከንቱ ነው ማለት ነው። 

Page 27: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 27/34

ሰበአዊ መብት፣ዲሞክራሲ፣ብልጽግና፣ ዳቦና ሥራ፣ፍትህና ፍርድ፣ሰላማዊ ኑሮ ፣ …ይህን  እኛው  እራሳችን  በአገራችን  ላይ  ከተደማመጥን፣ከተስማምን  እኛው፣እንደሌሎቹ  የምናመጣው  ሥርዓት  ነው።  ደግሞ  ይቻላል።  ማምጣትም እንችላለን። 

ቢኮሎ (ምናልባት  ሁሉም  ነገር  ፊልም  ስለሚመስለው) ከግምቱ  ውስጥ ያላስገባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። 

„ነጮቹ  ተመልሰው  ቢመጡልን“  አፍሪካ  „ምድራዊ  ገነት“  ትሆንልናለች የሚለው  ቢኮሎ፣በምን  ላይ  ተማምኖ  እንደሆን  አናውቅም።  አንድ  ግን  ከዓለም 

ታሪክና  ሥልጣኔ  ተነስተን  ለማለት  የምንችለው  ነገር  ቢኖር፣  „ ቁጥጥር 

የማይደረግበት ገዢ

“…በህግና

 በፕሬስ

 ሥር

  „ቁጥጥር

 የማይደረግበት

“ አንድ

 

ቡድን፣ሞራል  የሌለው  ኃይል፣…  ጥቁር  ይሁን  ነጭ፣…አረብ  ይሁን  ቢጫው ቻይና፣ሕንድና  ጃፓን፣  እነዚህ  ሁሉ  አፍሪካን  እንደገና  ተቀራምተው  ቢይዙ፣ ቢኮሎና ቢጤዎቹ እንደሚሉትና ወጣቱን አፍሪካዊ ለማሳመን እንደሚሞክሩት ያ 

የተባለው  „የዲሞክራሲና  የሰላም፣  የብርሃን  ዘመን“  ምንም  ጊዜ  ቢሆን አይመጣም። 

ትርፉ፣ምን  አለፋን፣ትርፉ  ባርነት  ነው።  ይልቅስ  ከእግዚአብሔር  በተፈጥሮ 

የተሰጠንን፣ የሰው ልጆች ሁሉ እኩልናቸው፣የሚለውን፣… የመናገር የመተቸት፣የመጻፍ  የመደራጀት  መብታችንን፣( ለዚህ  ደግሞ  ከማንም  ፈቃድ  ማግኘት 

አያስፈልግም፣ በእጃችን በደጃችን ነው) እንጠቀምበት። 

የቢኮሎ ግምትን ሁለት ጊዜ አገላብጦ ማየት አስፈላጊ ይመስለናል። 

እራሳቸውን ዛሬ ሥልጣን ላይ የተቀመጡትን የአፍሪካ ገዢዎች፣እነሱን ማን በርቱ 

ብሎ መርቆ እደሸኛቸው ለመሆኑ ቢኮሎ ያውቅ ይሆን?

ተፈሪ መኮንን 

 —————— -

(1 - Afr ika-Debatte _ Die Weißen sol len bi tte draußen bleiben  – Nachrichten Kul tur  – DIE WELT  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Page 28: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 28/34

“ራዕይ ራዕይ …. “ዶቸ ቬለ የጀርመን ራዲዮ፤ ውይይት 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

“….ራዕይ ራዕይ…” ስንል አንዱም ሳይያዝ፣ በመሃከል ያንድ ሰው እድሜ አለፈ።ኢትየጵያም አሁን ጥናቶች እነደሚመሰክሩት ” ከድንቁርናና ከድህነት ፈጽሞአልተላቀቀችም።” በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ሰዎች በሀገራችን በኢትዮጵያ ከልክ በላይስላለፈላቸውና ጠግበው ስላደሩ፣ ህዝቡ ጠግቦ ያደረና የተመቸው የሚመስላቸው አሉ።  

