+ All Categories
Home > Documents > ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the...

ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the...

Date post: 14-Feb-2018
Category:
Upload: truongthu
View: 245 times
Download: 12 times
Share this document with a friend
21
1 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህ ር ት ቤቶች አ ን ድነ ት ጉባዔ መተዳደሪያ ደንብ
Transcript
Page 1: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

1

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ

የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

በሰሜን አሜሪካ የ ሰንበት ትምህርት ቤቶች

አንድነ ት ጉባዔ

መተዳደሪያ ደንብ

Page 2: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

2

ማሳሰቢያ

አንድነት ጉባኤ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ቢሻሻሉ/ቢካተቱ መልካም ነው የተባሉት ነጥቦች በቀይ ዝርዝር

እንደየክፍላቸው እና እንደየ አንቀጻቸው ተጽፈዋል። አንዳንድ ነጥቦች ሙሉ በሙሉ አዲስ ሀሳብ ሲሆኑ ሌሎች

ነጥቦች ደግሞ አስቀድሞ የተሰጠውን ሀሳብ በይበልጥ የሚያብራራ እና አንዳንድ ቃላቶችን ህጋዊ ይዘት

እንዲኖራቸው በማሻሻል የተቀየሩ ናቸው።

ይህ ደንብ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት በሕጋዊው

ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር በሚመሩ የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ የወጣ የመተዳደሪያ ውስጠ ደንብ

ነው።

ደንቡ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ዓመታዊ መደበኛ አንድነት ጉባኤ ስምንተኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ

ለተካፋይ አባላት በንባብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኅዋላ በጉባኤው ላይ በተካፈሉ ሊቃነ ጳጳሳት፤ካህናት እና

የሰንበት ት/ቤት አባላት ግምገማና እርማት ተደርጎበት በሙሉ ድምጽ ጸድቆ በሥራ ላይ እንዲውል ተወስኖአል።

ደንቡን ያጸደቁ ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት።

1. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ

አህጉራት የአሪዞና ፤ የዪታ ፤የላስቪጋስ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ።

2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመካከለኛው

ምስራቅና አካባቢው የሚኒያፖሊስ ፤ ኖርዝ ዳኮታና አካባቢው ሊቀጳጳስ።

3. አባ ገብረስላሴ የአትላንታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሰባኪ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

ጉባዔ መምሪያ ሃላፊ::

ደንቡን የገመገሙ እና አስተያየቶችን የሰጡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች

1. የሚኒያፖሊስ ቅዱስ ዑራኤል ሰንበት ት/ት ቤት መላው አባላት።

2. የዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

3. የአትላንታ ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

4. የአትላንታ ቅድስት ማርያም ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

5. የሳንሆዜ ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

6. የሳንዲያጎ ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

7. የሎሳንጀለስ ቅድስት ማርያም ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

8. የሎሳንጀለስ ድንግል ማርያም ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

9. የኦክላንድ መድኃኒአለም ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

10. የካናዳ ቅድስት ማርያም ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

11. የሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

12. የፖርት ላንድ መድኃኒአለም ሰንበት ት/ት ቤት ተወካይ አባላት።

Page 3: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

3

ማውጫ

መግቢያ ............................................................................................................................................................ 5

አንቀጽ አንድ ...................................................................................................................................................... 6

ስያሜው ............................................................................................................................................................ 6

የአንድነት ጉባኤ ሕጋዊ ማህተም የድህረ ገጽ ስያሜ እና የደብዳቤ መላላከያ መግቢያ ..................................................................... 6

የድህረ ገጽ አድራሻ ............................................................................................................................................... 6

አንቀጽ ሁለት ...................................................................................................................................................... 6

ትርጓሜ............................................................................................................................................................. 6

አንቀጽ ሦስት ...................................................................................................................................................... 7

አቋም ............................................................................................................................................................... 7

አንቀጽ አራት ....................................................................................................................................................... 7

ዓላማና ተግባር .................................................................................................................................................... 7

ዝርዝር ተግባራት ................................................................................................................................................. 8

አንቀጽ አምስት .................................................................................................................................................... 8

አባልና አባልነትን በተመለከተ .................................................................................................................................. 8

አንቀጽ ስድስት .................................................................................................................................................... 9

የአንድነት ጉባኤው አባላት መብትና ግዴታ .................................................................................................................. 9

6.2 የአባላት ግዴታ .............................................................................................................................................. 9

አንቀጽ ሰባት..................................................................................................................................................... 10

መዋቅር ........................................................................................................................................................... 10

አንቀጽ ስምንት .................................................................................................................................................. 10

በቅዱስ ሲኖዶስ የተመደቡ የአንድነት ጉባኤ የመምሪያ ኃላፊ ......................................................................................... 10

አንቀጽ ዘጠኝ .................................................................................................................................................... 10

የቤተክርስቲያናን አባቶች ካህናት/ ሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ ድርሻ ......................................................................................... 10

አንቀጽ አሥር ..................................................................................................................................................... 11

10.1 የጠቅላላ ጉባዔው ተግባርና ኃላፊነት .................................................................................................................. 11

10.2 አመታዊ አንድነት ጉባኤ የአዘጋጅነት ፈቃድ በተመለከተ ........................................................................................ 11

አንቀጽ አሥራ አንድ ............................................................................................................................................. 12

የአንድነት ጉባኤው የሥራ አመራር ተግባርና ሃላፊነት ........................................................................................................ 12

አንቀጽ አሥራ ሁለት ............................................................................................................................................. 12

በስደት ያለው ሕጋዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ መዋቅር ............... 13

የሥራ አመራሩ የሥራ ድርሻ .................................................................................................................................. 14

Page 4: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

4

12.1 ሊቀ መንበር ............................................................................................................................................. 14

12.2 ፀሐፊ ....................................................................................................................................................... 14

12.3 ሒሳብ ክፍል ............................................................................................................................................ 14

12.4 ግንኙነት ክፍል .......................................................................................................................................... 15

12.5 ትምህርት ክፍል ........................................................................................................................................... 16

12.6 መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል........................................................................................................................ 17

12.7 ልማትና ሽያጭ ክፍል .................................................................................................................................. 17

12.8 ገንዘብ ያዥ .............................................................................................................................................. 17

12.8 ቴክኖሎጂ ክፍል ........................................................................................................................................ 18

አንቀጽ አስራ ሦስት ............................................................................................................................................ 18

የክልል የንዑሳን ኮሚቴ የስራ ድርሻ ......................................................................................................................... 18

አንቀጽ አሥራ አራት ........................................................................................................................................... 18

14.1 የአንድነት ጉባኤን ንብረት በተመለከተ .............................................................................................................. 18

አንቀጽ አስራ አምስት .......................................................................................................................................... 18

15.1 ስብስባና የስብስባ ሂደት ............................................................................................................................... 18

15.2 የስብሰባው ሂደት ........................................................................................................................................ 19

አንቀጽ አሥራ ስድሰት ......................................................................................................................................... 19

16.1 የሥራ አመራር የአገልግሎት ዘመንና አመራረጥ ................................................................................................... 19

16.2 የሥራ አመራር አመራረጥ ............................................................................................................................. 19

የአስመራጭ ኮሚቴ አመራረጥ ............................................................................................................................... 19

16.3 የአስመራጭ ኮሚቴ የሥራ ድርሻ .................................................................................................................... 20

