+ All Categories
Home > Documents > 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

Date post: 14-Feb-2018
Category:
Upload: buidung
View: 249 times
Download: 8 times
Share this document with a friend
27
/1/ ለምሥጢረ ቊርባን ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን ወይን በተመለከተ /Eucharistic Wine/ የቀረበ ሐተታ አዘጋጅ መጋቤ ሐዲስ መምህር ልዑለ ቃል አካሉ ዓለሙ ክብረ ቅዱሳን ፥ መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲያትል ዋሽንግተን 5500 south Roxbury St Seattle WA 98032 www.kibreqidusan.org [email protected] ጥቅምት/2008 /
Transcript
Page 1: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/1/

ለምሥጢረ ቊርባን ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን ወይን በተመለከተ

/Eucharistic Wine/

የቀረበ ሐተታ

አዘጋጅ

መጋቤ ሐዲስ መምህር ልዑለ ቃል አካሉ ዓለሙ

ክብረ ቅዱሳን ፥ መድኃኔ ዓለም

የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ሲያትል ዋሽንግተን

5500 south Roxbury St

Seattle WA 98032

www.kibreqidusan.org

[email protected]

ጥቅምት/2008 ዓ/ም

Page 2: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/2/

የጥናቱ ይዘት

መግቢያ

የቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ

የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

ሐዲስ ኪዳን

ቅዳሴያቱ ስለዚህ ምን ይላሉ ?

የቤተ ክርስቲያን ታሪክስ ስለዚህ ምን ይላል?

የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጸም ምስክርነት

የእኛ ገዳማት በኢየሩሳሌም ምስክርነት፦

የደረቀ ዘቢብ በውኃ በማሸት መቀደስ መቼ ተጀመረ ?

ፍትሐ ነገሥትና ሲኖዶስ ስለዚህ ምን ይላሉ?

ማጠቃለያ

Appendix 1 -Studies in Comparative Ritual Theology Fr. Shoenda Mahar Ishak,

Studies in Comparative Ritual Theology (Al-amba Ruweis 2000) 38- 43

የተነበቡ መጻሕፍት/ የመረጃ ምንጮች/

Page 3: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/3/

መግቢያ

ቤተ ክርስቲያናችን እንደ አገራችን ሁሉ እስላሞች ካየሉበት ዘመን ጀምሮ ከክርስቲያኑ ዓለም ተለይታ ፥ በእስላሞች

ተከባ ለብዙ ምዕት ዓመታት ኑራለች ፤ ይሁን እንጂ እራሷን በብዙ ተጋድሎ አስከብራ ፣ አገሪቱንም «የክርስቲያን ደሴት»

እስከማስኘት ደርሳ መኖሯ ሁላችንን የሚያኮራ ታሪክ ነው ። እስላሞች መካከለኛውን ምሥራቅና አፍሪካን ሲቈጣጠሩና

በሩን ሁሉ ሲዘጉት ቤተ ክርስቲያን ከክርስቲያኑ ዓለም ተለይታ ለብዙ ምዕት ዓመታት በመቆየቷና ከአብራኳ የተወለዱ

ልጆችም በእረኝነት በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ስላልተሾሙላት በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ኑራለች ። በብዙ ገንዘብ ገዝታ

የምታመጣው አንድ የግብፅ ጳጳስም የሀገሩን ቋንቋም ሆነ ትምህርት ስለማያውቅ ከቤት ተዘግቶ ከመዋል አልፎ መንጋውን

በዕረፍት ውኃና በለምለም መስክ ማሰማራት አልቻለም ነበር ። ይልቁንም በግብፅ ላይ የሠለጠኑትን የእስላም መሪዎችን

ፈቃድ ለማስፈጸም ይሠሩ የነበሩ ጳጳሳት ተብለው የመጡ ሰዎችም መኖራቸው ይነገራል ።

ወደ ተነሣንበት ርእስ ስንመለስ ምሥጢረ ቊርባን የሚፈጸመው በንጹሕ ኅብስትና በንጹሕ ወይን መሆኑ በዓለም

በምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ የታወቀና የተረዳ ነው ። በግእዝ ፥ በዕብራይስጥ ፥ በዓረብኛ «ወይን» ማለት የተጠመቀው

ወይን ማለት ነው እንጂ የወይን ፍሬ ፣ ወይም ዘቢብ ማለት አይደለም ። የወይን ፍሬ «ፍሬ ወይን» ሐረጉም «ሐረገ ወይን»

ግንዱም «ጉንደ ወይን» ነው የሚባለው ። ስለዚህ በዚህ ጽሑፍ «ወይን» ማለት የተዘጋጀን ከወይን ፍሬ የተጠመቀ ወይን

ማለት ነው ። ይህንንም በቅዱሳት መጻሕፍትና በቅዳሴዎቻችን አስተምህሮ መሠረት እንመለከተዋለን ። ግብፃውያን

በእስላሞች ጭቆና ሥር ሳሉ ፣ ቋንቋቸውን ፥ የሕግና የሥርዓት መጻሕፍቶቻቸውን አጥተዋል ። ብዙ ክርስቲያኖችም እንደ

በግ ታርደዋል ። በዚያ ጊዜ እንኳንስ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ለመምራት ለራሳቸውም አቅም አልነበራቸውም ። ስለዚያ

ዘመን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴዎሎጅያን (የነገረ መለኮት ምሁራን) እንደሚገልጹት ፣ የግብጽ

ቤተ ክርስቲያን ከንጹሕ ስንዴ ኅብስቱን ከንጹሕ ወይን ደሙን ታዘጋጅ ስለ ነበር ፣ እስላሞች ቤተ ክርስቲያኗን ለማዳከምና

ብሎም ለመዝጋት ሲሉ ወይን ወደ ግብፅ እንዳይገባ በሕግ ከለከሉ ። በዚህ ጊዜ ቅዳሴ እንዳይታጎልባቸው የሰጉ ግብጻውያን

ጥቂት የደረቁ የወን ፍሬዎችን /ዘቢብ/ በውኃ ነክረው በማሸት መቀደስ ጀመሩ ። እስላሞች ውሳኔውን በውሳኔ ሲሽሩላቸው

ግን ተመልሰው በወይን መቀደሳቸውን ቀጠሉ ። 1

1 Fr. Shoenda Mahar Ishak, Studies in Comparative Ritual Theology (Al-amba Ruweis 2000) page 38

Page 4: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/4/

በዚያ ጊዜ ግብጻዊው ጳጳስ በሀገሩ በነጻነት እጦት ምክንያት የተጀመረውን ሥርዓት ፣ ነጻ መንግሥት ባለባት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም አስገብቶት ይሆናል ፣ ይላል ግብፃዊው የሥነ መለኮት ሊቅ ቄስ ዶክተር ሽኖዳ ማር

ይስሐቅ የአኀት አብያተ ክርስቲያናትን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸም ባጠናበት አንጻራዊ ጥናቱ ። በዚህም ምክንያት

እስከ አሁን ከአኃት አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ከዓለም ቤተ ክርስቲያን ተለይታ በወይን በመቀደስ ፈንታ ዘቢብ አሽታ

ትቀድሳለች ሲልም ጥናቱ ያትታል ። ቅጥያ አንድን ይመልከቱ

2 ሥርዓቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ተጠንቶ ይሁን ተብሎ ተወስኖ ሳይሆን ፥ በክፉ ቀን ገብቶ መቅረቱን በታሪክም ፥

በትውፊትም ፥ በችግርም ፥ በእውቀት ማንስም ፥ በብዙ መልኩ ልንረዳ እንችላለን ። ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር

ቀረቤታ ያላቸው የኢትዮጵያ ገዳማት በኢየሩሳሌም የሚቀድሱት በንጹሕ ወይን መሆኑና የቤተ ክርስቲያናችን ቅዳሴያትም

በንጹሕ ወይን ላይ ማይ እየጨመርን እንድንቀድስ ማዘዛቸው እንደ ምስክር ሊጠቀሱ ይችላሉ ። በሀገራችን ክርስቲያኑ ገበሬ

ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይዞ እንደሚሄደው ፣ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ክርስቲያኖች ደግሞ ዘቢብ ሳይሆን ለቊርባን

የሚሆነውን ወይን ገዝተው እንደሚሄዱ የዓይን ምስክሮች ለዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ገልጸውለታል ።

አኃት አብያተ ክርስቲያናትም በንጹሕ ወይን ላይ ማይ እየጨመሩ ይቀድሳሉ እንጂ እንደኛ ዘቢብ አሽተው

አይጠቀሙም ። በሌላ መልኩ እንኳን ወይን በቂ ዘቢብ እንኳ በቀላሉ ለማግኘት የማይችሉት የሀገራችን አብያተ ክርስቲያናት

ከአምስት እስከ ሰባት ፍሬ ዘቢብ አሽተው ሲቀድሱ ኖረዋል ። አሁንም በዚያው መልክ ይቀድሳሉ ። ከችግራቸው አንጻር

ሲታይ እንዲሁም ወይን በሀገራችን በቀላሉ እንደ ስንዴ በገፍ የማይመረት በመሆኑ አሁን ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምበት

