+ All Categories
Home > Documents > 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC...

30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC...

Date post: 20-Mar-2020
Category:
Upload: others
View: 6 times
Download: 0 times
Share this document with a friend
24
FREE Bawza Newspaper is a Monthly Publication of the Ethiopian Yellow Pages 30/02/2008 የኑሮዎ ብርሃን” “በቅርቡ የልጅ አባት እሆናለሁ” ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና የክራሩ አባት” አርቲስት መላኩ ገላው KIDS www.bawza.com www.bawza.com The Gelada baboon was discovered in 1835 by the ex- plorer Ruppell, who named it by the local name used by the inhabitants of Gonder region where he first observed it. Geladas are found only in Ethiopian high- lands, with large population in the semien mountains ranging from 3,000 - 4,543 meters mountain heights. The social behaviour of the apes and monkeys is evi- dence of a very high degree of intelligence and studies of their rudimentary social structures are proving of considerable value in analysing the origins of human social behaviour. Geladas live along the edges and steep slopes of preci- pices. They never move far from the rim and thus their distribution is linear along the escarpment. At night they climb down the steep cliff faces to caves where they roost on ledges, often huddled close together for warmth as Semyen nights are frosty and bitterly cold. Babies cling tight to their mothers even in sleep. In the morning in the warm sun they climb up again to the top of the cliff and spread out to feed. Geladas are mainly vegetarian, living on herbs, grasses and roots, but they also eat insects and locusts. They never eat meat, or hunt or kill even small birds or mammals. As a result of this restricted diet they are obliged to spend a very high percentage of their lives foraging and browsing in order to obtain sufficient nutrients to survive. This may explain why they are so extremely peaceable by nature, with very little squabbling even amongst themselves. “65ሺ እስኴር ፉት ስፋት ላይ ያረፈው መዋእለ ህፅናት” ቴስቲ ኣምዳዬ በመኪና፣ በስራና በስፖርት ምክኒያት ለሚደርስባችሁ ጉዳቶች ያነጋግሩን ገጽ 5 ገጽ 7 ገጽ 2 ገጽ 2-3 በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ጭላዳ ዝንጀሮ የካቲት 22 ቀን 2000
Transcript
Page 1: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ �

FREEBawza Newspaper is a Monthly Publication of the Ethiopian Yellow Pages 30/02/2008

“የኑሮዎ ብርሃን”

“በቅርቡ የልጅ አባት እሆናለሁ” ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ

ETHIOPIA’S ENDEMICWILDLIFE The Gelada Baboon

“የዋሽንቱናየክራሩ አባት”

አርቲስት

መላኩገላው

KIDS www.bawza.com

www.bawza.com

The Gelada baboon was discovered in 1835 by the ex-plorer Ruppell, who named it by the local name used by the inhabitants of Gonder region where he first observed it. Geladas are found only in Ethiopian high-lands, with large population in the semien mountains ranging from 3,000 - 4,543 meters mountain heights.The social behaviour of the apes and monkeys is evi-dence of a very high degree of intelligence and studies of their rudimentary social structures are proving of considerable value in analysing the origins of human social behaviour.Geladas live along the edges and steep slopes of preci-pices. They never move far from the rim and thus their distribution is linear along the escarpment. At night they climb down the steep cliff faces to caves where they roost on ledges, often huddled close together for warmth as Semyen nights are frosty and bitterly cold. Babies cling tight to their mothers even in sleep. In the morning in the warm sun they climb up again to the top of the cliff and spread out to feed. Geladas are mainly vegetarian, living on herbs, grasses and roots, but they also eat insects and locusts. They never eat meat, or hunt or kill even small birds or mammals. As a result of this restricted diet they are obliged to spend a very high percentage of their lives foraging and browsing in order to obtain sufficient nutrients to survive. This may explain why they are so extremely peaceable by nature, with very little squabbling even amongst themselves.

“65ሺ እስኴር ፉት ስፋት ላይ ያረፈው መዋእለ ህፅናት” ቴስቲ ኣምዳዬ

በመኪና፣ በስራና በስፖርት ምክኒያት ለሚደርስባችሁ ጉዳቶች ያነጋግሩን

ገጽ 5

ገጽ 7

ገጽ 2

ገጽ �2-�3

በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ጭላዳ ዝንጀሮ

የካቲት 22 ቀን 2000

Page 2: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ 2ገጽ 2

ቤተሰብ www.bawza.com

ምንም እንኳን የፊደል ትምህርታቸውን ስድስተኛ ክልፍ ላይ ያቆሙ ቢሆንም በያሬድ ት/ቤት የባህላዊ ሙዚቃ የመጀመሪያው አስተማሪ በመሆን ለ28 ዓመት እነ አርቲስት ስለሺ ደምሴን (ጋሽ አበራ ሞላ) ጨምሮ በርካታና አንጋፋ አርቲስቶችን በማፍራት ለዘርፉ ዕድገት ትልቅና ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት አርቲስቶች መሃል አንጋፋው ናቸው።

ይህንኑ ሞያቸውን ከሃገራቸው አልፎ በብዙ ሃገራት ለዓብነትም ያህል ከብዙ በጥቂቱ በግሪክ ፡በስፔን ፡ በየጉዝላቪያ፡ ቤልጄም ፡ በወቅቱ ምስራቅና ምዕራብ ጀርመን ፡በፈረንሳይ፡ በእንግሊዝ ፡ በጣሊያን ፡ በኮሪያ ፡ በኢራን ፡ በግብፅና በመሳሰሉት አገሮች ከፍተኛ አድናቆትን በማፍረስ የሃገራቸውን ባሕል አስተዋውቀዋል።

«በአንድ ወቅት በጣም ቆንጆ ሱፍ ለብሰው በሚያስተምሩበት ሰዓት አንዱ ተማሪያቸው በጣም

እየረበሻቸው ስላስቸገራቸው ውጣ ብለው ያስወጡታል ። ወዲያው ያስወጡት ተማሪ የክፍል ጓደኛው የሆነች ሴት ተማሪያቸው የምታኝከውን ማስቲካ ካፏ ውስጥ ታወጣና ኮታቸው ላይ ወርውራ ትለጥፍባቸዋለች። በኋላም ተማሪዎች እየሳቁባቸው አስተምረው እንደ ጨረሱ ወደ ቤት በሚሔዱበት ሰዓት ያው ተማሪ አራት ድንጋዮችን ሁለቱን በሁለቱ ኪሶቹ ይዞ ይከተላቸዋል ። እግዚአብሔር ሲያተርፋቸው ሁለት ፖሊሶች ከፊት ለፊታቸው ስለመጡ ለፖሊሶቹ ነግረው አስጠርተው አንድ ካልቾ ቀምሶ ይሔዳል ። እግዚአብሔር ብሎ ፖሊሶቹ ባይመጡና በያዘው ድንጋይ ቢመታቸው ኖሮ እሳቸውም መሳሪያ ይዘው ስለነበር እኔንም አሳስቶኝ ነበር ይላሉ ። ይህንኑ ተማሪያቸውን እዚሁ አሜሪካም ከመጡ በኋላ ያገኙታል ። በአሁኑ ሰአት እሱ ከኔ ብሶ ተመልጧል ብለው እየሳቁ አጫውተውኗል። አርቲስት መላኩ ገላው በ �929 ዓ.ም ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከአባታቸው አቶ ገላው ወልዳ ተክሌና ከእናታቸው ወ/ሮ ትኩነሽ ተሰማ ለአምስት አመት በአርበኝነት በጎንደር ክፍለ ሃገር ፈርጣ አውራጃ መሃል ደብረ ሲና ማርያም የሚባለው ዋሻ እንደቤታቸው አርገው በሚኖሩበት ወቅት ነው የተወለዱት። ጣሊያን እስኪባረር ድረስ በዛው በዋሻ ውስጥ ዳዴና ወፌ ቆመች እየተባሉ በዚያው ደብረ ሲና ማርያም ቤተክርስትያን ነበር ክርስትና የተነሱት። ጣሊያን ከተባረረም በኋላ አባታቸው በሹመት የቀኝ አዝማች አጥናፍ ፀሐፊ በመሆን ወደ ጎንደር ክፍለ ሃገር ጃናሞራ ወረዳ ሲዛወሩ ከእናታቸው ጋር ዳቦት አራደጀን ጎርጊስ ፈደል ይቆጥራሉ ። የፊደል ትምህርታቸውን እንደጨረሱም ወደ አባታቸው ጋር በመሔድ ደጃዝማች ውቤ ባሰሯት በደረስኬ ማርያም ቤተክርስትያን ዳዊትን ጨምሮ የፀሎት ትምህርታቸውን በ �3ዓመታቸው አካባቢ ይጨርሳሉ። በኋላም አባታቸው የመንግስት ስራ የሚባል አልፈልግም አገሬ ገብቼ የአባቴን መሬት እያረስኩ እኖራለሁ ብለው ወደ ትውልድ ሃገራቸው ላስታ ሲወስዷቸው በነበራቸው ከፍተኛ የመማር ፍላጎትና ስላልተመቻቸው ወደ ሰቆጣ ይጠፋሉ። በሰቆጣም የጣሊያን ካምፕ በነበረበት ቤት ውስጥ አዳጋ ት/ቤት አንደኛ ክፍል ሲያስገቧቸው ይሔ ልጅ ለአንደኛ ክፍል አይሆንም አልፎታል ስለተባለ ደብል በመምታት ወደ ሶስተኛ ክልፍ ገብተው ከተማሩ በኋላ ተመልሰው በአባታቸው ሃገር ወደ ሰቆጣ አውራጃ በግና ውስጥ

የአጥቢያ ዳኛ ፀሐፊ በመሆን ይሰሩም ነበር። እንዲህ እንዲህ እያሉ ከትምህርትና ከስራቸው ጎን ለጎን ሚዳቆ በድንጋይ ገድለው በቆዳዋ ክራር እየሰሩ ዋሽንትም ከሸንበቆ እየሰሩ ይጫወቱ ነበር። በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ ሊበላሽ ነው (ሽፍታ ሊሆን ነው) እየተባሉ በአባታቸው ከአንድም ሶስት አራቴ ዋሽንትና ክራራቸው ተሰብሮባቸዋል ። በዚህ ወቅት ትልቁ ጉጉታቸው አዲስ አበባ ገብቶ መማር ነበር። አስራ ምስትና አስራአ ስድስት ዓመት እየሆናቸውም ስለመጣ አንዳንዴ የልብ ልብ ስሜት ይሰማቸው ስለነበር እንደገና አንዷ የእናታቸው ዘመድ ጋር ይሔዱና ለስደስት ዓመት ተቀምጠው ተመችቶአቸው በሚኖሩበት ሰዓት ልክ እንደሳቸው ዘመድ ብላ ከመጣች በጣም ከትልቃቸው ጋር ሌላ ነገር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ወንድ ልጅ ይወለዳሉ። ወዲያው እፍረትም አለ ከየጁ ተነስተው አዲስ አበባ ወንድማቸው ጋር ይመጣሉ ። የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ወንድማቸው አርሞኒካ ይጫወት ስለነበር ዋሽንታቸውን ከአርሞሪካው ቅኝት ጋር እየለወጡ ይጫወቱ ነበር ። በዚህ ላይ አዲስ አበባ ለአርቲስት መላኩ ገላው እጇን ዘርግታ አልተቀበለቻቸውም። ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ስራቸውን እየሰሩ ዋሽንት በሚጫወቱበት ወቅት የብዙ ሰዎችን ቀልብ ስለሳቡ ሰው ሁሉ እየወደዳቸው መጣ። በተለይ በዛን ወቅት የነ ጥላሁን ገሠሠ ዘፈን ምድር ቁና እስክትሆን ድረስ ይወድዱ ነበር። የአዲስ አበባ ስቴዲየም ይሰራ የነበረው በጥርብ እንጨት ነበር። ግንቡ ስር የተለያዩ የቤት ፍርስራሾችን ከሚሸጡት ነጋዴዎች መሃል ሸንበቆ የሚሸጡም ነበሩ። በዚህ ወቅት ሁለቱን ሸክም በሁለት ብር ገዝተው ቆሎና ዋሽንት እየዞረ ከሚሸጠው ጓደኛቸው «ተገኝ » ጋር እየሸጡ ይተዳደሩም ነበር። እዛው እነሱ ሰፈር ክራር እየቆረቆረ ከሚሸጥ ሰው በጣም ቆንጆ ክራር በአራት ሽልንግ አሰርተው ከነ ከበደ ወልደ ማርያም ( ከብዬ ) ማሞ ደምሴ በተለይ በወቅቱ እጅግ በጣም ጎበዝ የነበረው ገዛህኝ አየለ ጋር የሚወዱትን መጠጥ እየገዙለት ብዙ ነገር እያሳያቸው ይማሩ ነበር። ገዛህኝ አየለ የሚሉት በጀርመን ራድዮ ብቻ የሚተላለፍ “ በይ ነይ በለው በለው “ የምትል ዘፈን ብቻ ናት እስካሁን ድረስ ያስቀረፅው ከጉብዝው የተነሳ በእርሳስ ትዝታን ይጫወት ነበር። ሌሎች ግን ክራራቸውን አያስነኩኝም ነበር » ይላሉ ። በኋላም ሙያውን እጅግ እየተካኑት በሚመጡበት ወቅት በ �956 ዓ.ም ኦርኬስትራ ኢትዮጵያም ይቋቋማል ። እዛም ውስጥ በጣም በጥሩ ሁኔታ ክራራቸውን እያነገቱ ከዚህ በተጨማሪ ወደ ሰበታ አርብ ማታ ሔደው 2� ብር አካባቢ እየተከፈላቸው ማየት የተሳናቸውን ያስተምሩ ነበር።

በወቅቱ የያሬድ ሙዚቃ ቤት መስራች ዶ/ር አሸናፊም ሰበታ ለሚገኙት ማየት ለተሳናቸው ተማሪዎች ፒያኖ ያስተምራቸው ስለነበር። ጠራቸውና” አቶ መላኩ እዚህ የሚከፈልህ 2� ብር እንደሆነ አውቃለሁ። ለምን ቅዳሜ ቅዳሜ የኔን ተማሪዎችም አታስተምርልኝም ? እኔም 2� ብር እከፍልሃለው” አላቸውና ተስማምተው እዚያም እንደዚሁ ማስተማር ጀመሩ። በኋላም ስራቸው በጣም ጥሩ ስለነበር ለምን አንቀጥርህም ይባላሉ። ጥሩ እንግዲህ ከቀጠራችሁኝ �50ብር ትከፍሉኛላችሁ? አሉ። ዶ/ር አሸናፊም ማመልከቻ አስገባ ብለዋቸው ሰኞ ማመልከቻ እንዳስገቡ አርብ እንኳን ደስ ያለህ ተፍቅዶልሃል ተባሉ ። በወቅቱ �50 ብር ማለት ቀላል አልነበረም። በ �2 ብር መቶ ኪሎ የአዳ ማኛ ጤፍ ይሸጣል ። አተርና ባቄላም እንደዚሁ በ 7 ብር ይሸጣል ። ይህን ሁሉ ያደርጉና በል እንግዲህ ስራህን ቀጥል ይባላሉ። ከዚህ በኋላ ነው እንግዴህ ዓመት ሳይሞላቸው ኢትዮጵያን እየወከሉ በተለያዩ የአለም ሃገሮች ባህላችንን ማሳየት የጀመሩት እኝህን የሚያክል የሃገር ሃብት ከሃገራቸው ወጥተው በአሜሪካ መኖር ከጀመሩ ��ዓመት እያለፋቸው ነው ።በአሁኑ ሰአት አይናቸው በሞራ ተሸፍኖ እቤት ከዋሉ 3 ወር ሆኗቸዋል ። አይኔን የምታከመው ሃገሬ ገብቼ ነው ቢጠፋም እዚያው በሃገሬ ሰዎች ያጥፉት እንጂ እነዚህማ ቀኝ አይኔን መለማመጃ አድርገው አጥፍተውታል ይላሉ። እኛም ለመሔድ እየተሰናዱ ሳሉ ነበር ከሳቸው ጋር ቆይታ ያደረግነው ። አሜሪካ ለምንና እንዴት መጡ ? የሚሉትን ጥያቄዎችና ተወርቶ የማያልቀውን የህይወት ልምዳቸውን በቀጣይ በምናወጣቸው እትሞች በስፋት እናቀርብላችኋለን። እስከ ወር መልካሙን ይግጠመን።

“አርቲስት መላኩ ገላው “በአሜሪካ”በኤልያስ እሸቱ

Page 3: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ 2 Volume 1, Issue 2 ገጽ 3ገጽ 2

ርዕሰ ዓንቀፅ www.bawza.com

መቼም ይብዛም ይነስም ከጥቂቶቻችን በስተቀር የአብዛኛዎቻችን ወላጆች ሳይማሩ አስተምረውናል። ብዙ አመት አፈር ገፍተው ብዙ ችግር ፤ ረሃብ ፡ መከራና የመሳሰሉትን ነገሮች አሳልፈው የፊደልን ገበታ አስቆጥረውናል። በባህሪያችንም በኩል ቢሆን በጥሩ ስነ ምግባርና በፈሪሃ እግዚያብሄርም ጭምር አንፀው አሳድገውን ኢትዮጵያኖች የሚለውን ስም ጠብቀው አስረክበውናል። እኛም በባዶ እግራችን አቀበቱንና ቁልቁለቱን እየወጣንና እየወረድን እሩቅም መንገድ እየሔድን በየሰፈርና መንደሩ ውስጥ ባሉ ቄስና የቆሎ ትምህርት ቤቶች በየዋርካው ስርና በመሳሰሉት ቦታዎች መሬት ላይ ብርድና ቁር እየተፈራረቀብን እልህ አስጨራሹን የገጠርና የከተማውን ህይወት ተቋቁመን የህል ውሃችን ነገር ሆኖ ብዙዎቻችን በችግርና ረሃብ እንዲሁም ጥቂቶቻችን በፖለቲካና በትምህርት አሁን አሁን ደግሞ አብዛኛዎቻችን በዲቪና በመሳሰሉት ነገሮች የሃገራችንን ምድር ለቀን ኑሮአችንን በዚህ በአሜሪካ የመሰረትን ሰዎች ቁጥራችን እጅግ እየበዛ መጥቷል።አንዳንዶቻችን እንደውም ሶስትና አራት አስርት አመታት ያሳልፈን ሰዎች አንጠፋም።

ብዙውን ጊዜ እኛ ኢትዮጵያውያን ስማችን በጠንካራ ሰራተኛነታችና በጥሩ ስነ ምግባራችን በዚህም በአሜሪካም ቢሆን ተመስክሮልናል። እንደውም በሁሉም የቢዝነስ ዘርፍ ውስጥ በመሰማራት ብርቱና አኩሪ ዜጎች መሆናችን ን እያሳየን ነው። ለዚህ ሁሉ ትልቁን ሚና የተጫወቱት ከላይ የጠቀስናቸው ወላጆቻችን መሆናቸው አይዘነጋም።መቼም የሰው ልጅ ተፈጥሮ በሃሪዎች ውስጥ መወለድና መውለድ ፡ ዘር ተክቶ ማለፍ አንዱ ነው። ዛሬ ላይ ደርሰን በዚሁ በአሜሪካ ከአያትም አልፈው ቅድመ አያት የሆኑ ዕድለኞችንም እያስተዋልናቸው ነው።

ድሮ ድሮ አንድ አበሻ ከሌላ አበሻ ጋር ሲገናኝ የስጋ ዘመድ ያህል እንደ ብርቅ እየተያየን ሰላምታ የመለዋወጥንና የተለያዩ ነገሮችን አብሮ የመብላት ፤ የመስራቱና የመረዳዳቱ ባህላችን እንደተጠበቀ ነበር። አሁን ግን ቁጥራችን ከእለት እለት እጅግ እየበዛ ስለመጣ ይሆናል በተለይ በዲሲ ዙሪያ በአንድ ባስ ውስጥ እንኳን ከ 5 እስከ �0 አበሾችን አናጣም። እንደውም ባሱ ውስጥ አማርኛ ብቻ ሲወራ እንዴ! አዲስ አበባ ነው ወይስ አሜሪካ ነው ያለሁት በማለት ብዙዎቻችን ሳንገረም የቀረንም አልመስለንም። ከሁሉም በላይ እንዴት ዋልክ… እንዴት ዋልሽ… ሰላም… ሰላም… መባባላችን እጅግ የሚያኮራ ባህላችን ሆኖ ሳለ አይተን እንዳላየን ሰምተን እዳልሰማን ስንመስል ያሳፍራል። ሌላው በእረፍት ጊዜያቶቻችን በየአብያተ ክርስትያኑ እና በተለያዩ የራሳችን መመገቢያና ግሮሰሪዎች በጋራ ከልጆቻችን ጋር ሆነን ስናሳልፍ ፡ ልጆቻችን ሲቦርቁና ሲጫውቱ ማየቱ አንዳንዴ ዳግማዊት ኢትዮጵያን በአሜሪካ ምድር እንደፈጠረን ያህል ይሰማናል። እንደሚታወቀው ጊዜ ቆሞ እንደማይጠብቀን

ሁሉ እኛም ትልልቆቹ ዕድሜያችን ከዕለት እለት እየገፋ መምጣቱን መዘንጋት የለብንም። ልጆቻችንም የእኛን ቦታ እየተረከቡ ከአገሩም ከእኛም ጥሩ ትምህርት ቀስመው ብረት በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የኛም ልጆች በጥሩ ስነምግባር የተፈተኑ ዜጎች ሆነው ማህበረሰባቸውን የሚገነቡ ለዘር ግንዳቸው መሠረት ለሆነቸው ለአገራቸው ጠቃሚ ዜጎች እንዲሆኑ ከስር ጀምረን ስለ ውሏቸውና ስለ አስተዳደጋቸው አቅማችን በቻለ መጠን የትውልድ ተተኪ እንዲሆኑ የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ይጠበቅብናል። « ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም» ፡ «ልጅ ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም »የሚባሉት አባባሎቻችንና የልጆች አስተዳደጋችን ላይ ልጆች በራሳቸው እንዳይተማመኑ ፤ አርቀው እንዳያስቡና እንዳይመራመሩ ሲያደርጋቸው በራሳችን አስተዳደግ አስተውለነዋል። ልጆቻችንን ከዘመኑ ጋር በጥሩ ስነ ምግባር ማራመድ ይጠበቅብናል። ዛሬ በአሜሪካ ቁጥራችን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን እንደምንኖር ይገመታል።

“50ሎሚ ለ አንድ ሰው ሽክሙ ለ 50 ሰው ግን ጌጡ ነው” እንደሚባለው ሁሉ ሁሉም ወላጆች ለልጆጃቸው ፍሬ ማፍራት የበኩላቸውን ሲወጡ እንጂ አንድ ወላጅ ለራሱ ልጅ ብቻ ብዙ ቢለፋ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት አይቻልም። አሁን አሁን በልጆቻችን ባህሪ ላይ በጉልህ የምናስተውላቸው ነገሮች እየተከሰቱ ናቸው። በሌሎች ዜግች ላይ የምንጠላቸው ባህሪዎች በገዛ ልጆቻችን ላይ ሲከሰቱ በጣም ያሳፍራል። በተለያዩ አደንዛዥ ዕፅና መሰል ነገሮች ውስጥ ሲገቡና በፖሊስ ተይዘው የእስር ቤት ህይወትን ሲጋሩ፤ መቼም የእስር ቤትም አይነት አለው ከባህልም ከአስተዳደግም አንፃር አፅያፊና ጭንቅላታቸው ከሚቀበለው በላይ ባለመዱት ነገር ሞራላችው ላሽቆ በየአስፋልቱና በየሬስቶራንቶች በሮች ላይ ያለ ስራ ስናስተውላቸው እጅግ ያሳዝናል። «ከአንጀት ካለቀሱ እንባ አይገደንም »አይደል ያገሬ ሰው የሚለው? እናም ወገን እንኳን ለልጆቻችን ጥሩ ስብዕና ለትውልድ አኩሪ ዜጎች እንዲሆኑ የምናደርገው ጥረት ይቅርና ለሌላስ ቢሆን ምን ሊገደን!