16.4 የእጩነት መስፈርት .................................................................................................................................... 20

አንቀጽ አሥራ ሰባት ............................................................................................................................................ 20

የአመራር ኮሚቴ አባልን ያለጊዜው መቀየር አስመልክቶ ................................................................................................. 20

አንቀጽ አሥራ ስምንት .......................................................................................................................................... 21

18.1 ደንቡ ስለሚጸናበት ግዜና ደንቡን ስለማሻሻል ..................................................................................................... 21

ማጠቃላያ ....................................................................................................................................................... 21

Page 5: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

5

መግቢያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዪ የዓለማችን ክፍሎች በተላይም በሰሜን አሜሪካ በሰደት የሚገኙ ኢትዮዽያውያን የሀገራቸውን ኦርቶዶክስ ሃይማኖትና ባህላችውን በማስተማር ረገድ እየሰጠችው ያለው አገልግሎት በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡

በስደት ላይ ያለው ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ከሃገር ውጪ ተበትኖ የመሚገኘውን ሕብረተሰብ በማስተማር ፤ ህዝቡ በራሱ አነሳሽነትና በልዑል እግዚአብሄር ረዳትነት የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያንን በማስገንባትና መለኮሳትን ቀስውስትን፡ ዲያቆናትን የቅዱስ ወንጌል መምህራንን ከኢትዮዽያ እያስመጣ እንዲሁም በምንኖርበት በምድረ አሜሪካ ሊቃነ ጳጳሳትን፡ ቀሳውስትንና፡ ዲያቆናትን በመሾም መምህራንን በማሰልጠን ማህበረስቡ መንፈሳዊ ህይወቱ እንዲጎለብትና ቤተ ክርስቲያን በስደት ዓለም እንድትስፋፋና ለትውልድ የሚቆይ ታሪክ እንዲኖር በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ቅዱስ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎሰስ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አበው ካህናት ይህን አኩሪ ተግባራቸውን ለብዙዎች በረከት መሆኑን አሁን በየአህጉራቱ ተሰዶ የሚገኝው ኢትዮዽያዊ በተለይም ወጣቱ የህብረተሰባችን ክፍል በሚገባ ተረድቶታል፡፡ ይህም በመሆኑ ወጣቱ ትውልድ የሚኖርበት ሃገር የኑሮ ተጽኖ ሳይበግረው፡ ከአባቶቹ የተረከበውን ታሪክ፣ሃይማኖት፣ ባህልና የሃገር ፍቅር ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ በየፊናው ተገቢውን ጥረት ሲያደርግ ከመገኝቱ ባሻገር በስንበት ትምህርት ቤቶች በመታቀፍ እየሰጠ የሚገኘው አገልግሎት አጅጉን የሚያስደስት ነው።

ስለሆነም፦

1. ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን ከቤተክርስቲያን እንዳይርቁና በአገልግሎቶች እንዲሳተፉ ለማድረግ።

2. ወጣቱ ትውልድ በውጪ ባህል ተስቦ የዜግነት ማንነቱን ሳይዘነጋ ባህሉንና ሃይማኖቱን ጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ።

3. በተሻለ ዕውቀትና በኢኮኖሚ በሰለጠነ ሀገር ላይ ሆኖ እግዚያብሄር በሰጠው ስጦታ ቤተክርስቲያንን ሀገሩንና ወገኑን እንዲረዳ ለማድረግ።

4. የሰንበት ትምህርት ቤቶች ከአባቶች ስር በመሆን በህብረትና በቅንጅት ለአንድ አላማ እንዲሠሩ ማድረግ በማስፈለጉ

5. ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም አገልግሎቶች በተቀናጀ መልክ መፈጸም በማስፈለጉ ይህ ውስጠ ደንብ እንዲዘጋጅ ተደርጓል።

ይህ ደንብ በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህግና ሥርዓት መሠረት በተቋቋሙትና

ለወደፊት ለሚቋቋሙት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መመሪያ ይሆን ዘንድ የአንድነት ጉባኤ አመራር አባላት

አርቅቀውት፤በተለያዮ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶች አስተያየት ቀርቦበት ታርሞና ተሻሽሎ፤ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት

ተገምግሞ የወጣ የመተዳደሪያ ደንብ ነው።

Page 6: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

6

አንቀጽ አንድ ስያሜው

በስደት የሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች

አንድነት ጉባኤ ተብሎ ይጠራል።

የአንድነት ጉባኤ ሕጋዊ ማህተም የድህረ ገጽ ስያሜ እና የደብዳቤ መላላከያ መግቢያ

በስደት ያለው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሰንበት ትምሕርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ

The Legitimate Holy Synod in exile of the Ethiopian Orthodox Tewahedo

Church Sunday School Unity Forum

www.andinetgubae.org

የድህረ ገጽ አድራሻ www.andinetgubae.org

አንቀጽ ሁለት ትርጓሜ

1.1 አንድነት ጉባኤ ማለት በስደት የሚገኘው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ

ማዕከል ክፍል ነው።

1.2 መምሪያ ኃላፊ ፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰየመው አንድነት ጉባኤን በበላይነት የሚቆጣጠርና ለሥራ አመራር ኮሚቴ

እንዳስፈላጊነቱ መምሪያ የሚሰጥ እንዲሁም አመራሩ ተወያይተው የሚያቀርቡለትን ሃይማኖታዊና ከተመደበላቸው

Page 7: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

7

በጀት በለይ ለሚመጡ ጥያቄዎች በጥሞና ገምግሞ እቅዶችን የሚያጸድቅና የሚፈቅድ ክፍል ነው። ተጠሪነቱ

ለህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ነው።

1.3 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ፡ በጠቅላላ አባላት የሚመረጥና በመምሪያ ክፍሉ ጸድቀው የሚመጡትን

እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን እድገት እና ለእምነታችን ጥንካሬ የሚጠቅሙ ስራዎችን እርስ በዕርስ በመወያየት ስራ

ላይ እንዲውሉ በኃላፊነት የሚያስተባብር እና የሚመራ ክፍል ነው። ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመምሪያ ኃላፊ ነው።

የአመራር ኮሚቴዎች ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለኮሚቴው ሰብሳቢ ሊቀመንበር ነው።

አንቀጽ ሦስት አቋም

3.1 ይህ የአንድነት ጉባኤ በማንኛውም የፖላቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ አይገባም::

3.2 በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቱ ራሱን ከቤተክርስቲያን ስር አድርጎ የሚሰራ ነው።

3.3 ራሳቸውን በማህበራት ከሚሰይሙና ቤተክርስቲያን ከማትደግፋቸው ወገኖች ጋር ፈጽሞ ህብረት የለውም።

3.4 በዚህ አንድነት ውስጥ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

ትምህርተ ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና ያመኑና የተከተሉ ብቻ ይሳተፋሉ።

3.5 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሚመሩ ካህናትና መምህራን ጋር በአንድነት

ይሰራል።

3.6 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር በሚመሩ ቤተክርስቲያናት እንዲሁም

በስራቸው ካሉ የስንበት ት/ቤቶች የውስጠ ደንብ ጋር ሳይቃረን ሥራውን በህብረት ይሰራል::

አንቀጽ አራት ዓላማና ተግባር

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች

በስደትና በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገሩ ርቆ የሚገኝውን ምዕመን እና ወጣት በየቤተክርስቲያኑ በማሰባሰብ የቤተክርስቲያን