ሥርዓት ለችግራችን አጋዥ ሁኖ ስለ ተገኘም ሊሆን ይችላል ። አሁንም ቢሆን በየአብያተ ክርስቲያናቱ ለቅዱስ ቊርባን

ሊሆን የሚችል አዲስና ንጹሕ ወይን ለማቅረብ ዝግጁዎች ነን ለማለት አይቻለም ። ነገር ግን ከሚቻልበት አገር ደግሞ

ሁኔታውን አቅንቶ መጠቀም ተገቢ ይመስለናል ።

ቤተ ክርስቲያናችን የራሷ ሲኖዶስ ያላት ከሆነች በኋላ ደግሞ ፣ ይህን የወይን አቅርቦት ለማሻሻልና በወይን

እንዲቀደስ ለማድረግ በሲኖዶስ ደረጃ ብዙ ጥረት ይደረግ እንደ ነበር የዐይን ምስክር የሆኑ ሊቃነ ጳጳሳት ብዙዎች ናቸው ።

የዚህን ጽሑፍ አዘጋጅ ጨምሮ ብዙ ካህናት ወደ ውጭ መጥተን ቅዳሴ ስንቀድስ በወይን ሲቀደስ ስላየን ለምን

ብለን ከእኛ ቀድመው የመጡትን ጠይቀናል ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓቷን በሚገባ የሚያውቁ ብፁዓን ሊቃነ

ጳጳሳት ስላስረዱን ፤ ሐዋርያዊት የሆነች የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቊርባንን የምታከናውነው በዚህ መሆኑን በቃልና

በተግባር አስተምረው ጥያቄያችንን ስለመለሱልን ከልባችን ተቀብለነዋል ።

2 ዝኒ ከማሁ (page 42-43)

Page 5: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/5/

ይሁን እንጂ አሁን አሁን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወደ ውጭ ሀገር ተሰደውም ሆነ ለተሻለ ኑሮ የሚመጡ ካህናት እኛ

እናነሣቸው የነበሩ ጥያቄዎችን ያነሣሉ ። እንዳውም አንዳንዶቹስ ቤተ ክርስቲያንንም ወደ ኋላ እንድትመለስ ይጥራሉ ። ይህ

ጽሑፍም የተዘጋጀው ምሥጢራትን በልማድ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ መሠረት ወጥ በሆነ መልኩ

ለመፈጸም እንድንችል ለማድረግ ነው ።

የጥናቱም ዋና ዓላማ ለቅዱስ ቊርባን መቅረብ የሚገባው ወይን ምን አይነት መሆን አለበት ? ወይን ወይስ በውኃ

በታሸ ዘቢብ ? ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ስለዚህ ምን ይላል ? በሚሉት ጥያቄዎች ላይ የተብራራ ምክንያታዊ ሐተታ ማቅረብ

ነው ።

ጥናቱ ፣ መጀመሪያ የቅዱሳት መጻሕፍትን አስትምህሮ ያስቀድማል ፣ ከዚያ የቅዳሴያቱን ምስክርነት ያስከትላል ፣

ከዚያም አኃት አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎችም በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ምስክርነት ያሳያል ፣ መቼና እንዴት

በዘቢብ መጠቀም ጀመርን ? የሚለውን ጥያቄም ይመልሳል ። የእኛ የሥርዓት መጻሕፍት ፍትሐ ነገሥትና ሲኖዶስ ስለዚህ

ምን ይላሉ ? የሚለውንና ሌሎች ዋቢ መጻሕፍትን በማገናዘብ ሐተታውን ያጠቃልላል ። በዚህ ላይ ውሳኔ ሰጩ ቅዱስ

ሲኖዶስ ቢሆንም የሕግ ምንጮቹ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚሉትን መረዳት ደግሞ አስፈላጊ ነገር ነው ።

የቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ

ቅዱሳት መጻሕፍት የተባበሩበት ፥ ሊቃውንት በአጽንኦት ያስተማሩት ትምህርት የሚያስተምረን ቅዱስ ቊርባን

ከንጹሕ ወይንና ከንጹሕ ስንዴ መዘጋጀት እንዳለበት ነው ። የቤተ ክርስቲያን ትውፊትም የሚያረጋግጥልን ይህንኑ ነው ።

በቅድሚያ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስክርነት እንመለከታለን ። ዋና ዋናዎቹም የሚከተሉት ናቸው ።

ሀ/ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

1/ የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት በዘመነ አበው በአምሳል የተገለጠበት የካህኑ የመልከ ጼዴቅ መሥዋዕት ከንጹሕ

ወይንና ከንጹሕ ስንዴ የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል ። ይህም ክህነቱ እንደ መልከ ጼዴቅ ነው የተባለው የጌታችን አገልግሎት

መገለጫ ነበር ። በኋላም አብርሃም አራቱን ነገሥታት ኮሎዶጎምርንና ረዳቶቹን ድል ነሥቶ ሲመለስ ደስ ቢለው

«በመዋዕልየኑ ትፌኑ ወልደከ ወሚመ ታርእየኒሁ ኪያሃ ዕለተ አው አልቦ» ብሎ ሲጠይቅ የክርስቶስን የክህነት አገልግሎት

በመልከ ጼዴቅ በኩል እንደሚያሳው ተነግሮት አብርሃም ወደ መልከ ጼዴቅ ሄደ ። «የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም

እንጀራና የወይን ጠጅን አወጣ ፣ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።” ተብሎ እንደ ተጻፈ ። ዘፍ 14 ፥ 18 ።

Page 6: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/6/

ከንጹሕ ሥንዴ የተዘጋጀ ኅብስትና ንጹሕ የወይን ጠጅ ይዞ ተቀብሎታል ። ይህም የሐዲስ ኪዳን ቊርባን መገለጫ

እንደ ሆነ በልበ ሊቃውንት የተረዳ እውነት ነው ። 3 ወይን ማለት ፥ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ ማለት አይደለም ። ወይን

ሲባል የተዘጋጀ የወይን ጠጅ ማለት መሆኑን መረዳት ያሻል ። ምክንያቱም በእኛ ሐረጉንም ፥ ዛፉንም ፥ ቅጠሉንም ፥

ፍሬውንም ፥ የወይ ጠጁንም ሁሉንም ወይን ነው የምንለው ። ነገር ግን በዓረብም በዕብራይስጥም በእንግሊዝኛም ፣

የተጠመቀ ወይን ብቻ ነው ወይን የሚባለው ። «ወይን በቁሙ የተክል ዕንጨት ስም ፥ ሐረጋም ፣ ፍሬው ከእንጨት ኹሉ

ፍሬ የሚከብር ፥ ጠጅና ዐረቂ የሚኾን ። በግእዝና ባማርኛ ከሥር እስከ ጫፉ ዕንጨቱም ፍሬውም ጠጁ ሳይቀር

ኹለንተናው ኹሉ ወይን ተብሎ ባንድ ስም ይጠራል ፣ በዐረብና በዕብራይስጥ ግን ወይን የሚባል ጠጁ ብቻ ነው» ። 4

2/ ቅዱስ ዳዊት «ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል ፣ ዘይትም ፊትን ያበራል ፣ እህልም የሰውን ጉልበት ያጎለብታል»

/መዝ 104 ፥ 15/ ብሎ የተናገረው ኃይለ ቃልም በክርስቶስ ስለሚሠራው የሐዲስ ኪዳን ቊርባን የተነገረ መሆኑ ለቤተ

ክርስቲያን ጎልቶ የተረዳ የትንቢት ቃል ነበር ። «ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል» የሚለው ሐረግም ከኅብስቱ ጋር ለቅዳሴ

/ለአኰቴተ ቊርባን/ የምናቀርበው ከንጹሕ የወይን ፍሬ የተጠመቀ እውነተኛ ንጹሕ ወይን መሆን እንዳለበት ያመለክታል ።

3/ ባለ ሰባት ምሰሶ ቤትን የሠራች ጥበብ የሕይወት ማዕድን ላላዋቂዎች ስለማዘጋጀት የተነገረው የተስፋ ቃልም

ለቅዱስ ቊርባን የሚሆነው ንጹሕ ወይን መሆን እንዳለበት ያመለክታል ። «ጥበብ ፍሪዳዋን አረደች ፣ የወይን ጠጅዋን

ደባለቀች ፣ ማዕድዋን አዘጋጀች» ምሳ 9 ፥ 2 ፤ እዲሁም «ኑ እንጀራዬን ብሉ ፣ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ» /ምሳ

9 ፥5/ የሚለው ቃል ፥ ደሙ ከደረቀ ከወይን ፍሬ በታሸ ማይ ሳይሆን ለአይሁድ የፋሲካ በዓል እንደሚዘጋጀው ካለ ከንጹሕ

የወይን ፍሬ ከተጠመቀ ወይን መሆን እንዳለበት ያመለክታል ።

4/ «ለዘኢይሰቲ ወይነ ምንት ውእቱ ሕይወቱ» ብሎ ሲራክ የተናገረውም ይህንኑ ያመለክታል ። ሲራ 34 ፥26 ።

5/ በዘመነ ብሉይም ወይን በቊርባንነት ይቀርብ እንደ ነበር ይታወቃል። «የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን

ጠጅ ለመጠጥ ቊርባን ያዘጋጃል» ይላል ። ዘኊ 15 ፥ 4-5 ። ዓዲ ነጽር ። ዘኊ 15 ፥ 6- 10 ፥ ዘጸ 29 ፥ 40 ።

3 በስንዴ በወይን ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለ ምን ነው ? ቢሉ ትንቢቱ ምሳሌው ሊፈጸም ፤ ትንቢት ፣ «እም ፍሬ ስርናይ ወወይን

ወቅብዕ በዝኀ ፤ ቀዳሜ ሕይወቱ ለሰብእ እክል ወማይ ወይን ወስርናይ ፤ ለዘኢይሰቲ ወይነ ምንት ውእቱ ሕይወቱ» ተብሎ ተነግሯል ፤ ምሳሌም መልከ ጼዴቅ በስንዴ በወይን ይሠዋ ነበር ። አንድም በመሰለ ነገር ለመስጠት ፣ ስንዴ ስብ ሥጋ ይመስላል ፣ ወይንም ትኩስ