ለልጆቻችን ልክ እንደ ሌሎች አገር ልጆች የካቶሊኮች ት/ቤት እና ሌሎችም እንደሚባለው ሁሉ የኢትዮጵያኖች ት/ቤት እንዲሁም መዋያና መዝናኛ ቤቶች በሚል የራሳቸውን ቋንቋቸውን ፡ ባህላቸውንና ኢትዮጵያዊነት ስብህናቸውን ጭምር ሳይለቁ የሚማሩበትና የሚውሉበት ቦታዎችን ሌላው ቀርቶ መሠረት እንኳን ብንጥልላቸው ራሳቸው ተረክበውን ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚያደርሱን ተስፋ አለኝ ። ባውዛ ጋዜጣም በዚሁ ምክንያት ለልጆች ብሎ ያዘጋጀውን አምድ ከአንድ ገፅ ወደ ሁለት ገፅ በማሳደግ ልጆች እርስ በርሳቸው እንዲማሩ ፡ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስተምሯቸውና ተሳታፊዎችም እንዲያደርጓቸው ጥሪውን ያቀርባል።

ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸውን ተተኪዎች እንፍጠር አስተያየቶቻችሁ

አሁን ገና ጥሩ ጋዜጣ ማየት ቻልን።ባውዛዎች በሁሉ ነገራችሁ በጣም አርክታችሁኛል። በዚሁ ቀጥሉ በጣም ጥሩ ስራ ነው። በዚህ ጅምራችሁ ከናንተ ብዙ ነገር ነው የምንጠብቀው ። በተለይ ለእናቴ ልጆች ወይ አሜሪካ በሚለው ስር የተፃፈው እውነተኛ ታሪክ ብዙ ጠቃሚ ምክሮችን ቀስሜበታለሁ ። በርካታ ወገኖቻችን ብዙ ነገሮችን ማስተማር ይቻላል። አቶ ሰለሞን አያሌው ከቨርጂኒያ ።

አጠር አጠር ያሉ ቀልዶች ይብዙልን ።

ይድረስ ለባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አጠር አጠር ያሉት ቀልዶችና አባባሎች በጣም አስቀውናል። በርከት ብታደርጓቸው በጣም እንወዳችኋለን። ወጣት አንተነህ ማሙሽ ከዲሲ ።

ከድምፃዊ ነዋይ ደበበ ብዙ አዳዲስ ስራዎችን እንጠብቃለን ።

ድምፃዊ ነዋይ ደበበ ኢንተርቪውን በጣም ደስ እያለኝ አንብቤዋለሁ። ስለሱ በውስጤ የነበሩኝን ጥያቄዎች በከፊል ተመልሶልኛል። ድምፃዊ ነዋይ ደበበ በጣም የምንወደውና የምናከበረው ሃብታችን ነው እግዚአብሔር የሚያስበውን ሁሉ እንዲያመቻችለት ምኞታችን ነው። አቶ ታምሩ ፅጌ ከሜሪላንድ ።

በእማሆይ ቅመሟ ኃይሌ በጣም ተገርሜያለሁ ።

እማሆይ ለዚህ ሃገር በጣም ብርቅዬ እናታችን ናቸው። ዋው በጣም ገርሞኛል። እዚህ አገር ላለነው ለሁላችንም በፀሎታቸው እንዲያስቡን አደራ እላለሁ። ለምለም ተሻለ ከሜሪላንድ ።

የወ/ሮ ዘነበችና የአ/ቶ ገብረሃና ታሪክ በጣም አስተምሮኛል ።

በእውነት ሁላችንም ብንሆን አንድ ነገር ላይ ረግተን የምንፍጨረጨር ብንሆን ይሔኔ ትልቅ ድረጃ ላይ መድረስ እንችል ነበር። ሰው ከጣረና ከለፋ የሚፈልግበት ቦታ ላይ መድረስ እንደሚችል ምሳሌ

ሆናችሁኛል። በጣም እናከብራችኋለን ። ወ/ሮ አለምነሽ ከነቤተስቧ ከሜሪላንድ ።

ብታስተካክሏቸው።ስራዎቻችሁ በጥቅሉ ቆንጆዎች ናቸው። አንዳንድ የአማርኛ ቃላቶቻችሁ ላይ ትክክለኛውን ቃላቶች ብታስገቡ እንዲሁም ከጤና ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፅሁፎችን ብታክሉበት ጋዜጣችሁ የበለጠ ተወዳችነትን ያተርፋል ። ዲያቆን ዳዊት ተካልኝ ከዲሲ ።

ስለ አዲስ አበባ የተለያዩ ወሬዎችን ብታስገቡ ።ብዙ ጊዜ የዚህ ሃገር ሰው ስለሃገሩ ማንኛውንም ነገሮች ለመስማት ጆሮው ክፍት ነው። በተለይ በስፖርት ገፃችሁ ላይ የአፍሪካን ዋንጫንና አንዳንድ ስለ ፕሪሚየርሊጉ የተለያዩ መረጃዎችን ብትሰጡን ። አቶ ሙሉጌታ ኣጠንክር ከዲሲ።

ክብሩና የባውዛ አንባቢዎች ለተሳትፎዋችሁ እጅግ እያመሰገንን የሁሉንም ሰዎች አስተያየት ከቦታ ጥበት ምክንያት ለማስተናገድ ስላልቻልን የተወሰኑ ተሳታፊዎቻችንን ስሞች ዘርዝረናል።

በዓመቱ መጨረሻ ላይ ለሁል ጊዜተሳታፊዎቻችን ለየት ያለ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል። ተሳትፏችሁ አይለየን። ከዲሲ።አግዚ ልዑልሔዋን ታምሩ።አስረስ አለማየሁ ።

ከሜሪላንድ።ያሬድ አማረ።እጅጋየሁ አበበ።ማርታ ጥላሁን ።በላቸው ደገፋ።

ቨርጂንያ ኤልሻዳይ ምትኩ በለጠች ነገራ ሚሚ ትንሳኤ።አሸናፊ ሰለሞን ።

ዝግጅት ክፍሉ

Publisher - Feker Inc.Editor-In-Chief - Yehunie BelayExecutive Editor - Elias EshetuManaging Director - Makonnen TesfayeAssitant managing Editor -Henok TesfayeAssitant managing Editor for Kids section- Feker BelayGraphic Design - Araya AlemuLayout & Graphic Design - Yonathan Bekele

Bawza Newspaper1924 9th St. NW

Washington DC, 20001Tel:202-387-9322/202 387 9302/03

Fax: 202 387 9301www.bawza.com

Bawza Newspaper is a publication ofThe Ethiopian Yellow Pages

Page 4: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

(202) 460 3�95

Page 5: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ 5

ንግድ www.bawza.com

ውልደቷና እድገቷ በድሬድዋ ግሪክ ካምፕ ውስጥ ነው። ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል አባድር በሚባል የሙስልሊሞች ት/ቤት ተምራ እስከ ስምንተኛ ክፍል ደግሞ በሉተርዳም ት/ቤት ቀጥላለች።

የሃገሯን ምድር ገና በአስራዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው የለቀቀችው ።በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ለሁለት ዓመት የተለያዩ ቋንቋዎችን እየተማረች ቆይታ በአስራአራት ዓመቷ አሜሪካ የመግባት እድል አግኝታለች ።

በአሁኑ ሰአት አሜሪካ ከመጣች ሃያ ዓመት እያለፋት ነው። እንደማንኛውም ከሃገራቸው እንደሚሰደዱ ሰዎች እየተማረችና እየሰራች እንደውም በአንድ ወቅት ላይ ኑሮን ለማሽነፍ ከኮሌጅ ትምህርቷን አቋርጣ በሰአት ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም እየተከፈላት ትሰራ ነበር ።

አምስት ህጻናትን በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ በመጠበቅና በመንከባከብ ጀምራ በአሁኑ ሰአት ከእህቶቿ ጋር በመሆን ስልሳ አምስት ሺ እስኩዌር ፉት ስፋት ያለው መሬት ላይ ያማረና ሰፊ ዴይ ኬር <መዋለ ሕጻናት> ከፍታ ለሰባአንድ ሕጻናት አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለ ቴስቲ ሃምዳዬ።ከቴስቲ ጋር ብዙ ቁምነገሮችን አውግተናል ወደ ወጋችን።

ባውዛ መጀመሪያ አሜሪካ ስትመጪ ማን ጋር አረፍሽ? ከማንስ ጋር መጣሽ?

ቴስቲ ከእናቴና ከእህቴ ጋር ነበር የጣሁት። በወቅቱ ብዙ ዘመድ ስላልነበረን የታላቅ እህቴ ወንድም ጋር ነበር የምኖረው። ባውዛ ምን ትሰሪ ነበር?

ቴስቲ ህጻፃን ስለነበርኩ ቀጥታ ወደ ት/ቤት ነው የገባሁት።

ባውዛ የት ት/ቤት ቀጠልሽ?

ቴስቲ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ዌስካንሰን አቬኑ ላይ ያለው ውድሮዊልሰን ት/ቤት ገብቼ ተማርኩ። እስከ አስራሁለተኛ ክፍል ጨርሼ የሃይስኩል ዲፕሎማዬን ወሰድኩ።በኋላም ሞንትጎሞሪ ኮሌጅ ግብቼ ለአንድ አመት አካባቢ እንደተማርኩ ሳልጨርስ አቋርጬ ስራ መስራት ጀመርኩ። ያው እስካሁን ድረስ እየሰራሁ ነው። (ሳቅ)

ባውዛ በመጀመሪያ ስራ ስትጀምሪ የትና በምን አይነት ይስራ ዘርፍ ላይ ነው የተሰማራሽው?ቴስቲ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ መካርተር ግሎቫድ የሚባል የፊልም ቤት ውስጥ ለአምስት አመት በአሲስታንት ማናጀርንትእሰራ ነበር። ባውዛ አከፋፈላቸው ምን ይመስላል።? እድገትስ ነበረው።?

ቴስቲ በሁለት ሳምንት አንዴ ታክስና ሌሎች የተለያዩ ነገሮች እየተቆረጡ 650 ዶላር ነበር የሚደርሰኝ። በመጀመሪያ ግን ስራውን ገና እንደጀመርኩ ለማናጀርንት ከማሰልጠናቸው በፊት $7.25 ሳንቲም በሰአት ይከፈለኝ ነበር። እድግቱ ይህን ያሃል አይደለም በየአመቱ ሳስንቲሞች ናቸው የሚጨመሩልን። ባውዛ እየሰራሽ ትምህርትሽን ለመቀጠል አልሞከርሽም።?

ቴስቲ እየሰሩ መማር ጀምሬ ነበር አልቀጠልኩበትም እንጂ።ባውዛ ከአምስት ዓመት በኋላስ።? ቴስቲ አገባሁ (ሳቅ) እርግዝናም መጣና ስራውን ለማቆም ተገደድኩ። በኋላም ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ ምን መስራት እችላለሁ? ልጄንስ ማነው የሚጠብቅልኝ? ብዬ በማስብበት ሰዓት ለምን የራሴንም የለሎችንም ልጆች አልጠብቅም በሚል ሃሳብ ተነሳስቼ ኪንግስ ታውንና ብሉ ላይ በነበረኝ መኖሪያ ቤቴ ውስጥ እስከ ስድስት ዓመት ሰራሁ ። በኋላም ወደሌላ ጥሩ የሚባል አካባቢ ተለቅ ያለ ቤትና ሰፋ ያለ ቦታ ፈልጌ የነበረኝን ፈቃድ ከካውንቲ ወደ እስቴት ላይሰንስ ወይም ከአምስት ልጆች ወደ አስራሁለት ልጆች በማሳደግ እስካሁን ድረስ እዛው ቤት ውስጥም ጭምር እየሰራሁ ነው።

ባውዛ እስካሁን ድረስ ይህን ስራ ከጀመርሽ ስንት ዓመት ሆነሽ ማለት ነው።?

ቴስቲ ያው በልጄ እድሜ ነው። ልጄ አሁን 9 ዓመት ሆኖታል።

ባውዛ ወንደርፉል ቨርጂኒታ አካዳሚ በነማንና እንዴት ተከፈተ።?

ቴስቲ ከሶስት እህቶቼ ጋር በመሆን በጋራ ተነጋግረን የ2008

ዜናበዘጠነኛው ጎዳና ላይ የሚገኙ የንግድ ተቋሞች የንግድ ቅንቅስቃሴአቸው እያደገ መምጣቱ ታወቀ።

ዘጠነኛው ጎዳና (9th ST) በቅፅል ስሙ (little ethiopia) ላይ የሚገኙ የተለያዩ የንግድ ተቋማት የንግድ እንቅስቃሴአቸው ከእለት እለት እየተሻሻለና እያደገ መምጣቱን ሰሞኑን የባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በየተቋሟቱ የስራ ቦታ እየሄደ ባደረገው ጥናት መሰረት መረዳት ተችሏል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው በአካባቢው ከ 30 በላይ የ ኢትዮጵያ የንግድ ተቋምቶች መኖራቸውንና ደንበኞቻቸው በርካታ ኢትዮጵያውያንና ጥቂት ኤርትራውያንና አፍሪካ አሜሪካዊያን እንዲሁም ነጮች ጭምር ሲሆኑ በዚህ አካባቢ ያሉ የንግድ ተቋማት ስራ ከጀመሩ ከ �0ዓመት በላይ ያለፋቸው ድርጅቶች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ዝርዝሩን በ ገፅ ይመልከቱ።

ወሰን የለሽ ገበያ ተከፈተ ወሰን የለሽ ገበያ ሜሪላንድ 90� ሲልቨርስፕሪንግ አቬኑ በ 209�0 ውስጥ ከ ሲልቨርስፕሪንግ አቬኑና ፌንተን እስፕሪንግ የሚገናኝበት ላይ ተከፍቶ ሥራ መጀመሩን የድርጅቱ ባለቤት ወ/ሮ ሐረገወይን በሪሑን ለባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታወቁ። ወሰን የለሽ ገበያ የበግና የበሬ ስጋ ፡ እንጀራ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ፤ የኢትዮጵያውያን ጌጣ ጌጦችንና ሌሎችንም ነገሮች አሟልቶ የያዘ መሆኑን በተለይ ስጋቸው በጣም እየተወደደ መምጣቱን ጠቁመዋል።

. . ከ65 ሺ እስኴር ስፋት ላይ ያረፈው መዋለህፃናትበመኖሌ ፓፓፓጵሎስ

ወደ ገጽ �4 ዞሯል

ቤት የመሸጥና የመግዛት ስራቸውን አጠናክረው ጀመሩወ/ሮ ገነት አስታጥቄ በሜሪላንድና ዲሲ ህጋዊ ፈቃድ ያላችው ሲሆን ከዚህ በፊት የሚሰሩትን የተለያዩ ቤቶችን የመግዛትና የመሸጥ ስራቸውን በተጠናከረ መልክ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ወ/ሮ ገነትበአሁኑ ሰዓት የስራውን እንቅስቃሴ ጥሩ መሆኑንና ብድር ለሚፈልጉ ግለሰቦችም ለብድር ሰጪ ድርጅቶች ጋር የማገናኘትም ስራ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል ።

Page 6: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ 6ገጽ 6

በጌታቸው ለገሰ- ከአትላን ግጭት ማለት በሁለትና ከሁለት በላይ በሆኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መሃከል ያለ የአመለካከት አለመግባባት ነው ። ግጭት ሁሌ የሚኖር የሕይወት ክፍል ነው። በዚሁም ግጭት የሚያመለክተው ለውጥ መኖር እንዳለበት የሚያሳይ ምልክት ነው ። ግጭት ጠቀሜታ እንዲሁም ጉዳት አለው። አግዛኛውን ጊዜ ግጭት ሲታሰብ የሚታየው ጉዳታዊ ( negative ) ጎኑ ነው። እንዲሁም ግጭት በጥሞና ከታየ የመመሪያ መሰረት ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ ግጭት በሃቅ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በተለምዶ ( myth) ከሚነገሩ ነገሮች በጥቂቱ ፡

. ግጭት መኖር የለበትም ወይም ጥሩ አይደለም ።

. ግጭት ማለት መጣላት ማለት ነው ።

. ግጭት በንግድ ገጽታ ሲታይ ደንበኞችን በደንብ ማስተናገድ ግጭት አያመጣም ይባላል።

እንዲሁም ሁለት የግጭት መፍትሄዎች ወደ ስህተት የሚዳርጉ ፡

. ግጭቱን መደበቅ ወይም ችላ ማለት . በሃይል አስገድዶ ግጭቱን ለማስወገድ መሞከር

ግጭት ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ደግሞ

.የሌላውን በኩል ያለውን አስተሳሰብ ለመረዳት ያስችላል ።

. የተሻለ መግባባትና መነጋገር እንዲኖር እድል ይሰጣል ።

. ፍሬ ያለውና እንዲሁም ሁሉንም አቀፍ መፍትሄ ለመፈለግ ያስፍላል ።

.ሰፋ ያለ አመለካከትን ዋጋ የመስጠት አስተዋዖ አለው ።

. በህብረት የመስራትና ምርታዊ ለመሆን እድል ያበጃል ።

ግጭትን ለማስተዳደር አምስት ዘዴዎች አሉ ። የዘዴዎችና የአጠቃቀም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው።

�.ግጭትን ችላ ማለት (Avoiding)

ይህ ዘዴ የተጋጩትን ቡድኖች ወይንም ግለሰቦች ያላቸውን ችግር ሟሟላት በፍፁም የማይቻል ሲሆን መፍትሄው ከሚያመጣው ውጤት የሚያመጣው ችግር

የበለጠ ሲሆን ለጊዜው ስለ ግጭቱ የሚደረገው የመረጃ አሰባሰብ አሁን ከሚደረገው ውሳኔ የበለጠ ሲሆን ግጭቱ ውስጥ የተሳተፉትን ቀዝቀዝ እንዲሉና ረጋ ብለው ማየት እንዲችሉ ለማድረግ ነው ።

2. ግጭቱን ማለሳለስ ( Smoothing)