ዛሬ ሁሉንም ዜጋና ወገን እንደ ማንኛውም የዓለም ሕዝብ በአገሩ የፖለቲካና የኢኮኖሚመድረክ ሚያሳተፍበት ግልጽ የሆነ የነጻነትና የልማት የዕድገት ፕሮግራም የለም። የግልሀብት፣የመሬት ባለቤትንት መብት ክልክል ነው። ሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈሩት ሰበአዊመብቶች በሥራ በትክክል አልተተረጎሙም።

የፕሬስ ነጻነት የለም። የግለ ሰቦች መብቶች -አንድ ሰው የፈለገውን ለመከተል፣ለመተቸት፣ለመቃወምና ለመደገፍ፣ለመሰብሰብና ለመደራጀት-ይህ ሕገ-መንግሥቱ ላይየሰፈረው መብቱ አይከበርም ። የነጻ-ፍርድ ቤትና የነጻ-ዳኛ ጉዳይ አለ።አንድ ሰውጠበቃ ይዞ በሥነ-ሥርዓቱ ሳይከራከርና  በጥፋቱ ሳይፈረድበት ይወነጀላል።… 

ግን ምንነቱ የማይታወቅ፣ ብዙዎቹ እንደሚሉት፣እሰከ አሁን ድረስ ምንም በቂ ማብራሪያያልተሰጠው „ …ራዕይ አለ እሱን ተከተሉ” እንባላለን።

ይህ ” የአቶ መለሰ ራዕይ…የተባለው ሰነድ ” አንድም ቦታ ተጠርዞ ሲበተን አላየንም። ምን

ዓይንት መልዕክቶችን እንደያዘም እኛ  በዝርዝር የምናውቀው ነገር የለም።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ “ዶቸ ቬለ-የጀርመን ራዲዮ ጣቢያ ” ስለ ጊዜያዊው የኢትዮጵያሁኔታ አዘጋጅቶት የነበረውን አጠር ያለ ውይይት፣ እንድታደምጡት፤ መጽሔቱ „ለአእምሮ“ ይጋብዛችሁዋል። 

 ————————————————— -

https://soundcloud.com/ethiopia-leaimero/dw-discussion-ethio-poli 

 ——————–  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013 

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Page 29: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 29/34

ውርሰ፥ቅርስ 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

ውርሰ፥ቅርስ 

በየቤቱ  ብዙ  ሰነዶች  እንደአሉ  መገመት  ከባድ  አይደለም።  የተማረው  ክፍል 

በሕብረተሰቡ  ውስጥ  ብዙሃኑን  አይያዝ  እንጂ፣የጽሑፍ  ፊደል  ከጥንት  ጀምሮ በሚታወቀውና  በሚገለገልበት  በኢትዮጵያ  ምድር፣  ወረቀት  ላይ  ሳይሰፍሩ ተረስተው  የቀሩ  ነገሮች  አሉ  ብሎ  መገመት  በጣም  ይከብዳል።  ቢያንስ 

በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ፣ የገበሬ ቤትም ቢሆን አንድ ልጅ ለቤተ-ክርስቲያን 

አገልጋይነት ይሰጣል። በዚያውም ያ ልጅ (ቁጥሩን በደንብ አናውቅም እንጂ)…ድቁናና  ቅስና  ባይቀበልም  ፊደል  ቢያንስ  እንዲቆጥር  ይደረጋል። 

በጥንታዊ  ገዳሞቻችን እና በየቤተክርስቲያኑ አድባራት፣ ረዥም ዕድሜ ያላቸው ጥንታዊ  ጽሑፎች፣እንደ  ጥንታዊው  ዛፎች፣  ተደርድረው  እንደሚገኙ እናውቃለን። 