ትምህርተ ኃይማኖት፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና ትውፊትን በማስተማር ላይ ይገኛል። በመሆኑም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች በዚህ ታላቅ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ከአባቶች ጋራ በመሆን

የበለጠ በአገልግሎት ለመርዳት ይህንን የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ የሚሠሩበትን አንድነት ጉባኤ

መሥርቷል።

Page 8: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

8

ዝርዝር ተግባራት

4.1 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ የቤተ

ክርስቲያንን ትውፊት ከአባቶች በመማር ለተተኪው ትውልድ እንዳለ ጠብቆ ለማስተላለፍ ማስቻል።

4.2 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሰሜን አሜሪካ ባሉት አጥቢያ አብያተ ክርስትያናት ስብከተ ወንጌል፤ ዶግማና ቀኖና በተጠናከረ ሁኔታ እንዲስጥ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር በመሆን ማስተባበር። 4.3 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶችን ወጥ የሆነ አገልግሎት የሚሰጡበትን መንገድ በማመቻቸት እገዛ ማድረግ። 4.4 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ የያሬዳዊ ዜማ ሥርዓትን የጠበቀ የመዝሙር አገልግሎት እንዲጠናከር ማድረግ። 4.5 በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ሰንበት ትምህርት ቤቶች በተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም ላይ በመገናኘት የሥራ ልምድ ልውውጦችን ማድረግ። 4.6 ወጣቱ ትውልድ የሰንበት ት/ቤት አባል ሆኖ በዚህ በምንኖርበት ሀገር የተለያዩ የዕምነት ድርጅቶችና ማህበራት የቤተክርስቲያንን እና የአባቶችን ስም ለማጥፋት የተደራጁ ድርጅቶች የሚያደርጉትን የተልኮ ሥራ መከላከልና፤ቤተክርስቲያንን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች በንቃት መጠበቅ። 4.7 በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እና ለሰ/ት/ቤቶች መጠናከር እገዛ ማድረግ። 4.8 ከኢትዮጵያ ውጪ ተወልደው አማርኛ ቋንቋን ለማይናገሩ ታዳጊ ወጣቶች በሚችሉት ቋንቋ ስርዐተ

ቤተክርስትያንን እና ወንጌልን ማስተማር እንዲሁም አማርኛ ቋንቋ እና የግዕዝ ቋንቋ መማር የሚችሉበትን መንገድ

ከቤተክርስትያን አባቶች ጋር በመሆን መንደፍና ማዘጋጀት ነው።

አንቀጽ አምስት አባልና አባልነትን በተመለከተ

በአንድነት ጉባኤው አባል መሆን የሚችሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ የሆኑና ከዚህ

በታች የተዘረዘሩትን የአባልነት መመዘኛዎች ያሟሉ ናቸው።

5.1 በሰንበት ትምህርት ቤት ደረጃ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር የተደራጁ ሰንበት ት/ቤቶች፤

የአንድነት ጉባኤው አባል መሆን ይችላሉ።

5.2 በቤተክርስቲያን አባልነት ደረጃ

Page 9: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

9

አንድ ግለሰብ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አባል ሆኖ በሰንበት ት/ቤት ሲያግለግል ቆይቶ ነገርግን በተለያዩ ምክንያቶች

አገልግሎት መስጠት ቢያቆምና የቤተክርስቲያን አባልነቱን ቢቀጥል ፤ የአንድነት ጉባኤው አባል ለመሆን የሚካተሉትን

መስፈርቶች ማሙዋላት ይኖርበታል።

5.2.1 በአባልነት ከሚሳተፍበት ቤተክርስቲያን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል

5.2.2 ካገለገለበት ቤተ/ክ ሰ/ት/ቤት አገልጋይ እንደነበር የሚገልጽ ድብዳቤ ወይም በቃል ለሥራ አመራር ክፍል ማስመስከር

ይኖርበታል

5.2.3 ለሃይማኖቱና ለሥርዓቱ ቀናዊ ሆኖ ቤተክርስቲያን በምታዘው ሁሉ የሚሳተፍና የአንድነት ጉባኤውን መተዳደሪያ

ደንብ የሚቀበል መሆን ይኖርበታል

አንቀጽ ስድስት የአንድነት ጉባኤው አባላት መብትና ግዴታ

6.1 የአባላት መብት

6.1.1 አንድነት ጉባኤው የሚያዘጋጃቸውን ማንኛውም መንፈሳዊ ሥነ ጽሁፎች፤የትምህርት ስብከቶችና የመሳሰሉትን

በቅድሚያ ያገኛሉ::

6.1.2 እንደ አስፈላጊነቱ የአባልነት ማስረጃዎችን በፈለጉ ግዜ ያገኛሉ::

6.1.3 ለጉባኤው አገልግሎት የመምረጥና የመመረጥ ሙሉ መብት አላቸው ::

6.2 የአባላት ግዴታ

6.2.1 የአንድነት ጉባኤውን ህግና ሥርዓት መጠበቅ አለበት።

6.2.2 አባል ከሆኑ የአባልነት ክፍያ በየወሩ አምስት /5/ ወይንም በዓመት አንድ ጊዜ ክፍያ $60 የአሜሪካን ዶላር መክፈል

ይኖርባቸዋል።

6.2.3 የሰንበት ት/ት ቤት አባል መሆን እና ማገልገል ይኖርባቸዋል።

6.2.4 የአንድነት ጉባኤው ለአግልግሎት በጠየቀው የሥራ ዘርፍ መሳተፍ ይኖርባቸዋል::

6.2.5 ከቤተክርስቲያን አባላት ጋር በመሆን እንዲሁም ከአንድነት ጉባኤ አመራር ጋር ለአብያተ ክርስቲያናት እና ለሰ/ት/ቤቶች መጠናከር በማንኛውም መልኩ እገዛ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: 6.2.5 ለተማሪዎች፣ ሥራ ለሌላቸው እንዲሁም በሌሎችም አሳማኝ ምክንያቶች ወርሃዊ ክፍያ መክፈል ለምይችሉ ወጣቶች፤ ጉባኤው ምንም አይነት ጫና አያደርግም። ነገር ግን በሌሎች አገልግሎቶች አቅማቸው በሚፈቅደው መልኩ እንዲሳተፉፎ ያበረታታል። 6.2.6 አንድነት ጉባኤ በሚያደርጋቸው አመታዊም ሆነ ክልላዊ ጉባኤ ላይ መሳተፍ ይኖርበታል።

Page 10: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

10

አንቀጽ ሰባት መዋቅር

7.1 የአንድነት ጉባኤው ተጠሪነቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ

መምሪያ ሃላፊ ነው::

7.2 የአንድነት ጉባኤው በሰሜን አሜሪካ ባሉት አራቱም ክልሎች በሰሜን፡ደቡብ፡በምስራቅ፡በምዕራብ እንዲሁም

በመካከለኛው አገልግሎቱን የሚያቀናጁና የሚያስተባብሩ የንዑሳን ኮሚቴ ክፍሎች ይኖሩታል። እነኝህ የንዑሳን ኮሚቴዎች

ተጠሪነታቸው ለአንድነት ጉባኤው ሥራ አመራር ይሆናል።

አንቀጽ ስምንት በቅዱስ ሲኖዶስ የተመደቡ የአንድነት ጉባኤ የመምሪያ ኃላፊ

8.1 የአንድነት ጉባኤውን የሥራ ሂደት በቅርብ ይከታተላሉ ፤መመሪያ ይሰጣሉ።

8.2 የአንድነት ጉባኤውን የሥራ ሪፖርት በየስድስት ወሩ እየተቀበሉ ይገመግማሉ፤ ተገቢውን መመሪያ ይሰጣሉ።

8.3 የአንድነት ጉባኤውን ጠቅላላ የሥራ እቅድና ክንዋኔውን በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ በመገኘት ይገመግማሉ፤