ግጭቱ ከአንዱ የበለጠ ለሌላው ክፍል የበለጠ አንገብጋቢ ሲሆን ለወደፊት ለሚኖር ግንኙነት ጥሩ መግባባት እንዲፈጠር ለማደረግ ( relation-ship Credit ) በግጭቱ ላይ የመሸፈኛ ሁኔታው ግልጽ ሲሆን ከስር ያሉ ባልደረቦችን ከጥፋታቸው እንዲማሩ ለማድረግ።

3. ለግጭቱ ጊዚያዊ መፍትሄ በእኩልነት መደራደር (Bargaining)

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለተጋጩት ቡድኖች ለሁሉም ሊሰራ የሚችል መፍትሄ ለመፍጠር በጣም ከባድ ( complex ) ግጭቶች ግዚያዊ መፍትሄ ለማዘጋጀት የግጭቱን አካሎች እኩል ኃይል ኖሯቸው ግን ግባቸው በፍፁም እተቃረነ ከሆነ ( mutually exclusive ) 4. በማስገደድ መፍትሄ ማድረግ (forcing )

ባለው ግጭት ላይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ለማድረግ ። ግጭቱ እያለ በጣም ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስራውን ማስፈጸም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጉዳዮቹ በጣም ጠቃሚ ሆነው በእርግጥም መፍትሄው ትክክል ሆኖ ሲገኝ።

5. ዘለቄታዊ መፍትሄ መፈለግ ( ፕሮብሌም ስሎቪንግ )።

የተጋጩትን ቡድኖች ወይንም ግለሰቦች ሃሳብ በማቀላቀል መፍትሄ እንዲገኝ ሙሉ ትብብራቸውን ለማግኘት የሁለቱም ቡድኖች የያዙት አቋም ጠንካራ ሲሆንና ወደ አማራጭ መፍትሄ ለመጓዝ በግጭቱ ውስጥ ካሉ መሃከል የተለያየ ለመሰብሰብና ለመቀላቀል ።

በሚቀጥለው እትም ይቀጥላል ። source : conflict style

ግጭትን ማስተዳደር ( ማብረድ )

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያን ሙዚቀኞች ማኅበር በተለይ ለህልውናቸው ቅድሚያ በመስጠት በዘጠነኛው ጎዳና ላይ አዲስ ፅፈት ቤት በመክፈት ስራቸውን አጠናክረው መጀመራቸውን ከአዲሶቹ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴዎች ውስጥ ሊቀመንበር የሆኑት አ/ቶ ጌታቸው ገብረ ጊዮርጊስ ለባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታውቀዋል ።

አዲሶቹ ተመራጮች ስራ ከጀመሩ ስድስት ወር መሆናቸውና እስከዛሬ ግን የሙዚቃ ማኅበሩ ስራ ከጀመረ ከአስራስምት ዓመት በላይ እንደሚሆነው እንዲሁም ለረጅም ጊዜ አባላቱ በብዛት አርቲስቶች መሆናቸውንና የሚመራውም በነሱ ስለሆነ ብዙ አመቺ ያልሆኑ ጊዜያቶችን አሳልፎ በአሁኑ ሰዓት ቢሮውን እያንቀሳቀሱት ያሉት አምስት የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሲኖራቸው በምክትል ስራ አስኪያጅነት አርቲስት ኩራባችው ወልደ ማርያም ፡ በፀሃፊነት መስፍን ዘርጋ ፡ በሒሳብ ያዥነት ዓለም ከበደ፡ በህዝብ ግንኙነት ፋሲካ ዲምትሪና እሳቸውም በሊቀመንበርነት አምስት ሆነው እያገለገሉ እደሚገኙና ከዚህ በፊት ተግባራዊ ያልሆኑ እቅዶችን ተግባራዊ ለማደረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጽስዋል። ማኅበሩ ዘመናዊ በሆነ የአሰራር ዘዴ ተጠቅሞ የራሱ የሆነ ቢሮ ፡ ኢንተርኔት ፡ የስልክ ፤ የፋክስና የመሳሰሉት ነገሮችን አሟልቶ በመስራትና በቅድሚያ ህልውናውን በማስጠበቅ ለአባላቱ ሙሉ ቋሚ መታወቂያዎችን አሰርተው ለማከፋፈል በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና በዚህ በስድስት ወራቶች ውስጥ ለአርቲስት ተሻገር ይልማ በኢሚግሬሽን ጉዳይ ታስሮ በእስር ቤት ስለሚገኝ አባላቶቻቸውን አሰባስበው ወደ 3500 ብር ሰብስበው ለጠበቃና በሌሎች ነገሮች መብቱን እንዲያስከብር ገንዘቡን ልከው እርዳታ ማድረጋቸውን አስረድተውናል።

ሌላው ቀደም ሲል ከ �20-�30 አባላት እንደ ነበሯቸውበአሁን ሰዓት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢ ያሉት በተጠናከረ መንገድ የሚንቀሳቀሱት ወደ 60 አባላት መሆናቸውንና በኒዮርክ፡በአትላንታ፡በፔንሲሊቬንያና በመሳሰሉት አካባቢዎች የሚገኙትን ሲጨምር �00 አካባቢ እንደሚደርሱ ገምተዋል ።

በመጨረሻም በዚህ ወቅት ከሰላሳና ከአርባ በላይ አባሎቻቸው ወራዊ መዋጮዋቸውን እየከፈሉ እንደሚንቀሳቀሱና በአንዳንድ ምክንያቶች ለምሳሌ ከሃገር ውጪ በመገኘታቸውና በሌሎች ምክንያቶች በወቅቱ ለመክፈል ተዘጋጅተው ያልከፈሉ መኖራቸውን ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት ግን በሚዘረጉላቸው ዘመናዊ የሒሳብ መሰበስቢያ ዘዴዎች ሁሉም እንደሚከፍሉ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር ለህልውናው ቅድሚያ በመስጠት ስራውን አጠናክሮ መስራት ጀመረ

www.bawza.com

አርቲስት ጌታቸው ገብረ ጊዮርጊስ

Page 7: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ 6 Volume 1, Issue 2 ገጽ 7ገጽ 6

ጥበብና ባህል www.bawza.com

«እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቅርቡ የልጅ አባት እሆናለሁ » ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከወጣት ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው ። በሕብረተሰባችን ውስጥ ገና በመጀመሪያ ስራዎቹ የብዙዎቹን ቀልብና ጆሮ ስለሳበ ከአይን ያውጣህ ተብሎ ነበር ። በቅርቡም ወደ ባህር ማዶ በዚችው አሜሪካ አዳዲስ ስራዎቹን ሰንቆና ጉሮሮውን አስሎ ስራዎቹን በማቅረብ በሩቅ ላለነው አድናቂዎቹና ወዳጆቹ እዚህም አለሁ እያለን ነው ። ከአሜሪካ በኋላ የተለያዩ የአውሮፓና የአረብ ሃገሮች እየተዘዋወረ የሙዚቃ ዝግጅቱን አቅርቦ እንደጨረሰ በዋሽንግትን ዲስ ውስጥ በሚደረገው የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት እንደሚመለስ አጫውቶናል ። እኛም ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ ዘጠነኛው ጎዳና ላይ በኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ህንፃ ውስጥ በባውዛ ዝግጅት ክፍል ቢሮ ውስጥ ጋብዘነው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቆይታ አድርገናል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ። ወደ ወጋችን …… :

ባውዛ ፡ እንኳን ደህና መጣህ ካልንህ ስንት ወራት አስቆጠር ማለት ነው ?

ጎሳዬ ፡ ያው እንግዲህ እኔም እንኳን ደህና ቆያችሁኝ ካልኩ የፊታችን ፌብሩዋሪ �7 ላይ ሶስተኛ ወሬ ይመጣል ።

ባውዛ ፡ እንዴት ልትመጣ ቻልክ ? ጎሳዬ ፡ ከአሌክስ (አለማየሁ ብርሃኑ) ከሚባል ፕሮሞተር ጋር በመነጋገር ነው የመጣሁት ። የሰራናቸው ስራዎች በጣም ጥሩ ሆነዋል ።እኔ እንደውም እንደዚህ አይነት ዝግጅት አቀርባለሁ ብዬም አልጠበኩም ነበር።

ባውዛ ፡ የትኛው ስቴት ላይ ባሳየሃቸው ዝግጅቶች ብዙ ታዳሚዎች ታድመው አድናቂዎቼን አስደስቻለሁ ብለህ ታስባለህ ?

ጎሳዬ ፡ እስካሁን ባሳየናቸው ዝግጅቶች ላይ ሁሉ በጣም ጥሩ ስራዎችን ሰርተናል ። አድናቂዎቼም በጣም ተደስተዋል ። በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ ምንም እንኳን የአየሩ ሁኔታ ካፊያ አዘል ከመሆኑ በተጨማሪ ጥበቃውም ጥብቅ ቢሆንም እንኳን ቦታው ሞልቶ ከአንድ ሺ ሰዎች በላይ እንደተመለሱ አንዳንድ መረጃዎች ደርሰውኛል ። በዚህ ምትክ በ �5 የቫለንታይን ቀን በድጋሜ አቅርቤያለሁ። ባውዛ ፡ የዚህ ሃገርና የኢትዮጵያ አድማጮችን ስታነጻጽራቸው ለየት ያለ ነገር አስተውለሃል ? ጎሳዬ ፡ አሜሪካ ፡ ኢትዮጵያም ፡ አውሮፓም ፡ ሆነ አረብ ሃገር ኖርን የኢትዮጵያውያን ደም እስካለን ድረስ አንድን ዘፈን በእኩል ስሜት ነው የምንቀበለው ። እዚህ ነው የተወደደው እዛ ነው የቀዘቀዘው የሚል ነገር አልገጠመኝም ። በዚህ ላይ የኔ ስራ የተለያዩ ነገሮችን አካቷል ። ለምሳሌ ያህል ኦሮምኛና አማርኛ የተቀላቀለ ፤ ኦልዲስ የሚመስልና ከክራር ጋር የተቀነባበሩ ስራዎችን ስላካተተ በሁሉም ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል።

ባውዛ ፡ በዚህ በኮንሰርትህ ዙሪያ ቀጣይ ፕሮግራምህ ወዴት ለመሔድ ነው ያሰብከው ?

ጎሳዬ ፡ ከዚህ በኋላ ወደ አውሮፓ ነው የማቀናው። ስዊድን ፡ ጣሊያን ፡ ሰዊዘርላንድ ፤ ኖርዌይ ፡ ግሪክና ጀርመን የመሳሰሉት አገሮች ላይ የተለያዩ ዝግጅቶችን አቀርባለሁ ።

ባውዛ ፡ መቼ ነው በትክክል ይህን ሃገር የምትለቀው ?

ጎሳዬ ፡ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው የኳስ ጨዋታ ላይ ተመልሼ ለመምጣት አስቤያለሁ ።አሁን ግን እዚህ አሜሪካ ለግል ጉዳዬ አንድ ወር ያህል ሳልቆይ አልቀርም ከዚያ በኋላ ነው ወደ አውሮፓ የምሔደው።

ባውዛ ፡ በእስካሁኑ ቆይታህ አሜሪካንን እንዴት አገኘሃት ? እንደጠበቅካት ናት ?ጎሳዬ ፡ ይህን ያህል የተለየ ነገር አላጋጠመኝም ።ከፕሮሞተሬም ጋር ስነጋገር አለባበሴን እንዳስተካክል ተነግሮኛል። ባውዛ ፡ ሃገር ቤት እያለህ ምን ምን አይነት ስራዎችን ትሰራ ነበር ? ጎሳዬ ፡ የሙዚቃ ስራዬን አስመልክቶ የራሴ የሆነ ናይት ክለብ የለኝም። በሌሎች ቦታዎችም አልሰራም ። በዋናነት ከእጮኛዬ ጋር የግል ድርጅት አለን። እሱን አግዛታለሁ ።

ባውዛ ፡ የተለያዩ ኮንሰርቶችንስ ( የሙዚቃ ዝግጅቶችን ) አዲስ አበባ እያለህ ልክ

በኤልያስ እሸቱ

ወደ ገጽ �6 ዞሯል

Page 8: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ 8ገጽ 8

ሰአሊ ተስፋዬ ንጉሴ በርሊንግተን የሚገኘው ቬርሞንት እስቱዲዮ ሴንተር ጋብዞት የተለያዩ ስራዎቹን ኢትዮጵያን በመወከል ሰሞኑን

ለሰባት ቀን በሚያሳይበት ወቅት የተለያዩ ኤግዚብሽን አዘጋጆች በስራዎቹ አድናቆት ስላደረበቸው በተጨማሪ የተለያዩ ቦታዎች ላይ እንዲያሳይ እድሉን ሰጥተውታል።በተጨማሪም ስራዎቹን በሚያቀርብበት ወቅት የሃገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያና የተለያዩ ጋዜጦች በፊት ለፊት ገፃቸው ጭምር የዜና ሽፋን ማግኘት ችሏል።

ሰዓሊ ተስፋዬ ብዙውን ጊዜ የሚታውቀው ፈረሶች ላይ ተመርኩዞ ያለፈውን የኢትዮጵያን ታሪኮች የሚያመለክቱ ስራዎቹ ሲሆኑ በተለይ (black Africa Amer-ica three month ) ኒው ዮርሊን ሉዚያና ላይ በተከፈተው ኤግዚብሽን በርካታ ስራዎቹን በድጋሜ ለአንድ ወር እዲያሳይ ተጠይቆ እያሳየይገኛል።

ያሳየሁበት ስራዎች አሉኝ ። በሌላ በኩል አሁን ጎሳዬን ወስደህ ሙሉ በሙሉ ፍፁም የባህል የሆነ ሥራ ሥራ ብትለው ምናልባት የሱ ችሎታ ላይሆን ይችላል ። ለሱ የተሰጡ ሰዎች አሉ ። ይህንን ሃላፊነታቸውን ጠብቀው ይዘው የሚሔዱ አርቲስቶች እንዳሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ባውዛ ፡ እስቲ አዲሱ አልበምህ ላይ ለብሰህ ስለተነሳኽው ቲሸርትህ እንምጣ ሃሳቡን ማን አመነጨው ? ጎሳዬ ፡ (ረጅም ሳቅ) ለመሆኑ ቲሸርቴ እዚህ አገር መጥቷል ? (እረጅም ሳቅ) አንድ ወዳጄ እዚህ ሃገር ላይ ያለኝን ልንገርህ « የጎሳዬ በነጭ ወይም በጥቁር ምስል ላይ ያለው ያንተ ቲሸርት ሰማንያ ብር ገባ መቶ ብር ገባ ሲሉኝ ምንም ትርጉም ሳይሰጠኝ አለፈ” አለኝ። ይሄውልህ ቲሸርቱ ማለት በሁሉም የሃገራችን ክፍል በተለይ የገጠሩ ወጣቶች በሙሉ የሚያደርጉት ደረቱ ላይ ሸንተረር ሸንተረር ኖሯቸው የተለያዩ መልክ ያላቸው ቲሽርቶች ናቸው። አወካቸው ወይ ስለው እነሱን ነው እንዴ ብሎ ተገረመ። የቲሸርቱ ሐሳብ የመነጨው አንድ ወቅት ላይ እቤት ቁጭ ብዬ ቴለቪዥን እያየሁ ሳለ የአንድ ብሔረሰብ አኗኗራቸውና የለቅሶ ስርዓታቸው እንዴት እንደሆነ የሚገልፅ ስነ-ስርዓት ላይ ሳስተውላቸው ወዲያው መርካቶ ለሚገኘው ጓደኛዬ ስልክ አነሳሁና ይሔንን ልብስ እፈልገዋለሁ ። ይህ በኔና በአንተ ብቻ የሚቀር ይሁን ብዬው ፈልጎ አገኘልኝ ። ስንት ነው ስለው 28 ብር አለኝ። በል እንግዲያው በአረንጓዴ በቀዩም በሰማያዊውም ግዛልኝ። በሱ ፓስተር መስራት አለብኝ አልኩት ።ይህ ልብስ ሁሉም ሰው ስለሚለብሰው መለያችን እየሆነ መጥቷል። “እንዴት አሰብከው?” ሲለኝ ” እሱን ይዘህ ስትመጣ ይነገርሃል” አልኩት። ይዞ ሲመጣልኝ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እንደገለፁት ” ወደ ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ስሄድ ላሊበላዋን ፡ ወደ ምስራቅ ድሬ. . . ድሬ ፡ ወደ ምራብ እቫንጋዲ ፤መካከለኛውን ደቡብና ወደ ምስራቁን የሚገልጽልኝ ኦሮሞ ናት እሷ ( ኮያባቦ ) ብያለሁ። ይህን ሁሉ የሃገሬን ክልል ለጠራሁበት ስራ የ 500 እና የ 600 ብር ሸሚዝ አደርጌ ምስሌ ፖስተር ላይ ቢወጣ ምንም ትርጉም አይሰጠኝም ብዬ ስላስብ ነው” አለፍኩት።

ባውዛ ፡ ከዚህ በፊት ጓደኛህ 28 ብር የገዛውን ቲሸርት እኔ እስከማውቀው �2ብርም ሲሸጥ አውቀዋለሁ። ለመሆኑ አንተ ፖስተር ከሰራህበኩት በኋላ ስንት ብር ገባ ሲባል ነው የሰማኸው?

ጎሳዬ ፡ አሁን ወደ መጨረሻዎቹ ላይ መቶ ሃያ ምስት ብር ገባ ሲባል በጣም ነው የቆጨኝ ይሄኔ በኮንቴነር አስመጥቼ ብሸጠው ትልቅ ቢዝነስ ውስጥ ገብቼ ነበር።

ባውዛ ፡ ጣትህ ላይ የማየው የቃል ኪዳን ቀለበት ምንድነው ?ጎሳዬ በይፋ ሳያሳውቅ አገባ እንዴ እየተባለም ይወራል።

ጎሳዬ ፡ ( ረጅም ሳቅ ) አዎ ትክክል ነህ ። እግዚአብሔር ፍቅዶልን በጋብቻ እስክንቆራኝ ድረስ እጮኛ ይዣለሁ ። እሷም እኔም ከቤተሰብ ጋር ተዋውቀናል ። ጋብቻችንም እሩቅ የሚሆን አይመስለኝም።

ባውዛ ፡ የልጅ አባት ልትሆን ነውም ይባላል ?ጎሳዬ ፡ ( ረጅም ሳቅ ) እግዚአብሔር ሁሉን ነገር እሱ በፈቃዱ እንደጀመረው እሱ በሰላም ይጨርሰው ። ከጥቂት ወራት በኋላ በቅርብ የልጅ አባት እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ባውዛ ፡ ማሙሽን እንጠብቅ ወይስ ሚሚን?

ጎሳዬ ፡ ይህ የመድኃኒዓለም ፈቃድ ነው። እሱ የሰጠንን መቀበል ነው።

ባውዛ ፡ የጎሳዬ ልጅ ወደፊት የት ነው የሚያድገው ? አንዳንድ አርቲስቶች ወደዚህ ወደ አሜሪካ እያመጡ ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ እያየናቸው ነው።

ጎሳዬ ፡ አዲስ አበባ እኔና እጮኛዬ የግል ድርጅት ስላለንና በሌሎችም ምክንያቶች ኢትዮጵያ ላይ ነው መኖር የምንፈልገው ስለዚህ ልጄም ሃገሬ ነው የሚያድገው።

ባውዛ ፡ ድርጅታችሁ ምን አይነት ድርጅት ነው?

ጎሳዬ ፡ ከኬሚካል ድርጅቶች ጋር የተያያዘ ስራ ነው የምንሰራው።

ባውዛ እጮኛህ በዚህ ዙሪያ ዕውቀት ወይም ትምህርት አላት። ጎሳዬ ፡ በዚህ ዙሪያ ጥሩ ዕውቀትና ትምህርት ስላላት ነው እዚህ ቢዝነስ ውስጥ የገባችው። ባውዛ፡ እስቲ ስለ እጮኛህ ትንሽ አንዳንድ ነገር በለኝ ። በአንተ ሙያ ላይ አስተዋፆ ታደርግልሃለች?

ጎሳዬ ፡ በነገራችን ላይ እጅግ በጣም ጠንካራ ፤ ጎበዝና የስራ ሰው ናት።በተጨማሪም ጥሩ የቤት ዕመቤት የሆነች ባለቤት ነው ያለችኝ። እኔም እጅግ በጣም ነው የማከበራትና የምወዳት ። በኔም ሙያ በኩል ከምጠብቀው በላይ ነው አስተዋፆ እያደረገችልኝ ያለችው። ለምሳሌ ያህል በቅርቡ ሳታማሃኝ ብላ የሚለውን ካሴት ሳዘጋጅ በፕሮሞሽኑ በኩል ከሙዚቃ ቤቱ ውጪ የእኔን ፖስተርና ፍላየር እያሰራች በሁሉም ቦታዎች ላይ እያስበተነች በጣም ትልቅ ሚና ተጫውታለች ላመሰግናት እወዳለሁ ።ባውዛ፡ በሕይወቴ ላይ የኔ ጠንካርና ደካማ ጎን ይህ ነው የምትለው አለህ?