ደም ይመስላልና ፤… ወይንም አንድ ጊዜ የጣሉት እንደ ሆነ ኃይል እየጨመረ ይሄዳል ፤ ኃይል የምትሆን ሕግ ሠራሁላችሁ» ሲል ነው።

ትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ ።

4 ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፫፻፹፯

Page 7: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/7/

ለ/ በሐዲስ ኪዳን

በሐዲስ ኪዳን መድኃኒታችን የመጀመሪያ ተአምራቱን በቃና ዘገሊላ በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን የወይን ጠጅ

ባደረገ ጊዜ ፥ ለእናቱ ጥያቄ “ጊዜየ ገና አልደረሰም” የሚለው መልሱ የሚያመለክተው ፣ ጊዜውና ሰዓቱ በደረሰ ጊዜ በምሴተ

ሐሙስ የፋሲካውን ወይን የተመላውን ጽዋ አንሥቶ «ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ፣ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ

የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው» ማለቱን ነው ። መድኃኒታችን በቃልና በተግባር የሐዲስ ኪዳንን ሥርዓት ሲሠራም ሆነ

ወንጌልን ሲያስተምር በግልጽ ያስተማረው ቅዱስ ቊርባን የሚዘጋጀው ከንጹሕ ሥንዴና ከንጹሕ ወይን መሆኑን ነው ።

1/ በምሳሌ ሲያስተምር ሽፍቶች የደበደቡትና ያቆሰሉት መንገደኛ ቁስሉ የደረቀው ከቁስሉ ላይ ሳምራዊው

ባፈሰሰው የወይን ጠጅና ዘይት ምክንያት ነበር ። ወይን በባሕርዩ ከራሱ የሚፈጠር አልኮል ስላለው በቁስል ላይ

የሚሠለጥኑትን ተሐዋስያን የመግደልና ቁስልን የማድረቅ ኃይል አለው ። በመሆኑም ወይን መድኃኒት ስለ ሆነ የውስጥ

ደዌንም እንኳ ሳይቀር ይፈውሳል ። ሉቃ 10 ፥ 34 ። 1ጢሞ 5 ፥ 23 ። /ኢሳ 1 ፥7/።

2ኛ በምሴተ ሐሙስ ሐዲስ ኪዳን የተመሠረተው ከንጹሕ ኅብስትና ወይን ስለ መሆኑ

መድኃኒታችን የፋሲካን በዓል ሲያከብር በምሴተ ሐሙስ ለእራት ከቀረበው ኅብስትና ወይን ላይ ኅብስቱን አክብሮ

ይህ ሥጋዬ ነው ብሉ ፣ ወይኑንም ቀድሶ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ይህ ነው ጠጡ ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው።

ማቴ 26 ፥ 27-29 ።

በጸሎተ ሐሙስ እንደ አይሁድ የፋሲካ በዓል ሥርዓት በፊቱ በጽዋ የተቀዳውን ንጹሕ የወይን ጠጅ «ይህ ስለ

ብዙዎች ኃጢአት የሚፈስ ደሜ ነው» ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷቸዋል ። አይሁድ ለፋሲካቸው በዓል ይጠቀሙበት

የነበረው ደግሞ ንጹሕ የወይን ጠጅ እንደ ሆነ ይታወቃል ።

አባቶቻችንም በሐተታቸው «ስንዴ ልባም ሴት የያዘችው እንደ ሆነ ስብ ሥጋ ይመስላል ፤ ወይንም ደም

ይመስላልና በመሰለው ለማድረግ» ብለዋል ።5 ለሐዲስ ኪዳን ቊርባን የሚቀርበው ቀይ ወይን ብቻ ነው ።

ሐ/ ቅዳሴያቱ ስለዚህ ምን ይላሉ ?

በቅዳሴያት ወይን የሚለው ቃል ትክክለኛውን ወይን ነው እንጂ በውኃ ነክረን የጨመቅነውን የደረቀ የወይን ፍሬ

/ዘቢብ/ ጭልቃ አይደለም ። ምክንያቱ ቅዳሴያቱ ወይኑን ለማባረድ በወይኑ ላይ ማይ እንዲጨመርበት ማዘዛቸው ይህንኑ

5 ትልቁ ሙሉው አምስቱ አእማደ ምሥጢር ከጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት የተረጎሙት አ/አ ሁለተኛ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት 1979

ዓ/ም

Page 8: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/8/

የሚያረጋግጥ በመሆኑ ነው ። ከላይም እንደ ተመለከትነው በግእዝ ፥ በዕብራይስጥ ፥ በዐረብኛ ፥ ወይን የሚባለው

እውነተኛው ወይን ብቻ ነው ።

ስለዚህ ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት እንዲሆን ስንጸልይ እንዲህ እንላለን ። «እውነተኛ አምላካችን ጌታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የገሊላ አውራጃ በምትሆን በቃና በጠሩህ ጊዜ ወደ ሰርግ የሄድህ ፤ ውኃውንም ባርከህ ጠጅ

ያደረክላቸው ፣ ይህንን ወይን እንደርሱ አድርገው… ለተድላና ለደስታ የሚሆን ወይኑንም ለበጎ ነገር ምላው» ። 6 «ይህ

ንጹሕ ሥጋህን ይሆን ዘንድ ለውጠው ፣ በዚህ ጽዋ ውስጥ የተቀዳውም ወይን የከበረ ደምህን ይሁን» ። 7 «አምላካችን

ክርስቶስ በኢይሩሳሌም ሰማያዊት ዋጋቸውን ይከፍላቸው ዘንድ ዕጣንና ቊርባን ፥ ወይንና 8 ሜሮን ፥ ዘይትም መጋረጃም

የንባብ መጻሕፍትን ፣ የቤተ መቅደስንም ንዋያት በመስጠት የሚገለግሉትንም ባርክ» ።9

ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ንጹሕ ወይን አቅርባ በቅዳሴ ጊዜ ንጹሕ ማይ ከንጹሑ ወይን ላይ በመጨመር

ሥርዓተ ቊርባንን ታከናውን ነበር ። 10 ለቊርባን የሚሆነውን ኅብስቱንና ወይኑን ደግሞ ምእመናን ይዘው ወደ ቤተ

እግዚአብሔር ይመጡ ነበር ፤ ቤተ ክርስቲያንም ስጦታቸውን አምላክ እንዲቀበልላቸው ከላይ የተመለከትነውን ጸሎት

ትጸልይላቸዋለች ። ወደ ፊት የምናየው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትም ሆነ ትውፊት እንደየሚመለክቱት ፣ ወይኑ አሮጌ ወይን

መሆን የለበትም ፣ ወይም የደረቀ የወይን ፍሬ በውኃ ተነክሮ ታሽቶ በተሠራ ጭልቃ መሆን የለበትም ፤ ነገር ግን መሆን

ያለበት በአዲስ ወይን አንድ ሦስተኛ ማይ ተጨምሮበት ነው መከናወን ያለበት ። ኅብስቱም ያደረ መሆን የለበትም ፣

ትናንትና ተጋግሮ ለዛሬ መሆን የለበትም ፣ ዕለቱን የተሠራ /የተጋገረ/ መሆን አለበት ። ያ ሥርዓት እስከ አሁን ድረስ

በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እንደ ተለመደ ቀጥሏል ። የእኛም ቅዳሴያት ይህንኑ ይመሰክራሉ ። ነገር ግን ሥርዓተ

ቤተ ክርስቲያንን እያቀና በጥንታዊው ሥርዓት መሠረት ሁሉን የሚያከናውን ሲኖዶስ ስላልነበረን ፥ የጎደለውን የሚሞላ

የተዛባውን የሚያቀና አካል ባለመኖሩ ቤተ ክርስቲያናችን የግብፃውያን የክፉ ዘመን ታሪክ መታሰቢያ ጠባቂ ሁና ትገኛለች ።

6 ሥርዐተ ቅዳሴ ቊ 16

7 ሥርዐተ ቅዳሴ ቊ 49

8 ቊርባን በዚህ ላይ ኅብስቱን ይወክላል ። 9 ቅዳሴ ሐዋርያት ኦ ሥሉስ ቅዱስ ቊ 17 ላይ ይመልከቱ ። 10 The Oxford Dictionary of The Chrsistian Church , ed. F.L Cross and E.A. Livingston (Oxford:

Oxford Univeristy Press, 1997) 1754-1755.