ተገቢውን ሃሳብና መመሪያ ይሰጣሉ።

8.4 አንድነት ጉባኤው ለሚያደርገው የሥራ እንቅስቃሴ ሁሉ ተገቢውን ድጋፍና የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣሉ።

አንቀጽ ዘጠኝ የቤተክርስቲያናን አባቶች ካህናት/ ሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ ድርሻ

የአንድነት ጉባኤው ጠቅላላ አመታዊ ጉባኤ በተላያዮ የሰሜን አሜሪካና ካናዳ ከተሞች የሚያደርግ ሲሆን በዚህም ላይ

የቤተክርስቲያናት የሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ካህናት ክፍል አስፈላጊውን ትብብር የማድረግ ሃላፊነት ይጠበቅበታል።

የካህናት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቦርድ(ሰበካ ጉበኤ) ድርሻ

አንድነት ጉባኤው በተራ ዝውውር በሚያደርገው አመታዊም ሆነ ክልላዊ ጉባኤ ከአንድነት ጉባኤ መምሪያ ሃላፊ ወይም

አመራር በሚቀርብላቸው ጥያቄ መሠረት ለጉባኤ ክንውን አስፈላጊውን እውቅና እና ትብብር ይሰጣሉ።

9.1 የዓመታዊ ጉባኤ አዘጋጅ ቤተ ክርስቲያን ምርጫ

9.1.1 ዓመታዊውን ጉባዔ ፈቃደኛ የሆኑ ቤተ ክርስቲያናት እንዲያዘጋጁ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ፈቃደኛ

ከሌለ በዓመታዊው ጉባዔ ላይ በምርጫ የሚወሰን ይሆናል።

9.2 የዓመታዊ ጉባኤ አዘጋጅ ቤተ ክርስቲያኑ ኃላፊነት

Page 11: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

11

9.2.1 የጉባኤው አዘጋጆች ቤተ/ክ የሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ካህናት ክፍል ሊቀመንበር ከስንበት ት/ቤቱና ከጉባኤው ሥራ አመራር

አባላት ጋር በጋራ በመሆን ይስራል፤ ስብሰባዎችን ይካፈላል።

9.2.2 የጉባዔው አዘጋጅ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ ኮሚቴ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጋር በመተባበር አስፈላጊውን

ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል::

9.2.3 የምግብና የመጠጥ ወጪዎችን በመሸፈን ሰንበት ትምህርትቤቱን ይተባበራል።

9.2.4 አዘጋጅዋ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ ኮሚቴ የሁለት መምህራን የአየር ቲኬቶች ወጪ ይሸፍናል።

9.2.5 አዘጋጁ ስንበት ትምህርት ቤት በዓሉ ከመዘጋጀቱ አስቀድሞ ከአንድነት ጉባኤ ኮሚቴ ጋር በተወከሉ የሰንበት ት/ቤት አባ

ላት መሰረት የሥራ ክንውኖችን ይወያያል።

9.2.6 የአዘጋጅዋ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ ኮሚቴ/ካህናት እና ሰንበት ት/ት ቤቱ ከምዕመናን ጋር በመተባበር ለጉባኤ

የሚመጡ አባላትን ከአየር ማረፊይ ተቀብሎ ይሽኛል። እንዲሁም በዓሉ የተዋጣና የተሳካ ለማረግ አስፈላጊውን ሀሉ ነገር ያሟላል።

9.3 የተሳታፊው አብያተክርሰቲያናት ኃላፊነት

9.3.1 ቢያንስ ሁለት ከተቻለም ከዚያም በላይ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትን ጉባኤው ወደሚዘጋጅበት ከተማ ይልካል።

9.3.2 የተወካዮች የአየር ቲኬት ወጪ ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።

9.3.3 የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ከጉባኤው በኋላ የጉባኤውን የስራ ሂደትና ክንውኖች ሪፖርት ለሰንበት ት/ቤቱ

አባላትና ለቤተ ክርስቲያኑና ለሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ ካህና ት በጽሁፍ ያቀርባል፤በንባብ ያስማል።

አንቀጽ አሥር

10.1 የጠቅላላ ጉባዔው ተግባርና ኃላፊነት

በጠቅላላ ጉባኤው በአመት አንድ ጊዜ የሚያደርግ ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል።

10.1.1 የአንድነት ጉባኤው አመራር ለሦስት ቀን የሚቆየውን አመታዊ ጉባኤ፤ ጉባኤው እንዴት መካሄድ እንዳለበት በሚገልጸው

መመሪያ ሰነድ (ፕሮጀክት ቻርተር) መሰረት ያከናውናል።

10.1.2 የአንድነት ጉባኤውን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል::

10.1.3 አመታዊ እቅድና በጀት ያወጣል፤ ያጽድቃል::

10.1.4በሁለት አመት አንድ ግዜ የሥራ አመራሮችን ይመርጣል::

10.1.5 የሰንበት ት/ት ቤቶችን የስራ ሂደት በመገምግም ከአባላት ጋር ይወያያል::

10.1.6 ተወክለው የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች ስለየ ሰንበት ት/ቤትታቸው አመታዊ የሥራ ክንዉን ሪፖርት ያቀርባሉ። ይህም

ሪፖርት ሰንበት ት/ቤቶች የስራ ልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ያደርጋል እና አመራር ኮሚቴውም የሰንበት ት/ቤቶችን

እንቅስቃሴንም ይገመግማል።

Page 12: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

12

10.2 አመታዊ አንድነት ጉባኤ የአዘጋጅነት ፈቃድ በተመለከተ

10.2.1 ማንኛውም ሰንበት ትምህርት ቤት አመታዊ አንድነት ጉባኤን ማስተናገድ ከፈለገ አስቀድሞ ለአንድነት ጉባኤ አመራር

ከቤተክርስትያኑ አስተዳደር እና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ አመራር ለማስተናገድ ፈቃደኛነትን የሚገልጽ ደብዳቤ ማስገባት

ይጠበቅበታል። ጉባኤውን ለማዘጋጀት የሰንበት ትምህርት ቤት ደብዳቤ ብቻውን በቂ አይሆንም።

10.2.2 አመታዊው አንድነት ጉባኤ ፍታዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ ማንኛውም ቤተክርስትያን እና ሰንበት ትምህርት ቤት