ጎሳዬ ፡ መቼም ሰው እስከሆንክ ድረስ ጠንካራም ደካማም ጎን ይኖርሃል። በርግጥ ደካማ ጎንህን ላታስተውለው ትችላለህ ። ጠንካራ ጎኔ ነው የምለው በየቀኑ ስራዬን አስባለሁ። ሁል ጊዜ በአይምሮዬ ውስጥ ዛሬ ጥሩ ስራ ሰርተሃል ብሎ አድናቆት ለሰጠኝ ሕዝብ ነገ ከነገ ወዲያ ምን ሰርቼ ላስደስተው የሚል ነገር አለ። ሌላው ይቅርና እኔና አንተ እንኳን ቻው ቻው ተባብለን ከተለያየንበት ጊዜ ጀምሮ ሌላ የፈጠራ ስራ ላስብ የምችልበት ጊዜን ነው ለራሴ የምሰጠው። ስለ ራሴ ይህን ያክል ነው።

ባውዛ፡ አንተም ሆንክ እጮኛህ የወደፊት ዓላማችሁ ምንድነው?

ጎሳዬ ፡ እኔም ባለኝ ሙያ ከሷም በምትሰራው ስራ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሰን ሃገራችንን በጥሩ ስም ማስጠራት እንፈልጋለን ።በተረፈ አባወራነቱም መጥቷል ( ሳቅ )

ባውዛ፡ ልጅህን ለማሳደግ ምን ያህል ተዘጋጅተሃል?

ጎሳዬ ፡ እንግዲህ አሁን እያሟሟኩ ነው (ረጅም ሳቅ)።

ባውዛ፡ በተለይ እንደምታውቀው በዚህም በሃገራችንም በርካታ ወጣቶች በተለያዩየሞያ መስኮችና ባንተ የሞያ መስክ የተሰማሩ ወገኖቻችን አሉ ። እነዚህ ከአንተ ምን ሊማሩ ይችላሉ ። ምን የምትላቸው ነገር አለ ?

ጎሳዬ ፡ በዚህ አጋጣሚ ሁሉም ሰው ጠንካራ ለመሆንና ትልቅ ደረጃ ላይ ለመድረስ እያሰብን መጣር አለብን ።ሃገራችንም ገብተን ስማችን በጥሩ ጎን እንድናስጠራ በተለይ ከጦር በላይ እያስፈራራን ከመጣው ከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ራሳችንን ጠብቀን መዋጋት ይኖርብናል።

ባውዛ፡ እስካሁን ለነበረን ቆይታ በጣም አመሰግናለሁ።

ጎሳዬ ፡ እኔም ለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ ።

ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሓንስ ካሴቱን አስመረቀ

ድምጻዊ ፀሐዬ ዮሓንስ” ሳቂልኝ “የሚለውን አዲሱን የዘፈን ሲዲውን እ.አ.አ. በያዝነው ፈብራዋሪ �6 2008 በዋሽንግቶን ዲሲ (inter-national ball-room) ውስጥ ማስመረቁን የጋዜጣችን ሪፖርተር

ዘግቧል።

ዲጄ ጎልዲና ሃበሻ ኮንሰርት ተሳትፈው ዝግጅቱ ደቆ ማለፉንም ጠቁሟል።

ሰዓሊ ተስፋዬ ንጉሴ ስራዎቹን በማሳየት ላይ ይገኛል

www.bawza.com

.......በቅርቡ የልጅ አባት እሆናለሁከገጽ �4 የዞረ

Page 9: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ 8 Volume 1, Issue 2 ገጽ 9ገጽ 8

CLASSIFIEDS

JOBS REAL ESTATE AUTOMOTIVE MERCHANDISE SERVICE PUBLIC NOTICE

የራሱ መውጫ ፡ መታጠቢያ፡ማብሰያና 2 ክፍሎች Basement ውስጥ ለመከራየት (202) 725 7023 ይደውሉ ። Washington,DC NW �6 St Heights ላይ ከቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስትያን 5 ደቂቃ 2 ባለ � መኝታ ቤትና � ባለ 2 መኝታ ቤት አፓርትመንቶች ለመከራየት ( 202) 345 96�6 ይደውሉ ።

Washington,DC NW �� street &

ጆርጂያ አቬኑና ሚዙሪ በአራተኛው መንገድ ላይ ወረድ ሲሉ በእግር የአስር ደቂቃ መንገድ የራሳቸው ሁለት መውጫ ያላቸው፡፤ የጋራ መታጠቢያና የማብሰያ ያላቸው 3 መኝታ ቤቶች ከሳሎን ጋር በህብረት �000 ብር ፤ 2 መኝታ ቤቶች የራሳቸው መውጫ ያላቸው 700 ብር ፤ አንድ ክፍል የራሱ መውጫ ያለው ብ500 ብር ንፁህ ክፍሎችን ለመከራየት 202 327 0470 ይደውሉልን።

ወደ ገፅ �9 ይዞራል

ክፍት የስራቦታዎችየኢትዮጵያ ይሎው ፔጅስ የማስታወቂያናየሴልስ ስራዎችንየሚሰሩ ሰራተኞችን በደሞዝና በኮሚሽን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋልአድራሻ �924 9th NW Washington DC 202 387 9302/03

ባውዛ ጋዜጣ የአማሪኛ ጽሁፎችን በኪማን ግዓዝዩኒ ኮድ ታይፕ የሚያደርጉሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋልአድራሻ �924 9th NW Washington DC 202 387 9322

(ልጅ መጠበቅና የቤት ውስጥ ረዳት)

በቤትዎ ውስጥ ልጆችዎን እጠብቃለሁ ። (30�- 890- 4593 ) ይደውሉ ።

( patomac hopital )

አካባቢ በሚገኘው ቤቴ ውስጥ ልጆችዎን ከልጄ ጋር እጠብቃለሁ ። ስልኬ ( 703 – 822 – 38 72 ) ነው።

ኮሌጅ ፓርክ ሜሪላንድ በሚገኘው ቤቴውስጥ ሶስት ትምህርት ቤት የማይሄዱ ልጆቼን የሚጠብቅልኝና የቤት ውሥራ የሚረዳኝ እፈልጋለሁ ። ( 202 ) 4�5 99-�9 ይዳወሉ ።

የሚከራዩ ቤቶች

Virginia (ቨርጂንያ) S Alexandria ,VA old Town ውስጥ የራሱ መታጠቢያ ያለው ክፍል ለሴት ለመከራየት ( 703) 652- 08�6 ።

Alexandria ,VA S. Van Dorn ላይ ለትራንስፖርት አመቺ

የሆነ የራሱ መውጫና መታጠቢያ እንዲሁም የጋራ ማብሰያ ያለው Furnished የሆነ � ትልቅ ክፍል Basement ውስጥ ለሴት ለመከራየት ( 57�) 263 73�9 ወይም (57�) 527-9335 ።

ላይ � Alexandria, VA tele-graph road ላይ ከ Hunington Merto � ከግማሽ mile ርቀት ላይ የራሱ መውጫና የጋራ ማብሰያና መታጠቢያ ያላቸው 2 ክፍሎች ለማያጨስ ወንድ ለመከራየት (703) 929 8052 ይደውሉ ።

Woodbridge Va የራሱ መውጫ ፡ መታጠቢያ ፡ ትልቅ ሳሎንና � ክፍል ያለው Basement ለመከራየት ( 703) 980 �2�3 ይደውሉልን።

Washington DC (ዲሲ)

Washington,DC NE

36 Florida Ave. ላይ ከሜትሮ ½ ብሎክ 2 መኝታ ቤትና እያንዳንዳቸው ሳሎን ፡ መታጠቢያና ማብሰያ ያላቸው ለመከራየት (30�)793 �2�6 አቶ አማኑኤል ብለው ይደውሉ ።

Washington,DC NW ከ u street & Georgia Ave metro አጠገብ ሁሉን ነገር ያሟላ ቤት ለመከራየት ( 202) 422 8620 ።

Washington,DC NW N . capital &Farragut Pl. ላይ ከ Ft.lotton Metro 5 ደቂቃ ርቀት ላይ የጋራ መታጠቢያና ማብሰያ ያላቸው 2 ክፍሎች ለመከራየት (57�) 235 ��94 ወይም (57�) 296 5236 ።

Washington,DC NW 5 st Buchanan street ላይ ከላይ 2 አነስ ያሉ ክፍሎችና

BABY SITTERS

ከColumbia መሃል Colombia Heights Merro 3 ብሎክ የጋራ መታጠቢያና ማብሰያ ያላቸው 2 ክፍሎች ለመከራየት (202) 49� 5342 ይደውሉ ።

Washington,DC NW sherman & living ላይ ታውን ሃውስ ውጥ የራሱ መውጫ ማብሰያና መታጠቢያ ያለው Basement ና ሌሎች ክፍሎች ለመከራየት (30�) 655 7�46 ወይም (240) 645 8790 ይደውሉል።

House for rentals

Prize Winning QuestionsGeneral questions for this Month

1. What country is the biggest island Nation?2. What is the Chemical Symbol for Gold?3. Which is the Biggest city in the world?4. What was Zimbabwe called before 1957?5. What is the currency of India?

ANSWERS1. __________________________________________2. ______________________________________3. ______________________________________4. ______________________________________5. __________________________________________

Advertise on Bawza and make your business grow to New heightsTEL 202 387 9322 or 202-3879302/3/ FAX 202-387-9301

Last Issue ANSWERS1. DORMANT VOLCANO2. Fe3. ISTAMBUL4. GOLD COAST

5. SHEKEL

የዕርሶና የቤተሰብዎ ጋዜጣአገልግሎትዎንና ምርትዎን በባውዛ ጋዜጣ ማስተዋወቅ ብልሕነት ነው።

Jobs

Page 10: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ �0ገጽ �0

ቅምሻ www.bawza.com

ቀልድአንድ የአምስት ዓመት ሕፃን ልጅ ለአባቱ መኪና መንዳት እፈልጋለሁ ይለዋል። አባቱም ገና አንተ ህፃን ልጅ ነህ መኪና ለመንዳት ቢያንስ አስር አመት ይቀርሃል ይለዋል። ህፃኑም በንዴት እኔ ገና አስር አመት አልጠብቅ። አሁኑኑ መኪና መንዳት መጀመር አለብኝ ይለዋል። አባቱም በህፃኑ መጣደፍ በመገረም አሁን እኮ አንተ መኪና ብትይዝ ፂም ስለሌለህ ፖሊስ መንገድ ላይ አስቁሞ ይቀጣሃል ይለዋል። ህፃኑም በምላሹ እማዬ ጢም የላትም መኪና ግን ስትነዳ ፖሊስ አስቁሟት አያውቅም አለው ።

አራምባና ቆቦሁሉ አማረሽን... መኪና ገጫትያማረ ፍሬ ሁሉ…. ኢትፍሩት ብቻ አይገኝምየምበላው ሳጣ …ፋዘር ሰምቶ መጣሲያጌጡ … ክላስ ይቀጡጋኖች አለቁና…. ምንቸቶች አመለጡፍቅር ካለ … አንድ በሬ ለሁለት ይበቃል ።

በ�930ዎቹ

አባባሎችመናገርና ማድረግ በአንድ ማዕድ አይደሉምየንጉስ ውሻ የውሾች ንጉስ ነው።ራስህን ትልቅ አታድርግ ትንሽ አይድለህምና።የሮጠ አመለጠኝ የበላ በለጠኝ ።ከተያዙ ብዙ ነው መዘዙ ።የሚጠፋ ከተማ ነጋሪት ቢመቱበት አይሰማም ።ተልባ በጥባጯ እያለች ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት ።

የዳንስ አይነቶች

ብሬክትዊስትዘሼክዲስኮታንጎስማሽ ፖቴቶባሌት ።

ከሃገር በቀል ባህላዊ ስፖርቶቻችን ውስጥ

ጥቂቶቹ

ፈረስ ግልቢያኢላማ ተኩስ

ሰንጠረዥ ጨዋታምከታ

ቅምምጦሽ ገበጣ

የገና ጨዋታውሃ ዋናትግል ።

ጥንቸል አምጡልኝ ማስታወቂያ

የቀኛ ዝማች ሙሉጌታ ቤት የነበረውና የኡራኤል ቤተክርስትያን

አቅራቢያ ከሚገኘው ቤታችን ጥንቸል ላመጣልን ሰው በእያንዳንዱ

ጥንቸል ብር መስጠታችንን እናስታውቃለን።

አዲስ ዘመን ነሐሴ 30 �934

ለህትመት ከበቁት የሰንደቅ አላማችን ጋዜጣ ላይ የተወሰዱ ማስታወቂያዎችከሸዋ እስከ ሱዳን ጠረፍ የሚል መፅሐፍ ታትሞ ስለወጣ በጋዜጣና በማስታወቂያ ፅህፈት ቤት በመፃህፍት መሸጫ ክፍልና እንዲሁም በከተማው ካሉ ኪዎስኮች ውስጥ አንዱ በሦስት ሽልንግ ተኩል ሂሳብ መሸጡን እንገልፃለን ።

የኢምፔሪያል ሆቴል ሁል ጊዜ ራትና የዳንስ ጨዋታ ማዘጋጀቱን ያስታውቃል ። መግቢያ ለወንዶች አስር ሽልንግ ለሴቶች በነፃ ። ጠረቤዛ እንዲያዝላችሁ አስቀድማችሁ አስታውቁ ።

በፖስታ ቴሌግራፍና ቴሌፎን ሚኒስቴር የቴሌፎን ሚኒስቴር የቴሌፎን ስራ መምሪያ ክፍል የእንጨት ምሶሶ ላይ የሚውል አስር ሺ ሰባት መቶ ሃያ የብረት ወገል ከምናቀርበው ስኒ ጋር አዋዶ በጨረታ ማሰራት ስለሚፈልግ ይህንን መሳሪያ ለመስራት የሚፈቅዱ ሰዎች እስከ ጳጉሜ 5 ቀን �939 ዓ.ም ከቴሌፎን ስራ መምሪያ ፅህፈት ቤት ድረስ መጥተው ለመዋዋል መቻላቸውን እናስታውቃለን ።

የፖስታ ሚኒስቴር የቴለፎን ስራ መምሪያ ክፍል ።

የንጉስ ሰለሞን አልጋ አንጣፊ የፃፈው ማስታወሻ ከበዕውቀቱ ስዩም

ለአስር ዓመት ያህል የንጉስ ሰለሞንን አልጋ አንጥፌያለሁ ።ጃንደረባነቴ ለዚህ ሥራዬ ያስመረጠኝ ይመስለኛል።… አስር ዓመት ቀላል አይደለም !... በነዚህ ዓመታት ውስጥ ብዙ ነገሮች አይቻለሁ ። ለምሳሌ ለአንድ ስጋ ልባሽ ፍጡር በዓለም ላይ ያሉትን ቆነጃጅቶች ሁሉ በእውኑ ለማየት አይቻልም። እንኳን በእውን በህልም በቂ አይደለም ። እኔ ግን እችል ነበር። በአለም ያሉትን ቆነጃጅት ለማየት አለምን መዞር አያስፈልግም ። የንጉስ ሰለሞን አልጋ አንጣፊ መሆን ይበቃል ። ብዙ ታላላቅ እንግዶች ወደ ንጉስ ሰለሞን ይመጣሉ ። ሁሉም ግን አይኑን ለማየት እድል አያገኙም። የሚፈቀድላቸው መመዘኛውን የሚያሟሉት ብቻ ናቸው ። ለምሳሌ ዛሬ ስልሳ ሁለት እንግዶች ከተለያዩ ዓለማት ክፍሎች መጥተው ነበር ። ከነዚህ ውስጥ ስልሳ አንዱ በመጡበት እንዲመለሱ ተገደዱ። ምክንያቱም ወንዶች ነበሩ። በንጉስ ሰለሞን ቤተ መንግስት ውስጥ ወንድ ሆኖ ለመግባት ሌላ መመዘኛ ያስፈልጋል። ጃንደረባነት። የሆነው ሆኖ እና ከ ስልሳ ሁለቱ መሃከል የተፈቀደላት እንግዳ ማን ናት ? “ ማክዳ እባላልሁ “ ብላ ነው የተዋወቀችን። ጥቁር ናት ረጅም አንገት ወፍር ያለ ከንፈር አላት። ፀጉሯ ያረረ ጭጎጊት ይመስላል ።ድዷ እንደ ጊደር ምላስ የቀላ ጥርሷ እንደ ጊደር ወተት የነጣ ነው ። “ማን አልሽኝ “? አላት ሰለሞን። “ማክዳ” እንዴት ነሽ ? “ አለሁ “ ምን እግር ጣለሽ ? “አድናቂህ ነኝ “ እረ ባክሽ “ሙት… እንኳን እኔ እነዚህ ባልደረቦቼ

ሳይቀር ያደንቁሃል ። በዙሪያዋ ያሉ ጥቋቁሮች ጋሻ ጃግሬዎች ራሳቸውን እየነቀነቁ ብራና አውጥተው ንጉስ ሰለሞንን አስፈረሙት ። “ ሥራዬን ትከታተላችሁ ማለት ነው “ እያለ በንስር ላባ ፈረመላቸው ። ማታ ላይ “ ማክዳ የእግሯ ሸኮና እንደነጠላ ጫማ መታ መታ አድርጋ አውልቃ ገባች “ አረ ምንድነው ጉዱ “ ብዬ ጮህኩ “ምን ሆንክ ?አለኝ ሰለሞን። “ እግሯ ላይ የአህያ ሸኮና አላት “ “ ታዲያ እግሯ ላይ ንዋ “ ምን ማለትህ ነው ጃንሆይ ? “ “ የአንዳንዱ ሰው አህያነት አናቱ ላይ ነው ብዬ ነው” በሽሙጥ ፈገግ ብሎ ጆሮዬን በጥርጣሬ ዳበስኩ የሰው ነው። ራት ላይ ምግብ ቀረበ። ማክዳ አንድ ጉርሻ በላች እና “ ይህ ነገር ጨው በዝቶበታል አለች። “ሌላ ቀይሩላት” አለ ንጉስ ሰለሞን ። ሌላ መጣ ። ማክዳ ግን በማዕዛው ለየችው ። “ ይህማ የባሰ የጨው ባህር ነው። እንዴት ከጠቢብ ቤት እንዲህ ያለ ወጥ ይሰራል ? “ብላ ራሷን ነቀነቀች ። ሰለሞን አፈረ። እሱን ላለማስቀየም ስትል ጎረስ ጎረስ አደረገች ። ከእራት በኋላ ሰለሞን “ የኔን እቃ ከነካሽ የፈለገኝን ነገር አደርግሻለሁ” አላት” አረ እድሜ ለኢትዮጵያ አገሬ እኛ የሰውን አንነካም የራሳችንንም አናስነካም “ አለችው። ስለሞን ግን በልቡ “ አሄ አሄ እሱን እንኳን ተዪው “ ሳይል የቀረ አይመስለኝም። ከዚያ ወደ እኔ ዞሮ በሹክሹክታ “ ለማክዳ ውሃ አታቅርብላት ውሃውን እኔ ምኝታ ቤት ትራስ ላይ አስቀምጠው። “ ወደ እኔ ምኝታ በር የሚያስገባውን አትዝጋው አለኝ። በልቤ አሄሄ ውሃ ብላ ምኝታ ቤቱ ስገባ ውሃ ሊያደርጋተኮ ነው አልኩኝ ።እኩለ ሌሊት ላይ ንጉስ ሰለሞን አልጋው ላይ ይገለባበጣል ። ማክዳ ተነሳች ። ጧፍ አበራች “ ውሃ ጥም ለቀቀብኝ እኮ አለችና እና ከአልጋዋ ተነሳች ከዚያም ታምሪን ብላ ተጣራች። ታምሪን ታማኝ አሽከሯ ነው ። “አቤት” አለ ታምሪን “ እስቲ ከሃገሬ ይዠው ከመጣሁት ወይን ጠጅ አንድ ፅዋ ስጠኝ “አለች። አንድ ፅዋ ወይን ጠጅ ጠጥታ በማግስቱ ወደ ሃገሯ ስትመለስ ሰለሞን ሳይሸኛት ቀረ ። ከዚያ በኋላ እንዴት ያሉ አፈ ታሪኮች እንደተፈጠሩ ሳስብ ይገርመኛል። ማን ይናገር

የሚገርምና የሚመሳሰል አብርሃም ሊንከን �6ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሲሆን ጆን ኤፍ ኬኔዲ ደግሞ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነው ። ሁለቱም መሪዎች በስልጣን ላይ የኖሩበት ዘመን ቢያንስ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ የሆነ የጊዜ ልዩነት አለው ። ይሁን እንጂ በሚገርም ሁኔታ የሁለቱ መሪዎች ያለፉበት ሕይወት በእጅጉ የሚመሳሰል ሆኖ ነው የምናገኘው ። ለምሳሌ ያህል ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል ።

�. የሁለቱንም ፕሬዚዳንቶች የመጨረሻ ስሞቻቸውን ለመፃፍ ሰባት የ እንግሊዘኛ ፊደላት ያስፈልጋሉ። ( Kennedy) , ( Lincoln) ::2. ሁለቱም የህግ ተማሪዎች ነበሩ ።3. ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች በእለተ አርብ ጭንቅላታቸውን ተመትተው ነው የሞቱት ።4. ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች ከገዳዮቻቸው በተተኮሰ ትይት በሞቱበት ወቅት ከሚስቶታቸው ጋር ነበሩ ።5. ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች በአያቶቻቸው ስም ነበር የሚጠሩት ። 6. ሁለቱም ለወላጆቻቸው ሁለተኛ ልጆች ነበሩ ።7. ሁለቱም ያገቡት በሰላሳዎቹ እድሜ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ነበር ። ሊንከን 33 ኬኔዲ 36 ።8. ሁለቱም ሁለት ልጆች ነበሯቸው ። በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለቱ ልጆቻቸው ገና በታዳጊነት ዕድሜያቸው ሳሉ ሞተውባቸዋል ።

Page 11: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ �0 Volume 1, Issue 2 ገጽ ��ገጽ �0

ቅምሻ www.bawza.com

ቺርስ ገና ስንጀምር ለቺርስ ያጋጨነው ለኋላ ፀባችን ትንቢቱ ሆነና እርስ በእርሳችን አጋጨን እኛኑ እንደገና ።

ኔሽን ጋዜጣ ጥቅምት �2 �998 ዓ.ም

ግጥም

በዚህች ዓለም እንደሰው ተቆጥሬ ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ውሎዬ ከሰው ሆኖ አድሬ ከሆነ ከአውሬ ። �994 ዓ.ም

የዘፈን ግጥም ሺ ብር ባለኝ ጊዜ ደጃዝማች አለችኝ ።አምስት መቶ ሲቀር ቀኝ አዝማች አለችኝ ።ሰላሳ ሲቀረኝ ውሃ ጠጣ አለችኝ ።እባክሽ ገንዘቤ ተቀመጭ ከኪሴአንቺ ነሽ ለኔ ክብርና ሞገሴ።

ሕይወቴማ ለኔ በምትሃታዊ ፍቅሩ በረቂቅ ሚስጥሩ

ካጥንቴ አፋልጦ

ከጎኔም አጣብቆ

ያኖራታል ሁሌም

ዛሬም ወደፊትም

በሁለቱም ዓለም።

ሆኖ !