Page 9: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/9/

ከአሥራ አራቱ ቅዳሴያት ዘጠኙ ቅዳሴዎቻችን ወይኑ ከማይ ጋራ የሚቀላቀልበትን ቦታና ጊዜ በግልጽ ቃል

ያመለክታሉ ። ሌሎቹ ማለትም ቅዳሴ ሐዋርያት ፥ ቅዳሴ ማርያምና ሠለስቱ ምዕት ፥ ዲዮስቆሮስ ፥ ቄርሎስና ጎርጎርዮስ ካልዕ

ደግሞ ፣ ጌታ በምሴተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ ኅብስቱንና ጽዋውን የሰጠበትን ትእዛዝ በመጥቀስ ጽፈዋል ። የቅዳሴያቱ

ምስክርነትም እንደ ቅደም ተከተላቸው ከዚህ በታች ቀርቧል።

1/ ቅዳሴ ሐዋርያት

ግዕዝ፦ወከማሁ ጽዋዐኒ አእኲቶ ፥ ባሪኮ ፥ ወቀዲሶ መጠዎሙ ለእሊአሁ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ ንሥኡ ስትዩ ዝ

ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ለዘበእንቲአክሙ ይትከዐው ለቤዛ ብዙኃን ።

አማርኛ፦«እንዲሁም ጽዋውን አመስግኖ ባርኮ አክብሮ ለወገኖቹ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው ንሡ ጠጡ ይህ ጽዋ

ለብዙ ሰዎች ቤዛ ሊሆን ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው አላቸው» ።

ይህ ኃይለ ቃል ንጹሕ የጽዋዓ ፋሲካ አይሁድ ወይን የመላበትን ጽዋ ለደቀ መዛሙርቱ ባርኮና አክብሮ እንደ

ሰጣቸው ይመሰክራል ።

2/ ቅዳሴ እግዚእ

ግዕዝ «ሶበ ዘንተ ትገብሩ ተዝካረ ዚአየ ግበሩ ። ወከማሁ ጽዋዐ ወይን ቶሲሐከ አእኲተከ ፥ ባሪከከ ፥ ወቀዲሰከ

ወሀብኮሙ በአማን ደምከ ዝንቱ ዘተክዕወ በእንተ ኃጢአትነ።

አማርኛ፦«ይህን በምታደርጉበት ጊዜ የኔን መታሰቢያ አድርጉ ። እንደዚሁም የወይኑን ጽዋ ጨምረህ አመስግነህ

ባርከህ አክብረህ ሰጠሃቸው ። ስለ ኃጢአት በእውነት የፈሰሰ ይህ ደምህ ነው» ። የሚለው ኃይለ ቃል ወይኑን ከውኃ ጋር

/ማየ ገቦ/ ጋር ቀላቅሎ መስጠት የተለመደ መሆኑን ያመለክታል ።

3/ ቅዳሴ ወልደ ነጎድጓድ

ግዕዝ፦«ወከማሁ ሰብሐ ዲበ ጽዋዕኒ ፣ ወይቤ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ዘሐዲስ ሥርዓት ንሥኡ ስትዩ እምኔሁ

ኵልክሙ ።

Page 10: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/10/

አማርኛ፦እንዲሁም በጽዋው ላይ አመሰገነ ፣ ይህ ጽዋ የሐዲስ ሥርዓት የሚሆን ደሜ ነው ፣ ሁላችሁም ንሡ

ከእርሱ ጠጡ አላቸው» ።

ይህም እንዲሁ ንጹሕ የጽዋዓ ፋሲካ አይሁድ ወይን የመላበትን ጽዋ ለደቀ መዛሙርቱ ባርኮና አክብሮ እንደ

ሰጣቸው ይመሰክራል ።

ግዕዝ፦«ወከመ ቱስሕቱ ለዝ ወይን ምስለ ማይ ኢይትከሀል ይትፈለጥ አሐዱ እም አሐዱ ከማሁ ይደመር

መለኮትከ በትስብእትነ ፣ ወትስብእትነ በመለኮትከ ፣ ዕበይከ በትሕትናነ ወትሕትናነ በእበይከ፤

አማርኛ፦የዚህ ወይን ከውኃ ጋራ መጨመር አንዱ ካንዱ ይለይ ዘንድ እንዳይቻል ፤ እንደርሱ ጌትነትህ

በሰውነታችን ሰውነታች በመለኮትህ ገናንነትህ በትሕትናችን ትሕትናችን በገናንነትህ አንድ ይሁን» ። 11

4/ ቅዳሴ ማርያም

ግዕዝ፦ «ወከማሁ ጽዋዐኒ እም ድኅረ ተደሩ አንጸረ ወይቤ ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ለዘበእንቲአክሙ

ያነቅዖ ኲናት ።

አማርኛ፦ እንዲሁም ጽዋውን ከተመገቡ በኋላ አመለከተ ይህ ጽዋ ስለናንተ ጦር የሚያፈሰው ደሜ ነው ንሡ ጠጡ

አለ» ። ይህም እንዲሁ ንጹሕ የጽዋዓ ፋሲካ አይሁድ ወይን የመላበትን ጽዋ ለደቀ መዛሙርቱ ባርኮና አክብሮ እንደ ሰጣቸው

ይመሰክራል ።

ጎኑ በጦር ሲወጋ ደምና ውኃ እንደ ፈሰሰ ቅዱስ ወንጌል ይመሰክራል ። «ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር

ወጋው ፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ» እንዲል ። ስለዚህ ነው አባ ሕርያቆስ «ያነቅዖ ኵናት» ያለው ። ዮሐ 19 ፥ 34 ።

5/ ቅዳሴ ሠለስቱ ምእት

ግዕዝ፦«ወከማሁ ጽዋዐኒ ባረከ ፥ ወቀደሰ ፥ ወይቤ ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ለዘበእንቲአክሙ ይትከዐው

ለኅድገተ ኃጢአት ።

11 ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቊ 92 ይመልክቱ ።

Page 11: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/11/

አማርኛ፦እንዲሁም ጽዋውን ባረከ ። አከበረም ይህ ጽዋ ለኃጢአት ማስተሥረያ ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ንሡ

ጠጡ አላቸው ።»

ዝኒ ከማሁ ፣ ንጹሕ የጽዋዓ ፋሲካ አይሁድ ወይን የመላበትን ጽዋ ለደቀ መዛሙርቱ ባርኮና አክብሮ እንደ ሰጣቸው

ይመሰክራል ።

6/ ቅዳሴ አትናቴዎስ

ግዕዝ፦ወከማሁ ጽዋዐኒ ቶሲሐከ ማየ ወወይነ አእኰትከ ባረከ ወቀደስከ ወወሀብኮሙ እንዘ ትብል ንሥኡ ስትዩ ዝ

ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ዘአልቦ ተፈልጦ እምኔሁ ።

አማርኛ፦ እንዲሁም ጽዋውን ውኃውንና ወይንን ቀላቅለህ አመሰገንህ ባረክህ አከበርህም ይህ ጽዋ ከርሱ መለየት

የሌለበት ደሜ ነው ንሡ ጠጡ ብለህ ሰጠሃቸው ።

7/ ቅዳሴ ባስልዮስ

ግዕዝ፦ ወከማሁ ካዕበ ጽዋዐኒ እም ድኅረ ቶስሐ ማየ ወወይነ አእኰተ ፥ ባረከ ፥ ወቀደሰ ፥ ጥዕመ ወወሀቦሙ

ለእሊአሁ አርዳኢሁ ቅዱሳን ወለሐዋርያቲሁ ንጹሐን ወይቤሎሙ ንሥኡ ስትዩ እምኔሁ ኲልክሙ ፥ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ

ለዘበእንቲአክሙ ይትከዐው ለሥርየተ ኃጢአት ። (የአንድምታው ቅዳሴ ዘር ፣ ወከማሁ ካዕበ ጽዋዓኒ እምድኅረ “ተደሩ”

ቶስሐ ማየ ወወይነ ይላል)

አማርኛ እንደዚሁ ዳግም ጽዋውንም ውኃውንና ወይኑን ከቀላቀለ በኋላ አመሰገነ ባረከ አከበረ ወገኖቹ ለሆኑ

ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱና ለንጹሐን ሐዋርያቱ ሰጣቸው ይህ ጽዋ ኃጢአትን ለማስተሥረያ ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ነው

ሁላችሁ ንሡ ከእርሱ ጠጡ አላቸው ።

8/ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ

ግዕዝ፦ወካዕበ ነጸረ ዲበ ዝንቱ ጽዋዕ ማየ ሕይወት ምስለ ወይን አእኰተ ፥ ባረከ ፥ ወቀደሰ ፥ ወመጠዎሙ

ለእሊአሁ ሐዋርያቲሁ ፣ ወይቤሎሙ ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ስቴ ሕይወት ዘበአማን ። ዘሰትየ እምኔሁ ቦ

ሕይወት ዘለዓለም ንሥኡ ስትዩ እምኔሁ ኲልክሙ ይኩንክሙ ለሕይወት ወለመድኃኒት ።

Page 12: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/12/

አማርኛ፦ዳግመኛም በዚህ ጽዋ ላይ ከወይን ጋራ የሕይወት ውኃን ተመለከተ አመሰገነ ባረከ አከበረ ይህ ጽዋ

እውነተኛ የሕይወት መጠጥ የሚሆን ደሜ ነውና ንሡ ጠጡ ብሎ ለወገኖቹ ለሐዋርያት ሰጣቸው ። ከእርሱ የጠጣ የዘላለም

ሕይወት አለው ። ለሕይወትና ለመድኃኒት ይሆናችሁ ዘንድ ሁላችሁ ንሡ ጠጡ ።

9/ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ

ግዕዝ፦ወካዕበ ቶስሐ ጽዋዐ ወይን ምስለ ማይ አእኰተ ፥ ባረከ ፥ ወቀደሰ ፥ ወመጠዎሙ ለሐዋርያቲሁ ወይቤሎሙ

ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ሱታፌ ደምየ ውእቱ ዘይትከዐው በእንቲአክሙ ።

አማርኛ፦ዳግመኛም የወይንን ጽዋ ከውኃው ጋራ ቀላቅሎ አመሰገነ ባረከ ። አከበረ ይህ ጽዋ ስለናንተ ከሚፈስ ደሜ

ጋራ አንድ ነው ንሡ ጠጡ ብሎ ለሐዋርያት ሰጣቸው ። (የአንድምታው ቅዳሴ ትርጓሜ ፣ ዳግመኛ ወይኑን ከውኃ ጋራ

ቀላቀለው ይላል)