በተከታታይ ጉባኤውን እንዲያዘጋጅ አይፈቀድለትም። መደበኛ አመታዊ ጉባኤው በምስራቅ፣ በምራብ፣ እና በመካከለኛው

ግዛት ውስት በተራ በመዘዋወር የሚከናወን ይሆናል።

10.2.3 የአንድነት ጉባኤ አመራር ኮሚቴ ከየትኛውም ቤተክርስትያን እና ሰንበት ትምህርት ቤት አመታዊ ጉባኤውን

ለማስተናገድ ፈቃደኛነትን የሚገልጽ ደብዳቤ ካልደረሰው ከመምሪያ ኃላፊ ጋር በመወያየት ከላይ የተጠቀሰውን የተራ

መስፈርት ባሟላ መልኩ አዘጋጅ ቤተክርስትያንን እና ሰንበት ትምህርት ቤትን ይመርጣል።

አንቀጽ አሥራ አንድ የአንድነት ጉባኤው የሥራ አመራር ተግባርና ሃላፊነት

የሰሜን አሜሪካ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ የሥራ አመራር ክፍል ተጠሪነቱ ለመምሪያ ሃላፊ እና ለጠቅላላ ጉባኤው ሲሆን

ተግባራቱም ከዚህ እንደሚከተለው ነው።

11.1 የአንድነት ጉባኤውን ጠቅላላ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል:: 11.2 የመምሪያ ሃላፊው ያጸደቀለትን በጀትና እቅድ በአግባቡ መተግበሩን ይከታተላል:: 11.3 በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ከአዘጋጁ ሰ/ት/ቤት ጋር በመሆን ያዘጋጃል። አባላትን ይጋብዛል። 11.4 በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የሚገኙ አባቶችን፡መምህራንን፡ሌሎች ተጋባዦችንና የስብስባ አጀንዳዎችን ይወስናል:: 11.5 ለሥራ መቃናት የሚረዱ ከየሰንበት ትምህርት ቤቶች የተመደቡትን ተወካዮች በንዑሳን ክፍሎችን በስሩ

እንዲያገለግሉ በመጠቆም አመራር ኮሚቴው ለመምሪያ ክፍሉ እንዲጸድቁለት ያቀርባል።

11.6 ለአንድነት ጉባኤው የስራ ማስኬጃ ወጪዎች ከአንድነቱ ገቢ ወጪ እንዲሆኑ ይወስናል::

11.7 በምርጫ ጊዜ ከመምሪያ ኃላፊ ጋር በመሆን አስመራጭ ኮሚቴን ይመርጣል ያስመርጣል።

11.8 አንድነት ጉባኤውን ለሚመለከቱ ጉዳዮች ከመምሪያ ክፍል አካላት ጋር በቅርበት በመመካከር ይሰራል።

አንቀጽ አሥራ ሁለት

የአንድነት ጉባኤው የሥራ አመራር ክፍሉ የሚከተሉት የስራ አመራር ክፍሎች ይኖሩታል

12.1 ሊቀ መንበር

12.2 ፀሐፊ

12.3 ሒሳብ ክፍል

Page 13: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

13

12.4 ግንኙነት ክፍል

12.5 ትምህርት ክፍል

12.6 መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል

12.7 ልማትና ሽያጭ ክፍል

12.8 ገንዘብ ያዥ

12.9 ቴክኖሎጂ ክፍል

በስደት ያለው ሕጋዊ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ መዋቅር

ጠቅላይ ቤተክህነት

መምርያ ኃላፊ

የሰንበት ትምሀርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ኮሚቴ

ሂሳብ ክፍል ትምህርት ክፍል

ጸሐፊ ሊቀ መንበር

ህጻናት/ ታዳጊ ወጣቶች

ቴክኖሎጂ ክፍል ሕዝብ ግንኙነት

ገንዘብ ያዥ

ወጣቶች

መዝሙርና ስነጥበብ ልማት/ሽያጭ ክፍል

Page 14: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

14

የሥራ አመራሩ የሥራ ድርሻ

12.1 ሊቀ መንበር

12.1.1 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤውን የሥራ ሂደቶችን በኃላፊነት ይመራል::

12.1.2 ከበታች ያሉትን የኮሚቴ አባላት ሥራ ሂደትና ተፈጻሚነት ይከታተላል::

12.1.3 ከኮሚቴ አባላት የሥራ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል::

12.1.4 የጉባኤውን ገቢ እና ወጭ ይከታተላል፤ እንዳስፈላጊነቱ ከሒሳብ ክፍል ጋር በመሆን የጉባኤውን ገንዘብ

ያንቀሳቅሳል::

12.1.5 ለመደበኛም ሆነ ለአስቸኳይ ስብሰባዎች ዝግጅት በማድረግ ሰብስባዎችን ይጠራል፤ ይመራል::

12.1.6 ከአንድነት ጉባኤው የሚወጡ ደብዳበቤዎች ላይ ይፈርማል።

12.1.7 የሥራ አስፈጻሚው ሙላተ ጉባኤው ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ ወይም በድምጽ ብልጫ ያሳለፋቸውን ሃይማኖታዊ

ሆነም የተለያዩ እቅዶች በተመለከተ እና ከተመደበለት በጀት በላይ ሲያስፈልግ፤ ለመምሪያ ኅላፊው ኮሚቴውን

ወክሎ እንዲጸድቅ ያቀርባል።

12.1.8 የሥራ አምራር ኮሚቴ አባላት ያልተወያዩበትን እንዲሁም በድምጽ ብልጫ ያላሳለፉትን ነጥቦች አንድነት ጉባኤውን

በመወከል መመሪያ ሊያስተላልፍ አይችልም።

12.1.9 ሊቀመንበሩ ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ መምሪያ ሀላፊ ነው።

12.2 ፀሐፊ

12.2.1 ሊቀ መንበሩ በማይገኝባቸው ጊዜያቶች የእርሱን ቦታ በመተካት የሊቀ መንበሩን ሥራ ይሰራል።

12.2.2 ከሊቀ መንበር ጋር በመሆን የስብሰባ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል እንዲሁም የስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይይዛል።

12.2.3 ለሥራ ክንውን የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን እንዳስፈላጊነቱ ከሊቀ መንበሩ ጋር በመመካከር ያደላድላል።

12.2.4 የስብሰባ አጀንዳዎችን መፈጸማቸውን በጥንቃቄ በመገምገም ሪፖርት ያደርጋል::

12.2.5 ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት ሊቀ መንበሩ እንዲፈርምባቸው ያደርጋል፤ደብዳቤ ይልካል ይቀበላል::

12.2.6 ያለ ሊቀመንበሩ ፊቃድ ደብዳቤ መላክ አይችልም::

12.2.7 የአንድነት ጉባኤ መምሪያ ኃላፊ ልዮ ረዳት በመሆን የጉባኤውን ሥራዎች በተመለከተ የሚጻፉ ወይም መምሪያ ክፍሉ

እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ሥራዎች ያከናውናል።

Page 15: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

15

12.2.8 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ አመራር ኮሚቴ ሊቀመንበር ነው።

12.3 ሒሳብ ክፍል

12.3.1 የአንድነት ጉባኤው ሒሳብ ክፍል የጉባኤውን የሂሳብ መዛግብት በሙሉ ይቆጣጠራል ገቢና ወጪውን ይመዘግባል::

12.3.2 በተመደበለት በጀት መሰረት ገቢና ወጪዎችን በትክክል ሂሳቡን አወራርዶ ይከታተላል::

12.3.3 የአንድነት ጉባኤው ገቢው ከ አምስት ሺህ ዶላር በላይ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ለቅዱስ ለሲኖዶሱ ገቢ ያደርጋል፤በጀቱም ከዛው ላይ

ይመደብለታል::

12.3.4 የአንድነት ጉባኤው አባላት ወርሃዊ መዋጮ አሰባስብን ይከታተላል::