ዘራቸው  ሌላ  ቦታ  የማይገኝ፣  በቅጥር  ግቢው  ውስጥ  የቆሙትን  ጥንታዊ የአገራችንን  ዛፎች፣  እንኳን  ከቅርቡ  ከሩቁም  አፋፍ  ላይ  ስለሆኑ  በደንብ እናያቸዋለን።  በሌላ  በኩል  መጻሕፍት፣  በየአለበት  አሉ  ይባላል  እንጂ  እነዚህ መጻሕፍት  ምን  እንደአዘሉ፣  ምን  እንደተሸከሙ  ምን  ዓይነት  ሚሥጥራዊ 

መልዕክቶች  ለትውልዱ  እንደያዙ  ምንም  የምናውቀው  ነገር  የለም።…አናውቅም። 

እንደዚሁ  የአገራችን  ሥዕሎች፣  ድርሰቶች፣ግጥሞች፣  እራሱ  የምግብ  ዝግጅትና አሰራር፣  ስንት  እንደሆኑ? የት  እንዳሉ? በማን  እጅ  እንደሚገኙ- የተመዘገበ፣የተጻፈ  ነገር  ስለ  ሌለ፣  ምንም  የምናውቀው  ነገር  የለም።  እንዲያው  ብቻ 

„…የባላበት፣የፊውዳል፣የአቆርቋዥ …ባህል…“ ጥራዝ  ነጠቆች  እያሉ  ሁሉን 

ነገር አጥላልተውት ዞር ብሎ የአገሩን ቅርስ የት ደረሰ? ምን ሆነ ብሎ የሚጠይቅ ሰው  ጠፍቶአል። 

በ19ኛውና በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ብዙ ተማሪዎች ለትምህርት ወደ አውሮፓና ወደ  መካከለኛው  ምሥራቅ  ፣ወደ  ሰሜን  አሜሪካም  እንደሄዱ  እናውቃለን። 

እነዚህ  ሰዎች  በወጣትነት  ዘመናቸው  ምን  እንደጻፉ፣  ምን  እንዳጠኑ፣ለየትኛው የጥበብና የዕውቀት ክፍል ልባቸውንና አእምሮአቸውን ሰጥተው በዚያ እንደተሳቡ 

Page 30: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 30/34

 – አንዳንዶቹ  በእርግጥ  ጽፈዋል- ስለሌሎቹ  ብዙም  የምናውቀው፣ምንም  ነገር የለም። 

ጳውሎስ ኞኞ- ነፍሱን ይማረውና- አንዴ በርሊን መጥቶ ሲያጫውተን፣ ትልቁ 

ቤተ-መንግሥት  ውስጥ፣  ስለ  አጼ  ምኒልክ  ታሪክ  ለመጻፍ  ሰነዶች  ለመሰብሰብ በደርግ ዘመን በተፈቀደለት ጊዜ  ፣በቤተ-መንግሥቱ ምድር ቤቱ ውስጥ ያየውን ነገር እንደዚህ አድርጎ ተርኮልን ነበር። መዝገቦቹ ሁሉ ተበትነዋል። በእጅ የተጻፉ ወረቀቶች  ጣውላው  ላይ  ወድቀዋል።  ከውጭ  ክረምት  ስለሆነ  የዝናብ  ወሃ ይገባል። አንዳንድ ብጣሽ ወረቀቶች ወሃ ላይ ይንሳፈፋሉ።አንዲት ወረቀት ብድግ 