10/ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈ ወርቅ

ግዕዝ፦ወከማሁ ጽዋዐኒ ቶስሐ ማየ ወወይነ አእኰተ ፥ ባረከ ፥ ወቀደሰ ፥ ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ ወይቤሎሙ ዝ

ውእቱ ደምየ ስቴ ሕይወት ዘበአማን ፣ ዘሰትየ እምኔሁ ቦ ሕይወት ዘለዓለም ፣ ንሥኡ ስትዩ እምኔሁ ኲልክሙ ።

አማርኛ፦እንዲሁም ጽዋውን ውኃና ወይንን ቀላቅሎ አመሰገነ ባረከ ፣ አከበረ ፥ እውነተኛ የሕይወት መጠጥ ደሜ

ይህ ነው ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው ። ከእርሱ የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ፣ ሁላችሁ ንሡ ከእርሱ ጠጡ

አላቸው።

11/ ቅዳሴ ቄርሎስ

ግዕዝ፦ወካዕበ እም ድኅረ ተደሩ ነሥአ ጽዋዐ አእኰተ ፥ ባረከ ፥ ወቀደሰ ፣ ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ

ደምየ ውእቱ ዘሐዲስ ሥርዓት ለዘበእንቲአክሙ ይትከዓው ወይትወሀብ ለቤዛ ኲሉ ዓለም ለኅድገተ ኅጢአት ።

አማርኛ፦ዳግመኛም ራታቸውን ከበሉ በኋላ ጽዋውን ይዞ አመሰገነ ፣ ባረከ ፥ አከበረም ። ደቀ መዛሙርቱንም

አላቸው ንሡ ጠጡ ይህ ጽዋ ኃጢአትን ለማስተሥረይ ስለናንተ የሚፈስና ለዓለሙ ሁሉ ቤዛ የሚሰጥ ሐዲስ ሥርዓት

የሚሆን ደሜ ነው.።

Page 13: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/13/

12/ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ

ግዕዝ፦ ወካዕበ ቶሳሕከ ጽዋዐ ወይን ምስለ ማይ ከመ ተሀቦሙ ለሐዋርያቲከ ንጹሐን ፣ዘአሜሃ ቀደስከ ቀድሶ

ይእዜኒ ለዝንቱ ጽዋዕ ፣ ዘአሜሃ መጦከ መጥዎ ይእዜኒ ለዝንቱ ጽዋዕ።

አማርኛ፦ ዳግመኛም የወይኑን ጽዋ ከውኃ ጋራ ቀላቅለህ ለንጹሐን ሐዋርያቶችህ ትሰጣቸው ዘንድ ። ያን ጊዜ

ያከበርህ አሁንም ይህን ጽዋ አክብረው ። ያን ጊዜ የሰጠህ አሁንም ይህን ጽዋ ስጠው ።

13/ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ

ግዕዝ፦ ወካዕበ ቶስሐ ማየ ወወይነ አእኰተ ባረከ ወቀደሰ ወወሀቦሙ ለእሊአሁ አርዳኢሁ ቅዱሳን ወለሐዋርያቲሁ

ንጹሐን ወይቤሎሙ ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ለዘበእንቲአክሙ ይትከዐው ለቤዛ ብዙኃን ።

አማርኛ፦ዳግመኛም ውኃውን ከወይን ጋራ ቀላቅሎ አመሰገነ ባረከ አከበረ ፣ ንጹሐን ቅዱሳን ወገኖቹ ለሆኑ ደቀ

መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው ፣ ይህ ጽዋ ለብዙ ሰዎች ቤዛ ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ንሡ ጠጡ አላቸው ።

14/ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ ።

ግዕዝ፦ወከማሁ ዲበ ጽዋዕኒ ነገርኮሙ እንዘ ትብል ንሥኡ ስትዩ ዝ ጽዋዕ ደምየ ውእቱ ለዘበእንቲአክሙ ይትከዐው

ወይትወሀብ በዘይትኀደግ ኃጢአት ለሕይወት ዘለዓለም አሜን ።

አማርኛ፦እንደዚሁም በጽዋው ላይ ነገርሃቸው ይህ ጽዋ ኃጢአት በሚሠረይ ገንዘብ ለዘላለም ሕይወት ስለናንተ

የሚፈስ የሚሰጥም ደሜ ነው ንሡ ጠጡ ብለህ ፣ አሜን ።

በቅዳሴያቱ የታየው ይህ ሁሉ ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ንጹሕ ማይ ከንጹሕ ወይን ጋር በመቀላቀል ሥርዓተ ቊርባንን

ትፈጽም እንደ ነበር የሚያመለክት ነው ።

ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 13 ቊ 509 ላይ «ወይኑን ወደ ጽዋው ውስጥ ይገልብጡት ፥ ይመልከቱትም ፣ እርሱ

ጽሩይ ንጹሕ ካልሆነ በቀር አይሠዉ ። ጽዋውን የሚያዘጋጀው ሰው ጊዜ ያለፈውን ወይን አይጨምር ፤ ከሦስት እጅ የበለጠ

ብዙ ውኃ አይጨምር ።»

መ/ የቤተ ክርስቲያን ታሪክስ ስለዚህ ምን ይላል?

Page 14: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/14/

ቤተ ክርስቲያን በጉባኤ ኬልቄዶን ከመለያየቷ በፊትም ሆነ ከልዩነት በኋላ በአቀራረብና በአፈጻጸም መጠነኛ

የሥርዓት ልዩነት ቢታይም ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለሥጋው የሚሆነውን ኅብስቱን ከንጹሕ ስንዴ ፣ ለደሙ

የሚሆነውን ደግሞ ከንጹሕ ወይን ያቀርቡ ነበር እንጂ ፥ ዘቢብ በውኃ አሽተው እደሚጠቀሙ የሚያመለክት ምንም አይነት

መረጃ እስከ አሁን አልተገኘም ። 12

ሠ/ የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸም ምስክርነት

አራቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ፣ ማለትም የግብጽ ፥ የህንድ ፥ የአርመን ፥ የሶርያ አብያተ ክርስቲያናትም

ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን የሚፈጽሙት በንጹሕ ወይን ነው እንጂ ዘቢብ በውኃ አሽተው አለመሆኑን ለማረጋገጥ

ተችሏል ። በሌሎችም ኦርቶ ዶክሳውያን ዘንድ ለቅዱስ ቊርባን የሚቀርበው ንጹሕ ወይን ነው ። የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ

በሲያትል ከተማ ከምትገኘው የግብፆች ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአካል በመገኘት ካህኑን ቃል በቃል አናግሯል ፣

ለቁርባን የሚጠቀሙበትንም ወይን በዓይኑ አይቶታል ። በእኛ ቤተ ክርስቲያን ከምንጠቀምበት ወይን ጋር አንድ ነው ። 13

ረ/ የእኛ ገዳም በኢየሩሳሌም፦

በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን

የሚፈጽሙት ዘቢብ አሽተው ሳይሆን በንጹሕ ወይን መሆኑን የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ለማረጋገጥ ችሏል ። 14

ሰ/ «የቅዳሴያችን ይዘት» በሚል ርእስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ባቀረቡት ጥናት ላይ ፣ ስለ ተነሣንበት ርእስ

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠቅሰው ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ብለዋል ። «የሚቀደስበት ኅብስትም ዕለቱን የተሠራ ኅብስት

ነው እንጂ ያደረ መሆን የለበትም /ፍት ነገ 13 ቊ 508/ ። እንዲሁም በወይን እንጂ በጭልቃ እንዳይቀደስ ብዙ ጊዜ በቆየ

12 በዘቢብ መቀደስ መቼ ተጀመረ? የሚለውን ይመልከቱ 13 Saint Mary's Coptic Orthodox Church 4110 204th St SW, Lynnwood, WA 98036

14 የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ በኢየሩሳሌም ገዳም ሲያገለግሉ ከኖሩት አበው መነኮሳት አንዱን ጥቅምት 20/2008 ዓ/ም በስልክ ስለዚህ ሁኔታ ጠይቆ

ነበር ፤ እኒህ አባት ከዚህ የሚከተለውን ነግረውኛል ። «ገዳማቱ የሚጠቀሙት በወይን ነው እንጂ ዘቢብ አሽተው አይደለም ፤ ወይኑን ደግሞ ከግሪኮች ወይም ከካቶሊኮች መደብሮች ነው የሚገዙት ። በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ምእመናን አባቶችን ጠይቀው ለቊርባን የሚሆነውን ወይን ገዝተው

የሚመጡበት ጊዜ አለ ። ከኢትዮጵያ የሚመጡ ምእመናን ዘቢብ ይዘው ይመጣሉ ፤ ግን ገዳሙ ለቅዱስ ቊርባን አይጠቀምበትም» ። ብለውኛል ።

Page 15: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/15/

ወይንም እንዳይቀደስ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ። ውኃ በብዛት እንዳይጨመርበት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ያስጠነቅቃል» ብለዋል ።

15

ሰ/ የደረቀ ዘቢብ በውሀ በማሸት መቀደስ መቼ ተጀመረ ?