ሕይወቴ ሕይወቷ ሕይወቷ ሕይወቴ።

2000 ዓ.ም .

በስነቃል ውስጥ የሚጠቃለሉት በቋንቋ አማካኝነት የሚገለፁት እንደ ተረት ተረት ፡ እንቆቅልሽ ፡ አፈ ታሪክ ፡ ምሳሌያዊ ንግግር ፡ የአነጋገር ፈሊጥ ፡ ልዩ ልዩ የሠርግ፡ የለቅሶ ፡ የበዓላት የልመና የጀግንነት የአደን የጀግንነት የጦርነት የሃገረሰብ ግጥሞችና ዘፈኖች ወዘተ ናቸው ። ስነቃል ለብዙ ዘመናት ከሰው ልጅ ጋር በመኖር በግጥምና በስድንባብ ሲንፀባረቅ ሰንብቷል ፡ ይቆያልም ። ይህም አንድ የተወሰነ የእድገት መለኪያ ማለትም የትምህርትና የጽሁፈት ደረጃ ባለው ህብረተሰብ ብቻ አይደለም እድገቶቹ ሁሉ ስነቃል ፅህፈት ትምህርት የሌላቸው የተለያዩ ማህበረሰቦች የታሪካቸው ፡ የባህላቸው ፡ መከማቻ አድርገውት ኖረዋል።

የቃል ስነፅሁፍ ( Oral Literature ) በዘፈንና በቀረርቶ ግጥሞች ብቻ አይወሰንም ። ገበሬው እርሻ ሲያርስ ፡ ሲያርስም ፡ ሲያጭድ ሲወቃ ፡ የሚያንጎራጉራቸው ከስራ ጋር የተያያዙ እንጉርጉሮዎች ፡ ሚስቱ ስትፈጭ ፡ ስትወቅጥና ጥጥ ስትፈትል በዜማ እያጀበች የምትደረድራቸው ግጥሞች ፡ አዝማሪዎች በየጠጅ ቤቱና በየድግስ ቤቱ የሚገጥሟቸው ግጥሞችና ህብረተሰቡ ለአዝማሪ የሚሰጠው ግጥምና የመየመሳሰሉት ሁሉ የስነቃል ሃብቶች ናቸው ። የቃልቻና የዝየራ ስነግጥሞች ለምሳሌ እንደ ሼህ ሁሴን ጅብሪል ስራዎች የቃል ስነፅሁፍ ሃብት ናቸው ። የቃል ስለፅሁፍ ህዝባዊ ሃብት በመሆናቸው የተነሳ እንደ ማንኛውም ህዝባዊ ጥበብ ሁሉ የወጣበትን ማህበረሰብ ቀለም ይይዛል። የሕዝቡንም አጠቃላይ ገጽታ ያመለክታል ። በታሪክ በታዩት የሕብረተሰብ እድገቶች ሁሉ የተለያኡ ማህበረሰቦች ታሪካቸውን ሃማኖታቸውን ባህላቸውን የመሳሰሉትን ማከማቻ አድርገው አልፈዋል ። በአገራችን የሚገኙ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ስነቃል እንደየሀገራቸው ባህል በተለያዩ ቅርፆች ሲጠቀሙበት አለንበት ዘመን ደርሰናል ።

የስነቃል አይነቶች በርካታ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹን እጠቅሳለሁ ። ይሄውም የጀግንነት ግጥሞችና ዘፈኖች ፡ የልመና ግጥሞች ፡ የአነጋገር ለዛና ፡ አባባሎችን በመምረጥ ምን እንደሚመስሉ እስኪ እንመልከት ።

የጀግንነት ግጥሞችና ዘፈኖች

ህብረተሰቡ ለብዙ ዘመናት በየጊዜው በተለያዩ ማህበራዊ አጋጣሚዎች በጉብዝናው ፡ በሽንፈቱ ፡ በተለያዩ ስሜትና የመሳሰሉት ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰማ ያለንበት ዘመን ደርሰናል። በዚህ የተነሳም በሃገራችን የሚገኙ የተለያዩ ሕዝቦች ብሶታቸውን ፡ ሃዘናቸውን ፡ ምሬታቸውን ፡ ጀግንነታቸውንና በየእለቱ የሚሰማቸውን የተለያዩ ስሜቶች በስነቃል አማካኝነት በሰፊው ሲገልፁ ይታያል ። ፉከራና ቀረርቶ የመረረ ስሜት የሚገለፅበት ብቻ ሳይሆን የጀግንነት ስሜትን ለማግኘት የሚወላውል ስሜትን አንድ አቋም ለማስያዝና በጀግንነት የተፈፀሙ ገድሎችን ለማሳየት ጭምር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ። የሃገርን ውበትና ጥቃትን አለመውደድ እንዲገልፅ በፉከራና ቀረርቶ ከተነገሩት ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ ።

የዛፉ ሽታው የወንዙ ሞገድ ፡ የሰማዩ ቁጣ መብረቅ ነጎድጓድ ፡

አንድ ላይ ተባብረው እያንጎራጎሩ ፡ እንስሳት ሲያገሱ ወፎች ሲዘምሩ ። ይመስላል ሰርግ ቤት ሁሌም ደስታ መንፈስን ያሰክራል ያበቦቹ ደስታ

የሀገሬ አበባ የዛፍ ልምላሜ እንኳንስ ጤንነት ይቀጥላል ዕድሜ ። የንጉስ ነጋሪት አብጅር አብጅር ሲል ሰንደቅ አላማችን ኮኮብ ሲመስል ። መድፉ መትረየሱ እገጭ እጓ ሲል

ዘው ብሎ ገዳይ እጦሩ መሃል ። ይቀጥላል

ለዘመናት ከሰው ልጅ ጋር የኖረ ሃብት

Page 12: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ �2ገጽ �2

my best friends and I got to play a basketball tournament with my friend pom and we got third place. I met a lot of my family members like my 3 uncles, 3 aunts, and to many cousins to count. We had so much fun together with family and friends. My dad made a music video and I got to be in it with my sister and if you want to see it you can go on http://youtube.com/watch?v=KVMnii5ffw8 and see

how we made the music video. we went to the country side with cows and sheeps and shot the music video there. Then when I got back to America I said hi to my friends, my dog, my aunt and cousins and when I came to school I gave gifts to my classmates and teachers and I am preety sure that it was my best vacation ever and I hope you learned a lot about Ethiopia.

This is my beg(sheep) he is my pet sheep and I miss him a lot he was 3 months old and he was just a little kid and this is me and my sister hugging him. Dear kids,We are kids so we have to help each other share information about our country whether we are born in America or Ethiopia. Thank you for letting me share my trip. If you have any comments or questions send me an email and my email is [email protected]. GOD BLESS ETHIOPIA

ልጆችwww.bawza.com

My 25 days staying in Ethiopia was unforgettable. I had so much fun with my family and friends. I went to Ethiopia on December 16, 2007 and I got back on January 12, 2008. It took me from Washington D.C. to Addis Abeba about 16 hours and then we had to stop once at Rome for fuel in the middle of the ride because it takes about 9 hours from Wash-ington to Rome and about 7 hours from Rome to Ethiopia. I had a lot of reasons to like Ethiopia and the reasons are how the food was, how the people were, how Ethiopia was so beautiful, and how it was just a great country. I also met a lot of people while I was there like new friends, old friends and family members and some of my family members were in Dire dewa, but most of my family members were in Addis Abeba the capital of Ethiopia. I got to go to dire dewa, Addis Abeba, I almost got to go to Gojam but I didn’t have enough time.

The reasons why the food was great is because you get to try food you never had before and most of the food was very healthy. My favorite food from Ethiopia are injera, kolo/dabo kolo, and baklaba. The food is very cultural and they cook their food in dif-ferent ways like when we go to an old kitchen there is insera, dest, medosha, shincurt meffecha, bileuwa(knife), metad(to make injera), and mukecha. What you would usually eat for every meal is for breakfast tea and bread, for lunch injera with wot, and for dinner spaghetti or injera again.

The reasons why the people are great is they offer you anything even though you don’t want because they want to make sure you are ok. There are poor people in Ethiopia and they are in the streets with no home some ask for money and some are blind, some are deaf, and some have a very bad disease. We should pray for those people everyday. The population is over 74,678,000 and it advances every year.

The reasons why Ethiopia is beautiful and why it is a great country is because it has a very beautiful view. We also met Haile Gebrselassie and he is the worlds fastest runner with a world record and has over 50 trophies and I have been to his house and it is big. He also gave me advice he told me to do good in school. He gave me a post card with his signature. His house has five floors and he has a pool and he has four kids and a beautiful wife. He travels all over the world for marathons. He was born April 18, 1973 very young and his birthday is close to mine too. He is one of my dad’s favoriate friends. He lives near the mountains which is not far from the city and when I was at his house I could see all of Addis Abeba. He loves his country a lot.

I met friends too and they were called Pom, Tsion, and Arsayma. They were one of

My trip to Ethiopia was unforgettable

Page 13: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ �2 Volume 1, Issue 2 ገጽ �3ገጽ �2

KIDS www.bawza.com

My Interview with MickeyFeker- What is your name?Mickey- Mikael MulatuFeker- What is your is father’s and mother’s name?Mickey- Mulatu and SeniteFeker- How old are you?Mickey- 11Feker- when is your birthday?Mickey- September 12, 1996Feker- what is your aim?Mickey- to have a good life and to become a foot-ball playerFikir- what school do you go to? Mickey- Calvary Road Christian SchoolFikir- what is your favorite thing to do?Mickey- to play with my friends and listen to musicFikir- What is your favorite thing about sports?

Mickey- it’s fun and interactiveFikir- What is your favorite sport?Mickey- football

Fikir- Thank you for giving your time for interview and have a good day on behalf of bawza

Feker Belay & Mikael Mulatu

ጥያቄተረትና ምሳሌ-ጅብ ከሄደ .................................

-አፍንጫ ሲመታ ........................

ጠቅላላ ዕውቀት*ማንበብ ለምን ይጠቅማል?

*ሉሲ (ድንቅነሽ) ማን ናት? በየትኛ ክልል

ነው የተገኘችው? እንቆቅልሽ-ኩል ተኩሏ ገበያ የምት ወጣ?

የሳምንቱ ጥያዎችና መልሶቻቸው-ሲሮጦ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል ።

-የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ሰምበሌጥ ።

-በኢትዮጵያ ትልቁ ወንዝ አባይ ይባላል።

-ኢትዮጵያን የሚያዋስኗት ሃገሮች ሱዳን፡ኬንያ፡ሱማሊያ ፡ ጅቡቲ ፡ኤርትራ ናቸው ።

በሯን ዘግታ የምታጨበጭብ?መልስ፦ ሽሮ ወጥ።

ቢሔድ ቢሄድ የማይደክመው ?

መልስ፦ ወንዝ

መልሱን በትክክል የመለሱ ተሳታፊዎች

-ሔርሜላ ገ/ማርያም ዕድሜ 7 ክፍል 3 ት/ቤት በራይት ውድ

-ሜላት ገ/ማርእያም ዕድሜ 8 ክፍል 2 ት/ቤት ብራይት ውድ

ወላጆች ልጆቻቸውን የማስተማር ግዴታ አለባቸው

መዝሙር

በዛ በበጋ በዛ በበጋ በዛ በበጋ እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋመሸበትና ሰው ቤት ገባ ልጅቷን አያት ተከናንባ ወደደችው ወደዳት ይዟት ጠፋ በለሊት።ደግሞ ደግሞ ብዙ ተጓዙ አባይ ደረሱ በጣም ከሞላ ለመሻገር ሲሞክሩ ሰምጣ ቀረች የሱ ፍቅሩ አለቀሰ ሆዱ ባባአለቀሰ የፍቅር እንባየኔ ፍቅር የኔ ፍቅር አረሳሽም እስከ መቃብር ሄደሻል አንቺ አትመለሽም። መሞት እንደሆን አይቀርልሽም።

-ሀለሐመሠረሰሸቀበተቸኃነኘአከኸወዐዘዠየደጀገጠጨጰጸፀፈፐቨ

የፊደል ገበታንና ቁጥርን ተማሩ

መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ

እኛ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ነን

ልጆችዬ በአመቱ መጨረሻ ላይ ሽልማት አዘጋጅተንላችኋል። ባውዛን አንብቡ ተሰጥኦአችሁን ፤ችሎታችሁን ፤ የወደፊት ምኞታችሁን ፤ የምትወዱትንና ሌሎች ልጆችን ያስተምራል የምትሉትን በአድራሻችን ላኩልን።

አረ ልጆች ልጆች እንጫወት በጣም ከእንግዲህ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም

ልጅነቴ ልጅነቴ ማርና ወተቴ

በባዉዛ ጋዜጣ ላይ የልጆችዎን የልደት በአል ለማስተዋወቅ ይደዉሉ 202-387-9322/ 202-387-9302/3 www.Bawza.com

Page 14: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ �4ገጽ �4

እቅዳችን ነበር። ቤቱን 2007 ኖቬንበር ውስጥ ገዛን። አሁን ስራ ጀምረናል። እቅዳችን ተሳክቶልናል ማለት ነው።

ባውዛ በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ምን ያህል ህጻናትን እየተንከባከባችሁና እያስተማራችሁ ነው።?

ቴስቲ መንግስት በዚህ ግቢ ውስጥ �4� ህጻናትን እንድንጠብቅ፤ እንድንከባከብና እንድናስተምር ፈቅዶልናል። እኛ በቅርብ መጀመራችን ስለሆነ ሰባ ህጻናቶች ብቻ ናቸው ያሉን።

ባውዛ እህቶችሽም በዚህ ሞያ ላይ ተሰማርተው ነበር።?

ቴስቲ ሁለቱ እህቶቼ በየቤታቸው አስራሁለት አስራሁለት ልጆች አሏቸው። አንዷ እህቴ ብቻ ናት ቤቷ ውስጥ ህፃናትን የማትንከባከበው ሌላ ቦታ የራሷ ስራ አላት። ሁልጊዜ ማምሻዋን ዋናው ተቋማችን ውስጥ መጥታ ትሰራላች። ባውዛ የቤታችሁንና ዋናውን መአከላችሁን ጨምሮ ስንት ህፃናትን እየተንከባችሁና እያስተማራችሁ ነው፡፡?

ቴስቲ ሶስታችን ጋር አስራሁለት አስራሁልት ልጆች ሰላሳስድስት ይመጣሉ።ዋናው መአከላችን ውስጥ ሰባአንድ አሉን በአንድ ላይ ስንደምራቸው �06 ህፃናትን እየተንከባከብን ነው።

ባውዛ በየትኛው የእድሜ እርከን ላይ ያሉ ህፃናትን ነው እየተንከባከባችሁ ያላችሁት።?

ቴስቲ ከተወለዱ ጀምረው እስከ አራት ዓመት ያሉ ልጆች እንይዛለን።ከተወለዱ እስከ አስራስድስት ወር ፤ ከአስራስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት፤ ከሁለት ዓመት እስከ አራት ዓመት ያሉ ህፃናትን ከፋፍለን በተለያዩ ክፍሎች ሲውሉ ከዛበላይ እድሜ ላላቸው አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደትምህርት ቤታቸው ማድረስ ወይም ይዟቸው ለሚሄደው አውቶብስ ከስራቸው

አንፃር ማቀበል ስለማይመቻቸው ጠዋትና ማታ ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡና ሲወጡ እኛ ጋር ይቆያሉ። በኋላም በትምህርት ሰዓታቸው ት/ቤታቸው እንወስዳቸዋለን በመውጫ ሰአታቸውም ሄደን እናመጣቸዋለን።ማምሻውን ከአራት ሰአት እስከ ስድስት ሰአት ከአርባምስት ደቂቃ ክፍት ነን በዛ ሰዓት ውስጥ ወላጆች እየመጡ ልጆቻቸውን ይወስዳሉ። ባውዛ እነዚህን ህፃናቶች ከመጠበቁ ውጭ ምን አይነት አገልግሎት ትሰጣቸዋላችሁ።?

ቴስቲ በየ እድሜአችው መማር ያለባችው ይማራሉ፤ይመገባሉ፤ይጠጣሉ፤ይጫወታሉ፤ እንቅልፋቸውን ይተኛሉ ፤ንፅህናቸውን በይጊዜው የሽንት ጨርቅ እየቀየርን አስፈላጊውን እንክብካቤ እናደርግላቸዋለን። ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በደክማቸው ጊዜ እንቅልፋቸውን ሲተኙ ከፍ ያሉት ግን በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ይተኛሉሉ። ባውዛ አዳዲስ ህፃናትን ለማግኘት ወይም ቢዝነሳችሁን ለማሳደግ ምን አይነት መንገድ ነው የምትጠቀሙት።? ቴስቲ ያው የተለያዩ የማስታወቂያ አይነቶችን በመጠቀም ነው።ለምሳሌ ያህል መጀመሪያ ላይ የተለያዩ ወረቀቶችን የማደልና በየፖስታቸው የመላክ ስራ እንሰራ ነበር።አሁን ግን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የቢልቦርድ (yard sign) ማስታወቂያዎችን ሰዎች በሚያዩባቸው ቦታዎች ላይ መሬት ውስጥ በብረት በማቆም ስለምንጠቀም የተለያዩ ሰዎች ያንን እያዩ ይደውሉልናል። ባውዛ ምን ያህል መምሕራኖች አሏችሁ የትምህርት ደረጃቸውስ።?

ቴስቲ በጠቅላላ አስራሁለት መምራኖች ሲኖሩን ከሰርተፊኬት እስከ ባችለር ዲግሪ ያላቸው መምሕራኖች አሉን።በየደረጃቸው የሚያስተምሩት ትምህርት ይለያል። በተጨማሪም ሁሉንም መምሕራኖች ከህፃናቶች ጋር መስራት እንደሚችሉና

እንደማይችሉ የኋላ ታሪካቸውን አጥንተንና አረጋግጠን ነው የምንቀጥራቸው።

ባውዛ የዚህን ሃገርና የኢትዮጲያን ልጆች አስተዳደግ ስታነፃፅሪው የትኛው የተሻለ ነው።?

ቴስቲ በርግጥ የኢትዮጵያ ያለው የልጆች አስትዳደግ በጣም ጥሩ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሳይሆን እኛ ወደዚህ ሃገር በምንመጣበት ወቅት የተለያዩ የመማሪያና የመጫወቻ እቃዎች እንደልብ አልነበረም። በአሁኑ ሰአት ብዙ ነገሮች እንደ ተሻሻሉ ላለረጋግጥ ችያለሁ። እናትና አባቴ እኔን ሲያሳድጉኝ ጥሩ ስነምግባር እንዲኖረኝ አድርገው አሳድገውኛል። እኔም ልጆቼን ሳሳድግ እንደዚሁ አድርጌ ነው የማሳድጋቸው።

ባውዛ ይህን ስራ ለመጀመር ሞዴል ወይም አራአያ የሆናችሁ ሰው ወይም ድርጅት ነበር።?