12.3.5 በጀቱን በመምሪያው ኃላፊ መሰረት ለቅዱስ ሲኖዶስ ሒሳብ ክፍል ሃላፊ በደብዳቤ ጥያቄ ያቀርባል።

12.3.6 በአንድነት ጉባኤ አመታዊ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የጉባኤውን አመታዊ የሒሳብ ሪፖርት ያቀርባል

12.3.7 የገንዘብ ያዥ እና የልማት እና ሽያጭ ክፍሎችን በበላይነት ይቆጣጠራል።

12.3.8 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ አመራር ኮሚቴ ሊቀ መንበር ነው።

12.4 ግንኙነት ክፍል

12.4.1 የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘርፎች የዕርስ በዕርስ ትውውቅ እንዲኖር ያደርጋል።

12.4.1 ከተለያዩ የሰንበት ትምህርት ቤት ኃላፊዎች እና ከቦርድ አባላት ጋር በመገናኘት የአገልግሎት ሂደቶችን መገምገም

አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እገዛ ሊደረግበት የሚችሉ ሃሳቦችን በማመንጨት ከኮሚቴ ሊቀ መንበር እንዲሁም ከአባላት ጋራ

ይወያያል።

12.4.2 በአንድነት ጉባኤው ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን አሟአልቶ ይይዛል፤ አባላትም ሆኑ ሌሎች ስለአንድነት ጉባኤው ግንዛቤ እዲኖራቸው

ተገቢውን ሥራ ይሰራል::

12.4.3 ለአባላት የእንኳን አደረሳችሁ የበአል መልዕክቶችን ይልካል::

12.4.5 የአንድነት ጉባኤ አባላት በሙያቸው ቤተክርስቲያንን አንዲያገለግሉ ተገቢውን ሥራ ይስራል::

12.4.6 በስደተኛ ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩትን የሰንበት ተማሪዎች እያንዳንዳቸው የአንድነት ጉባኤ ተወካይ

በመምረጥ ከአንድነት ጉባኤ ሕዝብ ግንኙነት አመራር ጋር ይሰራሉ።

12.4.7 የያንዳንዱ የሰንበት ትምህርትቤት አንድነት ጉባኤ ተወካይ ክልላዊ ጉባኤዎች በተመለከተ በበላይነት ያስተባብራል

ይመራል።

12.4.8 የአንድነት ጉባኤ ያሁ ግሩፕ (yahoo group) እና ጉግል ግሩፕን (google group) በበላይነት ያንቀሳቅሳል።

በየጊዜውም አዳዲስ አባላትን እየጋብዛል ይጨምራል።

Page 16: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

16

12.4.9 ትምህርት ነክ ጽሁፎችን ከትምህርት ክፍል ጋር በመወያየት እንዲሁም የአንድነት ጉባአውን ህልውና እና የቤተ

ክርስቲያንን ህልውና የሚመለከቱ ጽሁፎች ሲመጡ ከሊቀ መንበሩ ጋር በመወያየት በመገናኛ መስመሮች ላይ እንዲወጡ

ያደርጋል።

12.4.10 በየሩብ አመቱ በየአመራር ክፍሎች የሚደረጉትን የሥራ ክንውን ሪፖርት ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቃል።

12.4.11 አንድነት ጉባኤ በተለያዩ ቦታዎች እንዲተዋወቅ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

12.4.12 እንደአስፈላጊነቱ ከሊቀመንበሩ እና ከጉባኤው አመራር ጋር በመወያየት አስተባባሪ የአንድነት ጉባኤ ተወካዮች

ከየቤተክርስትያኑ ሊጨምር ወይም ሊመድብ ይችላል።

12.4.13 ከቴክኖሎጂ ክፍል ጋር በመሆን የዳታ ሰነዶችን ይቆጣጠራል።

12.4.14 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ አመራር ኮሚቴ ሊቀመንበር ነው።

12.5 ትምህርት ክፍል

12.5.1 ሰንበት ትምህርት ቤቶች የትምህርተ ወንጌል ስርጭት እና የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት የማጠናከሪያ ጉባኤዎች በበቂ

ሁኔታ እንዲካሄዱ ፕሮገራም ያወጣል።

12.5.2 ለአንድነት ጉባኤው ድረ ገጽ የሚሆኑ ጽሁፎችን ያዘጋጃል::

12.5.3 አንድነት ጉባኤው ለአመታዊ ጉባኤ ለሚያወጣውን መጽሄት በሃላፊነት ያዘጋጃል::

12.5.4 የሥራ እንቅስቃሴና ያጋጠሙ ችግሮችን ሪፖርት ያቀርባል::

12.5.6 እንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ ለሚናገሩ ኢትዮጵያውያን የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ከመምራን ጋር በመሆን በሚናገሩት

ቋንቋ ትምሕርት እንዲዘጋጅ ያስተባብራል።

12. 5.7 መምህራን በሌላቸው ሰ/ት/ቤቶች ከኮሚቴዉና ከመምሪያ ኃላፊው ጋር በመሆን ጉባኤ ያዘጋጃል፤ መምህራን ይመድባል

12.5.8 ለዓመታዊ ጉባኤዎች ከመምሪያ ሀላፊው ጋር በመሆን የትምህርት ርዕሶችን እና መዝሙሮችን አዘጋዽቶና መምህራንን

በመጠቆም ለኮሚቴው የመጨረሻ ፍቃድ ያቀርባል

12.5.9 ሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤት የተሟላ አገልጋይ እንዲኖረው የአገልጋዮች ስልጠና መርሃ ግብርይዘረጋል፤ ያሰለጥናል።

12.5.10 እንደአስፈላጊነቱ ከሊቀመንበሩ እና ከጉባኤው አመራር ጋር በመወያየት አስተባባሪ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ሊጨምር

ወይም ሊመድብ ይችላል።

12.5.11 የህጻናት እና ታዳጊ ወጣት ክፍልን ያግዛል።

12.5.12 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ አመራር ኮሚቴ ሊቀመንበር ነው።

Page 17: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

17

12.6 መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል

12.6.1 ሰንበት ት/ት ቤቶች ስለቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ ተገቢው እውቀት እንዲኖራቸው በካሴትና በሥነ ጽሑፍ መልክ ዝግጅቶችን

በማዘጋጅት ሰራዎችን ይሰራል::

12.6.2 ለአንድነት ጉባኤው ድረ ገጽ የሚሆኑ ጽሁፎችን ያዘጋጃል::

12.6.3 በሰንበት ት/ት ቤቶች መካከል የሥነ ጽሑፍ አገልግሎቶች ልውውጥ እንዲኖር እገዛ ያደርጋል::

12.6.4 ሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ የመዝሙር አገልግሎቶች የሚሰጡበትን መጻሐፍት ያዘጋጃል::

12.6.5 አዳዲስ ለጉባዔው እድገትና መስፋፋት የሚረዱ ሥራዎች እንዲጠኑ ያደርጋል::

12.6.6 ከትምህርት ክፍል ጋር በመሆን ለአመታዊ ጉባኤ የሚያዘጋጀውን መጽሄት ሥራዎችን አሰባስቦ ያቀርባል።

12.6.6 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ ትምህርት ክፍል እና ለሊቀመንበሩ ይሆናል።