መልሱ ባጭሩ እስላሞች ግብጽን በተቈጣጠሩበት በመካከለኛው ዘመን ነው ።

የደረቀ የወይን ፍሬ /ዘቢብ/ ለምግብ ይቀርብ ነበር ። 1 ሳሙ 25 18 ።

በወይን ፈንታ ዘቢብ አሽቶ መጠቀምን የጀመረችው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን በእስላሞች ነጻነቷን ተነጥቃ በወይን

እንዳትቀድስ ወይንም ወደ ግብፅ እንዳይገባ በመካከለኛው ዘመን በግብጽ ሠልጥነው በነበሩት በአክራሪ የእስላም መሪዎች

ምክንያት እንደ ነበር ታውቋል ። በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረጉ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያጠኑት ጥናት

እንደሚያመለክተው ፣ እስላሞች የግብፅ ክርስቲያኖች ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን እንዳይፈጽሙ ብለው ወይን ወደ ግብፅ

እንዳይገባ ማዕቀብ ጥለው ነበር ። ምክንያታቸውም አልኮል አለውና ለምንም አገልግሎት መዋል የለበትም የሚል ነበር ።

ዶክተር ቄስ ሲኖዳ ይስሐቅ የተባለ የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮትና የቅዱስ መጽሐፍ

ፕሮፌሰር የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን ሥርዓተ ቅዳሴና ሥርዓተ ቊርባን በንጽጽር ባጠናበት ጥናቱ ላይ እንደ ገለጠው

፣ የደረቀ የወይን ፍሬ ወይም ዘቢብ በውኃ አሽታ የምትጠቀም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት ። በውኃ ዘቢቡን ነክራ

ጭማቂውን አጥልላ ትጠቀማለች ። በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በወይን ጠጅ መቀደስ ክልክል ነው ።

ይልና ፣ ይህን ልማድም በመካከለኛው ዘመን /Medieval ages/ ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን የወረሰችው ነው ለማለት

ያስችላል ። ምክንያቱም የእስላሞች ሕግ የወይን መጠጥን ስለሚከለክል የግብፅ ቤተ ክርስቲያን በእስላሞች ሥር ሳለች ወይን

እንዳትጠቀም ተከልክላ ነበርና ። ነገር ግን ነጻነት በተገኘበትና በሠለጠነው ዓለም የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከንጹሕ ወይን

በተጠመቀ የወይን ጠጅ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈጸም ነጻነትን አግኝታለች ይላል ። ቃል በቃል ጥናቱ

እንደሚከተለው ቀርቧል ።

«The Ethiopian Orthodox forbid the use of old wine in the Eucharist “They

often content themselves with steeping some dried grapes (zibibo) in a little water,

and extracting the juice” King 1, P 55716

15 አባ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ የቅዳሴያችን ይዘት ጣና ማተሚያ ቤት ፣ ቶሮንቶ ካናዳ 2003 ዓ/ም ገጽ 86 ። 16 King 1 King, A.A, The Rites of Eastern Chrtendom (2 Vols.) first Vol.Rome 1947.

Page 16: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/16/

This practice was possibly adopted from Egypt in the medieval ages, when

the Copts under Islamic rule were sometimes obliged to do so, since the Islamic law

prohibits drinking wine. But the Copts of the modern times are free to use wine in

the Eucharist, which they prepare by fermenting soaked raisin juice»17

ለበረለጠ መረጃ ቅጥያ አንድን ይመልክቱ ።

ሸ/ ፍትሐ ነገሥትና ሲኖዶስ ስለዚህ ምን ይላሉ?

1/ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 13 ቊ 2

«ንጹሕ ከሆነ ከስንዴ ፣ ንጹሕም ከሆነ ከወይን በቀር በቤተ ክርስቲያን አይሠዉ ። በእሳት ከሚበስሉ ከሚያሰክሩ መጠጦች

ወገን በማናቸውም ወይኑን አይለውጡ ። ዳግመኛም በመጀመርያ ጊዜ የደረሰውን የወይኑን ዘለላ የእሸቱን ያግቡ» ይላል ።

ይህም በግልጥ የሚያስቀምጠው በእሳት ኃይል ከወይን ተነጥሮ የሚወጣን የወይን አረቂ እና የአልኮል አይነቶች

/ለምሳሌ አረቂ/ ወይም ሌላ አይነት የአልኮል አይነቶችን ከንጹሕ ወይን የሚጠመቀውን ወይንን ይተካሉ ብለው

እንዳይጠቀሙ በንጹሕ ወይን ብቻ ሥርዓተ ቊርባን እንዲከናወን የሚያዝዝ ነው ።

ብዙዎቹ ደግሞ «የወይኑን ዘለላ እሸቱን ያግቡ» የሚለውን መሠረት በማድረግ ፥ የወይን እሸት ማለት በዚህ አገር

ቋንቋ “ግሬፕ” የሚባለው ታሽቶ ይሠራ ማለቱ ነውና በወይን እሸት መቀደስ ያለበት ይላሉ ፣ ግን ምክንታዊ አይደለም ።

መጽሐፉ በአጽንኦት የሚያሳየው ከሐረገ ወይን ከተገኘ ፣ ለመሥዋዕት ተብሎ እንደ ስንዴው ሁሉ ከወይኑ ሐረግ በጥንቃቄ

ተለቅሞ ከዚያ ንጹሕ ወይን ተጠምቆ ፥ እንደ ወይነ ፋሲካው ባለ ንጹሕና ኀዘንን ያሚያስረሳ ወይን መዘጋጀት ያለበት

መሆኑን ነው ፍትሐ ነገሥቱ የሚያሳየው ።

ሌላው ደግሞ የወይን ዘር ካልሆኑ ፣ ወይም ወይን ተቀላቅሎባቸው ከሚዘጋጁ መጠጦች ቊርባን እንዳይሠራ ነው

የሚያዘው ። ክርስቶስ በዕለተ ሐሙስ ካከናወነው ሥርዓት የተለየ እንዳይሆን ፥ ከንጹሕ የስንዴ ዛላ ከተገኘ ስንዴ ኅብስቱ ፣

ከንጹሕ የወይን ሐረግ ከተገኘ ንጹሕ ወይን ደሙ መዘጋጀት እንዳለበት ነው የሚያመለክተን ። ዘቢብ ማለት የወይን እሸት

ማለት እንዳልሆነ ለሁላችን ግልጽ ሊሆን ይገባል ። ይህንንም ግልጥ የሚያደርግልን ከላይ የተገለጠው አንቀጽ 13 ቊ 509

17 Fr. Shoenda Mahar Ishak, Studies in Comparative Ritual Theology (Al-amba Ruweis 2000) page

38

Page 17: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/17/

ላይ « «ወይኑን ወደ ጽዋው ውስጥ ይገልብጡት ፥ ይመልከቱትም ፣ እርሱ ጽሩይ ንጹሕ ካልሆነ በቀር አይሠዉ ። ጽዋውን

የሚያዘጋጀው ሰው ጊዜ ያለፈውን ወይን አይጨምር ፤ ከሦስት እጅ የበለጠ ብዙ ውኃ አይጨምር ።» ብለው አባቶቻችን

በማያሻማ ቃልና መንገድ ጽፈውልን አልፈዋል ።18

2ኛ/ መጽሐፈ ሲኖዶስ -አብጥሊስ ፫ እዲህ ይላል፣ ግዕዝ፦ «እመሂ ኤጲስ ቆጶስ አው ቀሲስ አው ዲያቆን ዘተዐደወ

ሕገ ክርስቶስ በውስተ ቊርባን ወአቅረበ ላዕለ ምሥዋዕ መዓረ አው ሐሊበ ፣ ወእመሂ አዕረገ ህየንተ ሥራበ ወይን ሥራበ

ሶከር ፤ ወኢምንተኒ ሜሰ ወይን ዘግቡር በእሳት ፥ አው ወይን ዘግቡር በፀሐይ ፣ ወኢምንተሂ እም አዕዋፍ ወእንስሳ ወኢባዕደ

ዘይሠውዑ ዘእንበለ ቊርባን ዘአዘዘ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እም ኅብስት ንጹሕ ስንዳሌ ወወይን ዘንጡፍ እም አስካል

ዘይነሥዑ እም ሐረጉ ወዘይገብር ዘእንበለ ዝንቱ ይሰደድ ፣ ወእም ሲመቱ ይሰዓር» ። 19

አማርኛ ኤጲስ ቆጶስም ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን የክርስቶስን ሕግ የተላለፈ ፣ ለቊርባን በመሠዊያ ላይ ማር

ወይም ወተት ፣ ወይም ስለ ወይን መጠጥ ፈንታ የስኳር መጠጥ (ስለ ወይን ጠጅ ፈንታ የስኳር ጠጅ) ወይም በእሳት ነጥሮ

የተሠራ የወይን አረቂ ፣ ወይም በፀሐይ ነጥሮ የተሠራ የወይን አረቂ ፣ ወይም ከእንስሳትና ከአእዋፍ ፣ ወይም ሌላ ነገር

የሚሰዉ ቢኖሩ ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቊርባን እንዲሆን ካዘዘው ከንጹሕ ስንዴ ከተዘጋጀ ኅብስትና ከንጹሕ የወይን ሐረግ

ከተለቀመ ከወይን ፍሬ ከሚዘጋጅ ወይን በቀር ለመሥዋዕት የሚያቀርብ ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን ይለይ ፣ ከመዓርጉም ይሻር»