አድርጌ  ስለመለከት፣የሚንስትሮች  ስብሰባ  ቃለ-ጉባዔ  ይዘት  የያዘች  የንጉሡ 

(የቀ.ኃ.ሥ.) ማስታወሻ  ነበረች። „…እምሩ ጥሩ ብሎአል።…አበበ ተሳስቶአል።…“ 

ደርግ  ከወደቀ  በሁዋላም  አንዱ  ያዳመጠውን  እንደዚህ  አድርጎ  ሁኔታውን አስቀምጦታል። 

ሥልጣኑን በምርጫ ሳይሆን ያኔ በጠበንጃ  ለሦስት የተረከቡት ድርጅቶች  ( …

ሻብያም  ፣ኦነግም፣ከሕዝባዊ  ወያኔ  ጋር  አብረው  አዲስ  አበባ  ገብተዋል) የእነሱ 

ወታደሮች  በዚያን  ጊዜ  ትልቁን  ቤተ-መንግሥት  የሚጠብቁት  ዘበኞች፣ያለ የሌለውን  ጥንታዊ  ሰነዶች፣  ለሻይ  ጀበናቸው  የከሰል  ማቀጣጠያ  እንዳደረጉት በርከት ያሉ ሰዎች አይተዋል። 

ምክንያቱ  ግልጽ  ነው።  አለማወቅ  ብቻ  ሳይሆን  ያው  „የአደሃሪ፣ የፊውዳል…የበዝባዣ …ታሪክ ከሚለው ጥላቻ ተነስተው ነው።“ እነዚያ የከሰል ማቀጣጠያ  የሆኑ  ሰነዶች  ስለ  ኢትዮጵያና  አሜሪካ  ግንኙነቶች  ሊሆን  ይችላል።ወይም ስለ ሌላ ጉዳይ። ግን ዛሬ ብንፈልጋቸው የማናገኛቸው ሰነዶች ናቸው። 

አንድ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክና ባህል ለረጅም አመታት ጥናት የሚያደርጉ 

አዛውንት፣  ፕሮፌሰር  ሆህናዚ  የሚባሉ  ምሁር  „ገንዘብ  ከአለህ  ኢትዮጵያ ስትወርድ ያገኘኸውን ቅርሳ ቅርስ ዝም ብለህ ግዛ፣ ወደፊት በቀላሉ የማታገኙት 

የአገሪቱ ንብረታችሁ እየተዘረፈ ነው“ ብለው መክረውኝ ነበር። ይህን ለማድረግ 

(ሮከፌለር  ወይም  ቢል  ጌት  መሆን  ያስፈልጋል) የአንድ  ሰው  ሥራ  አይደለም። ይህን  ማድረግ  የሚችለው  መንግሥት  ወይም  ብዙ  ሰዎች  ሰብሰብ  ብለው 

የሚያቋቁሙት  „ትሪስፓረንት“ ግልጽ  የሆነ  አባሎቹ  በየጊዜው  የሚቆጣጠሩት የበጎ አድራጎት፣የሽልማትም ድርጅት ሲመሰረት ነው። ለዚህ ደግሞ በወር አንድ 

ዶለርም በነፍስ ወከፍ ማዋጣቱ በቂ ነው። 

Page 31: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 31/34

 

ለምንድነው  ይህን  ጉዳይ  የምናነሳው? ለትውልድ  የሚተላለፉ  ጽሑፎች  የት እንዳሉ  አናውቅም  ብለናል።  የሚታወቁትም  ምን  እንዳዘሉ  እነደዚሁ  ስ  እነሱ የምናውቀው  ነገር  የለም  ብለናል።  የአገራችን  ሰዓሊዎች  የሳሉት  ሥዕሎች 

ተሸጠው  በዓለም  ዙሪያ  ተበትነዋል።  አንደ  ቤተ  መንግሥቱም  ሰነዶች  እነሱም አልተመዘገቡም ብለናል። 

የትምህርትና ሥነ-ጥበብ ሚኒስትር ተመራቂ ተማሪዎች ብዙ ናቸው። ሥራቸው 

የት  ገባ? የትይገኛል?… ቢያንስ  በምዝገባ  ሥራ  አንዳንድ  ነገሮችን  መጀመር ይቻላል። 

እንዳው ለመነሻ  ያህል፣ 

አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፣  እአአ 1965፣ ለንጉሠ፥ነገሥቱ 

የጻፉትን አቤቱታ  እዚህ እትም ውስጥ  አካተነዋል። 

*

የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ደብዳቤ ፣ ለንጉሠ፥ነገሥቱ (1965) 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ  ለረዥም ዘመናት በአምባሳደርነት አገራቸውንኢትዮጵያን ያገለገሉ ናቸው። 