12.7 ልማትና ሽያጭ ክፍል

12.7.1 በአንድነት ጉባኤው የሚዘጋጁ መጽሔቶች፤ ቲ-ሸርት፤በማሰባሰብ በጠቅላላው ጉባኤላይ እንዲሸጡ ያደርጋል ፤ ገንዘቡንም

በማሰባሰብ ለሒሳብ ክፍሉ ያስረክባል::

12.7.2 የልማት ሥራዎችን በማቀድ ለጉባኤው ገቢ ማስገኛ ያፈላልጋል::

12.7.3 ለአመታዊ ጉባኤ ቲ-ሸርት ያዘጋጃል::

12.7.4 ጥምቀትን በመሳሰሉ በዓላት ላይ የአንድነት ጉባኤ ድንኳን በመከራየት የገቢ ማስገቢያ ምንጮችን ለሽያጭ ያቀርባል፤

በዚህ ስራ ላይ ሥራ አመራር ረዳት እንዲመድብለት ጥያቄ ማቅርብ ይችላል::

12.7.5 በየአመቱ በሚዘጋጁ ጠቅላላ ጉባኤያት ላይ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች በቪዲዮና በሲዲ ተቀርጽው ለአባላት እንዲዳዳረሱ

ያደርጋል::

12.7.6 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ ሂሳብ ክፍል እና ለሊቀመንበሩ ይሆናል።

12.8 ገንዘብ ያዥ 12.8.1 ከአባላት መዋጮ በየጊዜው ይሰበስባል::

12.8.2 ከልማትና ሽያጭ ክፍል እና ከተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅትም ሆነ ከግለሰብ ልገሳ የተሰበሰበውን ይረከባል፡ ይሰበስባል

12.8.3 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ ሂሳብ ክፍል እና ለሊቀመንበሩ ይሆናል።

Page 18: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

18

12.8 ቴክኖሎጂ ክፍል 12.9.1 ለአንድነት ጉባኤው ድህረ ገጽን ያዘጋጃል።

12.9.2 ከተለያዩ የአንድነት ጉባኤ አመራር ክፍሎች የሚመጡለትን የምስል ወይም የጹሑፍ ሰነዶችን በድህረ ገጹ ላይ

በየወቅቱ ያወጣል

12.9.3 የድህረ ገጹን እንቅስቃሴ እና እድሳት በበላይነት ይመራል።

12.9.4 በአመራር ክፍሉና በመምሪያ ሃላፊው ያልጸደቁ ማንኛውንም አይነት ሰነዶች ድህረ ገጹ ላይ ማውጣት አይችልም።

12.9.5 ተጠሪነቱ ለአንድነት ጉባኤ ሊቀመንበሩ ይሆናል።

አንቀጽ አስራ ሦስት የክልል የንዑሳን ኮሚቴ የስራ ድርሻ

የአንድነት ጉባኤ ንዑሳን ኮሚቴ አባላት ከመላው አሜሪካ እና ካናዳ ከተለያዩ ከተሞች ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚመረጡ ለአንድነት ጉባኤ ተወካዮች ናቸው። 13.1.1 የሰንበት ትምህርት ቤት የአንድነት ጉባኤ ተወካዮች በአካባቢያቸው ለሚደረጉ የአንድነት ጉባኤ እንቅስቃሴ ከተመደቡት የሥራ አመራር ተወካይ ጋር በመሆን በቅርብ ይሰራሉ። 13.1.2 ተጠሪነታቸው ለአንድነት ጉባኤ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው። 13.1.3 የአንድነት ጉባኤው እንደአስፈላጊነቱ ለስብሰባ በሚጠራቸው ግዜ በስብሰባ መገኝት ይጠበቅባቸዋል:: 13.1.4 ከሥራ አመራር ክፍል በተመደባላቸው ግለስብ አማካኝነት ወርሃዊም ሆነ አመታዊ ሪፖርት ያቀርባሉ:: 13.1.5 የአንድነት ጉባኤ የክልል ንዑሳን ኮሚቴ የሥራ ዘመናቸውን ከጨረሱ በሁዋላ ለሥራ አመራር ኮሚቴነት የመመረጥ መብት አላቸው።

አንቀጽ አሥራ አራት 14.1 የአንድነት ጉባኤን ንብረት በተመለከተ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ በተለያዩ ጊዜአት በማንኛውም አይነት መንገድ የሚያፈራው እና እያፈራቸው ያሉ ንብረቶች፤ንብረትነታቸው ሙሉ በሙሉ ለሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ነው።

አንቀጽ አስራ አምስት

15.1 ስብስባና የስብስባ ሂደት 15.1.1 አንድነት ጉባኤ የሥራ አመራር አባላት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የሚውጣጡ ሰለሚሆኑ በተቻላቸው ሁሉ በአካልና በስልክ እየተገናኙ ስራቸውን ይሰራሉ። 15.1.2 የሥራ አመራር ሊቀመንበሩ ዘወትር በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ እንደአስፈላጊነቱ የጉባኤውን የበላይ ጠባቂ ካህን

ማሳተፍ ይኖርበታል።

15.1.3 የሥራ አመራር አባላት ከጉባኤው ውጪ ከሆኑ አካላት ጋር የሥራ አመራሩ ኮሜቴን እንዲሁም መምሪያ ሃላፊን

ሳያውቀው ጉባኤውን በመወከል ማንኛውንም አይነት ስብሰባ ወይንም ግንኙነት ማድረግ አይችልም።

Page 19: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

19

15.1.4 የሥራ አመራር ስብሰባ እንዳስፈላጊነቱ በሊቀ መንበሩ ይጠራል ጥሪውም በጸሃፊው ይወጣል።

15.1.5 የስብሰባ ጥሪ ሰዓት፥ ቦታ፥ የቴሌ ኮንፍረንስ ቁጥር እና ኮድ እንዲሁም የስብሰባውን አጀንዳ በግልፅ ያሰፈረ መሆን

ይኖርበታል።

15.1.6 የሥራ አመራር ኮሚቴው በወር ሁለት ጊዜ ወይም እንዳስፈላጊነቱ በስልክ በመገናኘት በየክልሉ ያለውን የስራ ሂደት የንዑሣን

ኮሚቴዎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል እንደ አስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራል።

15.2 የስብሰባው ሂደት

15.2.1 ሊቀመንበር ወይንም ጽሐፊ ስብሰባውን ይመራሉ

15.2.2 የሥራ አመራሩ ጸሐፊ በማንኛውም ስብስባላይ የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ ይይዛል::

15.2.3 የስብሰባው ቃለ ጉባኤ የሚከተሉትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል የስብሰባውን ቀን፥ ዕለት፥ ሰዓት፥ ቦታ፥ አጀንዳዎች፥ አስተያየቶች

እና በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን አባላት በጥንቃቄ መያዝ ይኖርበታል።

15.2.4 ስብስባው በሥርዓተ ቤተክርስቲያን መሠረት በጸሎት ተጀምሮ በጸሎት ይዘጋል::

አንቀጽ አሥራ ስድሰት

16.1 የሥራ አመራር የአገልግሎት ዘመንና አመራረጥ

16.1 የአገልግሎት ዘመን 16.1.1 የአንድነት ጉባኤው የሥራ አመራር የአገልግሎት ዘመን ሁለት አመት ብቻ ነው:: (ሦስት አመት ቢሆን)

16.1.2 አንድነት ጉባኤው የሥራ አመራር አባላት በተከታታይ ለሁለት ጊዜ ብቻ ተመርጦ ሊያገለግለል ይችላል::