ቴስቲ በርግጥ በርካታና በኮርፖሬሽን ደረጃም ያሉ ድርጅቶችን አይተናል የምንፈልገውንም ነገር ወስደናል:፤ይህን ስራ ከጀመርን ወደዘጠኝ ዓመት እያለፈን ነው።በራሳችን ጥሩ ልምድ ቤታችን ውስጥ አዳብረናል።በርግጥ ማንም ቁጭ ብሎ ያስተማረን ሰው የለም። ከራሳችን አልፈን ሌሎች በርካታ ጓደኞቻችን እየጠቀምን ነው። ባውዛ ቤትሽ ውስጥ ገና ስትጀምሪ በአንድ ልጅ ምን ያህል ነው የምታስከፍይው ? አሁንስ?

ቴስቲ በሳምንት ከሰኞ እስከ አርብ ተንከባክቤ የማስከፍው መቶ ሃምሳ ዶላር ነበር። አሁን ግን ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ዶላር ነው ። ባውዛ ፡ የተቋሙስ አከፋፈል እንደዚሁ ነው?

ቴስቲ በተቋሙ ውስጥ ያለው አከፋፈል በእድሜያቸው ይለያያል ።ከዜሮ እስከ

ሁለት ዓመት 205 ዶላር ነው ። ከሁለት ዓመት በላይ ለሆናቸው ደግሞ �65 ዶላር ነው።

ባውዛ ፡ የአመጋገብ ሥርዓታቸው እንዴት ነው ?

ቴስቲ ፡ ጠዋት ከ 6 ሰዓት - 9 ሰዓት ድረስ ቁርስ ይበላሉ ። ከ �� – �2 ሰዓት ምሳ ይበላሉ ። 2፡30 ላይ መክሰስ ይበላሉ። ትልልቆቹ ደግሞ 4፡00 ሰዓት ላይ ከትምህርት ቤት ሲመጡ መክሰስ ይሰጣቸዋል። ባውዛ ፡ ምግባቸውን የሚያዘጋጀው ማነው?

ቴስቲ ፡ ምግብ አብስለው የሚመግቡ ሰራተኞችን ለዚህ ብለን ቀጥረናል።

ባውዛ ፡ ብዙ ጊዜ የሕፃናት ቢዝነስ ብዙ ሃላፊነት የሚጠይቅ ነው። ከዚህ አንፃር ቢዝነሱ ምን ይመስላል ? ያዋጣል?

ቴስቲ ፡ በማንኛውም የቢዝነስ ዓይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ወይም ውጤት አያመጣም ። እኛ በዋነናነት ቀዳሚው አላማችን እስከ �4� ድረስ የቀሩንን ተማሪዎች የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እየተጠቀምን ለሟሟላት ነው ። ሕፃናትን የመንከባከብና ማንኛውንም ከልጅ ጋር ተያያዥነት ያለው ቢዝነስ ውጤታማ የማይሆን የለም ። ምክንያቱም ሁሉም የሕብረተሰባችን ክፍል መውለድ ባለባቸው ሰዓት ይወልዳሉ ይህ የሚቆም አይደለም። ብዙ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ገበያ ሲወጡ ልጃቸው ማስቲካ ካነሳ እሺ በቃ ውሰደው ብለን ፍላጎታቸውን እናሟላላቸዋለን። በዚህ ላይ ወላጆች ገንዘብ ለማምጣት ስራ መስራት አለባቸው ልጃቸውን የሚጠብቅላቸውና የሚንከባከብላቸው የግድ ያስፈልጋቸዋል።

ባውዛ ፡ ወደትዳር ሕይወት መቼ ገባሽ ? ስንት ልጆችስ ወለድሽ? ቴስቲ ፡ እኔ ያገባሁት በ �997 ዓ.ም ነው። ባለቤቴ አብዱልፈታህ መሃመድ ይባላል ።

www.bawza.com

ከገጽ 5 የዞረ

ወደ ገጽ �7 ዞሯል

Page 15: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ �4 Volume 1, Issue 2 ገጽ �5ገጽ �4

እየጎተተች ይዛው የመጣችውን ሻንጣ ከጎኗ በተቀመጠው ወጣት እርዳታ በአውሮፕላኑ የመንገደኞች የመቀመጫ አናት ላይ አስገቡት። አረንጓዴ ዩኒፎርም የለበሱ የአውሮፕላኑ ሆስቴሶች የተከፈቱ የሻንጣ ማስቀመጫዎችን እየዘጉና ቀበቶ ያላሰሩ ተሳፋሪዎች መኖራቸውንና አለመኖራቸውን እያስተዋሉ መለስ ቀለስ ይላሉ። ቁመናቸውን፤ ቅርጻቸውንና ፈገግታቸውን ከንግግራቸው ለዛ ጋር ላስተዋላቸው እጅግ ይስባሉ ። በራሷ ጊዜ ትታው ወደምድራዊ ገነት ብላ ወደሳለቻት አሜሪካ ከመሄዷ በፊት የነበራት ስራ ስለነበረ የያንጊዜዋን እራሷን አስታወሰች።ከወደ ካፒቴኑ በኩል ስለጉዞው ማብራሪያና የእንኳን ደህና መጣችሁ አይነት ንግግር በኋላ ከልጅነቷ ጀምሮ በጣም የምትወደውን ዘፈን በክላሲካል መልክ «የሽንብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ የትም ዞሬ ዞሬ ትዝ አለኝ አገሬ » « ጋራ ሸንተረሩ ትዝ አለኝ. . . .»የሚለውን ጣዕመ ዜማ መስማት እንደጀመረች ምን እንደሆነ ሳይታወቅ አንዳች ሃይል ከውስጧ ፈንቅሎ ስለወጣ አጠገቧ ተቀምጦ የነበረው ወጣት ፊቷ በአንዴ ሲቀያየርና አይኖቿ በእንባ ሲያዝሉና በፊቷ ላይ ከብለል. . . ከብለል. . . እያሉ ሲወርዱ በመደናገጥ ስሜት ፈራ ተባ እያለ « አይዞሽ የኔ እህት ሰው ከአገሩ ሲወጣ እንጂ ወደ አገሩ ሲገባ እንዴት ያለቅሳል ? » አላት ። ዞርም ብላ ሳታየው ይባስ አጎንብሳ ስቅ .. ስቅ. . . የሚል ድምጽ እያሰማች በአካባቢዋ የተቀመጡ ተሳፋሪዎችን በግርምት እስኪመለከቷት ድረስ እያለች አለቀሰች ።

ክላሲካሉ አልቆ ሌላ ክላሲካል ከጀመረ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ቀና አለች : ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿ በአንዴ ቀልተዋል። ቸኮሌት የመሰለው ፊቷ በእንባ ርሷል ። እነዚህን ከመሰሉ አይኖች ዕንባ ሲፈስ መመልከት በእውነት በቁጭት ያሳሳል ። እንደው ለነገሩ በጨርቅ ላስቲክ ያዝ ያረገችው ፀጉሯ በግራ በኩል በአንድ ላይ ተሰብስበው ጡቶቿ ላይ ዝርፍርፍ ብለዋል ። ከቦርሳዋ ለስለስ ያለ ሶፍት አወጣችና አይኗ ስርና ፊቷን አበስ አድርጋ በመስኮት በኩል ወደሚታየው ጉም ውስጥ አንጋጣ ቀስ በቀስ የአይኖቿን ቆብ ከደነቻቸው ። ገና በሶስት አመቱ ትታው የኮበለለችው ልጇ አሁን ዘጠኝ አመት ይሆነዋል ። ይረሳኝ ይሆን ? ገና እንዳገኘችው በጣም ወደራሷ አስጠግታ እቅፍ አርጋ ከሳመችው በኋላ እናትህ ነኝ ስትለውና ፀጉሩንም እሽትሽት ስታደርገው ስሯም ውሽቅ ሲል በህሊናዋ ይታያታል።ሌላው ሀሳቧ ደግሞ አላውቅሽም እስከ ዛሬ የት ነበርሽ ? ብሎ ወደ አባቱ ስር ውሽቅ ሲል ይታያታል ።

ባለቤቷን እቅፍ አድርጋውና ግራ እጁን ተንተርሳ የስድስት ዓመት ሙሉ ናፍቆቷን ስትወጣ ሌሊቱ ቶሎ የሚነጋባት ይመስላታል ። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄኔ ክንዱ ሌላ ሴት አቅፎ አድሮ ይሆን ? ቤቴ ውስጥ በኔ ቦታ ተክታ የምትኖ ሴት ትኖር ይሆን እንዴ? ሌኔ ሳያሳውቀኝማ አያደርገውም ….. አያደርገውም. . . ብላ በመደናገጥ ከራሷ ጋር የገጠመችውን ሙግት እንዲቀንስላት አይኖቿን ገለጥ አደረገቻቸው ።

አውሮፕላኑ የግማሽ መንገድ ጉዞውን አጠናቆ የጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ላይ ለ45 ደቂቃዎች በሚያርፍበት ወቅት ነዳጅ ቀድቶና የተለያዩ ምግብና መጠጦችን ጭኖ መንቀሳቀስ ሊጀምር ነው። ሆስቴስዎቹንና ፓይለቶቹን ጨምሮ ሰራተኞቹ በሙሉ እሮም ላይ ለሚጠብቋቸው ተረኞች ቦታቸውን አስረክበዋል። ድካም ስለተሰማት ይህ ሁሉ ሲደርግ ምንም አልታወቃትም። ከባለቤቷ ጋር የተዋወቁት ደንበል ሲቲ ሴንተር ውስጥ ከጓደኞቿ ጋር ማኪያቶ ጠጥተው በእግራቸው አንዳንድ ነገር እያዩ በደረጃው እየወረዱ ሳሉ አንድ ጠቆር ያለች ሚኒ ቀሚስ ከነኮቷ በጣም ስለሳባት እናንተ «ይህቺን ቀሚስ በጣም ነው የወደድኳት አይኔ አርፎባታል» እባካችሁ ዋጋዋን እንጠይቅ ተባብለው ወደ ውስጥ በሚገቡበት ወቅት

አንዲት ሴት ከፊት ለፊቷ ብትኖርም እርሷን አልፋ ከወደ መጨረሻ ላይ ልብስ የሚያሻሽጠውን ወጣት ያቺ ሚኒ ለኔ አትሆንም ? ብላ ጠየቀችው። በደንብ አየት አደረጋትና ፍሪ ሳይዝ ናት እንደውም አንቺ ላይ በጣም ነው የሚያምርብሽ ። የሚገርምሽ ነገር አንድ ፍሬ ብቻ ነው ለሳምፕል ያስመጣሁት ። እዚህ ከተማ ውስጥ የትኛውም ቦታ አይኖርም ከዚህ ሱቅ ውጭ በ እውነት እመኚኝ እንደውም ለኪውና እዪው » አላት። ለክታው ካየችው በኋላ < ዋጋው ለመሆኑ ስንት ነው ?> ብላ አውቃ <ልብሱ እንደጠበቅኩት አይደለም> አለችው ። ” ለአንቺ ስለሆነ 900 ብር የሚሸጠውን 750 ብር አድርጌልሻለሁ ሰው ሳይሰማን ዝም ብለሽ ውሰጂው” አላት ። ብዙም ቢከራከሩም አልወርድ ስላላቸው ከጓደኞቹዋ ጋር ተመካክረው “ ኪሳችን ውስጥ 400 ብር ብቻ ነው ያለን » አሉት። ” እናተ ሴቶች በእውነት የሆንኩትን አላውቅም ለጓደኛችሁ ስል 500 ብር እሸጥላችኋለው ነገ �00 ብሩን ይዛ ትምጣ “ አላቸው ። ሁሉም በደስታ ተስማሙ ። እንደዚያ የጓጓችለትን ሚኒዋን ይዛ ወደቤቷ ሄደች ።

ውላ ሳታድር በማግስቱ በተመሳሳይ ሰአት መቶውን ብር ይዛ መጥታ ሰጠችው ። ስልክ ተለዋውጠው ለብዙ ቀናት እየተደዋወሉ አንዳንድ አይኑ ውስጥ የገቡ አልባሳትንና ጫማዎችን ሆን ብሎ ለሷ ሲል እያስመጣ አንዳንዴ በነፃ እየሰጣት ደንበኝነታቸውና ወዳጅነታቸው ሲበዛ ተጠናክሮ ለትዳር ሊበቁ ቻሉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የተወሰኑ ጓደኞቿ ወደ አሜሪካም ሆነ ወደ ሌላ የአውሮፓ ሀገር ስራቸውን እየተዉ የሚወጡት ስለበዙና በተለይ በዝና ምድራዊቷ ገነት (የዶላሯ ሃገር) እየተባለች ወደ ምትወደሰው አገር እሷም እንደ ጓደኞቿ የዕድሏን ለመሞከር ባለቤቷ እስክንድርን እንዴት አድርጋ ማሳመን እደምትችል ቢጨንቃትም የልጇን የወደፊት ሕይወት የተሻለ ለማድረግ በሚለው ሃሳብ ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ የእስክንድር ወንድም እንዲቀበላት ተስማምተው በተለመደው መንገድ አድርጋ መስሪያ ቤቷንና ሃገሯን ትታ ኮበለለች።

የ እስክንድር ወንድም አሜሪካ ከመጣ ከሰላሳ ዓመት በላይ ይሆነዋል ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ከአንዴም ሶስቴ ሚስት አግብቶ ፈቷል ። አሜሪካ እንደዛሬ ኑሮ ሁሉ ባልተወደደበት ጊዜ መጥቶ ወይ አልተማረ ወይ በአግባቡ ስራ ሰርቶ ገንዘብ አልያዘ ሰርቶ ለቁማርና ለዘወትር ሶሶቹ እያዋለው አንዳንዴ የ እለት ኑሮውን እንኳን መኖር የሚያቅተው ሰው ነው ። በተለይ ለሱ ብቻ ተብለው የተሰሩ ቆጥ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ዲሲ ከተማ ውስጥ በርካታ ናቸው ። « ወይ ጉድ እንደዚህ አይነት ኢትዮጵያዊ እዚህ አገር ይኖራል እንዴ ? የሚል ጥያቄ ውስጧ እየፈጠረችና እየተገረመች ቤት ውስጥ ዝርክርክ መሆኑ ሳያንሰው ሲበዛ ወሬኛ ነው።በተለይ ስለሚደግፈው የፖለቲካ ፓርቲ ፀሃይ ጅብ ወለድች አይነት ወሬ ሁሌ እንደሰለቀ ነው። «ይሄ ድመት ከየት አባቱ እንዳገኘሽ አልነገረኝም የወንድሜ ሚስት ባትሆኚ ኖሮ አንቺን የመሰለች ቆንጆ አለቅሽም ነበር እያለ ሲዝትባት በመጣች በሁለተኛ ቀኗ ድሮ የምታውቃት የሴት ጓደኛዋ ጋር ሻንጣዋን ጠቅልላ ትወጣለች ። መቼም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም ፡በጓደኛዋ እርዳታ መሰረት አንድ የሃበሻ ጠበቃ አገናኝታት በየጊዜው ለብዙ ዚዜ እየተመላለሰች ለቀጠሮ ብትቀርብም አልተሳካላትም ። እስከ ይግባኝ ድረስ ከ$3000 ዶላር በላይ ከማውጣቷ በቀር ምንም የተረፋት አልነበረም ።

በመጨረሻ የቀረ ይቀራል እንጂ እንዴት ባዶ እጄን ሀገሬ እገባለሁ በሚል ስሜት አንድ የሃበሻ ሬስቶራንትና ሆቴል ውስጥ በቲፕ ብቻ በቀን

እንደ እድሏ ከሰዓት በኋላ የጀመረች እስከ ሌሊቱ አጋማሽ እየቆየች አንዳንድ ጊዜ 20 ዶላር መስራት ጀመረች።በተለይ ቅዳሜና እሁድ ዛሬ ጥሩ ሰርታለች የተባለ ቀን እስከ 50 እና 60 ዶላር እየሰራች ብትቆይም መልኩን ቀየረ እንጂ ከአገራችን የቡና ቤት ሴቶች ስራ ምንም ስላልተለየ በሁለተኛ ወሯ የስራውን ጠባይ መልመድ ስላቃታት በያዘችው ስራ መቀጠል አልቻለችም ።

እንዲህ ወዲህ ውዲያ እያለች ላለፉት 6 ዓመታት ካሁን ካሁን ሳልዘጋጅ ይዘውኝ አንጠልጥለው ባዶ እጄን እንዳይሰዱኝ ብላ በሰቀቀን ኑሮ አንዳንድ የኢትዮጵያውያን ነዳጅ ማደያዎች ፡ ሰቨን ኢለቨንና በተለያዩ ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ በዝቅተኛ ክፍያ ብትዳክርም የምታገኘው ገንዘብ ከቤት ኪራይና ከዕለት ወጪ እልፍ ሊል አለመቻሉን ስታውቅና በተለይ አንዳንድ ወንዶች የትዳር ጓደኛና ልጅ እንኳን አለኝ እያለችው ምንም የማይገባቸው በርካታ አውደልዳዮችን ስታስባቸውማ አንዳንዴ ሴት ሆኜ ባልፈጠርስ የምትልበትም አጋጣሚ ነበር ።

ዛሬ ብዙ የሷ ቢጤ እህቶቿን ስለ አሜሪካ ትክክለኛውን ገጽታ እያወሳች የብዙ ወገኖቿን አመለካከት ለማስተካከል ወስናለች ። ባለቤቷ የሚሰራውን ንግድ ይበልጥ ለማስፋፋትና ሌት ተቀን ቀጥ ብላ እንደምትሰራም በከፍተኛ ሞራል ተነስታለች ።

ከፊት ለፊቷ የተለያዩ አስተያየት መስጫ ወረቀቶችን እየበተነችና እየተቀበልች ወደሷ እየቀረበች የመጣች ሆስተስ ናት በሃሳብ ጭልጥ ካለችበት ዓለም የመለሰቻት ።ወዲያው <እጅግዬ > <እኔ አላምንም ምህረትዬ >እየተባባሉ እቅፍ ተደራርገው ተሳሳስመው አድራሻ ከተለዋወጡ በኋላ ምህረት የጀመረችውን ስራዋን ቅጠልች። እጅግ ጓደኛዋን ከኋላዋ እያየቻት አንዳንዴ አይን ላይን ሲገናኙ ፈገግታ እየተለዋወጡ « እንዴት አምሮባታል በ እማምዬ » አለች። አየር መንገድ ገና ስትቀጠር ስራ በደንብ ያለማመደቻት የልብ ጓደኛዋና ባለውለታዋ ነበርች።

ዛሬ ወደ ሃገሯ እንደምትገባ ሁሉም ዘመዶቿ ቢያውቁም ማን እንደሚቀበላት ግን የምታውቀው ነገር የለም ። አውሮፕላኑ ወደ ኢትዮጵያ ክልል መግባት ከጀመረባቸው ደቂቃዎች ጀምሮ ተሳፋሪው በደስተኝነት ስሜት እርስ በእርሳቸው ሲነጋገሩ ድምጻቸው ከፍ እያለ መጥቷል ። ከወደ ካፒቴኑ በኩል አውሮፕላኑ ሊያርፍ ስለሆነ ቀበቷችሁን እንድታስሩ የሚል ንግግር እየተስተጋባ ነው ። በአውሮፕላኑ መስኮት በኩል የአዲስ አበባን መንደሮችና ለማየት አይኗን ቁልቁል ሰድዳለች ። ቦሌ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ የአውሮፕላኑ ጎማ ሲያርፍ አንዴ ሕዝቡ በጭብጨባ ሞቅ አደረጉት ። ተሳፋሪዎች ሻንጣቸውን አስፈትሸው በመግፊያ ጋሪ እየገፉ ከአውሮፕላኑ እየወጡ ከዘመዶቻቸው ጋር መቀላቀል ጀምረዋል ። እሷም በተራዋ ሻንጣዋን ገፍታ በፍጥነት እየወጣች ነው ። ከሩቁ ብዙ ሰዎች እጃቸውን ያውለበልባሉ የትኛው እጅ የእሷ ዘመድ እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም ። ወዲያው አንድ ሕፃን ከተሰበሰቡት ሰዎች መሃል ወጥቶ እየሮጠ ጥምጥም አለባት ። « የኔ ጎረምሳ ጎርምሰህልኝ የለም እንዴ ? » ብላ በደንብ እቅፍ አድርጋ ሳመችው ። ባለቤቷንም ልጇ ስሯ እንዳለ በደንብ ጥብቅ ጥምጥም ብላበት አንገቱን ፡ ጉንጩን አንድም ሳታሥቅር ከሳመችው በኋላ ልጇን አቤልን አቅፋ ባለቤቷ ሻንጣውን እየገፋ ወደ ሚጠብቃቸው መኪና ውስጥ ገብተው ሶስቱም ከኋላ ወንበር ተቀመጡ ። አቤል እናቱን በሁለቱም እጆቹ እቅፍ አድርጓት እላይዋ ላይ ተኝቶ ቀና ሲል አይን ለአይን ሲገናኙ። በዚያ ቅፅበት ዓይኑን ሳም አደረገችው ። « እናቴ እጅግዬ ተመልሰሽ ትሔጃለሽ ? » አላት ፧« አልሔድም አባትዬ » ብላ እንደገና እቅፍ አድርጋ ሳመችው። መኪናቸው ከኤርፖርት ወጥታ በቀለበት መንገድ ወደ መገናኛ አቅጣጫ ሸመጠጠች ለአይንም ተሰወረች።

ወይ አሳይለም. . ! እንዲህ ነው እንዴ. . . !

እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አጭር ልብ ወለድ

ልብ ወለድ www.bawza.com

በልያት ነብዩ

Page 16: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ �6ገጽ �6

እዚህ እያሳየህ እንዳለኸው ለማዘጋጀት አላሰብክም ነበር ?

ጎሳዬ ፡ የሚገርመው ነገር አዲስ አበባ እንደዚህ አይነት ዝግጅት በትልቁ ለማዘጋጀት እያሰብኩ ባለሁበት ወቅት ነው ወደዚህ ሃገር በቶሎ መምጣት እንዳለብኝ ከፕሮምተሬ ጋር የተነጋገር ነው። ልክ እዚህ ሃገር እንዳዘጋጀሁት በአውሮፓና በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ ለሚግኙ አረብ ሃገር ከተሞች ውስጥ እንደ ዱባይ ፡ አቡዳቢ ፡ ባህሬን የመሳሰሉት ሃገሮች ላይ ከሰራሁኝ በኋላ በሃገሬ ላይ በትልቁ ቆንጆ ዝግጅት አዘጋጃለሁ ብዬ አስባለሁ።

ባውዛ ፡ የጎሳዬ የሙዚቃ ህይወት አሁን እስካለህበት ድረስ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ?

ጎሳዬ ፡ ልክ እንደ አብዛኛዎቻችን ያው ከትምህርት ቤት ነው የጀመርኩት። በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች ለምሳሌ ያህል መስታወት የሙዚቃና የቲያትር ክበብ፡ የክስታኔ ባንድና በመሳሰሉት ውስጥ እየሰራሁ በሸዋ ጌጥ ሆቴል ውስጥ ናይት ክለብ ለአራት ዓመት ያህል ሰርቻለሁ ። ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ቴክ ፋይፍ ፡ኢቫንጋዲና አሁን ሳታማህኝ ብላ የሚሉት ስራዎቼ እየተቀባበሉ የመጡት ማለት ነው።

ባውዛ ፡ አዲሱን ስራ ለመጨረስ ስንት ዓመት ፈጀብህ ማለት ነው?

ጎሳዬ ፡ አራት አመት አካባቢ።

ባውዛ ፡ አራት አመት በጣም የቆየህ አይመስልህም ?

ጎሳዬ ፡ እኔና አለማየሁ ሂርጶ(አሌክስ) ኢቫንጋዲን ስንሰራ በጣም ነው

ተጠንቅቀንና ለፍተን የሰራነው ። የአሌክስ አስተዋፆ ቀላል አልነበረም ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከአሌክስ ጋር ተነጋግረን ወደፊት ተገናኝተን በጋራ አንድ ላይ እስክንሰራ ድረስ ተለያይተን መስራቱ ጥሩ መሆኑን ተስማምተናል ። ኢቫንጋዲ ላይ የነበሩትን እነዛን የአሌክስን ጥሩ ስራዎች ብቻዬን ሸፍኜ ስሰራ ጊዜ ያስፈልገኛል ። በጠቅላላው ጉዳዩ ከጊዜው ጋር አይደለም። ትልቅ ኃላፊነት እስከተጣለብኝ ድረስ ጥሩ ስራ መስራት አለብኝ ለዚህ ነው የቆየበት ምክንያት ከዚህ በተጨማሪም አሌክስንም አንዳንድ ነገሮች አግዘው ነበር።

ባውዛ ፡ እንዴት ነው አለማይሁ ሂርጶ (አሌክስ) አዲስ ስራ ጨረሰ እንዴ ? ምንድነው አንተ ለአሌክስ ያደረግከው አስተዋፅዎ?

ጎሳዬ ፡ አሁን የደረሰበትን ባላውቅም አንድ ሶስትና አራት ዜማዎችን ሰርቼለታለሁ። እነሱን ተቀብሏቸዋል። ያው እንደሚታወቀው አሌክስ የሚኖረው ኖርዌይ ነው። የተለያዩ ስራዎችን እየሰበሰበ መሆኑን በስልክ አጫውቶኛል።ባውዛ ፡ አዲሱ ስራህ ውስጥ ምን ምን ለየት ያሉ ነገሮችን ለማካተትሞክረሃል? ጎሳዬ ፡ እንደሚታወቀው ኢቫንጋዲ ለሳታማኸኝ ብላ ትልቅ ምንጭ ነው ። ሳታማሃኝ ብላ የሚለው በራሱ ሙዚቃውን ከሰጠኝ ልጅ እውነተኛ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው ። ስሜት የሚነካና ትርጉም ያለው ስራ ነው ። ኦሮምኛ በአማርኛውም እንደዚሁ ለየት ያለ ስሜት አለው። ባውዛ በስራው ላይ እነማን ተሳትፈውበታል?

ጎሳዬ በሙዚቃው በኩል ምናልባት

ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ። አቀናባሪዎቹ ብቻ ስምንት ናቸው። በተጨማሪ ቤዝ ጊታር ፡ክራር፡ማሲንቆ፡ ሳክስፎንና የመሳሰሉት የገቡ አሉ ። እነዚህን ሁሉ ስንደምራቸው አስራ ሁለትና አስራ ሶስት ሙዚቀኞች ተሳትፈዋል ። ከነዚህም ውስጥ በዋናነት አበጋዝ፡ኤልያስ መልካ ፡ ዳዊት ጥላሁን ፡ሁናንተ፡አማኑኤል ይልማ ፡ አሸብር ፡ ሳሚ የሚባሉ ሙዚቀኞች ተሳፈዋል።

ባውዛ ፡ በግጥምና ዜማውስ በኩል?

ጎሳዬ ፡ ሃብታሙ ቦጋለ ፡ታመነ መኮንን ፡ እራሴ በአብዛኛው እንዳለ አድምቄ ከዜማው በኩል እና ታምራት ደስታም እናትዬ የሚለውን ስራዎች አግዘውኛል ። ያው በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰግናቸው አላልፍም። ባውዛ ፡ ስራውን ከጨረስክ በኋላ ለማን ነው የሰጠኸው?

ጎሳዬ ፡ ለኤክትራ ሙዚቃ ቤት ነው እዚህም ሃገር በወኪሉ አልፋ ፕሮዳክሽን በኩል ጥሩ እንዲሰማ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አድርገውኛል። ባውዛ ፡ የኢቫንጋዲን የሙዚቃ ቅንብር ማን ነበር የሰራው? ጎሳዬ ፡ ሙሉውን ኤልያስ መልካ ነው የሰራው።

ባውዛ ፡ በዲቪዲ መልክ የተለያዩ ስራዎችህን ለመስራት አላሰብክም? ጎሳዬ ፡ እነዚህን በዲሲ፡ በኤልኤ፤ በዳላስና በሜኒሶታ ያዘጋጀኋቸውን ስራዎች ተቀርፅዋል። አገሬ እንደገባሁ እነሱን ኤዲት አድርጌ ዲቪዲውን እለቀዋለሁ።

ባውዛ ፡ አንዳንድ በሙዚቃው አለም

ላይ የሚገኙ አንጋፋ አርቲስቶች ሂስ ሲሰጡ በዚህ ዘመን ያሉ የወጣቶቹ ስራ ለፈረንጆች እጅ ወደ ላይ ሳይባል እንደሰጠ ምርኮኛ ቀድመው እጃቸውን ሰጥተዋል ።ጥርት ያለውን ሃገረኛ ስሜትያላቸውን ስራዎች እየናፈቁን መተዋል ። እነዚህ ስራዎች ባህላችን እያጠፉት ነው ። ይላሉ። አንተ በዚህ ላይ ምን ያህል ትስማማለህ?

ጎሳዬ ፡ በዚህ በኩል ይህን ነገር እኔ ብዙም አልስማማበትም ። ምክንያቱም ሙዚቃ በራሱ ቋንቋ ነው ።ለምሳሌ አውሮፓውያን ወይንም አሜሪካዊያን የነሱን የሚመስል ስራ በአማርኛ ቀይጠን ብንሰጣቸው እንደውም ይህ ስራ የኛን ሃገር ይመስላል ብለው ይስባቸዋል እንጂ ባሕላችንን እያጠፋ ነው ለሚለው እንግዲህ በኔ በኩል በተቻለኝ መጠን ኦሮምኛ በአማርኛ ላሊበላ እያልኩ ድሬድሬ የሚለውን በራሳችን እስክስታና ከክራር ጋር የተያያዙም በጣም ጥሩ ሃገረኛ ስሜት ያላቸውን ስራዎችን ሰርተናል የቱ ጋር እንደ ጎደለ ባይገባኝም ይህ ነገር ለምሳሌ ላቲኖች ወደ ዓለም ሙዚቃ የገቡት ከተሰሩ ሙዚቃ ጋር እያመሳሰሉ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በሃገራችንም በድሮ ጊዜም ቢሆን አንጋፋዎቹ ድምፃዊያን ሳይቀሩ ከሱዳን ሜሎዲ እየወሰዱ የሚሰሩበት አጋጣሚም ነገር። በኛ በወጣቶቹ ላይ ብቻ ተተኮረ እንጂ ድሮም ያለ ነገር ነው አዲስ ነገር አይደለም።

ባውዛ ፡ ጥርት ያለው ባህላችን ከዘመናዊ ሙዚቃ ጋር ቢሰራ ኖሮ ይሄኔ የት በደረስን ነበር። በቀጥታ የውጪውን ስራ በመኮረጅ ስም በማጥፋት ላይ የሚገኙም አሉም ይላሉ ?ጎሳዬ ፡ ባይሆን እዚህ ላይ እደግፋቸዋለሁ። በኔ በኩል የሃገራችን ሙዚቃ ከዘመናዊው ጋር ተቀላቅሎ ቢሰራ ምን ያህል ሊጣፍጥ እንደሚችል

ጥበብና ባህል www.bawza.com

ወደ ገጽ 8 ዞሯል

ከገጽ 7 የዞረ

Page 17: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ �6 Volume 1, Issue 2 ገጽ �7ገጽ �6

ሶስት ወንዶችና አንድ ሴት ልጅ አሉን። የመጨረሻዋ ሴት ልጃችን �9 ወሯ ነው።

ባውዛ ፡ እንዴት ነው አቶ አብዱልፈታህ ስራሽን የማገዝና አብሮ የመስራት ሁኔታ አለው?

ቴስቲ ፡ አዎ አብረን እንሰራለን። እሱ ግን የራሱ ስራ ስላለው በዋነናነት ያንን ነው የሚሰራው። ባውዛ ፡ በተለይ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ሃይስኩል ይወድቃሉ ወደ ሌላም መጥፎ ባህሪ ውስጥ ሲገቡ እያስተዋልናቸው ነው ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው ብለሽ ታስቢያለሽ?

ቴስቲ ፡ እኔ እንደሚመስለኝ ቤተሰብ ብዙውን ጊዜ ከልጆቹ ጋር በቂ ጊዜ አሳልፈው ልጆቻቸው በፍቅር የሚፈልጉትና የማይፈልጉትን ነገሮች ማወቁ ጥሩ ነው። በተለይ ወንድ ልጅ ከፍ እያለ ሲመጣ ከጓደኞቹ ይልቅ ከአባቱ ጋር ብዙውን ጊዜ ቢያሳልፍ ጥሩ ነገር ከአባቱ ይቀስማል።

ባውዛ ፡ ዛሬ ላይ ሆነሽ ትላንት ይህን ባደርግ ኖሮ ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ እደርስ ነበር የምትይው ነገር አለሽ?

ቴስቲ ፡ እኔ በሕይወቴ ውስጥ ባለፈ ነገር ምንም አይቆጨኝም። ምክንያቱም ይነስም ይብዛም ከትላንቱ ዛሬ ጥሩ ልምድ ነው የማዳብረው።

ባውዛ ፡ በትምህርትሽስ በኩል?

ቴስቲ ፡ በርግጥ ብማር ደስ ይለኝ ነበር ። አሁንም ቢሆን በ (Early child hood Department) ውስጥ ትምህርት እጀምራለሁ ። ከሰርተፊኬት ፤ አሶሺየት ዲግሪ ፡ ባችለር ዲግሪና ማስተር ዲግሪ እያልኩ እስከ ፒ ኤች ዲዬ ድረስ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅብኝ ከስራዬም ጋር ተያያዥነት ስላለው እስከ መጨረሻው ድረስ አላህ ካለ እማራለሁ።

ባውዛ፡ ለቤተሰብሽ ስንተኛ ልጅ ነሽ? ቴስቲ ፡ እኔና እህቴ መንታ ነን ፡ ለቤተሰባችን ዘጠነኛ ልጆች ነን።

ባውዛ፡ ከህቶችሽ ጋር ይህን ት/ቤት ከፍታችኋል ። የወደፊ እቅዳችሁስ ምን ይመስላል?

ቴስቲ ፡ አሁን መቶ አርባ አንድ ህፃናትን የሚይዝ ቦታ ነው ያለን። ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ ሌላ እስከ 250 ተማሪዎች ድረስ የሚይዝ ቦታ ላይ ነው መክፈት የምንፈልገው ። ከዛም በየሃገሩ አንዳንድ እንዲኖረን እንዲሁም ሁሉ ነገር ባሰብነውና ባቀድነው ዕቅድ ከሔደልን ኮርፓሬሽናችንን(franchise) በማድረግ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ቦታውንና ሁሉን ነገር እኛ ከፍተንላቸው ለኛ የተወሰነ ክፍያ እየከፈሉን እራሳቸውንና ሌሎችንም የሚጠቅሙበትን መንገድ መፍጠር እንፈልጋለን።

ባውዛ፡ እዚህ ሀገር ብዙ ሀበሾች በግሮሰሪዎች ፤ በሱፐርማርኬቶችና በሆቴሎች አካባቢ ያሉ ቢዝነሶችን ብቻ ነው የሚከፍቱት። ወደ ሌላ ቢዝነስ ውስጥ ገብተው ሲሰሩ አናያቸውም ለምን ይመስልሻል?

ቴስቲ ፡ ማንኛውም ሰው ምንም አይነት ነገር ለመክፈት ልምድ ፤ ድፍረትና በገንዘብ በኩል ጠንካራ መሆን ያስፈልገዋል ። ለምሳሌ አንድ ሰው ዴይኬር ሊከፍት ሲል የዴይኬር ላይሰንስ ለማግኘት በመጀመሪያ ቤቱ የግላቸው ሊሆን ይገባል ። ያም ቢሆን እንደየ ካውንቲው ይለያያል።ለምሳሌ የሰፈሩ ሰዎች በዚህ ሰው ምክንያት ሰፈራችን ውስጥ ብዙ መኪና ስለሚገባና ስለሚወጣ ሰፈራችን ውስጥ ዴኬር አንፈልግም ብለው ከተቃወሙ ላይሰንስ ሊሰጥ አይችልም ። ሌላው እኛ

አራት በመሆናችን በደንብ ነው የምንይዘው ። ምንም እንኳን የራሳችን ስራ ቢኖረንም የገንዘብ እጥረት አይገጥመንም። አንድ ሰው ጥሩ ሰው እስካላገኘ ድረስ ብቻውን ከሆነ የተለያዩ ሰዎችን ስለሚወክል የገንዘብ ምንጩ ሊዳከምበት ይችላል።

ባውዛ፡ የኢትዮጵያውያንን ልጆችስ እየጠበቅሽ ነው?ቴስቲ ፡ አዎ ባውዛ፡ ስንት ናቸው?ቴስቲ ፡ ሁለት ናቸው።ባውዛ፡ ቁጥራቸው ያነሰው ለምን ይመስልሻል?

ቴስቲ ፡ ይመስለኛል ብዙ ኢትዮጵያውያን በሰራተኛ ልጃቸውን ቤታቸው ውስጥ ያስጠብቃሉ። የዚህ ደግሞ ጠቃሚም ጎጂም ጎን አለው። ለምሳሌ ቤት ውስጥ ሲጠበቁ ከማያነብና ከማይጽፍ ሰው ጋር ሊሆን ይችላል። ሰራእኞቹ ቤተሰብ ከሔደ በኋላ ለምንም ነገር ግድ ሳይኖራቸው ቁጭ ቲቪና ሌሎች ነገሮችን እንደሚከታተሉ እንሰማለን። ሌላው አንድ ሕፃን ከሌላ ሕፃን ጋር ሲውል እርስ በርሳቸው በጥሩ ሁኔታ ይማማራሉ ። በተጨማሪም እዚህ እራሱን የቻለ ከአጠገባቸው ለደቂቃ እንኳን ዞር ሳይል ፡ የሚያበላቸው ፡ የሚቀይርላቸውና የሚያስተምሯቸው የተለያየ ዕውቀት ያላቸው አስተማሪዎች ናቸው። ሌላውና ዋናው እኔ ስራዬ ብዬ የተለያዩ ኢትዮጵያውያን የሚበዙበት አካባቢ ድርጅታችንን ስላላስተዋወቅነው ነው። ወደፊት ግን በሰፊው እያሰብንበት ነው።

ባውዛ፡ ወደ ኢትዮጵያ ሔደሽ ተመሳሳይ ድርጅቶች የመክፈቱ ሁኔታስ አላሰብሽም?

ቴስቲ ፡ ከፍተኛ ፍላጎት ነው ያለኝ። እዚህ ካደግን በኋላ የመጀመሪያው አላማዬ ኢትዮጵያ ሔደን መክፈት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ብቻ ሳሆን ድሮም ጭምር ነው ያማስበው እንደውም እህቶቼን ቤት ካገኛችሁ ንገሩኝ መጥቼ አስከፍታለሁ እላቸው ነበር።

ባውዛ፡ በአብዛኞቹ የኢትዮጵያዊያን በጋራ ሆነው ሲሰሩ አናስተውላቸውም። እንደውም ሀገር ቤት የሌለ እዚህ ሀገር በተገላቢጦሽ ሁኔታ ሲከፋፈሉ ሲራራቁ እናያቸዋለን። ይህ ለምን ይመስልሻል?

ቴስቲ ፡ እኔ ለምን እንድሆነ በትክክል አላውቅም። እኔንም አንዳንዴ ያሳስበኛል። እኔ እንደሚመስለኝ እርስ በእርሳችን የምንራራቀው ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን ባለማግኘታችን ነው። ባውዛ፡ በጋራ ሆነን ሁሉም የኢትዮጵያዊያን መሃበረሰቦች የሚሰበሰቡበት ትልቅ ት/ቤት ፤ ዪኒቨርሲቲና ፡ የልጆች መዋያ ፡ እራሳችን በራሳችን ከቁጥራችን ብዛት አንጻር መስራት አንችልም ነበር?