በማለት መሥዋዕተ ወንጌል ከንጹሕ ስንዴ ብቻ ከተዘጋጀ ኅብስትና ከንጹሕ የወይን ሐረግ ተለቅሞ በተዘጋጀ ወይን

ብቻ መዘጋጀት እንዳለበት በአጽንኦት ይደነግጋል ። ይህም ማለት ስንዴው ኅብስት ለመሆን ከተረቀቀ በኋላ ማይና ነድ

እንሚያስፈልገው ሁሉ ፤ ከወይን ሐረግ የተለቀመው የወይን ፍሬም ወይን ለመባል የፋሲካው ወይን በሚጠመቅበት ሥርዓት

ተጠምቆ ወይን መሆን አለበት ። ስለዚህ ከላይ ለምሳሌ ያክል የተጠቀሱት የሥርዓት መጻሕፍት ባጭሩ የሚያመለክቱት

ከስንዴና ከወይን በቀር ሌላ ነገርን ቤተ ክርስቲያን እንዳትጠቀም ፤ ጌታ በጸሎተ ሐሙስ እንዳደረገው ሥርዓተ ቊርባንን

በኅብስትና በወይን ብቻ እንድትፈጽም ነው እንጂ ፥ አንዳንድ ወንድሞች እንደሚሉት በዘቢብ ስለመጠቀም አብነት የሚሆን

አይደለም ።

18

ፍትሐ-ነገስት አንቀጽ 13 ቊ 509 19 መጽሐፈ ሲኖዶስ

Page 18: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/18/

ማጠቃለያ

በእኛ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች በውኃ ተነክሮ በታሸ ደረቅ የወይን ፍሬ /ዘቢብ/ ጭልቃ እንጂ በወይን መቀደስ

የለብንም የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሣል ። ጥያቄው ደግሞ ተገቢ ጥያቄ ነው ። ምክንያቱም ለምንና እንዴት በመላው

ዓለም ከምትገኝ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተለይተን በዘቢብ መቀደስ እንደ ጀመርን የሚታወቅ ነገር አልነበረምና ።

ያደግነውም በዚያው መልክ ነውና ። ቅዱስ ሲኖዶስም በኢትዮጵያ ሁኔታውን አስጠንቶ ለምሥጢረ ቤተ ክርስቲያን ብቻ

የሚውል የወይን መጥመቂያ ለማዘጋጀት ቢሞክርም በልዩ ልዩ ምክንያት እስካሁን አልተሳካም ።

እንደዚሁ ደግሞ ሌላው ጥያቄ ፣ “ወይን አልኮልነት ስላለው በእሱ አንቀድስም” የሚል የሚገርም ጥያቄ ነው ።

አንደኛ ወይኑ ራሱ በተፈጥሮው የራሱ የሆነ አልኮሆል ስላለው እንጂ ከውጭ የመጣ አይደለም ። «ወይንም አንድ

ጊዜ የጣሉት እንደ ሆነ ኃይል እየጨመረ ይሄዳል ፤ ኃይል የምትሆን ሕግ ሠራሁላችሁ» ሲል ፣ የሚለው የአባቶች ትርጓሜም

የሚያስረዳው ከወይን የሚገኘው ኃይል ራሱን የቻለ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው መሆኑን ነው ። 20

ይህም «ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን» ከሚለው የዳዊት ትንቢት አንጻር ሲታይ የጌታ ድል ነሽነት ምልክት ሁኗል ።

ስለዚህ የወይንን ተፈጥሮ ያሚያውቅ ጌታ በአርዓያ ወይን ደሙን ሲሰጠን ዕለት ዕለት በውስጣችን ኃይሉን የሚገልጽ አምላክ

መሆኑን ለመግለጽ ነው ። ይህንም ራሱ ባለቤቱ በምሴተ ሐሙስ የሠራው ፥ የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት ነው ።

ሁለተኛ ለምሥጢረ ቊርባን የሚውለው ወይን ለዓለም መጠጥ ከሚውለው ወይን በአዘገጃጀቱ የተለየ በመሆኑ

ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያለው አይደለም ። ከዚያውም ላይ እንደ ቅዳሴያቱ ትእዛዝ አንድ ሦስተኛ (1/3) ውኃ

ይጨመርበታል 21። ይህም ኃይሉን በእጅጉ ይቀንሰዋል ።

ሦስተኛ የሚሰጠው መጠኑ በጣም ትንሽ በሆነች እርፈ መስቀል ነው ። አንድ አንድ ካህናት ይህንን በተመለከተ

ላነሡት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሁኔታውን ያጠኑ አንድ የቤተ ክርስቲያን ወንድም ፣ ሳይንሳዊ በሆነ ቀመር አሁን

የምንጠቀምበት ወይን ማይ ከተጨመረበት በኋላ በእርፈ መስቀል ሲሰጥ የሚኖረው የአልኮሆል መጠን 0.4125 ml of

alcohol per serving መሆኑን አሳይተዋል ። 22 ይህ ማለት እጅግ በጣም አነስተኛ መሆኑን ያሳያል ።

20 ትርጓሜ ወንጌል - ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ ። 21 Fr. Shoenda Mahar Ishak, Studies in Comparative Ritual Theology (Al-amba Ruweis 2000) page

41 22 I have tried to explain the Dogmatic aspect of the subject. One of the unique features of the Orthodox Church is that all the Church’s belief, Dogma and practice are enclaved by common sense, practicality and Love. What do I mean by that? For Example, during worship some in the protestant world in the West do hold a venomous snake to ‘prove’ their faith. Our

Page 19: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/19/

አራተኛ እኛ የምናምነው ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ፣ ኅብስቱ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል ብሎ ለየሚያምን

አካል ይህ አባባል ሕጸጸ አሚን በመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ።

ያም ሆነ ይህ በዚህ ላይ ሕግ ሠሪው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው ። ቅዱስ ሲኖዶስ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ሁላችን

መራመድና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን መፈጸም አለብን ። ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ሠራዔ ሕግ እንደ መሆኑ አንድ አይነት

መመሪያና ውሳኔ ያስተላልፋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። በወይኑ ላይም ሆነ በኅብስቱ ላይ /ኅብስቱ የሚሠራበት ሐሪጽ

/ዱቄት/ ከገበያ የሚገዛ በመሆኑ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ። በጥራት ለማዘጋጀት ወጥ የሆነ አሠራር ቢደረግ በቀላሉ ሁኔታው

ይታረማል ብለን እናምናለን ።

Church does no such thing because the EOTC and the Orthodox Churches in general are cognizant of all aspects of practices of faith. That brings me down to the wine and its alcohol content, for use of Communion. If one Googles, “use of wine for Communion” or something of that nature, one will realize that this is a conversation amongst all Christian churches. What makes it unfortunate in our church is that it is becoming such a divisive and hateful topic. Some are trying to use it to attack/vilify their own brethren within the church. So, to my knowledge, the wine used is called “Manischewitz, Manischewitz Concord grape wine”. I have observed in different part of this Country that this specific brand is used by most Ethiopian churches including sister Oriental churches and some Greek Orthodox Churches. Here are reasons why this is used, it’s affordable and readily available. It’s with very low alcohol content (11% ABV) and sweet in its flavor. The bottle comes with 750 ml with an alcohol content of 11% ABV (Alcohol by Volume). With most conservative estimate a third of water is added for each Worship use. A third of 750 ml. Manischewitz wine will be 0.25L of water, which brings down the ABV of the whole bottle down to 8.25%. Here is the formula for anyone who care to know (.75 x ((11ABV/8.25ABV)-1) = 0.25L (water)). Now remember, 8.25% ABV is for the whole bottle. Practically, it’s served with a smaller than typical teaspoon. But let’s say a teaspoon. Here is a rough yet conservative estimate of how much is offered based on age. 0-6 months: For newly Christened infants and infants in general, the Priest dips his finger and blesses the infant on his/her mouth. 6-12 months: The Deacon offers a tad bit on the spoon (Erfe Meskel), almost negligible amount. 1-4 years: The Deacon offers half-full of a spoon (Erfe Meskel) 4 and older: Usually almost full to full for fully adults. Now, let’s see the alcohol content of a full teaspoon of wine. 1 teaspoon = 5ml. That is 1/150th of the whole content Whole bottle 750ML with a 3rd of dilution water has 8.25% of ABV. Now how much of alcohol does 1/150th of it has, 5ml x 8.25% = 0.4125 ml of alcohol per serving! That is 0.4125ml of alcohol within a full teaspoon serving. To put into perspective, one serving of Nyquil has 3ml of alcohol per serving. That is seven times more than what we are serving to an adult. I went to this great detail to shed some light on the scientific explanation of its alcohol content. Obviously, when our Church Fathers approved the use of such a minimal amount, they did not go thru a thorough calculation as I detailed above. But rather, as I mentioned, they are equipped with wisdom and knowledge to determine it’s a safe and acceptable approach. Legal Nationally The First Amendment to the United States Constitution clearly declares religious freedom. Also, States do have their own specific rules and regulation and exception as far as alcohol and minors. Such practice, as I have explained above, within a church is within the intent of the letter of the law. As stated in law of State of Georgia, the use of alcohol for religious practices is exempted. Even in the most liberal states, no liberal atheist prosecutor with an ill intent of hurting people of faith would be naïve or stupid enough to prosecute such practice. One does not need to be a graduate of a law school to understand the above.

http://www.ethiofreedom.com/eat-my-flesh-drink-my-blood-john-6-dn-amde-mariam-s/

Page 20: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/20/

ይህ ለመነሻ ያክል የቀረበው አጭር ጥናታዊ ጽሑፍም ፣ ለብዙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በዚህ ምክንያት

ከመወዛገብ ድነው አንድ ልብ ሁነው ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ሥርዓት የተሻለ ጥናት ለማጥናት መነሻ ምክንያት ይሆናቸዋል

ብለን ተስፋ እንደርጋለን ።

! ይቆን !

Page 21: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/21/

Appendix 1

Studies in Comparative Ritual Theology Fr. Shoenda Mahar Ishak, Studies in

Comparative Ritual Theology (Al-amba Ruweis 2000) 38- 43

(3.4) IV .THE EUCHARISTIC WINE

(34.1) A Mixed Chalice

(341.1) From the earliest period it has been the custom to mix water with the wine

in the Eucharist. From allusions in the writings of Justin martyr, irenaeus,

Clement of Alexandria, and Cyprian it would appear that the ancient Church

continued what had most likely been the practice of the Lord at the Last Supper.