16.1.3 የንዑሣን ኮሚቴ የአገልግሎት ዘመን ሁለት አመት ብቻ ነው።

16.2 የሥራ አመራር አመራረጥ የአስመራጭ ኮሚቴ አመራረጥ

16.2.1 የመምሪያ ኃላፊው እንዳስፈላጊነቱ ከጉባኤው አመራር ጋር በመወያየት ከ3 ያልበለጡ አስመራጭ ኮሚቴን

ይመርጣሉ።

16.2.2 የተመረጡት አስመራጭ ኮሚቴዎች በሕዝብ ግንኙነቱ አማካኝነት ለአንድነት ጉባኤው አባላት እንዲተዋወቁ

ይደረጋል።

Page 20: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

20

16.3 የአስመራጭ ኮሚቴ የሥራ ድርሻ

16.3.1 አስመራጭ ኮሚቴው የድምጽ መስጫ የምርጫ ቅጾችን ለአንድነት ጉባኤ አባላት እንዲደርስ በማድረግ ጥቆማ

ይሰበስባል።

16.3.2 ጥቆማ የተደረገላቸውን በማነጋገር ከ15 ያልበለጡ እጩዎችን ያሳውቃል።

16.3.3 በድምጽ መስጫ ቅጹ መሰረት እያንዳንዱ እጩ ስንት ድምጽ እንደተሰጠው ይቆጥራል። ቆጠራው በሚካሄድበት

ሰአት ከአንድነት ጉባኤ ፈቃደኛ የሆነ/ች ተሳታፊ በገለልተኝነት ታዛቢ እንዲሆን ይደረጋል።

16.3.4 ቆጠራው ካለቀ በኋላ አስመራጭ ኮሚቴው እያንዳንዱ እጩ ስንት ድምጽ ከአባላት እንደደረሰው ለሙላተ ጉባኤ

ያሳውቃል።

16.3.5 የተመረጡ የሥራ አመራር አባላት ዝርዝር ለመምሪያ ሃላፊው ቀርቦ ሲጸድቅ ምርጫው የፀና ይሆናል።

16.4 የእጩነት መስፈርት

16.4.1 አንድ እጩ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር በሚተዳደር ቤተክርስትያን የሰንበት ት/ቤት አባል መሆን አለበት::

16.4.2 አንድ እጩ በክልላዊ ጉባኤ ላይ እና በአመታዊ ጉባኤ ላይ ቢያንስ ለ ሶስት ጊዜ የተሳተፈ መሆን አለበት::

16.4.3 አንድ እጩ ለአንድነት ጉባኤ የሚጠበቅበትን ግደታ መወጣት አለበት።

16.4.4 አንድ እጩ የአንድነት ጉባዔን መተዳደሪያ ደንብ መቀበል አለበት።

16.4.5 አንድ እጩ ሥራው ለሚጠይቀው ኃላፊነት በመታመን ኃላፊነቱን ለመወጣት ፈቃደኛ መሆን አለበት::

16.4.6 አንድ እጩ ከሚያገለግልበት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከሁለት የቤተ ክርስቲያን አባቶች የድጋፍ ደብዳቤ ያቀርባል::

አንቀጽ አሥራ ሰባት የአመራር ኮሚቴ አባልን ያለጊዜው መቀየር አስመልክቶ

17.1 አንድ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል በተለያየ ችግር ኅላፊነቱን ማከናወን ካልቻለ በጹሁፍ ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ለአንድነት

ጉባኤ ኮሚቴ ሊቀመንበር ግልባጭ ለመምሪያ ኃላፊ ማስገባት ይኖርበታል።

17.1.1 አንድ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል በተደጋጋሚ ስብሰባ የማይካፈል እና ሀላፊነቱን መወጣት ካልቻለ በቅድሚያ

ሊቀመንበሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ያናገረዋል። ችግሩ ካልተፈታ ግን ሥራው እንዳይበደል የሥራ አመራር ኮሚቴው ከመምሪያ

ኃላፊው ጋር በመሆን ጊዜአዊ ተጠባባቂ ቦታውን ሸፍኖ እንዲሰራ ይደረጋል። እንደ አስፈላጊነቱ የአንድነት ጉባኤ ሕዝብ

ግንኙነት የተለያዩ የመገናኛ ስልቶችን በመጠቀም ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጊዜአው ተጠባባቂ ሆኖ/ና የሚያገለግል ግለሰብ

ጥቆማ መሰብሰብ ይችላል።

Page 21: ሲኖዶስ - Andinet Gubae - Light to the worldandinetgubae.org/.../2013/06/UnityForumBylawlatestedit07272013.pdf · አገልግሎቶችና የትምህርተ ወንጌል ፕሮግራም

21

17.1.2 የአንድነት ጉባኤ ኮሚቴ ሊቀመንበር በተደጋጋሚ ስብሰባ የማይካፈል እና ሀላፊነቱን/ቷን መወጣት ካልቻለ በቅድሚያ

መምሪያ ኃላፊው ጉዳዩን አስመልክቶ ያናገረዋል። ችግሩ ካልተፈታ ግን ሥራው እንዳይበደል በመምሪያ ኃላፊው አማካኝነት

የሥራ አመራር ኮሚቴው ጸሐፊ የሊቀመንበሩን ቦታ ተክቶ እንዲሰራ ያደርጋል። የጸሐፊውን ቦታ ለመሸፈን የሥራ አመራር

ኮሚቴው ከመምሪያ ኃላፊው ጋር በመሆን ጊዜአዊ ተጠባባቂ ቦታውን ሸፍኖ እንዲሰራ ይደረጋል።

አንቀጽ አሥራ ስምንት

18.1 ደንቡ ስለሚጸናበት ግዜና ደንቡን ስለማሻሻል

18.1.1 ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ወደፊት እየታየ የአንድነት ጉባኤውን እድገት በሚያቅፍ መልኩ የማሻሻያ ነጥቦችን አመራር

ኮሚቴው ተወያይቶበት እና በጉባኤው ከታቀፉት ሰንበት ተማሪዎች አስተያየት የጊዜ ገደብ ባለው መልኩ ከተሰበሰበ

በውሀላ ለመምሪያ ኃላፊው በጹሁፍ ያቀርባል። መምርያ ኃላፊውም አርሞ ለጠቅላይ ቤተክነት እንዲጸድቅ ይመራዋል።

18.1.2 ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ጠቅላይ ቤተክህነት አርሞት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

ማጠቃላያ

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች

አንድነት ጉባዔ ከቅዱስ ሲኖዶስ በሚመደብለት ከመምሪያ ሃላፊ ጋር በመሆን ከላይ የጠቀሳቸው ዓላማዎቹን

ተግባራዊ ለማድረግ ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሙሉ ተሳትፎ ይጠበቃል።

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ የምትገኙ

ቤተክርስቲያናት አስተዳዳሪ ካህናት፤እንዲሁም የሰበካ ጉባኤ/ቦርድ/ አባላት ይህ የሰንበት ት/ት ቤቶች

አንድነት ጉባኤ ካላይ የጠቀሳቸውን ተግባራት ለማከናውን ይረዳ ዘንድ በሚያስፈልጋቸው ሁሉ

ትተባብሩ ዘንድ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ስም እንጠይቃለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በሕጋዊው የ.ኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰሜን አሜሪካ ሰ/ት ቤቶች አንድነት ጉባኤ።


Recommended