ቴስቲ ፡ ይቻላል ለምን አይቻልም? አሜሪካኖችን ብናይ (volunteers) የሚሉት ነገር አላቸው። ለምሳሌ አንዲት ሴት በጣም ችግረኛ ከሆነችና ባል ከሌላት የፈለገ ቢሆን ሰዓታቸውን አጣበው ቤት ይሰሩላታል። እንደውም ሌላም ነገር ያደርጉላታል። የእኛ ሰው ጋር ግን ይህን አላስተውለውም።

ባውዛ፡ በተለይ ብሩህ አእምሮ ሰንቀው አዳዲስ ነገሮችን መክፈት ለሚፈልጉ የሕብረተሳባችን ክፍል አንቺ ምን የምትያቸው ነገር አለሽ? ቴስቲ ፡ በመጀመሪያ ደረጃ አላማ ሊኖራቸው ይገባል ። እኔ በዚህ ጊዜ እንዲህ መሆን አለብኝ ብሎ ከትንሽ ነገር ተነስቶ የታሰበበት ቦታ መድረስ ይችላል ። ዋናው ነገር የሚያስቡትን በተግባር መለወጥ ያስፈልጋል።

ባውዛ፡ አመሰግናለሁ ።

የፍቅረኞችን ቀን በማስመልከት በርካታ አበቦችን ሸጡ

በዘጠነኛው መንገድ ላይ የሚገኘው ኮንቬንሽን አበባ ቤት የፍቅረኞችን ቀን (valentine day ) አስመልክተው በርካታ ቀይ አበቦችን መሸጣቸውን የድርጅቱ የአበባ ዲዛይነርና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ኑቢያ ፋሲል ለባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታውቀዋል። አንዳንድ አበቦች በየአገሩ የተለያዩ ትርጉሞች እንዳላቸዋና ብዙውን ጊዜ ቀይ አበባ ለሴትም ሆነ

ለወንድ በጣም መውደዳቸውንና ማፍቀራቸውን ሲገልፁበት፤ ሮዝና ቢጫ ጓደኝነትን እንደሚያመለክት በሌላ በኩል አንዳንድ ሃገሮች ደግሞ መጠራጠርንም የሚጠቀሙበት አገሮች እንዳሉ ይታወቃል ። ነጭ አበባ ብዙውን ጊዜ ለሐዘንም ለደስታም ሲያገለግል በተለይ ንፁህነትን ያመለክታል ። አበቦች በህብረት ሲቀላቀሉ የትለየ ትርጉም ሳይኖራቸው ለዓይን በጣም ስለሚስቡና ስለሚያስደስቱ ሰዎችን ለማስደሰት ይጠቀሙበታል። ከተለመዱት የአበባ ዘሮች ውጪ በርካታ እንደ ብርቱካናማና አረንጓዴ መልክ ያላቸው አበቦች መኖራቸውን ወ/ሮ ኑቢያ አስረድተውናል ።

www.bawza.comጥበብና ባህል ከገጽ �4 የዞረ

Page 18: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2

ሰሞኑን ከባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ዘጠነኛ ጎዳና(9th ST) ላይ ባሉ የንግድ ድርጅቶች ውስጥ ማይክና ካሜራችንን ይዘን ቤት ለእምቦሳ እንደሚባለው ሁሉ ቢዝነስ ለእምቦሳ ብለንላቸው ነበር። አንዳንድ በአካል ያላገኘናቸውንም በስልክ ለማግኘት ሞክረናል።ወደዋናው ነጥባችን ከመሄዳችን በፊት አንድ አንባቢያችን ወደ ቢሯችን መጥቶ ስለ ዘጠነኛው ጎዳና ያጫወተንን እናውጋችሁ፡፡ቀኑ እሁድ የእረፍት ቀን ነበር ወደ አንድ ጓደኛው ጋር ለመጫወት በሚሄድበት ወቅት ። ጓደኛው ልጆቹን ሰብስቦ እንቆቅልሽ ሲያስተምራቸው ይደርሳል ። ጠያቂ - እንቆቅልሽ/ህ?መልስ ሰጪ- ምን አውቅልሽ/ህጠያቂ------------------- ?መልስ ሰጪ - በቃ አላወቅኩትም።ጠያቂ- እንግዲያውስ አገር ስጠኝመልስ ሰጪ - ዘጠነኛውን ጎዳና (9th ST)ጠያቂ- ዘጠነኛ እስትሪት ገብቼ ምን አጥቼ ሁሉ በ እጄ ሁሉ በደጄ……. እየተባባሉ ሲጠያየቁ ሰማሁና ገረመኝ ብሎ አጫወተን ። እኛም በአንባቢያችን ገጠመኝ መሰረት ነው ርዕሳችንን ዘጠነኛው ጎዳና (ናይንዝ ስትሪኢት) ገብተን ምን አጥተን ሁሉ በ እጃችን ሁሉ በደጃችን ብለን ልንፅፍላችሁ የተነሳነው።

የዝግጅት ክፍላችንም ቢሮ በዚሁ በዘጠነኛው ጎዳና ላይ ስለሚገኝ ወጪና ወራጁን ሁሉ ሳይቀር አካባቢውን በደንብ ለመቃኘት ዕድል አግኝተናል። ብቻ በአጠቃልይ ወደ ዘጠነኛው ጎዳና ሲመጡ የማያገኙት ድርጅት አለ ቢባል ይደነቃሉ። ምክንያቱም በሁሉም ቢዝነስ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን መሰብሰቢያና መገበያያ ማእከል ስለሆነ አካባቢውን ለየት ያደርገዋል።ከብዙ በጥቂቱ የተለያዩ ዘመናዊና ባህላዊ ሬስቶራንቶች፡ ኬክ ቤት፡ ግሮሰሪዎች፡ የወንድና የሴት ፀጉር ቤት፡ ፎቶ ቤት፡ የታክሲ ድርጅት ቢሮ ፡ ሱፐር ማርኬቶች ፡ የዲዛይንና የህትመት አገልግሎት መስጫ ፡ ሙዚቃ ቤቶች ፡ የአበባ መሸጫ ቤት፡ የቤትና የመኪና ሻጭና አጋዢዎች(brokers) ቢሮ ፡ የሪል ስቴት ካምፓኒዎች ፡ የጠበቃ ቢሮ ፡ የትርጉም ስራዎችን የሚሰሩ በርካታ በስራቸው ትጉዎችና በቀልጣፋነታቸው የሚታወቁ ሩጫቸው ከጊዜ ጋር የሆኑ ድርጅቶች አሉ።

ወደነዚህ ተቋሞች በቀን ምን ያህል ሰዎች ይመላለሳሉ ብትሉን እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ መገመት ያዳግተናል ። አንዳንድ ለደቂቃ እንኳን እረፍት የሌላቸው ቢዝነሶችን መኖራቸውንም ታዝበናል ። አንዳንዴ እንደውም የበርካታ ሰዎች መሰብሰቢያና መቀጣጠሪያ እዚሁ በመሆኑ ይመስላል በተለይ በምሳ ሰዓትና በጀንበር መጥለቂያ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ሁሉ ስለሚጠፋ መኪና በመኪና ላይ ሲደራረቡ ሰፈሩ በብዙ ሃበሾች ትርምስ ፤ ግርግር እና መጨናነቅ ሲወጠር እንዲሁም በሃበሻ ባህላዊና ዘመናዊ

ሙዚቃ ሲደምቅ ያመሻል። ከዘጠነኛው ቢዝነስ አሶሴሽን በኩል በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ለሰፈሩ ደህንነት ሲባል ፖሊስ በአካባቢው ላይ ከፍ ያለ ካሜራ በመስቀል ጥበቃውን ካጠናከረ ሰነባብቷል።ይህ በመሆኑም በፊት ከነበረው ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ተዝናንቶና ተጫውቶ በሰላም ወደየቤቱ እየገባ ይገኛል።

ሁሉም ሬስቶራንቶች የራሳቸው የሆነ የቤቱ ስፔሻል (መለያ) ምግብና መጠጥ እንዳላቸው አስተውለናል። ለምሳሌ በዶሮ ወጥ ፡ ጎረድ ጎረድ ፤ ጥብስ፡ ጎረድ ጎረድ ጥብስ ፤ ዱለት ፡ ሽሮ፡ በያይነቱ ፤ የጎድን ጥብስ ፤ ዝልዝል ጥብስ ፡ ላዛኛ ፡ እና የመሳሰሉትን ስፔሻል ምግባቸው ን ይዘው ኪሰዎን በማይጎዳ መልኩ ደንበኞቻቸውን እያስደሰቱ በማስተናገድ ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።በአጠቃላይ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሃበሾች ከአውሮፓም ሆነ ከሌላ እስቴቶች በሚመጡበት ወቅት ዘጠነኛውን ጎዳና ላይ ትንሹዋን ኢትዮጵያ (little ethiopia) በሚል ቅፅል ስሟ የምትታወቀውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እግራቸው ሳይረግጧት እንደማይመለሱ ይታወቃል።

በዚህ ዘጠነኛ ጎዳና ላይ የሚገኙ የንግድ ተቋሞች መሃል እቴቴ ሬስቶራንት ፤ ሳሎን ሪቫይቭ ፤ንግስተ ሳባ ሬስቶራንት፤ አክሱም ሬስቶራንት ፤ኤክስፖ ሬስቶራንት ፤ ላካርቦናራ የጣሊያን ሬስቶራንት ፤ የኢትዮጵያዊያን ንግድና ማስታወቂያ ድርጅት ፤ የኢትዮጵያን የሎው ፔጅስ ፤ባውዛ ጋዜጣ ፤ ኮንቬሽን የአበባ መሸጪያ ፤ ዲጄ ፎቶ ቤት፡ የኛ ሬስቶራንት ፤ናሆም ሪከርድስ ፤ ፍቅር ሳውንድ ፤ ራስ ዳሽን ሬስቶራንት ፤ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች መሃበር ፤ ጊፍት ሪል እስቴት ፤ዙላ ሬስቶራት ፤ ሊከር ሃውስ ፤ ሃበሻ ገበያና ሬስቶራንት ፤ ንግስት ሳባ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ፤ ሼዝ ሃረግ ኬክ ቤት ፤ ሻሸመኔ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ፤ ናይንዝ እስትሪት ሱፐርማርኬት ፤ ተስ ታክስ ኤንድ አካውንቲንግ ፤ ግሎባል ቢዝነስ ብሮከርና የመሳሰሉት ድርጅቶች ከብዙ በጥቂቱ ይገኛሉ።

አብዛኞቹም ድርጅቶች የናይንዝ እስትሪት ቢዝነስ አሶሰሽን (9th ST busenes as-sociation) አባል መሆናቸውንም ለማወቅ ችለናል።በሚቀጥለው ዕትማችን ላይ ከናይንዝ እስትሪት ቢዝነስ አሶሴሽን ፕረዘዳንት የሆኑትን ወ/ሮ የሺመቤት ተስፋዬ ስለማሃበሩ አጀማመር ፤እስካሁን ምን ምን ስራዎችን እንደሰራና ስለወደፊት እቅዶቹ ስለምናናግራቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች ካሏችሁ በአድራሻችን ብትልኩልን መልስ የሚሰጡበት መሆኑን እናሳውቃልን።

ውድ አንባቢዎቻችን በሚቀጥሉት እትሞቻችን ላይ ሌሎች ሃበሾች የሚበዙባቸውን ሰፈሮች ስለምንዳስስ ከወዲሁ ስለሰፈራቹ የተለያዩ መረጃዎችን እያሰባሰባችሁ ጠብቁን።

ዘጠነኛው ጎዳና ( 9th St) ገብተን ምን አጥተን ሁሉ በእጃችን ሁሉ በደጃችን።

www.bawza.com

ገጽ �8

Page 19: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ �9

www.bawza.com

Hassete Melaku

ለህፃን ሃሴት መላኩ እንኳን ወደዚች ዓለም በሰላም መጣሽ ከናትሽ ሰላም እና ካባትሽ መላኩ (በጣም እንወድሻለን)

New Openings/በቅርቡ የሚከፈት

Queen St Gourmet Groceryእንጀራ፣ቅቤ፣አንባሻ

ቅመማ ቅመምና የመሳሰሉትን ይዞላችሁይመጣል!

��0� Queen St Alexandria VA 22314

Tel 703 992 6179የሚከራይ ቢሮ

በዋሽንግተን ዲሲ ዘጠነኛው ጎዳና ላይ በኢትዮጵያ የሎፔጅስ ህንፃ ውስጥ ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች ስላሉን በ202 387 9302/3 ደውለው ያነጋግሩን።

ምስጋና ከዘጠኝ ዓመት በፊት በደረሰብኝ የመኪና አደጋ ተርፌ በ እግዚያብሄርና በወገኖቼ ድጋፍ ዛሬ በ እግሬ ለመንቀሳቀስ ችያለሁ በተጨማሪ በፈጣሪ ፍቃድ ከሞት ተርፌ ሶስተኛ ልጅ በማግኘቴ ታላቅና ድንቅ ደስታ ይሰማኛል ለሑሉም ያበቃችኝ ከጎኔ ሆና ለተንከባከበችኝ ባለቤቴም ትልቅ የሆነ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ። ፍቃደ ገብረመድህን

ገጽ �8

ከቤትዎ ወዴ ኤርፖርት ወይም ከተለያዩቦታዎችና ለተለያዩ ዝግጅቶች ፋንታሁንን ደውለው ያነጋግሩ

ከገጽ 9 የዞረ

Washington DC NW ለrhode Isld. ሜትሮ ቅርብ የሆነ የራሱ መታጠቢያ ፤ ማብሰያና ምግብ ቤት ያላቸው 2 ክፍሎች በጋራ ወይም በተናጥል ለማከራየት 202 360 29�5 ይደውሉ።

Washington DC NW 434 Sheperd ST ከፒቶርዝ ሜትሮ 5 ደቂቃ እርቀት ላይ የጋራ ማብሰያ ያላቸው በግሩፕና በተናጥል 3 ክፍሎችን ለመከራየት 240 472 7829 ወይም 240 472 8360 ይደውሉልን።

Maryland (ሜሪላንድ) New Carrlton ,MD ለአውቶቡስና ለሜትሮ አመቺ የሆነ የራሱ መውጫ ማብሰያና ልብስ ማጠቢያ ያለው 2 መኝታ ቤት ያለው ለመከራየት። ( 30� ) 257-3� 40 ይደውሉልን።

Clinton , MD Branch Ave ላይ ለመድኃኔ ዓለም ቤተክርስትያን አካባቢ ቅርብ የሆነ ፡ የራሱ መውጫ ፡ መታጠቢያ ማብሰያና ልብስ ማጠቢያ ያለው Basement ውስጥ � ክፍል ለማያጨስና ለሚነዳ ወንድ ለመከራየት ( 240 ) 744 -6546 ወይም ( 30� ) 868 – 7�62 ይደውሉ ።

Hyattsville, MD ለ PG plaza metro & Maryland Univer-sity በጣም ቅርብ የሆነ የጋራ መታጠቢያና ማብሰያ ያለው � ክፍል ለመከራየት ( 202 ) 257-7229 ይደውልሉን።

New Carrolton & Hyattsville ,MD ከሜትሮ አውቶቡስና ሾፒንግ በእግር ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ ክፍሎች ለመከራየት (204) 432-4078 ወይም 30�-73�-7� �� ።

Adelphi, MD new Hampshire Ave. East-est HWY col-

lege park አካባቢ ልብስ ማጠቢያና ኬብል ያላቸው 2 ክፍሎች ለመከራየት ( 703) 300-�3�3 ይደውሉ ።

Silver Spring MD, univer-sity Blvd & caddington Ave. አካባቢ የራሱ መውጫ መታጠቢያና ማብሰያ ያለው efficiency Basemen $550 ለመከራየት ( 57�) 332 3949 ይደውሉ ።

Silver Spring ,MD univer-sity Blvd & Caddington Ave ላይ ለአውቶቡስ ቅርብ የሆነና መታጠቢያና ማብሰያ የጋራ ያለው � ክፍል ለማያጨስ ሰው $ 330 ለመከራየት ( 30�) 385 3266 ይደውሉ ።

Maryland, New Hamp-shire Ave. & East-West Hwy አራዳና ሸገር ገበያዎች አካባቢ ልብስ ማጠቢያ ያላቸው ክፍሎች ከ $350 እስከ $ 450 ድረስ ለመከራየት (240) 432 9045 ይደውሉ ።

Adelphi, MD university Blvd & Riggs Rod. አካባቢ ለሾፒንግ ቅርብና መኪና ማቆሚያ ያለው ሲንግል ሃውስ ውስጥ � ክፍል ለመከራየት (202) 247 �6�3 ይደውሉ ።

Maryland ከ Glenmont metro በእግር 5 ደቂቃ ርቀት ላይ � መኝታ ኮንዶ ለመከራየት (30�) 933 80�8 ይደውሉ ። (ካጡን መልዕክት ይተዉ )

Gaithersburg, MD shady Grove Metro አካባቢና ከአውቶቡስና ከሾፒንግ � ብሎክ ርቀት ላይ � ክፍል ለማያጨስ ሰው ለመከራየት (703) 20� 943� ። ከ 6፡30በኋላ ይደውሉ ።

Silver Spring ,MD ለ Glen-mont Merto ቅርብ የራሱ መውጫ መታጠቢያና ማብሰያ እንዲሁም ሳሎን ያለው ቤዝመንት ወይም ሙሉ ቤቱን ለመከራየት (240) 462 8823 ። ይደውሉ ።

Clinton,MD Branch Ave ላይ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስትያን አካባቢ የራሱ መውጫ ኬብል ልብስ ማጠቢያ መታጠቢያና � ክፍል ለሚነዳ ለማያጨስ ሰው ቤዝመንት ውስጥ ለመከራየት (202) 744 6546 ወይም (30�) 8687�62 ይደውሉ ።

Silver Spring MD �3�9 Dilston Rd ላይ ለትራንስፖርትና ለገበያ አመቺ የሆነ የራሱ መውጫ መታጠቢያ ማብሰያና ሳሎን ያለው � ክፍል ለመከራየት (202) 27� 22 94 ።

house for saleየሚሸጥ ቤት

ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በቅርቡ የታደሰ 4 ዩኒት ያለው አፓርትመንትለቢሮ ወይም ለመኖሪያ8 ክፍሎች 4 ባዝሩም4 ኪችን ያለው መግዛት የምትፈልጉ ኢንቬስተሮች202-360-29�5 ይደውሉ

ለሽያጭ የተዘጋጀ ቤት ! በስፕሪንግ ፊልድ አካባቢ ለሜትሮ ቅርብ ለቤተሰብ ት/ቤት በቅርብ ያለ ለመኖሪያ የሚሆን 4( አራት ) መኝታ 2 (ሁለት ) መታጠቢያ ቤት ሁለት የራሱ መኪና ማቆሚያ ያለው ቤት ለመከራየትም ሆነ ለመግዛት ሲፈልጉ በ 703 597 6364 ይደውሉልን ።

CLASSIFIED SPACE

Page 20: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Volume 1, Issue 2 ገጽ 20ገጽ 20

allfreight ad

Advertise on Bawza and make your business grow to New heights

TEL 202 387 9322 or 202-3879302/3/

FAX 202-387-9301

1-877-752-2746www.allfreightshipping.com

4810 Beauregard Street, #100

Page 21: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

ገጽ 20 Volume 1, Issue 2 ገጽ 2�ገጽ 20

Page 22: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Sportswww.bawza.com

Ethiopia’s Bekele set a New World Record for two milesSource: Reuters

LONDON - Ethiopian Kenenisa Bekele set a world best for the men’s indoor two miles of eight minutes 4.35 seconds at a meeting in Bir-mingham, England, on Saturday.Bekele’s time was faster than the 8:04.69 mark set by fellow Ethiopian Haile Gebreselassie in 2003.“I’m very pleased. It’s incredible for me,” Bekele, the world and Olym-pic 10,000 meters champion, told BBC television.Norwegian Jaysuma Saidy Ndure won the men’s 60 meters in 6.56 seconds, with Briton Simeon Williamson in second in a personal best time of 6.57.

Williamson will hope his time is good enough to secure the second British place for next month’s world indoor championships in Spain alongside Dwain Chambers, whose selection has been a hot topic of debate this week because of the two-year ban he served for failing a drugs test in 2003.Chambers, who won last week’s British trials, was not invited to the Birmingham grand prix.Sweden’s Susanna Kallur, who set a world record of 7.68 seconds for the women’s 60 meters hurdles last week, easily won the event in Bir-mingham with a time of 7.75.In the men’s 400 meters, Canadian Tyler Christopher cruised to vic-tory in 45.80, while American David Oliver won the men’s 60 meters hurdles in 7.55.

Athlete of the MonthMamo Wolde(June 12, 1932 – May 26, 2002)

Considering the honors that he would even-tually win, the life and Olympic career of Mamo Wolde had very humble beginnings. Demisse (“Mamo”) Wolde an Ethiopian long distance track and road running athlete and winner of the marathon at the 1968 Summer Olympics was born in Diri Jille in 1951. He moved to Addis Ababa and joined the Impe-rial Bodyguard and later served as a peace-keeper in Korea from 1953 to 1955. At his first Olympic appearance in 1956, Wolde competed in the 800 m, 1,500 m and the 4x400 relay. He didn’t compete in the 1960 Summer Olympics at which Abebe Bikila became the first Ethiopian to win a gold medal. Wolde claimed his absence was due to the government’s desire to send him on a peacekeeping mission to the Congo dur-ing the Congo Crisis. According to him, in the government’s ensuing conflict with the Ethiopian Olympic Committee, who wanted him to compete, he didn’t get sent to either

event. Beginning in the 1960s, Wolde’s focus changed from middle distance races to long distances. He placed fourth in the 10,000 m at the 1964 Summer Olympics. After Abebe Bikila had won the 1964 Olympic marathon, Wolde became the second Ethiopian to win the title in that race. Earlier in the same Olympics, Wolde had already won the silver medal in the 10,000 m. In 1972, Wolde won a third Olympic medal at the age of 40, winning bronze in the marathon. He won the marathon race of 1973 All-Africa Games.Wolde died of an undisclosed illness and had been married twice and had three children; a son with his first wife and two children with his second wife.

ቀነኒሳ የዓለም የ2 ማይል ሩጫ ሪከርድ ሰበረለንደን፦ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፌብሩዋሪ �6 2008 በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተደረገው የዓለም የቤት ውስጥ የሁለት ማይል ርቀት የሩጫ ውድድር ላይ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸናፊ ሆነ።አትሌት ቀነኒሳ ያስመዘገበው የ8 ደቂቃ 04፡35 አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ከ2003 የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የነበረውን፣ የ8፡04፡69 ውጤት በማሻሻል መሆኑን ከሮይተርስ ያገኘነው ዜና ያመለክታል በዚህ ወቅት ቀነኒሳ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት ባገኘው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኑን ገልፅዋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከዚህ የ2 ማይል ክብረ ወሰን ባለቤትነት በተጨማሪ የዓለም የ�0.000 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት መሆኑ ይታወሳል።(ምንጭ ሮይተርስ)

Advertise on Bawza and make your business grow to New heightsTEL 202 387 9322 or 202-3879302/3/ FAX 202-387-9301

Page 23: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

zelalem ad

703.628-57�6Bakery & Wholesale

Page 24: 30/02/2008 የካቲት 22 ቀን 2000 ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFEbawza.com/wp-content/uploads/2011/03/issue2.pdf · ETHIOPIA’S ENDEMIC WILDLIFE The Gelada Baboon “የዋሽንቱና

Recommended