ገና ጥዋት፣ በኢትዮጵያ ሀገራችን ዛሬ የምንመለከታቸው የህዝብና የአእምሮ ትርምስከመድረሱ በፊት፣ ለኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር በመመኘት ለንጉሠ፥ነገሥቱ የጻፉትንደብዳቤ ለመዝገብና ለማገናዘብ ይሆን ዘንድ፣ ያላችሁት እንድትመለከቱት በእጅየተጻፈውን ሰነድ አስቀምጠነዋል።

በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ እነ ጄኔራል አብይ አበበ፣ እነ አቶ ሓዲስ ዓለማየሁ፣ እነ ልዑልአሥራተ ካሣ፣ እንደ ደጃች … ተክለ ሐዋሪያት የሰነዘሩአቸው ሐሳቦችም አሉ። 

Page 32: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 32/34

 

የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ደብዳቤ 

 ——————–  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Ethiopia to Yemen  –  The Most Dangerous Journey on

Earth (BBC) 

http://www.youtube.com/watch?v=ihQ4oL4Iwf4 

Posted on August 29, 2013  by ለ አእምሮ / Le'Aimero 

 ——————–  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013 

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  

Page 33: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 33/34

እስክንድር / Tribute to Skunder Boghossian 

Posted on August 28, 2013 | Leave a comment 

http://www.africa.upenn.edu/Smithsonian_GIFS/Boghossian.gif  

እስክንድር፣ 

በኪነ ጥበብ ፀጋው፣ ማዕከሉ ላይ ያለችውን ሰላም ለማግኘት፣

በዘመናችን ያለውን አምባ ጓሮ፣

ከንቱ ዕልቂትና ውዳሴ ሲያስመዝግበን ይሆን ? 

አዎ ሰሚ አእምሮ ካገኘ! 

 ____ 

Boghossian was born on July 22, 1937 in Addis Ababa, at the time the capital of the Italiancolony Italian East Africa, one and half years after the Second Italo-Abyssinian War .[1] His

mother, Weizero Tsedale Wolde Tekle, was Ethiopian.[1]  His father, Kosrof Gorgorios

Boghossian, was a colonel in the Kebur Zabagna  (Imperial Bodyguard) and of  Armenian 

descent.[1]  Kosrof’s father, Gregorios Boghassian, an Armenian trader, had established a

friendship with Emperor  Menelik II  and worked as a traveling ambassador in Europe on

 behalf of the Emperor .[4] 

Boghossian’s father was active in the resistance against the Italian occupation and was

imprisoned for several years when Boghossian was a young child.[1] His mother had set up a

new life apart her children and although both he and his sister Aster (Esther) visited their 

mother frequently, they were raised in the home of their father’s brother Kathig Boghassian.[4] 

Kathig, who was serving as the Assistant Minister of Agriculture, together with other uncles

and aunts brought them up during their father’s imprisonment.[4] 

Page 34: LeAimero-ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05-08-7

7/30/2019 LeAimero- – I-05-08-7

http://slidepdf.com/reader/full/leaimero-i-05-08-7 34/34

He attended a traditional Kes Timhert Betoch kindergarten where he was taught the Ge’ez

script.[1] In primary and secondary school, he was taught by both Ethiopian and foreign tutors

and become fluent in Amharic, English, Armenian and French.[1] He studied art informally at

the Teferi Mekonnen School.[5]  He also studied under Stanislas Chojnacki, a historian of 

Ethiopian art and watercolor painter .[5] 

READ MORE 

https://www.google.de/search?q=Skunder+Boghossian-and-more 

SKUNDER TRIBUTE 

Celebration of Art & Culture 

 ——————–  

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer  


Recommended