The only exception is furnished by the Armenians, who use only wine in the chalice.

Their practice goes back at least to the seventh century or before. “Canon 32 of

the Trullan Synod of 692 condemns the Armenians for using unmixed wine in their

Eucharistic service, while James the Brother of the Lord and Basil the Great of

Caesarea, who handed down the Liturgy in written form, prescribe wine mingled

with water “(Quasten III , p 226). The Armenian Council held in 719 at Tovin

(Duin) under patriarch John VI decreed the use of an Unmixed chalice (i.e .only

wine in the chalice) (Day, p. 9)

The absence of water in the liturgy of the Gregorian Armenians was adversely

commented on by George the Arabian (686-724 ) ,John X Bar Shushan (1058; 1064-

1073 ) and Denys Bar Salibi (1171 ) (King I, p 107).

(341.2) In the Church of England the admixture was not ordered after 1549, though

its use was known in the seventeenth century and was generally revived in the

Page 22: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/22/

nineteenth. It was sanctioned by the Judicial Committee of the Privy Council in

1892, and refered to by the proposed prayer Book of 1928 as ‘an ancient tradition of

the Church’ (ODCC ed .2, p 1492) .

(341.3) The practice of mixing water with wine for drinking was general in

the ancient world. (Ibid) “pfaff (after R Ob de Bartenora and Maimonides, in

Mishnam de Benedict , chap . 7, parag.5) asserts that the Jews as a rule mixed

water with the wine in their cup of Blessing” (DCA, P.604).

(341.4) “Justin Martyr (c .100-c.165), the first after the apostles who

gives any account of the celebration of the Eucharist says;“ There is then brought to

the brother who presides a cup of water and mixed wine”. And afterwards he tells

us that “the deacons distribute to each one present that he may partake of that

bread and wine and water which has been blessed by thankgiving; “and this food, he

says, is called Eucharistia” (apol.l chap.65). Irenaeus (c.130-c.200) also (adv Haer.

lib. v, chap.2,p.294) speaks of the mixed cup”(DCA,p.,604).

Clement of Alexandria (c .150 – c .215) has a plain reference to the use of the

mixed cup in the Lord’s Supper. Thus he says: “And to drink the blood of Jesus is to

become partaker of the Lord’s immortality; the Spirit being the energetic principle

of the world, as blood is of flesh. Accordingly, as wine is blended with water, so is

the Spirit with man. And the one, the mixture of wine and water, nourishes to faith,

while the other, the Spirit conducts to immortality. And the mixture of both-of the

water and of the word – is called Eucharist, renowned and glorious grace; and they

Page 23: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/23/

who by faith partake of it are sanctified both in body and soul” (Clement of Alex

.The instructor, Book ll, chap.2).

Cyprian (d.258) (Epist.63, ad Caecilium) has several passages bearing on this

question. He says (chap.2) that to mix wine with water is to follow the Lord, water

cannot be offered alone, as neither can wine be offered alone, for if the wine be

offered by itself the blood of Christ begins to be without us, and if the water be

alone the people begins to be without Christ “ ( DCA,p.604).

Canon 24 of the third council of carthage (397) orders “that in the sacrament

of the body and blood of our Lord, nothing else be offered but what the lord himself

commanded, that is bread and wine mixed with water “The African code, both

Greek and Latin, has this same canon with further directions added (canon 37 in

Latin, 40 in Greek).

(341.5) All the ancient liturgies, either contain a direction for mixing water

with the wine, or else in the canon the mixing is alluded to. Thus in the Clementine

Liturgy (Apostolic Constitution VIII, chap .12), when reciting the words of

institution, the priest says: “in like manner also, He took the cup and mixed it of

wine and water, and blessed it and gave it to them.” The Greek Liturgies of St.

Gregory contain like words; while the Byzantine liturgies of St.Basil and St. John

Chrysostom order the deacon to put wine and water into the cup before the priest

places it on the altar, in like manner, in some form or another, the mixing is

mentioned in the Liturgies of Ethiopia, Syria, India & the Roman and Gallican

Page 24: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/24/

Liturgies. In some liturgies when the water is mixed with the wine, a reference is

made to the blood and water which flowed from the Lord’s side (John 19: 34).

(341.6) The wine in use in the church has in general been red, apparently

from a desire to symbolize as much as possible the blood of our Lord . According to

the Talmud red wine was offered at the Passover (DCA, p.605).

(341.7) The proportion of water to wine in the Coptic and Ethiopian

Churches is not more than one third, but if there is much wine he shall add one

tenth. He shall not depart from the measure of this proportion. This rule is given in

canon 99 of St.Basil in the Coptic collection, adding also that pure, i.e. unmixed

wine should not be presented, giving a reference to the blood and water which

flowed from our Lord’s side.

“The Jacobites have an equal quantity of wine and water, adding

unconsecrated wine if the supply runs short. This practice was enjoined in the 5th

canon of John Bar Cursos (538), and quoted by Bar Hebraeus (1286, Nomocanon,

chap.lV, section l):

(And there should be half wine and half water mixed in the chalice: and if

the quantity of liquid (for the communion of the faithful) should fail, the priest

himself can add to it from that which has not been conscrated”(King l,p.107)

(34.2) B.The Mixing of consecrated Wine with unconsecrated wine:

(342.1) contrary to this Syrian practice, the copts now never add

unconsecrated wine to the consecrated chalice. They take great care not to let the

Page 25: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/25/

supply run short, using a big chalice from the beginning if the number of

communicants is expected to be large.

(342.2) But the medieval Coptic liturgists like lbn Kabar , ( The Lamp of

Darkness , chap . 17 ) and lbn Sibac (pretiosa Margarita , chap . 84 ) speak of the

use of a second unconsecrated chalice or more according to the need using also a

similar number of Despotikons putting them in the consecrated chalice and then

taking three spoons of the consecrated wine adding them together with a

Despotikon to each unconsecrated chalice ,while saying : “Blessed be the Lord Jesus

Christ the Son of God, the sanctifincation of the Holy Spirit. Amen” to which the

people respond: “One Holy Father, One Holy Son, One Holy Spirit. Amen”. At the

same time the celebrant takes back three spoons of wine from each chalice to the

first one. This practice, however, is not known to the present-day copts.

(342.3) in the large Coptic churches nowdays, when several priests are

concelebrating ,especially in the feasts ,one large loaf and one big chalice are

consecrated and then distributed after the last confession on several empty patens

and cups , so that the concelebrant priests might carry them giving communion to

the communicants in a shorter time .

This present-day practice is mentiond and preferred by the tenth century

Coptic bishop Amba Sawirus of Ashmunein in his book: The Order of priesthood

(chap.20),as the best method . He does not accept the use of a second unconsectrated

chalice after mixing it with what remains in the consecrated one, as against our

belief in the unmixedness in Christ. But he accepts the use of several patens with

Page 26: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/26/

one loaf in each and equal number of chalices from the beginning of the anaphora

(lbid.).

(34.3) C .The Use of Hot Water:

A peculiar rite of the Byzantine church is the mingling of hot water

with the wine, after the fraction of the oblate before the communion, accompanied

with special prayers recorded in the liturgy of St.Chrysostom.

(34.4) D .The Use of Unfermented Wine:

The Ethiopian Orthodox forbid the use of old wine in the Eucharist “They

often content themselves with steeping some dried grapes (zibibo) in a little water,

and extracting the juice “ .( King l , p . 557)

This practice was possibly adopted from Egypt in the medieval ages, when

the Copts under Islamic rule were sometimes obliged to do so , since the Islamic law

prohibits drinking wine . But the Copts of the modern times are free to use wine in

the Eucharist, which they prepare by fermenting soaked raisin juice (cf.King l , p

.406).

Page 27: 1/ · PDF fileትርጓሜ ወንጌል ማቴ 26 ፥ 31 ላይ ይመልከቱ

/27/

የተነበቡ መጻሕፍት /የመረጃ ምንጮች/

አባ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ የቅዳሴያችን ይዘት ጣና ማተሚያ ቤት ፣ ቶሮንቶ ካናዳ 2003 ዓ/ም ገጽ 86

ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የግእዝ መዝገበ ቃላት - ገጽ ፫፻፹፯

መጽሐፈ ቅዳሴ ግእዝና አማርኛ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት

አምስቱ አእማደ ምሥጢር ከጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት የተረጎሙት አ አ ሁለተኛ ዕትም ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ

ቤት 1979 ዓ/ም

ቃለ መጠይቅ - በኢሩሳሌም በቅዳሴ ካገለገሉ አባት ጋር ጥቅምት 16/2008 ዓም

ቃለ መጠይቅ -የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስክርነት- Saint Mary's Coptic Orthodox

Church 4110 204th St SW, Lynnwood, WA 98036 (425) 774-3499

ፍትሐ ነገሥት ግእዝና አማርኛ የታተመ

መጽሐፈ ሲኖዶስ -ግእዝ

King 1 King, A.A, The Rites of Eastern Chrtendom (2 Vols.) first Vol.Rome 1947.

Shoenda Mahar Ishak,/ Fr. /Studies in Comparative Ritual Theology (Al-amba

Ruweis 2000) page 38

The Oxford Dictionary of The Chrsistian Church , ed. F.L Cross and E.A.

Livingston (Oxford: Oxford Univeristy Press, 1997) 1754-1755.

On line article - http://www.ethiofreedom.com/eat-my-flesh-drink-my-blood-john-6-

dn-amde-mariam-s/


Recommended